የተዋሕዶ ፍሬዎች

@yetewahedofera


Buy ads : here
https://telega.io/c/yetewah
🎯 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
👉 መዝሙር
👉ብሒለ አበው
👉ስብከት
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
🎯የሚለቀቅበት መንፈሳዊ ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ

የተዋህዶ ፍሬዎች መንፈሳዊ ቻናል
ለአስተያየት 👉 @Teyaka_Lemtykebot
ማስታወቂያ ለማሰራት ከፈለጉ @fikreabe ላይ ያናግሩን

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Oct, 19:11


👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 ግብረ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ወደ ቦቱ ይግቡ 👇👇

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Oct, 19:01


የመጥምቁ ዩሐንስ አባት ስም ማን ይባላል?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Oct, 16:52


" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው


ድምፀ ተዋሕዶ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Oct, 11:32


የተዋሕዶ ፍሬዎች pinned «»

የተዋሕዶ ፍሬዎች

21 Oct, 12:10


#ሼር
#የካህኑን_ልጅ_እንድረስላት

በዓለም ዙርያ የምትኖሩ ልጅ የምትወዱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቼ በምስሉ የምናያት ህጻን ስርጉት ጥዑመ ልሳን ትባላለች።

ገና የአንድ አመት ከስምንት ወር ህጻን ስትሆን ዕድሏ ሆኖ መናገርም መንቀሳቀስም በሰላም መተንፈስም መቦረቅም አልቻለችም ከተወለደች ጊዜ ጀምሮ በህመም ላይ ነችና።

ወላጆቿ ምንም ገቢ ስለሌላቸው የተሻለ ህክምና ማግኘት አልቻለችም። ዛሬ ላይ #ወገን_ቢያግዘን_የተሻለ_ህክምና ብንሞክርላት ብለው ፊታችን ቆመዋልና ደጋግ ወገኖቻችን ከቻላችሁ በገንዘብ ካልቻላችሁ በሀሳብ፣ በጸሎትና ለሌሎች ረጂዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንድታግዟቸው እንማጸናችኋለን።

ቄስ ጥዑመ ልሳን ገደፋው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000561662014

ለበለጠ መረጃ
ቄስ ጥዑመ ልሳን ➛ +251967438386

የተዋሕዶ ፍሬዎች

21 Oct, 11:12


በሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚጋባ ሁሉ ጤንነትም ከሰው ወደ ሰው ይጋባል ጤናማ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር መዋል ጤናማ ያደርጋል!

መጽሐፍም እንዲህ ይላል “ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።” መዝሙር 18፥25-26

አብራችሁ የምትውሏቸው ሰዎች በእናተ ሕይወት ላይ በጎም ክፉም ተጽኖ አላቸው። ማንነታችሁ የሚወሰነው አብራችሁ በምትውሏቸው ሰዎች ነውና አብሯችሁ የሚውሉ ሰዎችን ምረጡ ። መልካም ነገር እንኳን ቢኖራችሁ “አትሳቱ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።” 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥33 እና ተጠንቀቁ
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

21 Oct, 04:45


የተዋሕዶ ፍሬዎች pinned «»

የተዋሕዶ ፍሬዎች

20 Oct, 17:46


አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት

"ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?"
ቅዱሱ አባት መለሰለት

"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው

ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው

ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል

ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው
በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

⛪️⛪️⛪️⛪️

ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል።

⛪️⛪️⛪️⛪️

"ፍቅር እንዴት መቆጣት እንዳለበት አያውቅም"
ቅዱስ ማር ይስሐቅ

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም ይፈርዱበታል።
⛪️⛪️⛪️⛪️

“የሚጾሙ የሚጸልዩና የሚተጉ ድቃቂ ሳንቲም እስካላስወጣቸው ድረስ በምንም ነገር ላይ የሚገኙ በችግር ላይ የሚሰቃዩትን ግን ዞር ብለው የማያዩ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ" ቅዱስ ባስልዮስ

⛪️⛪️⛪️⛪️

"እኛ መነኮሳት ነን:: እኛ የሠለጠንነው ሰዎችን ለመግደል ሳይሆን ምኞታችንን ለመግደል ነው" አባ ጴኤሜን

★ ★ ★
አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?
ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?
ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?
ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?
ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?
መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?
ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?
በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?
የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?
ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?
ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

ምንጭ: Orthodox Notes (ON)
ትርጉም: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

20 Oct, 06:13


share ይደረግ
🌐 @Ortodoxawit_wallpaper 🔂
🌐 @Ortodoxawit_wallpaper 🔂

የተዋሕዶ ፍሬዎች

20 Oct, 06:13


🌺በድንግል አማረ ህይወቴ🌺

በድንግል አመረ ህይወቴ
በማርያም አማረ ህይወቴ
ስጠራት ገብታልኝ ከቤቴ

በድንግል አማረ ከሞት መሀል ነጥቀሽ
በድንግል አማረ ነፍስን ዘራሺብኝ
በድንግል አማረ ሀጢያተኛ ሳለሁ
በድንግል አማረ ሰው አድርገሽ አ
ቆምሺኝ
በድንግል አማረ ሀዘን መከራዬ
በድንግል አማረ ታሪክ ሆኖ ቀረ
በድንግል አማረ ህይወቴም በአንቺ
በድንግል አማረ በድንግል አማረ
በማርያም አማረ
              አዝ====

በድንግል አማረ ሀጢያትን አብዝቼ
በድንግል አማረ ለምፅ ቢያጠቃኝም
በድንግል አማረ አንቺ እያነፃሽኝ
በድንግል አማረ ዳግም ብጨቀይም
በድንግል አማረ እሩሩ ነሽና
በድንግል አማረ ምልጃሽ አይዘገይም
በድንግል አማረ ስምሽን ስጠራ
በድንግል አማረ አታሳፍሪኝም(×፪)
               አዝ====

በድንግል አማረ ሀዘኔ በርትቶ
በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድመኝ
በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ
በድንግል አማረ ሁሉ ፊቱን ሲያዞርብኝ
በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሺልኝ
በድንግል አማረ ስሜ ተቀየረ
በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ
በድንግል አማረ በድንግል አማረ
በማርያም አማረ
                   አዝ====

በድንግል አማረ ሀዘኔ በርትቶ
በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድመኝ
በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ
በድንግል አማረ ፊቱን ሲያዞርብኝ
በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሺልኝ
በድንግል አማረ ስሜ ተቀየረ
በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ
በድንግል አማረ በቃጥላ አማረ
በግሸን  አማረ
share
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Oct, 05:35


ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።

ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን🌸

የተዋሕዶ ፍሬዎች

18 Oct, 06:46


“እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።”
— ማቴዎስ 7፥1-2

“አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።”
— ሉቃስ 6፥37

“በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።”
— ሮሜ 14፥1


አትፍረዱ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

18 Oct, 04:59


እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ  እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

15 Oct, 18:33


ቅምሻ - ፩

አሐቲ ድንግል - አንዲት ድንግል

ድንግል ማርያም ለምን አንዲት ድንግል ትባላለች?

እመቤታችን ድንግል ማርያም በምድርም በሰማይም አቻ የማይገኝላት አንዲት ድንግል ናት። ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌልም የምትልቅ በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች በወንጌል የተፃፈች አንዲት ድንግል አለች። ይላል ቅዱስ ያሬድ።

ከዚህም ተነስቶ አንድ ሰው ተነስቶ በወንጌል ሌሎች ደናግል የሉምን? ስለምን በወንጌል የተጻፈች አንዲት ድንግል ትላለህ? ብሎ ቢጠይቀው ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌል የምትበልጥበት የድንግልና ዘውድ ያላት አንዲት ድንግል አልኩህ እንጂ ደናግላንማ ብዙ ደናግል አሉ ብሎ ይመልስለታል።

ቀጥሎም በመላዕክት ክንፍ የምትጋረድ በክብሩ መንበር በፊት ምህረት የምትለምን በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊል የተቀዳጀች አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል አለች።

አሁንም ቅዱስ ያሬድን ስለምን አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል ትላለህ አርሱ የመረጣቸው ብዙ ደናግላን የሉምን? ብሎ የሚጠይቀው ቢኖር፥ አማኑኤል ሥጋን ይለብስ ዘንድ የመረጣት፤ ከእርስዋም ሥጋን ለብሶ አማኑኤል የተባለባት፥ በመላእክት ክንፍ የምትጋረድ፥ እግዚአብሔር በክብሩ ዙፋን በፊቱ ለመቆም የመረጣት፥ በእናትነት የሰለጠነ የባለሟልነት ዘውድን የተቀዳጀች አንዲት ድንግል አልኩ እንጂ እርሱ የመረጣቸው ደናግላንማ ስንቱ! ብሎ ይመልስለታል።

ደግሞም ፀጉሯ እንደ ሐር ፈትል ያማረ፥ የአንደበቷ መዓዛ እንደ እንኮይ የጣፈጠ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች የልዑል ንጽሕት አዳራሽ የሆነች አንዲት ድንግል አለች።

የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆኑ ሌሎች ደናግላን የሉምን ስለምን ለይቶ እርሷን አንዲት ድንግል አለ ቢሉ? ከእርሷ ስጋ ይነሳ ዘንድ እግዚአብሔርን በማህፀኗ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የወሰነች እውነተኛ የእርሱ ማደሪያ ሌላ ድንግል ከማርያም በቀር ወዴት አለ ይለዋል! ብቻዋን የእግዚአብሔር መቅደስ ለመሆን የበቃች እንደሆነች ሁሉ ከቅዱሳን ሁሉ ተለይታ በእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው እንደ እንኮይ የጣፈጠ አማላጅነት ያላት አንዲት ድንግል እርሷ ብቻ ናት! ስለዚህ እንደ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችን ብቻዋን አንዲት ድንግል የተሰኘችበት ወላዲተ አምላክነቷ፤ ንፅሕናዋ ፤ማኅደረ መለኮትነቷ አማላጅነቷ እና ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ ናቸው ማለት ነው።

፩.በድንጋሌ ሥጋ ዘለዓለማዊ
በተፈትሆ የማይመረመር ድንግልናዋ ነው። ይህም ሥስት የማይመረመሩ ግብራት አሉት። ድንግል እንደሆነች መፀነስ፥ ድንግል ሆና ሳለ መውለዷ፥ ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና መኖሯ ናቸው። እነዚህ በህገ ተፈጥሮ የማይታሰቡ ረቂቅ ግብራት ናቸው። ሰው ድንግል ሆኖ ያለ ወንድ ዘር መፀነስ አይቻለውም፥ በድንግልና እያለ የፀነሰ መሆን አይችልም፥ ሰው በድንግልና መውለድ አይቻለውም፥ ከወለደ በኋላ ደግሞ ድንግል መሆን እንዴት ይችላል? ድንግል የሆነች ሌላ ሰው እናት አይደለችም፥ እናትም ከሆነች ድንግል አይደለችም። ይህ ለአንዲቱ ለድንግል ማርያም ብቻ የተቻለ ነው።

፪. ድንግል በቃሏ - በቃሏም ድንግል
የቃል ድንግልና በሦስት ወገን ነው። እኒህም ክፉ አለመናገር፥ ምስጋና አለመብላትና በጎውን መናገር ናቸው። ሰው በንግግሩ ብዙ ኃጢአቶች ይሰራል። ሐሜት፣ ማጉረምረም፥ ቁጣ፥ ብስጭት፥ መዋሸት፥ መርገም፥ መሳደብ፥ ዋዛ ፈዛዛ፥ ያለጊዜው መሳቅ መሳለቅ፥ ዘፈን፥ ተውኔት፥ ድንፋታ፥ መንፈግ ነገር ማመላለስ፥ ቃል መለዋወጥ፥ አደራ መብላት፥ በሀሰት መማል፥ ሰጥቶ መንሳት፥ ክህደት፥ ማታለል፥ ማስነወር፥ አድልዎ፥ መጠራጠር፥ ማሽሟጠጥ፥ አሽሙር፥ ኃጢአትን ማመስገንና ማስፈራራት እነዚህን የመሳሰሉ ሁሉ ናቸው።

እመቤታችን በማንም ክፋትን ተናግራ አታውቅም አንደበቷ የለዘበ የለመለመ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና የማይታሰብ ዕፁብ ድንቅ የመውለዷን ዜና ሲነግራትም እኔ ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል ብላ ነገሩን ወደ መረዳት ተሻገረች እንጂ ይህ የማይሆን ነገር ነው ብላ ወደ መጠራጠር ወይም መልአኩን ወደ መንቀፍ አልቃጣችም። የአንደበት ድንግልና ማለት የማይቻል ጭንቅ ፍጹም ከተፈጥሮ ህግ በላይ የሆነን ነገር በመስማት ጊዜም ቢሆን ያለመጠራጠር በሃይማኖት መጠየቅና ፍፃሜውን በትዕግሥት መጠበቅ ነው።

መከራ በደረሰ ጊዜ ብዙ የቃል ድንግልና ያላቸው ቅዱሳን ችግሩን የፈጠሩትን ከመንቀፍ ይልቅ በእኔ ችግር የተከሰተ ነው ብለው ራሳቸውን ይወቅሳሉ። ነገር ግን እነርሱ ቀድሞ መበደላቸውን እያስታወሱ ነው። የድንግል ማርያም ግን የሚደንቀው ምንም ነውር የሌለባት ስትሆን በቃሏ ድንግል ስለሆነች እኔ ኃጢተኛ ነኝ ትል ነበር። በብስራተ መልአክ አምላክን የፀነስኩ እናት ነኝ ስትል ገናንነቷን አትናገርም። መልካም በመናገር ንግግሯ ሁሉ ሃይማኖት ተስፋና ፍቅር ናቸው።

፫. ድንግል በኅሊናሃ - በኅሊና ድንግልና የፀናች አንዲት ድንግል፦
ሰው በተግባር ቢነጻ በንግግር አይነጻም፥ በንግግር ቢነጻ በኅሊናው መንፃት አይቻለውም። ጻድቃንም ቢሆኑ ወድቀው ተነስተው በተጋድሎ ለክብር ይበቃሉ እንጂ ከጅማሬ እስከ ፍፃሜው አለመበደል ከቶ የተቻለው የለም። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በኅሊናዋ እንኳን ያልበደለች ፍጽምት አንዲት ድንግል ነች። ጽድቅን ሁሉ የተሞላች ድንግል ማርያም ንጽሕት በመሆኗ በኅሊናዋን ድንግልና፤ የቃሏን ድንግልና፤ የስጋዋን ድንግልና በአንድ ላይ "እንዘ ኢይአምር ብእሴ" "ወንድ ስለማላውቅ" በሚል የንፅህና ሸማ ጠቅልላ ተናገረች (ሉቃ.፩፥፴፬) በዚህ ድንግልናዋም አምላክን ለመፀነስ በቃች።.....(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል መጽሐፍ ገፅ 241-251 የተቀነጨበ)