ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

@mahtotetonetor1


ማኅቶት ማለት መብራት ነው ቶኔቶር ደግሞ የኢትዮጵያ የጥንት ስሟነው እናም ማኅቶተ ቶኔቶር ማለት የኢትዮጵያ መብራት ማለት ነው መብራቷ ደግሞ መካከሏን ገነት ዳሯን እሳት እያለች የምትጠብቃት የምትጸልይላት እምነቷ ቅድስት ተዋህዶ ጥንት የሌላት ጥንታዊት ዘመን የሌላት ዘመናዊት ናት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምሮ ነው
አስተያየት ካለዎት
@mahtotetonetor2
@mahtotetonetor1

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

21 Oct, 07:02


ሴትየዋ ችግሯን ልታማክር ወደ ዶክተር ሄደች።
"ዶክተር እባክህ አንድ ችግር ገጥሞኛል።"
"ምን ገጠመሽ?"
".…ከወለድኩ ገና አንድ አመት አልሞላኝም። ሆኖም ሌላ ልጅ አርግዣለሁ። እኔ ደግሞ ተጨማሪ ልጅ በዚህ ወቅት እንዲኖረኝ አልፈልግም።"
"እና ምን ልርዳሽ?""
"ሆዴ ውስጥ ያለውን ልጅ ማስወረድ እፈልጋለሁ!"
ዶክተሩ ትንሽ አሰብ አደረገና “ለምን ከዚህ የተሻለ ሀሳብ አላቀርብልሽም?” ሲል ጠየቃት።
“ምን አይነት ሀሳብ?”
“አየሽ ይሄን ልጅ ከሆድሽ ለማስወረድ ብዙ ችግር ውስጥ ትገቢያለሽ፣ ደም ይፈስሻል ልትሞቺ ወይም በቀጣይ ላትወልጂ የምትችይበት አጋጣሚም ሊፈጠር ይችላል። ስለዚህ ይሄን ሁሉ ችግር ከምታይ ለምን በእጅሽ ያቀፍሽውን ልጅ አንገድለውም?” አላት
ሴትየው ደነገጠች። ዶክተሩ ንግግግሩን ቀጠለ።
“አዎ! ለእናት እንደሆነ ሁሉም ልጅ እኩል ነው። ስለዚህ አንዱ መሞት ካለበት ሆድሽ ውስጥ ያለው ከሚሞት ይሄኛው የተወለደው ቢሞት ምንም ችግር ሳይገጥምሽ ሀሳብሽን ታሳኪያለች…” እያለ ምክረ ሀሳቡን መተንተን ጀመረ።
ሴትየዋ ግን በጆሮዋ የሚንቆረቆረው የዶክተሩ ሀሳብ ሳይሆን የአምላክ ማሳሰቢያ መሆኑን እያሰበች ለማስወርድ የዘረጋቻቸውን ሁለት እግሮቿን ሰብስባ ብድግ ብላ ክፍሉን ለቃ መውጣት ጀመረች።..…ልጆቿን አንዱን በክንዷ ሌላውን በሆዷ እንዳቀፈች ወደ ቤቷ ተመለሰች። አዎ! የተወለደም በሆድ ውስጥ ያለም ቢሆን ለእናት ልጆቿ ሁሉ እኩል ናቸው!

ህጻናትን በውርጃ መግደል ወንጀልም ኃጢዓትም ነው!
@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

20 Oct, 17:12


መድኃኔዓለም በእድሜ ይጠብቅልን

በእውነት እግዚአብሔር አምላክ በጎደለ ይሙላላችሁ መድኃኔዓለም ያላሰባችሁትን ይስጣችሁ።
  አስራታቸውን ስዕለታቸውን እንዲያስገቡ በረከቱን እያበዛላቸው እየባረካቸው ለምሕረት የማይታጠፉ እጆቹ እንደማይጎድል ውሃ  እያፈሰሰላቸው ነው ።
እግዚአብሔር ይቀበልላችሁ እም ብርሃን አትለያችሁ የሰላም አምላክ ሰላምን ይስጣችሁ።



በሚሞት ሥጋችን አንመካ በገንዘባችን ባለን የኃብት መጠን አንመዛዘን።
ገንዘባችሁ አያጸድቃችሁም መቶ ሺ ብር ሰርቃችሁ ሃያ ሺ ብር ብትሰጡ አትጸድቁም ገንዘባችሁ ከንጽሕና ጋር ሲሆን እንጂ ።እግዚአብሔርን በአስራታችን አንስረቀው እግዚአብሔር ከአስር ብር ውስጥ አንድ ብር የሚጠይቀን ዘጠኙን ሲጠብቅ ነው ሲያበዛልን የበረከት ሲያደርግልን ነው

EGUA D/MIHRET MEDIHANIALEM
እጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን
🫴🫴አቢሲኒያ ባንክ 182395657

🫴🫴በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000273479744
  
በምንም ጉዳይ ለምትፈልጉት መረጃ ስልክ:-የእጅ ስልኮቻችን 

+15092943369 አሜሪካ ለምትገኙ

+251912494703  =ኢትዮጵያ ለምትገኙ
ይደውሉልን ወይም ቴሌግራም @sekokaw ላይ ይጻፉልን



ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

20 Oct, 16:44


👌አኑረን እንዳንል ኑረን ምን አፈራን፣
ግደለን እንዳንል እሳትህን ፈራን፣
ጸሎቱ ጠፍቶናል በፈለግኸው ምራን።
🙏

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ይህ ቀረሽ የማትባል ዘመን የሌላት ዘመናዊት ናት ይሁን እንጂ በዓመት አንድ ጊዜ በሚከወነው የዓለም አቀፍ የሰበካ ጉባኤ ትዝብቴን ላካፍላችሁ እንዲያው የእናንተንም አስተያየት ወዲህ በሉኝ።
፩) ከንቱ መሞጋገስ መንቆለጳጰስ እገሌ ይቀየማል እገሌ ቅር ይለዋል ብለው መሰለኝ 😂

፪)የአንድ ሊቀ ጳጳስ ሥራው ምንድነው ?ወደ ሀገረ ስብከቱ ሲመጣ አቀባበል አደረግንለት፣አንድ ጳጳስ አስቀደሱ ፣ባረኩ ፣ክህነት ሰጡ ብሎ ሪፖርት ማድረግ ይህን ማኅበረ ምዕመናን መናቅ አይመስልም ወይ? እና ሥራቸው ምንድነው ድሮስ ? በዚህ ዓመት ክህነት ሰጡ ቀደሱ ተብሎ ሪፖርት ቀረበ ወትሮስ ምንድነው ሥራቸው ክህነት ያልሰጡበት ጊዜ አለ??
፫)በስልክ በሰጡት መመሪያ እንዲህ አደረግን ምን ማለት ነው አዲስ አበባ ተቀምጦ ቤተክርስቲያንን ማስተዳደር ወጀብ ለበዛባት መርከብ መልካም ነው ወይ?

አስተያየት :-ቤተክርስቲያን ውስጥ መሸላለም ቢቀር ያልተሸለመ አድፍጦና እእእኽ እያለ ከሚሄድ አርአያ የሚሆን አንድ ሀገረ ስብከት ሥራን በተግባርና በVideo በታገዘ ቢያሳይ ሪፖርት ቢያቀርብ ።
ደብቆት የኖረው
ለራስ እውነት ያለው
ሁሉም ውሸት አለው!



ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

19 Oct, 20:52


ማኅሌተ ጽጌ በሰዓሊተ ምሕረት አዲስ አበባ
https://youtube.com/live/RJ9ZcjNpeAE?feature=sharedhttps://youtube.com/live/RJ9ZcjNpeAE?feature=shared

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

18 Oct, 18:44


ዚቅ፦
====
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ
በውስተ አህዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይዕቲ
ማኅሌተ ጽጌ፦
==+++====
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤
ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ
(ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት
ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ
ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።
ወረብ፦
=====
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ
ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪

ዚቅ፦
===
እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን
አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ
ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።
ማኅሌተ ጽጌ፦
===+=====
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ
ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

ወረብ፦
====
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ፦
===
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ
ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ
ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤
በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤
ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።

ዚቅ(ዓዲ)፦
=======
ወይቤላ ንዒ ንሑር፤ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ
አውግረ ስኂን፤ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት።

ማኅሌተ ጽጌ፦
=====+++
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ
ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
ሰቆቃወ ድንግል፦
===========
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን
ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል
ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ
በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት
ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።

ወረብ፦
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ
ግብጽ ተዓይል/፪/
ዚቅ፦
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤
0አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም
ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ።
ወረብ፦
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/፪/
እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ እምአዕይንትኪ
አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/፪/

ሰቆቃወ ድንግል ዓዲ
====+++===++
ኀበ አዕረፍኪ እግዝዕትየ ማርያም ታሕተ ጽላሎተ
ዕፅ እምፃማ፤ፈያት ክልኤቱ ሶበ በጽሑኪ በግርማ፤
እምትሕዝብተ ሞቱ ማሕየዊ ለወልድኪ ንጉሠ
ራማ፤እፎኑ አዕይንትኪ ማያተ አንብዕ አዝንማ፤
አዕይትየ ለገብርኪ ክልኤሆን ይጽለማ።
ዚቅ፦
=+=
ሐፃቤ ርስሐትየ ይኩን አንብዕኪ ዘአንፀፍፀፈ ዲበ ምድር አመ ወልድኪ ይፄዓር በመልዕልተ

መዝሙር፦
====+==
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፣ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ
እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ
አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወበጽጌያት ምድረ
አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፤ ወመኑ
መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀይል መላትሒሁ፤
ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤ ወመኑ
መሐሪ ዘከማከ ሰማይ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ
ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ በከዋክብት ሠማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት
ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ
ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ
ዕለት፤ማ፦ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፥ ወኩሉ ይሴፎ
ኪያከ።

አመላለስ፦

ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/፪/
ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ/፪/

መልካም ማኅሌት !!
ጥቅምት 09/2017

         @mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

18 Oct, 18:44


ሥርዓተ ማኅሌት ዘጽጌ፣ አንደኛ ዓመት ሦስተኛ ሳምንት
============+++==================
መልክዓ ሥላሴ፦
========++
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ
አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው
በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት
መስቀል፡፡
ዚቅ፦
==++
ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤
ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ህይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ
ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ
መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን
ተስፋሆሙ ለጻድቃን
ማኅሌተ ጽጌ፦
==+++====
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤
ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤
ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል
ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ
በትእምርተ መስቀል።

ወረብ፦
=====
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል/፪/
ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ያሬድ ወይብል ሐጹር
የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል/፪/

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

18 Oct, 04:17


የእኛ ናቸውና እናግዛቸው
እኛም ነገ ምን እንደምንሆን አናውቀውም ምን እንደሚገጥመን እሱ መድኃኔዓለም ብቻ ነው የሚያውቀው ።
በትናንትናው ዕለት የገዳሙ አበምኔት ደውለው በሰላም እጦት(ጦርነት ) ምክንያት ጸበለተኞች ስንቅ አመላልሰው ራሳቸውን እየመገቡ ሱባኤያቸውንና ጸበል መከታተል አልቻሉም እባካችሁ የምትችሉ ከሆነ ለጸበለተኞች ገብስ ገዝተን አስፈጭተን በሶ ለመስጠት ፣ስኳር እና ሌሎች ነገሮችን መደጎም እንችል ዘንድ አሳስብልን አሉኝ
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ከአሁን በፊት ለኮቪድ ጊዜ እንዳደረግነው ለገዳሙ ቅርብ የሆናችሁ ገብሱን ወይም ሽንብራውን ገዝታችሁ ማቅረብ ብትችሉላቸው በሩቅ ያለን ደግሞ የምንችለውን ከታክሲ ከቁርስ ከአስራታችን ቀንሰን ይህን ብናደርግ

ዲ/ን ኤርምያስ


0912494703

@sekokaw
@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

17 Oct, 10:06


ይህ የእኛ ግሩፕ አይደለም ይጠንቀቁ ፕሮፋይልም ስምም አንድ አይነት በማድረግ በቴሌግራምም በቲክቶክ በእንስታግራም የሚንቀሳቀሱ አሉ
የእኛ ብቸኛ ፔጅ
@mahtotetonetor2
እና @mahtotetonetor1 ነው

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

17 Oct, 09:42


ክርስቲያኑም ሙስሊሙም በአንድ ቃል"አባ" የሚላቸው የፍቅር ሰው የዘመናችን ጻድቅ አባ መፍቀሬ ሰብእ አረፉ።
@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

15 Oct, 20:20


በሚሞት ሥጋችን አንመካ በገንዘባችን ባለን የኃብት መጠን አንመዛዘን።
ገንዘባችሁ አያጸድቃችሁም መቶ ሺ ብር ሰርቃችሁ ሃያ ሺ ብር ብትሰጡ አትጸድቁም ገንዘባችሁ ከንጽሕና ጋር ሲሆን እንጂ ።እግዚአብሔርን በአስራታችን አንስረቀው እግዚአብሔር ከአስር ብር ውስጥ አንድ ብር የሚጠይቀን ዘጠኙን ሲጠብቅ ነው ሲያበዛልን የበረከት ሲያደርግልን ነው

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

15 Oct, 17:45


ምክራችሁን እንሻለን

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓለ ክብር አደረሳችሁ።የእጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ገዳምን በዘላቂነት ራሱን ችሎ እንዲቆም ብዙ ስንረባረብ እንደሆነ ሁላችሁም የምታውቁት ሐቅ ነው ።
፩) ማለትም በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ የወረዳ ከተማ ላይ 300ካሬ የሚሆን ቦታ በዚሁ ግሩፕ በተሰበሰበ ገንዘብ እንደገዛን ታስታውሳላችሁ ግንባታውን እንዳንጀምር በአካባቢው ባለው ሰላም እጦት ምክንያት ሲምንቶ ፣ብረት ፣ብሎኬት ሎሎችም ማስገባት አልቻልንም ስም ለማዛወር ቢያንስ ኮለን ማቆም እንዳለብን በጊዜው ተገልጾልን ነበር ።
፪) መሬት ከገዛንበት ገንዘብ ውጪ አሁን ላይ በዚሁ ግሩፕ እየተሰበሰበ ያለ 547,000ብር አካባቢ ደርሰናል ።ገንዘቡ ባንክ ተቀምጦ ዋጋ እያጣ እንዳይሄድብን ማሰባሰባችን እንዳለ ሆኖ
ምን እንስራበት ሀሳብ አስተያየታችሁን በ @sekokaw ላይ ጻፉልን ወይም 0912494703 ላይ ይደውሉልን

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

14 Oct, 18:31


ይህቺኛዋ ደግሞ ተማሪ ኤልዳና መስፍን ትባላለች እጅግ ትሁትና እያንዳንዱ እንቅስቃሴዎቿ ሁሉ እግዚአብሔር ያዝልቅልሽ የምትሏት ዓይነት ልጅ ናት እመ ብርሃን አትለይሽ በርቺ እግዚአብሔር ፍጻሜሽን ያሳምረው ።


0912494703
ዲ/ን ኤርምያስ
@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

14 Oct, 10:40


መንፈሳዊ እኅታችን ማርታ ኃይሉ ትባላለች በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ናት የምትስላቸውን መንፈሳዊ ሥዕላት ስትመለከቱ በጣም ትደመማላችሁ ይህ ከላይ ከመድኃኔዓለም ካልሆነ በቀር እንዴትም ሊቻል አይችልም ስዕል ለጸሎት ቤታችሁ እንዲሁ ለገጠር አድባራትና ገዳማት ማሳል የምትፈልጉ ደውሉላት ውድ እህቴ እጆችሽን ይባርክልሽ ።+251943804311 Marta Hailu


0912494703
ዲ/ን ኤርምያስ

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

13 Oct, 09:05


አንድ  ካህን  ለሁለት  ምዕመን 
ውድ  የተዋህዶ  ልጆች  በእጓ  ደብረ  ምሕረት  መድኃኔዓለም  ገዳም   ካህናት  ከሚገባው  መጠን  በላይ  በጣም  ችግር  ላይ  ናቸው      የሚያገለግሉት  በነፃ  ነው   መነኮሳትስ  ሚስትም  ድስትም  ልጆችም  የላቸውም  የባለትዳር  ካህናቶች  ጉዳይ  ግን  በጣም  አሳዘኑኝ   በየጊዜው  በአገኘኋቸው  ቁጥር  እኛስ  እንደምታየን  ክረምት  ከበጋ  ያለመሰልቸት  ግርማ  አራዊቱን  ቅዝቃዜውን  ሙቀቱን  ታግሰን  እናገለግላለን  የልጆቻችንን  ጥያቄ  ግን  መመለስ  አልቻልንም  ልጆቻችን  ተምረው  ካህን  እንዳይሆኑ  በእኛ  ክህነትን  እያስጠላናቸው  ነው  ብለው  አሉኝ  እኔም  አንድ  ካህን  ለሁለት  ምዕመን  መልዕክቱን  አደርሳለሁ  ብዬ  አልኳቸው  ።ይህን  በምን  መንገድ  ይሆናል  ሰበካ  ጉባኤ  ለካህናት  ደመወዝ  ብሎ  አካውንት  ይከፍታል  በዚያ  በማስገባት  ብናግዛቸው  ።ፈቃደኛ  የሆናችሁ  በሀገር  ውስጥም  በውጭም  ያላችሁ  ፈቃደኛነታችሁን  አሳዩኝ  ከዚያ  አካውንቱን  እንዲከፍቱላቸው  እነግራለሁ  ።  በጽዋ ማኅበር ፣አስራታችንን ሰብስበንም ቢሆን በወር  5000  ብር   ለአንድ  ካህን  ።

0912494703   whats up ,telegram   ,IMO ስልኬ ነው   ደውሉልኝ 
ወይም  ቴሌግራም  @sekokaw  ብለው  ይፃፉልኝ


ዲ/ን  ኤርምያስ 

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

12 Oct, 21:03


እግዚአብሔር ከአስር ብር አንድ ብር የሚጠይቀን ዘጠኙን ለመጠበቅ ነው ።




ስርዓተ ማህሌት ዘካልዕ ጽጌ በዓለ በዓታ ለማርያም
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@mahtotetonetor2
መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከተ፤ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ።

ማኅሌተ ጽጌ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ(ጽላተ) ኪዳን፤ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡

ወረብ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ዘኮንኪ ለዕረፍት ትእምርተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/

ዚቅ
ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ኅቡረ ንትፈሳሕ ዮም በዛቲ ዕለት፡፡
@mahtotetonetor2

ማኅሌተ ፅጌ፦
ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ፤በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ


ወረብ፦
እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ  ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ/፪/
ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ/፪/
@mahtotetonetor2
ዚቅ
አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን ድንግል ኅሪት ዘነበረኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ሥርግው በወርቅ ንጡፍ ወልቡጥ በዕንቍ ባሕርይ ዘየኃቱ ዘብዙኅ ሤጡ ከመዝ ነበርኪ በቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽሑ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ አሠርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ

ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/

ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎሕ ሠናይት ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጣስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት

ዓዲ ዚቅ
ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።

ወቦ ዘይቤ ዚቅ
ይዌድስዋ ትጉሃን፤ይቄድስዋ ቅዱሳን፤ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርይዪ ወአጽምዒ ዕዝንኪ

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/

ዚቅ
ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤መራኁቱ ለጴጥሮስ፤አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ
@mahtotetonetor2
ሰቆቃወ ድንግል
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ሥሩዓ፣ ኅብስተ ኅቡዓ ወጽዋዓ ወይን ምሉዓ፤እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ዘኃጥአ፤ተአገሠት በብሔረ ግብጽ ረኃበ ወጽምዓ፤አልቦ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ

ወረብ፦
እፎ ከመ ነዳይ ዘኃጥአ ሲሳየ ዕለት/፪/
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ኅብስተ መና ኅቡዓ/፪/

ዚቅ
እሴብሕ ጸጋኪ ኦ ዑጽፍተ ልብሰ ወርቅ እግዝዕትየ ወለተ ዳዊት ንጉሥ ዘተሐፀንኪ በቤተ መቅደስ ወተዓንገድኪ በፈሊስ እምሀገር ለሀገር እንዘ ተዓውዲ በተፅናስ

መዝሙር፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።
@mahtotetonetor2
አመላለስ፦
መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/
ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

12 Oct, 17:51


“ቤተ ክርስቲያን መነገጃ አይደለችም! ሌቦች ይውጡ! ጉበኞች ይውጡ! ሠርተው ይብሉ! በቤተ ክርስቲያን አውደልዳይ አይብዛ፤ ቦታ ይሰጠው፤”“በጎጥ እና በቋንቋ የምንመራው እስከ መቼ ድረስ ነው?”ቢሮው የማን ነው? በጉቦ የገባ ማን ነው? ወንጌሉ የሚሰበከው ለማን ነው?

ሕዝቡ ተሰብኮ፣ ተሰብኮ ዐውቆታል፤ ከቢሮ ውስጥ ነው ችግሩ፤ ጥያቄው ሲጎርፍ አለመመለስ ነው ችግሩ፤ በዚኽ ዓለም ያልታመነ በእግዚአብሔር መንግሥትስ ቦታ አለው እንዴ? ትምህርቱ የጆሮ ቀለብ ኾኗል፤ ውስጥ ገብተው ሲያዩት ያስለቅሳል፡፡”

“ምርጫ በሞያ ይኹን፤ በጎጥ አይደለም፤ ሲጠየቅ መልስ የሚሰጥ ቤተክርስቲያንን የሚያውቅ የሕዝብ አባት ይኹን፤ ድኻ ተበደለ፤ ፍርድ ተጓደለ የሚል አባት ከሌለ ትርጉሙ ምንድን ነው መሰብሰባችንም ምንም በቈዔት የለውም፤”
“አእምሯችን ሳይገራ፣ ለሕጉ ተገዥ ሳንኾን ከየትም ከየትም መጥተን እግዚአብሔርን የምናስቀይም ነው የምንኾነው፤ ያልተቀጣ ልጅ ኹልጊዜ እንደሰረቀ ይኖራል፤ ልቡናው በእግዚአብሔር ቃል እና ምስጢር ያልተቀጣ ሰውም ኹልጊዜ እንደበጠበጠ ይኖራል፤

- ፖለቲካ ከቤተ ክርስቲያን ይውጣ፤ እውነት ይገለጥ ቅዱስ አባታችን፤ ስለእውነት እንቁም፤ በአራቱ ማዕዝን ጥያቄ ተቀስሯል፤ ስለ ሃይማኖት ጥያቄ እየተነሣ ነው፤ ጥያቄውን የሚመልሰው ማን ነው? ብዙ ችግሮች ቀርበዋል፤ የሚፈታቸው ማን ነው? አእምሮ ያስባል፤ ጆሮ ይሰማል፤ ድኻ ተበደለ፤ ፍርድ ተጓደለ፤ የሚል አባት ከሌለ ትርጉሙ ምንድን ነው? ዙሪያውን ሰይፍ ተመዞ እየተብለጨለጨ የደነዘዘውን አእምሮ እናስወግደው፤ ቃሉን እንጠይቀው፡፡

ሕጉ ይከበር፤ ስም ብቻ አንያዝ፤ ሕጉን ወደ ኋላ አሽቀንጥረን ትተን እንዴት መምራት እንችላለን? ተንኰል ይቅር፤ በውሸት አንመን፤ በዝባዥ ይጋለጥ፤ ጨርሻለኹ፡፡

ብፁዕ አቡነ እንድርያስ 2008 ዓ. ም የተናገሩት ነው።
@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

12 Oct, 16:47


መድኃኔዓለም በእድሜ ይጠብቅልን

በእውነት እግዚአብሔር አምላክ በጎደለ ይሙላላችሁ መድኃኔዓለም ያላሰባችሁትን ይስጣችሁ።
  አስራታቸውን ስዕለታቸውን እንዲያስገቡ በረከቱን እያበዛላቸው እየባረካቸው ለምሕረት የማይታጠፉ እጆቹ እንደማይጎድል ውሃ  እያፈሰሰላቸው ነው ።
እግዚአብሔር ይቀበልላችሁ እም ብርሃን አትለያችሁ የሰላም አምላክ ሰላምን ይስጣችሁ።


EGUA D/MIHRET MEDIHANIALEM
እጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን
🫴🫴አቢሲኒያ ባንክ 182395657

🫴🫴በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000273479744
  
በምንም ጉዳይ ለምትፈልጉት መረጃ ስልክ:-የእጅ ስልኮቻችን 

+15092943369 አሜሪካ ለምትገኙ

+251912494703  =ኢትዮጵያ ለምትገኙ
ይደውሉልን ወይም ቴሌግራም @sekokaw ላይ ይጻፉልን



ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

12 Oct, 08:19


እግዚአብሔር በጎደለ ይሙላልህ ሰላመ እግዚአብሔር አይለህ።
በእውነት እግዚአብሔር አምላክ በጎደለ ይሙላላችሁ መድኃኔዓለም ያላሰባችሁትን ይስጣችሁ።
  አስራታቸውን ስዕለታቸውን እንዲያስገቡ በረከቱን እያበዛላቸው እየባረካቸው ለምሕረት የማይታጠፉ እጆቹ እንደማይጎድል ውሃ  እያፈሰሰላቸው ነው ።
እግዚአብሔር ይቀበልላችሁ እም ብርሃን አትለያችሁ የሰላም አምላክ ሰላምን ይስጣችሁ።


EGUA D/MIHRET MEDIHANIALEM
እጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን
🫴🫴አቢሲኒያ ባንክ 182395657

🫴🫴በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000273479744
  
በምንም ጉዳይ ለምትፈልጉት መረጃ ስልክ:-የእጅ ስልኮቻችን 

+15092943369 አሜሪካ ለምትገኙ

+251912494703  =ኢትዮጵያ ለምትገኙ
ይደውሉልን ወይም ቴሌግራም @sekokaw ላይ ይጻፉልን



ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

11 Oct, 16:05


ታጥባችሁ ብሉን
አንድ ሰው በቤቱ የተዘጋጀለትን ምግብ ንጽህናውን የጠበቀ ቢቀርብለትና ተመግቦም እንዲስማማው ከፈለገ በክብር በስነ ሥርዓት ህጉን አክብሮ ሊመገበው ይገባል ከእሱ ንጽሕና ጉድለት የተነሳ ሊሰጠው ከነበረው ጥቅም ይልቅ መርዝ ሊሆንበት ይችላል።
~የቤተክርስቲያን ልዕልና እኔ ወይም ሌላው የሚደፍራት አልነበረችም ምክንያቱም መሰረቷ ይታወቃል።የማይኖረውን የማያምነውን የሚሰብክ የሃይማኖት አባት  መናፍቅ  ነው ለራሱ ያልሆነ የሌሎችን ነፍስ ሊታደግ አይችልም ለይምሰል መኖር ለእምነቱ ይቅርና ለህሊናው እረፍት አልባ ኑሮ  ነው።
ጥቂት ህዝብ ሲሰበሰብ የማይመጣ ለኪዳን ለማኅሌት ለሰዓታት በአጠቃላይ ለጸሎት የማይተጋ ሌሎች ጉድጓድ ገብተው ትቢያ ነስንሰው አመድ መስለው ሰርተው ካላቸው ከፍለው በሙዳይ ከአስቀመጡት ገንዘብ የቅቤ ቅል መስሎ መታየት እንዴት ያስጠላል ።የንጹሐን እምባ የቅዱሳን አውደ ምሕረት የህሙማን ጸሎት አፈር ያስቅማል ይህ ደግሞ ቢዘገይ እንኳን የሚቀድመው የለም ።
እግዚአብሔር ወርቅ ሊሸልም ሲል አያያዝን በመዳብ ይፈትናል ።
~አዛዥ ናዛዥ መሆናችሁ በራሱ ምን አጉድሎባችሁ ነው ሳትታጠቡ የምትበሉን ቢያንስ ድጋሚ ለራሳችሁ መርዝ ሳንሆንባችሁ ታጥባችሁ እንኳን ብሉን።

ዲ/ን ኤርምያስ
@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

11 Oct, 14:54


እግዚአብሔር በጎደለ ይሙላልህ ሰላመ እግዚአብሔር አይለህ።
በእውነት እግዚአብሔር አምላክ በጎደለ ይሙላላችሁ መድኃኔዓለም ያላሰባችሁትን ይስጣችሁ።
  አስራታቸውን ስዕለታቸውን እንዲያስገቡ በረከቱን እያበዛላቸው እየባረካቸው ለምሕረት የማይታጠፉ እጆቹ እንደማይጎድል ውሃ  እያፈሰሰላቸው ነው ።
እግዚአብሔር ይቀበልላችሁ እም ብርሃን አትለያችሁ የሰላም አምላክ ሰላምን ይስጣችሁ።


EGUA D/MIHRET MEDIHANIALEM
እጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን
🫴🫴አቢሲኒያ ባንክ 182395657

🫴🫴በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000273479744
  
በምንም ጉዳይ ለምትፈልጉት መረጃ ስልክ:-የእጅ ስልኮቻችን 

+15092943369 አሜሪካ ለምትገኙ

+251912494703  =ኢትዮጵያ ለምትገኙ
ይደውሉልን ወይም ቴሌግራም @sekokaw ላይ ይጻፉልን



ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

1,444

subscribers

2,364

photos

30

videos