ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

@joinchat_yonas_holet_debreedom


በዚህ ቻናሌ ላይ የኦርዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ትምህርቶች፣መዝሙሮች፣እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛሉ። ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

22 Oct, 05:40


# ቅዱስ ሚካኤል
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ’ ካ-ከመ’ ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡

🔷👉 ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡

🔵👉 ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡

🔴👉 በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።
በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።
( ኦሪ ዘፀ 23፥20–21)

🔶👉 በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

👉 ሚካኤል ማለት “ከመ እግዚአብሔር እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?” ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው?
መልሱ የለም ነው፡፡

🔵👉 ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል ፣መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ ናቸው፡፡

🔴👉 መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ፣ ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡

🔵👉 መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡

👉 መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡

🔷👉 ለዝክረ ስምከ፦

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልኝ።

🔶👉 ለአዕይንቲከ፦
ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! ለሰው ልጅ ይቅርታን ለማስገኝት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅበው ለሚማልዱ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል።

🔴👉 ለገጽከ፦
ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! መሬትና ውኃ ያልተቀላቀለበት ከነፋስና ከእሳት ብቻ ለተፈጠረው መልአካዊ ገጽታህ ሰላም እላለሁ።

👉 ለርእስከ፦
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ ፍጹም የማዳንህን ትድግና በኔ ላይ ትገልጽ ዘንድ፥ በስተቀኜ ቁመህ አለሁልህ በለኝ እንጂ በሩቅ ሆነህ አትመልከተኝ።

👉 ለስእርተ ርእስከ፦
የእግዚአብሔር ባለሟል ሆይ፤በእግዚአብሔር ፊት በጐ መዓዛ ያለውን መሥዋዕት የምታሳርግ አንተ ሚካኤል ነህና።

የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ፣ጸሎትና ጥበቃው ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

21 Oct, 20:04


https://youtu.be/Zt_nyTmKtM4?si=75AFQ-GnPCWjGyf4

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

20 Oct, 03:45


https://youtu.be/JbrWaH8nej4?si=V9wz4p4Fs6Qqu6GX

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Oct, 19:06


https://youtu.be/KvXp7B06iJ4?si=otzBbVFozTT0tCvH

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Oct, 14:59


ሆለታ ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

18 Oct, 06:25


#ጻድቁ_አባታችን_አባ_ኪሮስ 
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
  🔴👉 አባታቸው ንጉሥ ዮናስ
            እናታቸው   አንስራ   ይባላሉ።

   🔷👉  የቀደመ ስማቸው ዲላሶር የተሰኘ ሲሆን
    ሁለተኛ ስማቸው ደግሞ ❖ #ኪሮስ ❖

            🔴👉 በታህሳስ 8  ቀን ተወልደዋል
በ8 ዓመታቸው ያላቸውን ገንዘብ ከወንድማቸው ጋር በመካፈል ወደ አባ በብኑዳ ገዳም ገብተዋል።

👉 እስከ 17 ዓመታቸው ረድዕ ሆነው እያገለገሉ ስርዓተ ምንኩስናን ከተማሩ፤ ከተረዱ በኋላ የምንኩስናን ማዕረግ ተቀብለዋል።

🔵👉 ስለ እግዚአብሔር ፍርድ እንዲሁም ስለ ሰው ልጆች ይቅርታ 40 ዓመት በመሬት ላይ ተኝተው ስጋቸው ከመሬት ጋር ተጣብቆ ሣር እስኪበቅልባቸው ድረስ ጸልየዋል።

🔵👉 ጌታችንም ስለ መታመናቸው እና ስለ ተጋድሏቸው አክብሯቸዋል ።

👉 ቃል ኪዳናቸውም ፡-  መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡

🔷👉 በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ  ሐምሌ 8 አርፈዋል።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ኪሮስ
  🔹ምልጃና በረከታቸው አይለየን
       
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
    ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

  ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
      ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም
                 ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

17 Oct, 16:57


https://youtu.be/8L8wb3RaPd8?si=4YQlnIWfj3jt9cyp

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

17 Oct, 04:35


#ስላሴን_ለምን_ቅድስት_ስላሴ
               🔴#እንላለን?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 ሥላሴን  ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር፡-

🔶👉 አንድም ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብሎ አይጠረጠሩም፡፡

🔵👉 አንድም ሴት በባህሪዋ ልጅን ታስገኛለች፣ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ፡፡

🔴👉 አንድም ሴት አዛኝ ናት፣ለታናሹም ሆነ ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ፣ ይራራሉ፣ ምህረትን ይሰጣሉ፡፡

🔵👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ”ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንፃር
ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ የምህረት ወንዶች ሥላሴ" በማለት ያመሰጥራል፡፡

🔶👉 ስለእዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው፣ ርህራሄያቸውና፣ ይቅር
ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡
አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም፣ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያቢሎስ እጅ ተይዞ በሐጥያት እንዲታመሙ አይወዱም፣ አይፈቅዱም በመሆኑም “ቅድስት” ይባላሉ፡፡

🔴👉 አንድም ሴት የልጇን ነውር አትፀየፍም ልጄ ቆሽሿል፣ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም፣ ሥላሴም የሰውን በሐጥያት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎብኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንጻር ቅድስት እንላቸዋለን፡፡

🔴👉 አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እነደዛው ናቸው በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ፡፡ ስለእዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንፃር ቅድስት ይባላሉ፡፡

በዚህ ምክንያት ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን በፍቅር እንጠራለን፡፡

🔷የቅድስት ሥላሴ ረድኤት በረከት አይለየን🔷

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
    ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

  ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
      ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም
                 ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

16 Oct, 04:25


https://youtu.be/gt0cfy_hsZw?si=Pr094Y2XutXHC-Y4

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

14 Oct, 17:52


#ጥቅምት_5 #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 የቅዱስ አባታችን 👉 አባታቸው ስምዖን
👉 እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ::

🔷👉 እነርሱም ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል :: ታዲያ አንድ ቀን አቅሌያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን " ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ የሚል ድምጽ ሰማች ::

በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ

🔴👉 ፃዲቁ አባታችን አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንደሚያርፍ ሁሉ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው " ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን " ብለው በማመስገናቸውና ኋላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላእክትን ይመስላሉ ። አባታችን ገና በተወለዱባት ዕለት ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ በማለት ለሥላሴ ምስጋና አቅርበዋል።

🔵👉 ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ከአንድ አበምኔት ደጃፍ ወስዶ አኖራቸው :: አበምኔቱም አባ ዘመደ ብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ #ፍሱሐ_ገጽ ሆኖ አግኝተዋቸዋል :: አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአርገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።

🔷👉 በገድለህ በትሩፋትህ ከሞት ነፍስ ከርደተ ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ :: ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው :: ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? " #ዘኬድከ_ጸበለ_እግረከ_ይልህሱ_ወበ_ውእቱ_ይጽግቡ ።" የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ :: ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ ::

🔵👉 ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር ።

🔷👉 ከዚህ በኋላ ሑር ምድረ ኢትዮጵያ " ወበህየኒ ሐልውከ ነፍሳተ ወታወጽኦሙ" ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው :: ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ #ምድረ_ከብድ አድርሷቸዋል :: ዳግመኛም ወደ #ዝቋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጸልዩ ነበር ::

🔴👉 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ #ዘገብረ_ተዝካርከ_ወዘጸውአ_ስመከ_እምህር_ለከ " (ስምህን የጠራውን መታሰብያህን ያደረገውን ምሬልሃለው ) ብሎሀል አላቸው :: እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል :: ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ " #ተንስእ_ወጻእ_መሀርኩ_ለከ_ኵሎ_ኢትዮጵያ ( ተነስተህ ውጣ መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ) ብሏቸው ወጥተዋል ::

🔷👉 ከዚህ በኋላ #ምድረ_ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7 አመት እንደ አምድ ተክል ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ እጃቸውን ሳያጥፉ ራሳቸውን ዝቅ ሳያደርጉ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ወደ ሰማይ አቅንተው ቆመው ጸልየዋል ::

🔴👉 ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ ( በቁራ ተመስሎ) መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው :: 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አይናቸውን አድነዋቸዋል ::

🔴👉 ለ100 ዓመት ሕዝበ ኢትዮጵያን ማርልኝ ብለው በዝቋላ ተራራ በሚገኘው ሐይቅ ተዘቅዝቀው ለምነው የምሕረት ቃልኪዳንን የተቀበሉበት እንዲሁም እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው። ነገር ግን ይህ ዕለት በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ስለሚውልና ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ስለሚከለክል።

🔵👉 ዓብይ ፆም የጽሞና የጸሎት ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ደስታ የለም ስለዚህም መጋቢት 5 ይከበር የነበረው የአባታችን የዕረፍታቸው መታሰቢያ ወደ #ጥቅምት_5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተወስኖልናል።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት አይለየን

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

14 Oct, 12:14


https://youtu.be/khHD0Nuw1wU?si=aY55oJXOfSWq_4F5

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

11 Oct, 14:11


ማኅሌተ ጽጌ 2ኛ ሳምንት

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

3,556

subscribers

1,680

photos

18

videos