ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

@tseomm


በዚህ ቻናል ላይ አበው ያስረከቡንን መጻሕፍትን እንዲሁም መንፈሳዊያት ጽሁፎችን ለምዕመናን ተደራሽ ማድረግ ነው።
https://linktw.in/mejQ6H
ሰብስክራይብ ያድርጉ

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

22 Oct, 15:26


https://youtu.be/e94qysdWHnY

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

21 Oct, 13:36


የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ ጸሎት መረሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጸሎት እናግዛቸው መልካም ውሳኔዎች ይወሰኑ ዘንድ። 🙏🙏🙏🙏

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

21 Oct, 13:02


ዳግማዊ ግርማ ወንድሙ የ“አጥማቂ“ ሔኖክ ተፈራ (ዘሚካኤል) ነገር

ወዳጄ ሕዝብን መብላትና መጋጥ ከፈለክ “ፈዋሽ ነኝ… እግዚአብሔር አሳየኝ መንገዱን ገለጠልኝ” ብለህ ቅረብ!

-ዳግማዊ ግርማ ወንድሙ “አጥማቂ“ ሔኖክ ተፈራ(ዘሚካኤል) አይነት በዩቲዩብ “ፈዋሽ ነን እግዚአብሔር ገለጠልኝ” በማለት የሚያስተላልፉትን አጋንንትን የሚሰብክ ትምህርት እና የሐሰት ሰይጣናዊ ምስክርነትን ማድመጥ አይጠቅመንም፡፡ ማቆም ይገባናል፡፡

-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዘመን አንዳንድ የፈውስ ዛር ሰፍሮብኛል፣ መተት አባራሪ ነኝ በማለት በፈዋሽነት ስም ከውስጥ እስከ ውጭ ድረስ በዩቲዩብ በምእመናን ላይ ፍርሐትና ጥርጣሬ ለማንገስ የሚያላግጡ “ፈዋሽ ነኝ… እግዚአብሔር አሳየኝ መንገዱን ገለጠልኝ” የሚሉ ወገኖች አሉና ብንጠነቀቅ መልካም ነው፡፡ ለምሳሌ በዩቲዩብ የቀሲስ ሔኖክ ተፈራ የሚባልን ሰው “ትምህርት” የሚከተል ካለ አጋንንት፣ደብተራ፣ጠንቋይ፣ሟርተኛ፣ ዛር፣ ቡዳ፣ መተተኛ፣ ልክፍት፣ ዓይነ ጥላ፣ የአየር አጋንንት፣ከእናት አባት የመጣ ዛር፣… በሚሉ የጋኔላም ትምህርት መገለጫ በሆኑት ቃላትን ሲጋትና ሲከታተል መክረሙ ነው፡፡ ሕዝቡ ለምን ይሆን በዩቲዩብ ፈውስ በማለት የሚለቁትን እና አጋንንታዊ ስብከትን ማድመጥና ማየት የመረጠው? በቀን Jun 25, 2022 “የፈውስ አገልግሎት ክፍል 4” በሚለው ርእስ በዩቲዩብ በቀሲስ ሔኖክ ፊት የቀረበች አንዲት ምስኪን እህት “ነጋዴዎች ነን አለችና፡፡ ሁሌ ከባለቤቴ ጋር ያንተን ከፍተን እናያለን አለች፡፡” ያሳዝናል፡፡ እንደዚች እህት በጣም ብዙ እህቶች ከአጋንንታዊ ትምህርት የሚያላቅቃቸው የሚፈልጉ ያሉ ይመስለኛል፡፡ ብዙ ሰዎች “ፈዋሽ ነን” በሚሉት ሰለባ እየሆኑ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ የምጠይቀው ከወንዶች ይልቅ ለምንድር ይሆን ሴቶች እህቶችና እናቶች የፈዋሽ ነኝ ባዮች ሰለባ እየሆኑ ያሉት? በጣም ማሰብና መፍትሔ መፈለግ ያለብን ይመስለኛል፡፡ ወገኖቸ ጠንቋይ መተተኛ ከሚሉ ኮተታሞች ትኩረታቸው ያልሆነ ኢየሱስ ክርስቶስን የትምህርታቸው ማዕከል በማድረግ በዩቲዩብ የሚያስተምሩ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መምህራንን እንወቅ እናሳውቅ፡፡

-ቪዲዮዎችን በአግባቡ ለተከታተለ ቀሲስ ሔኖክ ተፈራ(ዘሚካኤል) ማለት በብዙ መንገድ ዳግማዊ ግርማ ወንድሙ ማለት ነው፡፡ በተለይ ሴቶች እሰኪ ልብ ግዙ የማንም መቀለጃ አትሁኑ፡፡ “ፈዋሽ ነኝ” የሚሉ ጋኔል ሰባኪን የሚከታተለው ብዛቱ ይገርመኛል፡፡ እስኪ የማኅበረ ቅዱሳንና መሰል ዩቲዩቦችን የሚተላለፉትን ጠንካራ ትምህርቶችንና መልእክቶችን ተመልከቷቸው፡፡ በነገራችን ላይ የማኅበረ ቅዱሳን እና መሰል ዩቲዩብን የሚከታተለውን አጠቃላይ አጋንንታዊና የሐሰት ትምህርት ከሚያደምጠው ተመልካች ብንደምር በግማሽ እንኳን አይታይም አይደመጥም ማለት የሚቻል ይመስለኛል፡፡ በትክክል ማድመጥና መማር የሚገባን ግን የትኛውን ዩቲዩቦችን ነበር? ወዳጄ ሕዝብን መብላትና መጋጥ ከፈለክ “ፈዋሽ ነኝ …እግዚአብሔር አሳየኝ መንገዱን ገለጠልኝ፡” ብለህ በዩቲዩብ ሆነ በአካል ቅረበው!!

-ለምሳሌ ያህል በቀን May 27, 2022 ቀሲስ ሔኖክ ተፈራ በዩቲዩብ ከተናገራቸው በከፊል የሚከተለውን ማንሳት ይቻላል፡፡

1.) "ደስ ይበላችሁ የመተት እድሳት ማስቆም ተቻለ! የመተት እድሳት ማስቆሚያ የማያዳግም መፍትሄው ተገኘቷል!"

2.) “የመተት እድሳት ከዛሬ ጀምሮ ይቆማል፡፡ ምንድር ነው መፍትሔው እግዚአብሔር ይህን ማስቆም አይቻልም ወይ እግዚአብሔር ሆይ እስከ መቸ ድረስ ትተወናለህ እግዚአብሔር አሳየኝ …እግዚአብሔር አሳየኝ መንገዱን ገለጠልኝ፡፡ በእድሳት የተቸገራችሁ መፍትሔውን ዛሬ እነግራችኋለሁ፡፡ “

3.) “እግዚአብሔር የገለጠልኝን ነው ለእናንተ የምነግራችሁ፡፡ እግዚአብሔር ከገለጠልኝ ጀምሮ በዚህ በመተት እድሳቱ የሚሰቃዩ ሰዎችን በእግዚአብሔር ኃይል አግዟቸው የመተት እድሳቱ አቁሞላቸዋል፡፡”

4.) “ለመተት አድሳት የመጨረሻው ብቸኛ መፍትሔ አጋንንቱን ወደ መጣበት መመለስ ነው፡፡”

5.) “350 ሺ ብር በትዳርና በንብረት ላይ የተላከና በእድል የተሰራ መተት ተሸነፈ”

6.) ቀሲስ ሔኖክ ሰይጣን አለባት የተባለች አንዲት ምስኪን ሴት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ምን ብላ መለሰች መሰላችሁ “አሜሪካ የምትኖረው ቄስ ሔኖክ የሚባለውን ላይክ አድርጊ ስልካቸውን እየፈለግን ነው አለች፡፡” ላይክ አድርጊ ሃሃሃ

7.) በቀን Nov 24, 2021 ካስተማረው በከፊል “በትዳራችን መተት እንደተደረገብን እንዴት እናውቃለን ሚስት መጥፎ ሽታ ባሏን እንዲሸታት ያደርጋል፣ በመኛታ ቤታችን በአልጋ ስር አይጥ ይበዛል፣ በየቀኑ ጭቅጭቅ፣ በትዳራችን ደስታ አልባ መሆን፣ የፍች ሐሳብና ንግግር ማድረግ…”

8.) "የመተት እድሳት ማስቆሚያ 5 ቱ ወሳኝ መንገዶች…"

-የተናገሩትን ስሜት አልባ ሐሳቦችን ስለጻፍን ፈዋሾቹ እና የፈዋሾቹ ደጋፊዎች ቅናት ነው ይላሉ፡፡ ድንቄም ቅናት አያ፡፡ “ሰይጣንን ቃለ ምልልስ በማድረግ ፈወስን” በሚሉ ሐሰተኞች ፈጽሞ የሚቀና የለም፡፡ መንፈሳዊ ቅናት የሚቀናው የሚናገሩትንና የሚያደርጉትን በሚያውቁ በአብነት ትምህርት በአግባቡ ተምረው በፆምና በጸሎት ተቀጥቅጠው የሚችሉትን ያህል በተረጋጋ መንፈስ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው ያለፉና አሁን ባሉ እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊያን መምህራን ነው፡፡ ለምሳሌ በማን ትቀናለህ? ብባል “እግዚአብሔር የገለጠልኝን ነው ለእናንተ የምነግራችሁ” በሚል “ፈዋሽ ነኝ” በማለት በሚያጭበረብረው ሳይሆን የእቅበተ እምነት ጠበቃ በሆኑት አንብበው አንብበው ባልጠገቡት ከእውነተኛ ጸሎታቸው የተነሳ ልጃቸውን ከሞት ባስነሱት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ እና መሰሎቹ እቀናለሁ፡፡

-ወገን እባካችሁ ጠቃሚ የሃይማኖት ትምህርት ያለበትን የኢትዮጵያ ቤ/ን ቲቪ እና ዩቲዩቦችን ለመማር እንጠቀም፡፡ “ፈዋሽ ነን እግዚአብሔር ገለጠልኝ” በሚሉ የሚያስተላልፉትን አጋንንታዊ ትምህርት እና የሐሰት ሰይጣናዊ ምስክርነትን ማድመጥ አይጠቅመንም፡፡ እናቁም፡፡

✍️yosef fisiha እንደጻፈው

https://youtu.be/9o3TQ5RRgVY

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

19 Oct, 05:27


https://www.youtube.com/watch?v=6YEeRr3F4q8

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

13 Oct, 15:31


https://youtu.be/YXd-jf3iYyk

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

10 Oct, 06:19


https://t.me/divineliturgy12

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

07 Oct, 19:42


ታላቅ ደስታ!

ኀዘን ያካፈሉትን ወገን ደስታን እንዴት ይደብቁታል!?

ያ የጮኽንበት፣ ብዙዎቻችን በጋራ የቆምንበት፣ አስጨናቂው ችግር መፍትሄ ተሰጥቶታል! ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ ያስተምሩበት የነበረ ጉባኤ ቤት ወደ ቀደመ ክብሩ ተመልሷል!

መምህራችንም ወደ ወንበራቸው ተመለሰዋል! ተመስገን! ብፁዕ አቡነ አብርሃም የልጆችዎን ድምፅ ሰምተው ጉባኤ ቤቱን ወደ ሚመጥነው ልዕልና ስለመለሱት እጅጉን እናመሰግናለን።

ድሮም ጩኸታችንን ወደ እርስዎ ያበረታነው ይህንን መፍትሄ እንደሚሰጡን ስለምናውቅ ነበር። በዚህ ችግር ላይ ያዘናችሁ በጉባኤ ቤቱ መበተን የተከዛችሁ፤

ውግንናችሁን ለቤተ ጉባኤው ያአድርጋችሁ ወገኖቻችንና እንዲሁም ሁሉን ነገር ትታችሁ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ከምትሳሉበት ተቋም በግፍ የተባረራችሁ ደቀ መዛሙርት ሆይ እንኳን ደስ አላችሁ!

መምህር ምስጢሩ ታዬ እንደጻፉት

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

05 Oct, 11:00


https://youtu.be/0yTSIvyyJ9A

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

03 Oct, 11:25


የፌደራል ፍርድ ቤት ውሳኔ

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

01 Oct, 05:17


እንዴት አደራችሁ?

ግብዣ👇👇👇👇

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

29 Sep, 19:04


https://t.me/+so-wOHmNj-w4Nzk0

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

27 Sep, 17:36


https://youtu.be/ZzXSeJ4NmJI?si=rP5DkI5mXa1mrSVf

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

27 Sep, 17:35


በመስቀል ጉዳይ ከትውፊታውያን አብያተ ክርስቲያናት የምንጋራቸው ምንባባትና ሥርዓታት
--
1.ውዳሴና ክብረ መስቀል
ውዳሴ መስቀል የሚባል የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ድርሰት አለ፡፡ በእንግሊዝኛ ከምናገኘው Exaltation of the Holy Cross የሚል የምሥራቃውያን ትውፊት ተዛምዶ ሊኖረው ይችል ይሆናል፡፡ የነገረ መስቀል ታሪክና ድርሰቶች በምሥራቁም በምዕራቡም ተቀራራቢነት አላቸው፡፡ ከመስቀል ጋራ የተገናኙ ተዛማጅ ምንባባት አሉን፡፡ እንጥቀስ፡- “ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፣ ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኵልነ፣ ይዕዜኒ፡፡ ወዘልፈኒ - መምህራችን ሆይ! ለመስቀልህ እንሰግዳለን፣ ቅድስት ትንሣኤህን እናወድሳለን፣ ዛሬም ዘወትርም - Before thy Cross, we bow down in worship, O Master, and thy holy resurrection we glorify” ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ ‹‹The cross is the helper of the wretched, assisting all the oppressed.›› ሲል የደረሰው ድርሰት በቅ/ያሬድና አባ ጊዮርጊስ ቃል በቃል ‹‹ለአግብርት፡ ግዕዛን፣ ጽንዕ፡ ለድኩማን፡ መስቀል፡፡ - መስቀል ለባሮች ነጻነት፣ ለደካሞችም ረዳት ነው›› በሚል ሰፍሯል፡፡

በበረከት አዝመራው ( Bereket Azmeraw አነጋገር መስቀልን እንደ ግዑዝ ሳይሆን እንደ ሕያውና ሰማኢ ባለግዕዛን አካል አድርጎ መናገር (Personification) በእኛም በሌሎችም አለ፡፡ በፕ/ር ጌታች የተሰባሰበ የነገረ መስቀል ድርሳን፡- ‹‹ወሶበ ተቀኖከ መስቀል ምስለ እደ ክርስቶስ ክቡር፡፡ ሞተ መልአከ ሞት መኰንነ ኵሉ ፍጡር፡፡ ወሙታንሂ ተንሥኡ እምዝህር - መስቀል ሆይ! ከከበረ የክርስቶስ እጅ ጋራ ብትቸነከር፣ የፍጥረታት ሁሉ ገዢ የሆነ የሞት መልአክ ሞተ፣ ሙታንም ከመቃብር ተነሡ›› ይላል፡፡ መስቀልን እንደ ሰው ያናግረዋል፡፡ ግባጻውያን በውዳሴያቸው (Doxology) መስቀልን ግዕዛን ሰጥተው እንዲህ ያናግሩታል፡- ‹‹ We carry you, O Cross, the strength of the Christians, powerfully around our necks, and we proclaim openly. - የክርስቲያኖች ብርታት የምትሆን መስቀል ሆይ! በአንገታችን ዙሪያ አጽንተን እንይዝሃለን፤ በይፋም እንሰብክሃለን፡፡›› እንደ ሰው ያናግሩታል፡፡ ‹‹Hail to you, Praise to You, We bow down - ስብሐት ለከ፣ ንሰግድ ለከ - እናመሰግንሃለን፣ እንሰግድልሃለን›› የሚል መነሻ ያላቸው ድርሰቶች በሁላችንም ዘንድ አሉ፡፡ መስቀል ይከበራል፣ የጸጋ ስግደት ይሰገድለታል! የመስቀል ድርሰቶች ቢነጻጸሩ ዝምድናቸው ሰፊ ነው፡፡

---
2.መታሰቢያ
የመስቀል ከተዳፈነበት በንግሥት ዕሌኒ መውጣት ከሞላ ጎደል ዓለም አቀፋዊ ታሪክ ነው፡፡ አከባበሩና የሚከበርበት ቀን በመጠኑ ሊለያይ ይችል ይሆናል፡፡ መስቀል ሁለት ጊዜ ይታሰባል፡፡ መጋቢት 10 እና መስከረም 17፡፡ የመጋቢቱ ዐቢይ ጾም ወይም የኢየሱስ ጾም (ጾመ ኢየሱስ) ላይ ይውላል፡፡ (አሁን አሁን በንግሥ ዙሪያ ትውፊቱ ቢሸረሸርም) በኢየሱስ ስም በተሠየው ጾም በዓልን ያውም የአደባባይ በዓል ማክበርን ቀኖናችን አይፈቅድም፡፡ (መስቀሉንና የመስቀሉን ጌታ ልዩነት አበጥረን እናውቃለን! ብንል አጉል ትምክሕት አለመሆኑን እዚህ ላይ አስተውል!) በዓሉ የጌታን ጾም ክብር እንዳይጋፋ ተጠቃሎ መስከረም ላይ ይከበራል፡፡ መስቀል በዝክር ብቻ አይቀርም፡፡ በስሙ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፡፡ ‹‹መስቀለ ኢየሱስ›› የሚባል ቤተ ክርስቲያን አለን፡፡ በወላጆቼ አካባቢ ‹‹ወር/ዕ/ያ መስቀል›› የሚባል ደብር አለ፡፡ በግብፆች፣ በምሥራቆችና በካቶሊኮች ‹‹Holy Cross Church of Coptic Orthodox Church, Holy Cross Greek Orthodox Church, Holy Cross Catholic Church›› በሚል ስም አብያተ ክርስቲያናት መትከል የተለመደ ነው፡፡
---
3.የመከበሩ ፋይዳ
መስቀል ለክርስቲያኖች የስቃይ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ከስቃይ በኋላ የሚገኝ ድል አድራጊነት ይዘከርበታል፡፡ ተዘክሮውን Contemplation ሲሉት ሰምቻለሁ፡፡ ነገረ ድኅነት ይታሰብበታል፡፡ የድኅነት መሣሪያ (Instrument of Redemption) ይሉታል፡፡ በተደጋጋሚ እንደምንለው መስቀል የክርስትና አርማ ነው፡፡ ባንዲራ ነው፡፡ ባንዲራውን ስታይ አገርህ ትታሰብሃለች (ከፈለግህ ክልልህም ትዝ ትበልህ! ምሳሌ ነውና)፡፡ ባንዲራው ጨርቅ መሆኑ አይጠፋህም፣ አይጠፋንም፡፡ ውክልናው ግን ከፍ ይላል፡፡ የሚመጣልህ ሐሳብ ጨርቁ ከምን ተሠራ አይደለም፡፡ ለክብሩ የተከፈለው ዋጋ ነው፡፡ መስቀል ክቡር ደም ፈስሶበታል! የሌላ ደም አይደለም፡፡ የፈጣሪ ደም ነው! ‹‹አኮ ደመ ካልዕ፡ አላ ደመ ወልድ ክቡር!›› እንዲል መስተብቊዕ ዘመስቀል፡፡
---
4.ማማተብ
ማማተብን ዕድሜ ለብሔራውያንና ዓለም አቀፍ ስፖርተኞች የክርስትና ቋንቋ አድርገውታል፡፡ ስናማተብ ‹‹በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ›› እያልን ከግንባራችን ጀምረን ወደታች፣ ከዚያም ወደግራና ቀኝ እናማትባለን፡፡ ጸሎትና የእምነት አዋጅ ነው! ‹‹በሥላሴ ሦስትነትና አንድነት አምናለሁ!›› ብሎ እምነትን ማወጅ ነው፡፡ በዚህ አዋጅ ሠይጣንን እንገሥጻለን፡፡ ይህም ድንበር ተሸጋሪ ትውፊት ነው፡፡
--
5.ሥርዓቱና ደመራው
በእኛ ታሪኩ በቃል ብቻ ተነግሮ አይቆምም፡፡ መስቀሉ የወጣበት ሒደት በአደባባይ በተምሳሌት ይገለጻል፡፡ የክርስትናው የአምልኮ ጠባይ ነው፡፡ ከምዕራቡ ለየት ያደርገናል፡፡ የእኛ ከዊንን/ ክዋኔን (Performance) ሲከተል የምዕራቡ ቃላዊ ገለጻን (description) ያዘወትራል፡፡ በመስቀል ዙሪያ ጥቅሶችን እየነካኩ ‹መስቀል የተባለው እንደዚህ ነው፣ እንደዚያ ነው እንጅ ዕንጨት ማለት አይደለም› የሚል ተቃዋሚ ቢነሣ አይገርምም፡፡ ማለፍ ነው! የአምልኮ መንገዳችን ስለሚለያይ፡፡ የተግባሩን ገለጻ ጥሬ ቃልና ጥቅስ በመፍተል ለመዳኘት የሚደረግ የሚዛን መለያየት ያመጣው ጣጣ ነው፡፡ እንለፈው! ላደለው ምልጣኑ ላይ ያለቺው ንሺ (የቅብብሎሽ ዜማ) ‹‹እመኑ ብየ፡ ወእመኑ በአቡየ፡ አበርህ በመስቀልየ - በእኔ እመኑ፣ በአባቴም እመኑ፣ በመስቀሌ አበራለሁ / ጨለማውን እገፋለሁ/›› የሚል ነው፡፡
በመስቀሉ ያብራልን!

#ማስታወሻ:- የተያያዘው ቪዲዮ የግሪክ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት ስለ ነገረ መስቀል ያደረጉት ውይይት ነው፣ " ዮም መስቀል ተሰብሐ - The Cross is elevated today" ብሎ ይጀምራል።

✍️ደብተራ በአማን ነጸረ እንደጻፈው

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

26 Sep, 14:11


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

25 Sep, 17:57


ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመስቀል ደመራ በዓል ፍፁም መንፈሳዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካል የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያደርግ መግለጫ ተሰጠ።
(#EOTCTV መስከረም ፲፬/፳፻፲፯ ዓ.ም )

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመስቀል ደመራ በዓል ፍፁም መንፈሳዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካል የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያደርግ መግለጫ ተሰጠ።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ፳፻፲፯ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁና የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት አስተላለፉ።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዚሁ መልዕክታቸው ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን እንኳን ለ፳፻፲፯ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት በዓሉ በድምቀት፣ ባማረና በሰመረ መልኩ ተከብሮ እንዲውል ሕዝበ ክርስቲያኑ በንቃትና በኅብረት በመሆን ከጸጥታ አካላትና ቤተክርስቲያኒቱ ለዚሁ ዓላማ ካቋቋመቻቸው የኮሚቴ አባላት ጭምር በመተባበር እንዲሠራ አደራ ብለዋል።
ሕዝበ ክርስቲያኑ ከበዓላችን መንፈሳዊ ሥርዓት ውጪ የሆኑ መልዕክቶች፣ አለባበሶች እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱ መገለጫ ከሆኑ ዓርማዎች ውጭ መያዝ አይገባውም ያሉት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዓሉ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ እንደመሆኑ መጠን ቤተክርስቲያኒቱን ከማይገልጹ ሆታዎችና ጭፈራዎች እንዲርቅ በአጠቃላይ የመስቀል ደመራ በሚከበርባቸው ቦታዎች ሁሉ ያልተፈቀዱ ነገሮችን ይዞ መገኘት ፍጹም መንፈሳዊ የሆነውን በዓላችንን የሚያደበዝዘው ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ልጆቻችን ከሚያቀርቡት መንፈሳዊ ትርኢትና ዝማሬ ጎን ለጎን አካባቢያቸውን በመቆጣጠር በዓላችንን በሰላም እንዳናከብር የሚያደርጉ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ በጥንቃቄ መጠበቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በሌላ መልኩም የሌሎች እምነት ተከታዮችም በነበረውና በኖረው የመከባበርና የመደማመጥ የአብሮነት ስሜት በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ የአደራ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የበዓሉ ዝግጅት በየደረጃው በተቋቋሙት የበዓል አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጥረት በጥሩ ሁኔታ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን የገለፁት ብፁዕነታቸው ከንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ወዲህ ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሦስተኛ ጊዜ የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ማክበር የሚያስችል የስቴጅ፣የድምጽ ማጉያና የክብር እንግዶች ማስተናገጃ ቦታዎችን በማዘጋጀት የሚያደርገውን ተሳትፎ ያደነቁት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በራሳቸውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም በዓሉን ስናከብር ፍቅር ሰላምንና አንድነትን እንዲሁም መግባባትን መርሕ ባደረገ አግባብ መሆን አለበት ያሉት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዓሉ ሥጋዊ ፈቃዶቻችንን የምንፈጽምበት ሳይሆን ንስሐ ያልገቡ ንስሐ የሚገቡበት የተጣሉ የሚታረቁበት የተለያዩ አንድ የሚሆኑበት የተራራቁ የሚቀራረቡበት ፍፁም የደስታና የሰላም በዓል ሆኖ እንዲከበር ማድረግ ይኖርብናል በማለት መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

ምንጭ:- የኢኦተቤክ ሕዝብ ግንኙነት

4,583

subscribers

946

photos

20

videos