ማር ይስሐቅ

@mar_yisihak


" መንፈስ ግን በግልጥ.....አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል'' 1ኛ ጢሞ 4÷1 ስለዚህ እንንቃ!!!

ማር ይስሐቅ

26 Jul, 09:59


“ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?”
ዕብራውያን 1፥14

እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ቂርቆስን እና ቅድስት ኢየሉጣን ላዳነበት ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደርሳችሁ!

ማር ይስሐቅ

17 Jun, 04:49


📖ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትራችሁ የምትመጡ ይህን ልመናዬን ስሙ፤ ሰነፍ የኾኑትን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመሄድን አስፈላጊነት አስተምሯቸው፡፡ የትምህርቷን ውበት ቀምሳችኋልና እናንተ ያወቃችሁትን ሳያውቁ እንዳይቀሩ፡፡

     ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት እንጂ የነፍስ ፍርድ ቤት አይደለችም። የኃጢአትን ስርየት ትሰጣለች እንጂ ኃጢአትን አትፈርድም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደምናገኘው ምስጋና በሕይወታችን ውስጥ እንደዚህ ያለ አስደሳች ነገር የለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ደስተኞች ደስታቸው ይበዛላቸዋል፡፡ የሚጨነቁት፤ ያዘኑት፣ ሰላምን ያገኛሉ፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ፤ የተቸገሩ ሰዎች እፎይታ ያገኛሉ፤ ኹሉም ከተሸከሙት ያርፋሉ፡፡

    ቤተክርስቲያን ኹሉን ታቅፋለች፡፡ ውስጥ ከሆንክ ተኩላው አይገባም፣ ብትሄድ ግን አራዊቶች ይይዙሃል፡፡ ከቤተክርስቲያን አትራቅ፣ ከቤተክርስቲያን የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን መዳንህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን ከሰማያት ከፍ ትላለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከድንጋይ ትከብዳለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከዓለም ትስፋለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን አታረጅም፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እራሷን ታድሳለች፡፡

"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ በመከራና በኃጢአታችሁ የከበደ ኹሉ' ወደ እኔ ኑ" ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡" (ማቴ ፲፩፥፳፰)
ይህንን ድምጽ ከመስማት የበለጠ ምን ደስታን ሊሰጠን ይችላል? ከዚህ ግብዣ የበለጠ ጣፋጭ ምንድነው? ጌታ ወደ ቤተክርስቲያን የሚጠራችሁ ለታላቅ ግብዣ ነው፡፡ ከትግል ወደ እረፍት፣ ከስቃይ ወደ እፎይታ ያሸጋግራችኋል፡፡ ከኃጢአታችሁ ሸክም ያገላግላችኋል፡፡ ጭንቀትን በምስጋና፣ ሐዘንንም በደስታ ይፈውሳል፡፡ለክርስቶስ ከሚኖረው በቀር በእውነት ነጻ፣ በእውነት ደስተኛ የሆነ ማን ነው? እንዲህ ያለው ሰው ክፋትን ኹሉ ያሸንፋል ምንም አይፈራም!ቤተ ክርስቲያን ለኹሉም መጠጊያ ሆና ቆማለች፡፡

   የአምላክን ትዕዛዝ የምትፈጽም መልካም ሰው ከሆንክ ቅድስናህን ለመጠበቅ ግባ፤ ኃጢአተኛ ከሆንህ መዳንን ለማግኘት እርምጃህን ፈጠን አድርገው:: የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሳይሰሙስ እንዴት ነፍስን ወደ መልካም መንገድ መምራት ይቻላል?የእግዚአብሔር ቃል 'ብርሃን' በመባል ይጠራል፤ ፀሐይ ከምታፈልቀውና እኛም ከምናየው ብርሃን፣ እጅግ በጣም የከበረ ብርሃን፣ የነፍሳችንን ጥልቀት የሚያበራ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ እውነት እንዲህ ሲል መስክሯል፣ “በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው::"

    ከእናንተ መካከል በታማኝነት ቤተ ክርስቲያን የምታገለግሉ፤ 'ስራ በዛብኝ፣ ልመጣ አልችልም' እንዳይሉ ሌሎቹን ምከሩ፡፡ ወደ ንጉሡ ግብዣ የተጋበዙ ግን መምጣት ያልቻሉትን እንደ ምሳሌ እንመልከት፡፡ አንደኛው አምስት ጥማድ በሬዎችን ሊገዛ እንደሄደ ተናገረ፣ ሌላው አዲስ መሬትን ሊገዛ እንደሄደ ሲናገር ሌላው ደግሞ ሚስት ማግባቱን ተናገረ፡፡ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን፣ ንጉሡ ግብዣውን ንቀው ስለቀሩ የሚታገሳቸው ይመስልሃል? እናም ንጉሡን በሰበብ አስባቡ አታናዱት፡፡

  ከጊዜህ ላይ አንድ ሰዓት ያህል እንኳን መቆጠብ ያቅትሃል? ቤተክርስቲያንን ከተሳለሙ በኋላ ወደ ሥራ መሄድ በእውነት ይህን ያህል ከባድ ነውን? አንድ ሰው ወርቅ፣ ብር፣ ማር ወይም ወይን በነጻ እየሰጠ ነው ቢባል፤ ማንም ሳይቀድማችሁ ለመድረስ አትቸኩልም? ነገር ግን፣ ከወርቅ የሚበልጥ፣ ከማርም ከወተትም የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማድመጥ ወደ ቤተክርስቲያን የምትመጡት አልፎ አልፎ ነው፡፡

   ስለዚህም፣ ይህን ችላ ማለታችሁን አውግዣለሁ፤ ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ያላችሁን ግድየለሽነት እቃወማለሁ፡፡ ከመንፈሳዊ ትምህርቶቿ በመራቃችሁ፣ በውስጣችሁ የእግዚአብሔር ፍራቻ የለም፤ እግዚአብሔርን የማትፈራ ነፍስም ለኃጢአት የተገዛች ትሆናለችና ነፍሳችንን እንጠብቃት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው

https://t.me/Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

07 May, 16:53


1000608839295

Asefa Abera & Tezerach Fikre

ማር ይስሐቅ

28 Apr, 16:45


ወደ ፈጣሪያችን በቃል ሳይሆን በተግባር የምንመለስበት ሳምንት ይሁንልን!
@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

12 Apr, 20:31


https://www.tiktok.com/@dn_yishak_kelemework/photo/7356715062100233478?_r=1&u_code=e5550g2911k2jl&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=e55503klgbl4cc&share_item_id=7356715062100233478&source=h5_m&timestamp=1712932199&user_id=7171054631740982278&sec_user_id=MS4wLjABAAAA4GlMFMdzyEXbekarR6OKQYnozmr5pdfk8Fo_q8A8wETkQ2x6b-ZbsKQVuA_5cskO&aweme_type=150&pic_cnt=1&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7323179210347579141&share_link_id=4ab1efc5-1d6b-4611-9ca2-2712a0c10e39&share_app_id=1233&ugbiz_name=UNKNOWN&ug_btm=b8727%2Cb2878&enable_checksum=1

ማር ይስሐቅ

09 Apr, 06:04


እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ ፣ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ 29:27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከነዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር

በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም
ዓይን ያላየችውን
ጆሮ ያልሰማውን
በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

መንፈሳዊው መንገድ
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንደ ጻፉት
አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።
@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

08 Apr, 17:06


እንዴት አረፈዳችሁ ?
    2 ቀን ብቻ ነው የቀረው !!!
cbe 1000214420477

(በመርዳት እና ሼር በማድረግ ተባበሩኝ) ወንድማችን  ቢኒያም ሐለፎም
የ 23 ዓመት ወጣት ሲሆን
ተወልዶ ያደገውም በአዲስ አበባ(አየር  ጤና )
ሲሆን በአሁን ሰዓት ላይ በሊቢያ ስለተያዘብን እሱን በህይወት ለማስለቀቅ 1,200,000(አንድ ሚልየን ሁለት መቶ ሺ ብር  ) ስለተጠየቅንና የሰጡን ጊዜ የ 1 ሳምንት ጊዜ ብቻ ስለሆነ፤ ቤተሰቦቹ ደግሞ የመክፈል አቅም ስለሌለን
እንድታተርፉልን በፈጣሪ ስም እንማጸናለን።
ሁላችሁም ከጎናችን ሁኑ 🙏🙏
50 ሎሚ ለ 50 ሰው ጌጥ ነው ።

ማር ይስሐቅ

08 Apr, 05:45


ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫው🙏🏽
***

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሰ አሐዱ አምላክ አሜን
++++++++++++
የጋራ የስምምነት ነጥቦች
ፍኖተ ጽድቅ በአንድ በኩል የአቶ ጸጋዬ ደበበ ሱፐር ደብል ቲ ሮዳስ የሮቶና ቀለም ፋብሪካ ሠራተኞች የመንፈሳዊ ትምህርት መማሪያ ማኅበር ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የማኅበሩ የዩቱብ ሚዲያ ስያሜ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በማኅበሩ አገልግሎትና የማኀበሩ ሚዲያ በአሠራጫቸው ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ላይ የትምህርተ ሃይማኖት፣ የሥርዐተ አምልኮና የትውፊት ጥያቄዎች ሲቀርቡበትም ነበር፡፡
በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር ጉባኤና በጉባኤው በሚመደቡ መምህራንና መዘምራን፣ በጉባኤው በሚሰጡ ትምህርቶችና በሚዘመሩ መዝሙራት፣ በመዝሙር መሣሪያዎች አጠቃቀምና የአዘማመር ስልቶች ላይ ጥያቄዎች ሲነሡና አንዳንድ ጊዜም በአንዲት የቤተ ክርስቲያን ልጆች መካከል የልዩነትና የውዝግብ ምክንያት ሲሆንም ታይቷል።
ይህን ተከትሎም የፍኖተ ጽድቅ ማኅበር ኦርቶዶክሳዊ መሠረተ እምነትን፣ ሥርዐተ አምልኮንና ትውፊትን ብቻ ማዕከል አድርጎ ማገልገል በሚያሰችሉት ጉዳዮች ላይ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምህራነ ወንጌልና በማኅበራዊ ሚዲያ በፍኖተ ጽድቅ ላይ አተኩረው የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን የሚሠሩ ወንድሞች፤ የፍኖተ ጽድቅ መሥራች ከሆኑት ከአቶ ጸጋዬ ደበበና ከማኅበሩ አመራሮች ጋር ለበርካታ ጊዜያት ውይይትና ምክክርም ሲያደርጉም ቆይተዋል፡፡ የተለያዩ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱም ሲያሳስቡም ሰንብተዋል።
ይልቁንም በማኅበራዊ ሚዲያ የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን በፍኖተ ጽድቅ ላይ አተኩረው የሚሠሩ ወንድሞች ፍኖተ ጽድቅን በተመለከተ ሰነድ አዘጋጅተውና ፍኖተ ጽድቅም በሰነዱ ለተነሡ ጥያቄዎች ማብራሪያ እንዲሰጥም ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ መልኩ ለረጅምና ለተደጋጋሚ ጊዜያት በተደረጉት ውይይቶችና ምክክሮች የፍኖተ ጽድቅ መሠረታዊ ችግሮች ተብለው የተለዩት አምሰት ነበሩ፡፡ መተማመን እና ስምምነት ላይ የተደርስባቸውም ችግሮች ፦
**
1)
ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርትን አዛብቶ   ማስተማር፤
2) ከኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትና የአዘማምር ይትባሃል ያፈነገጡ መዝሙራትን መዘመር፤
3) ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቀኖኗ ከፈቀደቻቸው የዜማ መሣሪያዎች ውጭ የሙዚቃ መሣሪያዎችን መጠቀም፤
4) በማኅበሩ ጉባኤ ላይ የሃይማኖት ነቀፋ ያለባቸው አንዳንድ መምህራን እንዲያስተምሩ መመደብ፤
5) በፕሮቴሰታንት መድረኮች ላይ ሲዘምሩ የነበሩ ዘማርያን በማኀበሩ የኅብረት መዘምራን ውስጥ አባል ሆነው መገኘታቸው ናቸው፡፡
*****
ፍኖተ ጽድቅ እነዚህን መሠረታዊና ጉልህ ችግሮች አርሞና አስተካክለሎ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት የራሱን በጎ አሰተዋጽኦ እንዲያበረክት፤ ኦርቶዶክሳውያን ታዛቢዎችና አወያይ ኮሚቴዎች በተገኙበት የፍኖተ ጽድቅ መሥራች ከሆኑት ከአቶ ጸጋዬ ደበበና ከሥራ ሓላፊዎቻቸው እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ ፍኖተ ጽድቅ ላይ አተኩረው የዕቅበት እምነት ሥራዎችን ከሚሠሩ ወንድሞች ጋር  ሰፋፊ ውይይቶች ተደርገዋል። በውይይቱም መሠረት ፍኖተ ጽድቅን በተመለከተ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ እነዚህም፦
1. በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር በመደበኛ መምህርነት ተቀጥረው የሚያስተምሩ መምህራን ማስተማር አቁመው በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ገዳም ሔደው ጥሞና እንዲወስዱና በሚመደቡላቸው ኦርቶዶክሳውያን መምህራን ሥልጠና እንዲወስዱ፤

2. ከኦርቶዶክሳዊ መሠረተ እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮና ትውፊት ያፈነገጡ መዝሙራትም ሆኑ ያልሆኑ ከፍኖተ ጽድቅ የዩቱብ ቻናል ሙሉ በሙሉ እንዲወርዱ፤

3. ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለመዝሙር አገልግሎት ከምትጠቀማቸው የዜማ መሣሪያዎች ወጭ ያሉት የሙዚቃ መሣሪያዎችና ማቀናበሪያዎች በሙሉ እንዲወገዱ፤

4. በኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትና የዜማ መሣሪያዎች አጠቃቀም ላይ የፍኖተ ጽድቅ የኅብረት ዘማርያንና የዜማ መሣሪያ ተጫዋቾች ሥልጠና እንዲወስዱ፤

5. ፍኖተ ጽድቅ ወደፊት በሚሰጣቸው የትምህርትና የመዝሙር አገልግሎቶች ኦርቶዶክሳውያን መምህራንና ዘማረያን ብቻ እንዲያገለግሉ፤

6. የፍኖተ ጽድቅ መሥራችና የሥራ ሐላፊዎች ኦርቶዶክሳውያንን ይቅርታ እንዲጠይቁ፤
7. በፍኖተ ጽድቅና በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን መምህራን ላይ አተኮረው የሠሩ ቲክቶከሮች የሠሯቸውን ቪዲዮዎች እንደያወርዱ፤ መምህራኑም እንዲሁ እንዲያደርጉ።

እነዚህ ስምምነቶች ላይ ለመድረስ የአቶ ጸጋዬ ደበበ ቅንነት የተሞላበት ውሳኔ ታሪክ የሚዘነጋው አይደለም። በእነዚህ የጋራ ስምምነት መሠረትና የወደፊቱን አገልግሎት በማሰብ ፍኖተ ጽድቅ የሚከተሉትን የእርምት እርምጃዎችን ወስዷል፡፡                                             
1. የፍኖት ጽድቅ መደበኛ መምህራን ማስተማር አቁመው በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና እና ጥሞና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው፤
2. ኦርቶዶክሳዊ መሠረት እምነት ፣ ሥርዓት አምልኮ ፣ ትውፊት የተላለፋም ሆኑ ያልተላለፋ መዝመሮች በሙሉ ከዩቱብ ቻናል እንዲውርድ ተደርጓል፤
3. ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የዜማ መሣሪያ ውጭ የሆኑ የሙዚቃ መሣሪያዎች በማኀበራዊ ሚዲያ የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን የሚሠሩ ወነወድሞቻችን በቪዲዮ እየቀረጹና ታዛቢዎች በተገኙበት ሙሉ በሙሉ ተወግደዋል፤
4. ፍኖተ ጽድቅ ለተፈጠረው ትምህርት ሃይማኖት እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መተላለፍና ውዝግብ ምክንያት በመሆኑ ይቅርታ ጠይቋል።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የዚህ መርሐ ግብር ተሳታፊዎች!
ዛሬ እዚህ ደረጃ ለመድረስ ብዙ ዋጋ ተከፍሏል። በርካታ ሌሊቶችን ያለን እንቅልፍ አንግተናል። በእነዚህ ሌሊቶች ተሰባስበናል፤ ተውያይተናል፤ ይበጃል ያልናቸውን መፍትሔዎች ጠቁምናል፤ ክፋና ደግ ተነጋግረናል፤ ተጨቃጭቀናል፤ ተከራክረናል፤ ተለቃቅሰናል፤ ይቅርታ ተጠያይቀናል፤ በአጭሩ የብዙ ብዙ ሆነናል። ሂደቱ መራራና አድካሚ ቢሆንም፤ በአደባባይ ከመነቃቀፍና ከመዘላለፍ ወጥቶ፥  በርን ዘግቶ ችግሮችን በውይይትና በምክክር የመፍታትን ዋጋ በሚገባ  እንድንረዳ አግዞናል።
ይሁንና ድል አድራጊዋ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ድል አድርጋለች። አሸናፊዋ ቤተ ክርስቲያን በማሸነፏ፥ ሁላችንም አሸንፈናል፡፡ አንዱ አሸናፊ፤ ሌላው ተሸናፊ አልሆነም፡፡
የእኛ ድርሻ ፍኖተ ጽድቅን እስከዚህ ማምጣት ነው። ፍኖተ ጽድቅን ማጽናትና መዋቅራዊ መልክ ማሲያዝና መቆጣጠር የቤተ ክርስቲያን ድርሻ ነው። ይህ ማለት ግን ፍኖተ ጽድቅ እንደከዚህ ቀደም መሠረት እምነትን፣ ሥርዓት አምልኮንና ትውፊትን ሲተላለፍና ሲጥስ አፋችንን ዘግተን፤ እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጣለን ማለት ግን አይደለም። እነርሱ በተለወጡ ማግስት እኛም በእነርሱ ላይ ያለን አቋም እንደሚለወጥ ከወዲሁ ለማሰሰብ እንወዳለን። ከዚህ በተረፈ እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ፍኖተ ጽድቅን በሁሉም ነገር ለመተባበርና ለማገዝ ዝግጁ መሆናችንን በታላቅ አክብሮት ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ማር ይስሐቅ

05 Apr, 19:00


በአንዳንድ መምህራን ዘንድ የጌታ ምጽዓት
1. እለቱ: - እሑድ
2. ወሩ: - መጋቢት
3. ቀኑ: - 29
4. ዘመኑ: - ዮሐንስ
5. ??? ተብሎ ይነገራል

እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዘንድሮ ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች ተገጣጥመዋል እና ዘንድሮ የዓለም ፍጻሜ ይሆን? 😥😥😥

እስቲ ይህንን እናስተውል

ዘንድሮ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2016 ዓ.ም ነው።

በጌታ ዘንድስ?

“እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመትሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።”
2ኛ ጴጥሮስ 3፥8

እናም በጌታ ዘንድ ዘንድሮ መጋቢት 29 ነው?

አናውቅም።

ሲጀመር ጌታ ከቀን አቆጣጠር ውጪ ነው።

የቀን አቆጣጠር ከመፈጠሩም በፊት ነበርና።

ለምሳሌ አዳምን ለማዳን 5,500 ዘመን ሲፈጸም ተወለደ እንላለን
ነገር ግን በጌታ አቆጣጠር 1 ሺህ ዓመት እንደ 1 ቀንም ስለሆነ 5 ቀን ከግማሽ ብለንም እንናገራለን።

ሌላውና 5ኛው ነጥብ

“እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።”

ተብሎ በዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 13 ከቁጥር 13 ላይ የተነገረለት  ሐሰተኛው ክርስቶስስ መች መጣ?

በዮሐንስ ራእይ የተቀመጠው ቃል ገና መቼ ተፈጸመ?

ስለዚህ የጌታን አቆጣጠር አናውቅምና ተዘጋጅተን እንጠብቅ
እስከዚያ ድረስ ይህችን ዓመት ተወን? እንበል።

@Gamel_Media