Farankaa - ፈረንካ

@farankaa


The primary goal of this page is to enhance the financial literacy of Ethiopians by offering valuable insights on investment, banking, insurance, capital markets, and taxation.

Farankaa - ፈረንካ

22 Oct, 11:06


https://youtu.be/xNNMraqMuxk?si=dqYNsWyyPbUXcV37

Farankaa - ፈረንካ

18 Oct, 16:38


የድንገቴ የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ነገር..

***

የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ለህዝብ ሽያጭ ይፋ ከሆነ ወዲህ ብዙዎች የኢንቨስትመንት አማካሪ ሆነው ብቅ ብለዋል። የእራስን ሐሳብ መግለጽ ችግር የለውም። ይሁንና ምክንያታዊ ባልሆነ መረጃ ላይ ተመስርቶ "በመሰለኝ እና በደሳለኝ ለሌሎች ምክር መስጠት ዘርፉን ጠንቅቆ ባለማወቅ የሚደረግ ድፍረት ነውና ሊቆም ይገባዋል።

አንዳንዶች የአምናውን የተጣራ ትርፍ ላይ ተመርኩዘው Earning per Share ወይም Dividend per share በማስላት ከወለድ ያልበለጠ ነው ብለው ሲያብራሩ ገጥሞኛል። ተቋሙ ለህዝብ ይፋ ያደረገውን comparative financial statement ስቃኝ፣ አምና ላይ ኢትዮ ቴሌኮም ገቢው በከፍተኛ ደረጃ ቢጨምርም (ከ71 ቢሊዮን ወደ 90 ቢሊዮን) የሰጣቸው ብድሮች/Financial assets በወቅቱ ባለማስከፈሉ ምክንያት IFRSን ተከትሎ በተዘጋጀው የሂሳብ መግለጫ ላይ በያዘው ወደ ስምንት ቢሊዮን የሚጠጋ impairment provision ምክንያት ትርፉ ከካቻናው ትርፍ ጋር ተቀራራቢ ሆኗል። ይሁን እንጂ ተቋሙ የብድር አሰባሰቡን ካሻሻለ፣ የብድር ጥራቱን ካሻሻለ ይሄ ወጪ ከprovision ወደ ገቢነት መቀየሩ አይቀሬ ነው።

ኢንቨስተሮች አክሲዮን የሚገዙት Dividend ለመሰብሰብ ብቻ አይደለም። Capital appreciation ሌላኛው ባለአክሲዮኖች የሚያገኙት ትርፍ ነው። በአመቱ ዋጋዬን እመልሳለሁ የሚል የዋህ ኢንቨስተር ሊኖር አይችልም። የኢትዮ ቴሌኮም አፈጻጸም ሲጨምር በአክሲዮን ገበያው ላይ ዛሬ ላይ የገዙትን አክሲዮን በተሻለ ዋጋ በመሸጥ ትርፍ ለማግኘት አክሲዮን የሚገዙ ብዙዎች ናቸው።

አገሬው "ሥራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው" የሚለው ያለምክንያት አይደለም። በሙያው ላይ authority ያላቸው ሰዎች በጉዳዩ ላይ አስተያየት ይስጡ፣ ሌላው ያዳምጥ። በሁሉም ጉዳይ ላይ ሁሉ ተንታኝ፣ ሁሉ አውሪ፣ ሁሉ ጸሀፊ ሊሆን አይችልም።

Farankaa - ፈረንካ

17 Oct, 12:32


Ethiotelecom የአክሲዮን ሽያጩን በይፋ ጀምሯል። ምዝገባውን ከመጀመራችሁ በፊት፣

1. የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት
2. ጉርድ ፎቶ ግራፍ

አዘጋጁ።

ምዝገባውን ከፈጸማችሁ በኋላ ክፍያውን አሁኑኑ አልያም በ48 ሰዐት ጊዜ ውስጥ መፈጸም ትችላላችሁ።

Farankaa - ፈረንካ

17 Oct, 05:11


ባንክ ያልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች የኮምፕሊያንስ ነገር...

*
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አምስት ለሚደርሱ ባንክ ያልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች ፈቃድ መስጠቱን ከሰማን ብዙም አልቆየንም።

እኒህ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች ገዢው ባንክ የሚያወጣውን መመሪያ እንዲሁም መመሪያውን መጣስ የሚያስከትለውን ቅጣት በተመለከተ ያላቸው ግንዛቤ እምብዛም ይመስላል። እኒህ ተቋማት ብሔራዊ ባንኩ የውጪ ምንዛሪ አስተዳደርን ለሚያወጣቸው ፖሊሲዎች ከባንኮች እኩል ተጠያቂ ናቸው።

በብሔራዊ ባንኩ ስር መተዳደር እና በጥቁር ገበያ ስር መስራት እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ማሊያ የጥቁር ገበያን አደራለሁ ብሎ ፈቃድ ያወጣም አይጠፋም። ናይጄሪያ ለብዙ ሺህ ባንክ ያልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች ፈቃድ ሰጥታ በኋላ ላይ ህገ-ወጥ ግብይት ላይ በመሳተፋቸው ፈቃዳቸውን ሰርዛለች። ብልጥ ከሌላው ይማራል።

National Bank of Ethiopia ፈቃዱን ባንክ ላልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ተቋማት መስጠቱ ይበል የሚያስብል ቢሆንም ለእነዚህ ተቋማት በቂ የአቅም ግንባታ ከመስጠት አንስቶ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ የአልማዝን ጠባሳ እያዩ በእሳት እንደመጫወት ይቆጠራል።

ከእዚህ ጽሁፍ ጋር የተያያዘው የውጪ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ዋጋ በትላንትናው እለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ከጎበኟቸው ባንክ ያልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች መካከል በአንዱ ውስጥ የተሰቀለ የዶላር መግዣና መሸጫ ዋጋ ገዢው ባንክ በቅርቡ ያወጣውን የ2% spread ህግ የጣሰ ሆኖ ተገኝቷል። ነገሩ ሳይቃጠል በቅጠል ነውና ገዢው ባንክ ተቋማቱ ልክ እንደባንኮቹ ሁሉ ለሚወጡ ህጎች ተገዢ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅበታል።

Farankaa - ፈረንካ

15 Oct, 13:53


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ ፖሊሲ እንምታ ምንድነው?

አዲሱ ፖሊሲ ባንኮች spreadን (በዶላር መግዣና መሸጫ መካከል ያለ ልዩነት) በተመለከተ የሚያስቀምጡት ልዩነት ከ2% እንዳይበልጥ ተገድቧል።

ለምሳሌ የዛሬውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመግዣ እና የመሸጫ ዋጋ ብናይ፣

መግዣ = 113.1308

መሸጫ = 113.1308 + (2%*113.1308)
= 115.3934

ይሆናል ማለት ነው።

ይሁን እንጂ መመሪያው ባንኮቹ ለሚሰጧቸው የተለያዩ ከውጪ ምንዛሬ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች (የመተማመኛ ሰነድ/LC, ዶክመንት ሲቀርብ ካሽ ይከፈል/CAD እና ቅድመ-ክፍያ/TT የመሳሰሉት) ላይ ተጨማሪ ክፍያዎችን፣ ማለትም እንደ...

📌LC opening commission

📌PO approval commission

📌 Service Charge

📌Confirmation Charge

📌SWIFT Charge

እና የመሳሰሉ ክፍያዎችን የማስከፈል መብት ተሰጥቷቸዋል።

ከእዚህ ቀደም በነበረው የኢብባ ፖሊሲ መሰረት ባንኮች የአገልግሎት ክፍያዎችን በሙሉ Spread ውስጥ እንዲያካትቱ ይጠይቅ የነበረ ሲሆን አዲሱ ፖሊሲ የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎች ከSpread ተለይተው ለብቻ ከአስመጪዎች እንዲሰበሰቡ አዝዟል።

ብዙዎች ባንኮች የሚሸጡት ዶላር ላይ ቅናሽ እንደተደረገ አድርገው እየዘገቡ ያሉት ነገር ትክክል አይደለም።

ይሁንና አዲሱ ፖሊሲ አስመጪዎች ቀደም ሲል በተጋነነ የመሸጫ ዋጋ መሠረት ሲከፍሉ የነበረውን import duty ስለሚቀንስ የገበያ ዋጋው ተረጋግቶ ከቀጠለ የገቢ ንግድ እቃዎች ላይ የተወሰነ ቅናሽ ያመጣል።

Farankaa - ፈረንካ

15 Oct, 04:33


https://youtu.be/A06NXBP49r0?si=n2kH1ROXBvC3-a9p

Farankaa - ፈረንካ

12 Oct, 10:32


የእለቱ አባባል፣ በታዋቂው ቦክሰኛ መሐመድ አሊ!

Farankaa - ፈረንካ

12 Oct, 09:15


አዲስ ረቂቅ መመሪያ‼️

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የDematerialization directive ረቂቅ ለህዝብ ውይይት ክፍት አድርጓል።

በአማርኛው ሰነደ መዋዕለ ነዋዮችን/አክሲዮኖችን/ ግዑዝ አልባ ማድረግ ተብሎ የተተረጎመው dematerialization በቀላሉ ከእዚህ ቀደም በወረቀት ሰርተፊኬት የሚሰጡ የአክሲዮን ባለቤትነት ማረጋገጫዎችን በአንድ ማዕከል/Central Depository/ በሚቀመጥ በSoftcopy certificate መተካትን የሚመለከት ነው።

Dematerialization አክሲዮኖችን በቀላሉ ከአንድ ባለአክሲዮን ወደሌላው በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚረዳ ነው። ሂደቱ በዋናነት አክሲዮናቸውን በኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ ላይ የማስመዝገብ ግዴታ የተጣለባቸው ተቋማትን (ባንኮች፣ የኢንሹራስ ኩባንያዎች እንዲሁም ሌሎች የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ተቋማት) እና አክሲዮን ለህዝብ በመሸጥ የሚደራጁ ተቋማትን የሚመለከት ነው።

Farankaa - ፈረንካ

11 Oct, 14:16


ኢትዮ ቴሌኮም በሚቀጥለው ሳምንት 10% የባለቤትነት ድርሻ አዲስ በተቋቋመው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ/Ethiopia Securities Exchange-ESX/ አማካይነት አክሲዮን ለህዝብ በመሸጥ የመጀመሪያው ተቋም ለመሆን ዝግጅት መጨረሱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ገልጸዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ👇

https://www.reuters.com/business/media-telecom/ethio-telecom-kick-off-ethopian-stock-trading-with-10-flotation-next-week-2024-10-09/

Farankaa - ፈረንካ

11 Oct, 05:27


አዲሱ የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ረቂቅ አዋጅ በዘርፉ ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ ብዙ ችግሮችን ይፈታል ተብሎ ይገመታል።

ከእንግዲህ አማላይ ፎቶ መሸጥ አይቻልም፣ ቢሸጥ እንኳ ገንዘቡ በዝግ ሒሳብ ይቀመጣል፣ የተገነባው ሪልስቴት ስሙ ለባለቤቱ እስኪዘዋወር ድረስ በእግድ ውስጥ ይቆያል፣ እንደድሮው ከቤት ገዢ ገንዘብ ሰብስቦ ለባንክ ማስያዝ አይኖርም። ዘርፉ ስርዓት ሊይዝ ይገባል፣ እንደውም ዘግይቷል። ብዙዎች ጥሪታቸውን ተነጥቀዋል፣ አልቅሰዋል፣ ይበቃል መባሉ ትክክል ነው።

Farankaa - ፈረንካ

10 Oct, 11:45


አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቀድሞ ተማሪዎቹ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ተሰባስበው ትዝታቸውን ያወጉ ዘንድ፣ ቤታቸውንና መነሻቸውን ይጎበኙ ዘንድ፣ ስኬታቸውን ያወጉ ዘንድ ጋብዟል።

እኔም እንደቀድሞ ተመራቂነቴ በኢሜል አድራሻዬ የጥሪ ካርድ ደርሶኛል። ከሁለቱ ቀን በአንዱ ተገኝቼ ትዝታዬን ከወዳጆቼ ጋር አወጋለሁ፣ ከሰዎች ጋር እተዋወቃለሁ።

መገኘት የምትችሉ የቀድሞ ተመራቂዎች ሁሉ ቤታችሁን፣ መነሻችሁን ትጎበኙ ዘንድ ተጋብዛችኋል።

Farankaa - ፈረንካ

09 Oct, 11:20


በፋይናንስ ገበያ ውስጥ Haircut ምንድነው?

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ከአበዳሪዎቹ ጋር አዲስ የብድር ማራዘሚያ ድርድር የጀመረ ሲሆን በዩሮቦንድ የተበደረው 1 ቢሊዮን ዶላር ብድር ላይ 20% Haircut እንዲደረግለት ጠይቋል።

በፋይናንስ ገበያ ውስጥ ተበዳሪ ከአበዳሪው ጋር በሚያደርገው አዲስ የብድር ማራዘሚያና አከፋፈል ስምምነት መሠረት ከዋናው ገንዘብ ላይ ተበዳሪው የተወሰነ ቅናሽ እንዲደረግለት ሲጠይቅ Haircut ተብሎ የሚገለጽ ሲሆን ቅናሹ የሚገለጸው በፐርሰንት ነው።

ለምሳሌ፣

የኢትዮጵያ መንግስት 20% haircut እንዲደረግለት ጠየቀ ማለት ከዋናው የዩሮቦንድ ብድር ላይ 20% እንዲቀነስለት ጠይቋል ማለት ነው።

በእዚህ መሠረት አበዳሪዎቹ ከተስማሙ አዲሱ የዩሮቦንድ የብድር መጠን፣

= $1,000,000,000 - (20%*$1,000,000,000)
=$800,000,000/ስምንት መቶ ሚሊዮን ዶላር ይሆናል ማለት ነው።

Farankaa - ፈረንካ

08 Oct, 06:36


https://youtu.be/9zeSXD04Hk4?si=sQdC3uTT32uSuShU

Farankaa - ፈረንካ

07 Oct, 05:35


የመሬት ንዝረቱ ትዝብት፣

በትላንትናው የመሬት መንቀጥቀጥ በስድስተኛ ፎቅ ላይ ሆኜ ንዝረቱ እንደተሰማኝ ለክፉ ለደጉ በሚል ቆጣሪ አጥፍቼ፣ በር ቆላልፌ በደረጃ እግሬ አውጪኝ ብዬ ምድር ላይ ስወርድ ከእኔ እና አብሮኝ ከነበረ ጓደኛዬ በቀር አንድም የወረደ ሰው አልነበረም።

ይሄ ነገር ቅዥት ይሆን እንዴ ብዬ በመጠራጠር እዛው በምኖርበት ሰፈር ወዳለ ጓደኛዬ ስልክ መታሁ። "እኔ እኮ አዙሪት የያዘኝ መስሎኝ ነገ ሐኪም ቤት ስለ መሄድ እያሰብኩ ነበር?" አለኝ። በፍጥነት ከፎቅ እንዲወርድ መክሬው ተለያየን።

ታች ያሉ የህንጻው ጠባቂዎች ዘንድ በመሄድ ንዝረቱ ተሰምቷቸው እንደሁ ብጠይቅ ምንም እንዳልተሰማቸው ነገሩኝ። ምናልባትም 3ኛ ፎቅ ላይ የሆነ ዝግጅት ስለነበር የዝግጅቱ ሙዚቃ ሰዉን አዘናግቶት ሊሆን እንደሚችል ነገሩኝ። ወዲያው ወደ ማህበራዊ ድረ ገጽ አማተርኩ። ነገሩ እውነት መሆኑን አወቅኩ።

ስለጉዳዩ እርግጠኛ ከሆንኩ በኋላ ለጥበቃዎቹ ነዋሪውን እንዲያነቁ ነገርኳቸው። አንደኛው ሲከንፍ በየበሩ እያንኳኳ ያለውን ችግር ተናገረ። የሚደንቀው ነገር በጣት ከሚቆጠሩ ሰዎች ውጪ ሌላ ሰው የጥበቃውን መረጃ ከቁብ ቆጥሮ ከፎቁ የወረደ አልነበረም።

ይሄኔ ነበር እግዚአብሔር አይበለውና የከፋ ነገር ቢመጣ አንድም የተዘረጋ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ስለሌለን አንድ ላይ ማለቃችን አይቀሬ የመሆኑ ነገር ውል ያለኝ።

አምላክ ሀገራችንን ይጠብቅ!

Farankaa - ፈረንካ

06 Oct, 17:52


ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር። በምኖርበት ኮንዶሚኒየም ላይ የተወሰንን ሰዎች ንዝረቱ ተሰምቶን ወደ ታች ወርደናል። ይሄንኑ ለማረጋገጥ Earthquake track የተሰኘ ገጽ ላይ ሳማትር እውነትነቱን አረጋግጦልኛል።

https://www.google.com/url?sa=t&source=web&rct=j&opi=89978449&url=https://earthquaketrack.com/et-44-addis-ababa/recent&ved=2ahUKEwi-7KqCqPqIAxWyBdsEHfsSKacQFnoECBIQAQ&usg=AOvVaw0n73D67_LsiJn1s8c3stEz

Farankaa - ፈረንካ

05 Oct, 08:54


Baga ayyaana irreechaaf geessan!

እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ!

Farankaa - ፈረንካ

03 Oct, 15:43


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱ የውጪ ምንዛሪ ህግ ከመተግበሩ አስቀድሞ ከነዳጅ ጋር የተያያዘ የተጠራቀመ ክፍያ ላለባቸው ባንኮች 175 ሚሊዮን ዶላር ሊሸጥ መሆኑን አሳወቀ።

Farankaa - ፈረንካ

03 Oct, 10:04


ግልጽነት የጎደለው የባንኮች የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ማስታወቂያ፣
*
ሰሞኑን ከሚደርሱኝ የስልክ ጥሪዎች መካከል "ባንክ ገንዘብ ዲፖዚት ሳደርግ ቫት ይቆረጥብኛል? በተመሳሳይ ባንክ ውስጥ ገንዘብ ባዘዋውር ቫት እከፍላለሁ? ብድር ስወስድ ቫት እከፍላለሁ?" እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።

አብዛኞቹ ባንኮች በአጭር መልእክት የሚልኩት የተጨማሪ እሴት ታክስ እናስከፍላለን መልእክት ግልጽነት የጎደለውና ደንበኞች ላይ ውዥንብር የፈጠረ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

የአዋጅ ቁጥርን ጠቅሶ VAT ልናስከፍል ነው ተብሎ የሚላከውን መልእክት ስንቱ ደንበኛ ይረዳል? ቢያንስ በአዋጁ ላይ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የተደረጉትን የተቀማጭ ገንዘብና የብድር አገልግሎቶችን እንደማይመለከት መግለጽ እጅግ ከባድ ነገር ሆኖ ይሆን?

Farankaa - ፈረንካ

03 Oct, 05:42


የማይክሮፋይናንስ ተቋማት የውጭ ኦዲተር አሿሿም መመሪያ

Farankaa - ፈረንካ

03 Oct, 05:42


ብሔራዊ ባንክ ለአምስት የግል የውጪ ምንዛሪ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ ሰጠ።