Abrham Yohanes Law Corner

@ethiopianlegalbrief


A blog about Ethiopian Law

Abrham Yohanes Law Corner

17 Oct, 06:24


ያለፈው ዓመት የያዝነውን ቀጠሮ አስታውሳችሁ በዕለቱና ከዛ በኋላ ደውላችሁ ያስታወሳችሁኝ ውድ ወዳጆች ከባድ ምሥጋና ይገባቸዋል።

ቀጠሮው ብዙም አልተዛነፈም።
ከማተሚያ እንደወጣ ለገበያ ይፋ ይሆናል።

በነገራችን ይህን መፅሐፍ በመፃፍ ሂደት አንድ የተገለጠልኝ ነገር
የሰበር ችሎት አስቀድሞ ይዞት የነበረውን የህግ በሰባት ዳኞች ሲቀይር ለምንድነው የስር ፍ/ቤቶችን ስህተት ሰርታችኋል ብሎ የሚተቸው?
ምን ዓይነት ነው የሰሩት? የሱ የችሎቱ ስህተትም አይደል?
ስህተት ባይባልም ችሎቱን ራሱን የስር ፍ/ቤቶችን አይመለከትመሰ

Abrham Yohanes Law Corner

06 Oct, 09:32


ቸርቹ ና ጠጅ ቤቱ ፊት ለፊት ናቸው።
ጠጪዎች እየተሳለቁ እየተሳሳቁ ይጠጣሉ: ገበያ ለጉድ ነው።
ቸርቹም የዋዛ አይደለም: የመጠጥ ሀጢዓትነት ቢያንስ አንዴ ይሰበካል: ስም ሳይጠቀስ ‘ወጋሁ ይባላል’
ቀስ በቀስ ነገሩ እየተጋጋለ ወደ next level ተሸጋገረ።
የ ቸርቹ ፓስተር ‘ጠጅ ቤቱ ብን ብሎ እንዲጠፋ: እንዲከስም በገሀድ መፀለይ ጀመረ።
ይባስ ብሎ ትንቢት ተናገረ:
እና ትንቢቱ ደረሰና ጠጅ ቤቱ በእሳት ጋየ ወደመ።

የጠጅ ቤቱ ባለቤት የዋዛ አይደለም: ብቀጥንም ጠጅ ነኝ አለና በህግ አምላክ’ ብሎ ተነሳ። ቸርቹንና ፓስተሩን ከውል ውጭ ሀላፊነት በአንድነት ና በነጠላ ተጠያቂ ናቸው ሲል ፍርድ ቤት ገተራቸው።
ቸርቹ ና ፓስተሩ መቃወሚያ ና በፍሬ ነገሩ መልስ ሰጡ።
“ፀሎት ሆነ ትንቢት የእሳቱ መንስዔ ስለመሆኑ ማስረጃ የለም። እኔ ስለፀለይኩና ትንቢት ስለተናገርኩ ጠጅ ቤቱ በእሳት አይወድምም። እንደዚህ ዓይነት ሀይል ና ስልጣንም የለኝም”

የጠጅ ቤቱ ባለቤት ግን “ጠጅ ቤቱ በእሳት የወደመው በተከሳሽ ፀሎት የተነሳ ነው። ባይፀልይ ና ትንቢት ባይናገር ኖሮ ስንት ጥሬ ግሬ ያፈራሁት ጥሪት አይወድምም ነበር” ሲል ወጥሮ ተከራከረ።

የችሎቱ ዳኛ የግራ ቀኙን ክርክር ና ማስረጃ መርምረው ብይን ሰጡ።
ብይን
በፀሎት ና ትንቢት በሚያምን የጠጅ ቤት ባለቤት እና
በፀሎት ና ትንቢት በማያምን ፓስተር መካከል የሚደረግ ክርክር መፍታት ከፍርድ ቤቱ አቅም በላይ ነው።
መዝገቡ ተዘግቷል: ወጪ ና ኪሳራ ይቻቻሉ።

Abrham Yohanes Law Corner

25 Sep, 10:42


በገበያ ላይ ያልዋለ አዲስ መፅሐፍ

Abrham Yohanes Law Corner

20 Sep, 19:54


"Lawyers for Human Rights" held its 6th Regular General Assembly Meeting for the 2016 Fiscal Year.
September 15, 2024.

Abrham Yohanes Law Corner

20 Sep, 19:53


"የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች" የ2016 ዓ.ም. በጀት አመት 6ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ!!
መስከረም 05 ቀን 2017 ዓ.ም

ድርጅቱ በ2016 ዓ.ም. የ6ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው ከ90% በላይ አባላቱ በተገኙበት ዝርዝር የማህበሩን ስራዎች በጥልቀት ገምግሟል:: ከዚህም በመነሳት ድርጅቱ በቀጣይ ዓመታት ሊከተላቸው የሚገባቸውን አቅጣጫዎች አስቀምጧል። ከዚህም በተጨማሪ ጉባኤው የድርጅቱን የ2016 ዓ.ም. ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት የስራ እና የበጀት እቅዶች ላይ በጥልቀት በመወያየት አስፈላጊውን ማሻሻያዎች በማድረግ አፅድቋል::

እንደዚሁም በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የሥራ ጊዜያቸዉን የጨረሱ የጠቅላላ ጉባኤ እና የስራ አመራር ቦርድ አባላትን አስመልክቶ ገሚሶቹ ለተጨማሪ አንድ የስራ ዘመን እንዲያገለግሉ፣ በተወሰኑት አመራር አባላት ምትክ ደግሞ አዳዲስ የአመራር አባላትን መርጧል። በመጨረሻም የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ አባል ለመሆን በቀረቡ አዳዲስ ማመልከቻዎች ላይ ተነጋግሮ ሁሉም አመልካቾች የድርጅቱ አባል ለመሆን ያቀረቡትን ማመልከቻዎች ተቀብሏል።

የዚህ ዓመት ጉባዔ በአባላቱ መካከል የበለጠ ግንኙነትን እና ትብብርን ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ የማህበሩን አባላት ያሰባሰበ ሆኖ ነው ያለፈው።

------------------------------------------
"Lawyers for Human Rights" held its 6th Regular General Assembly Meeting for the 2016 Fiscal Year.
September 15, 2024.

At its 6th Annual General Assembly, the Association thoroughly reviewed its activities with the participation of over 90% of its members. Based on this, the organization has outlined the strategic directions it will pursue in the year ahead.

During the session, the association’s 2016 auditor report was presented by external auditor, reviewed and endorsed by the members. Additionally, the 2017 activity plan and budget were discussed and approved by the assembly. In line with the organization's bylaws, the General Assembly re-elected certain board members and the General Assembly leader with an ending term for an additional term, while others were elected as replacements. In conclusion, the General Assembly reviewed the new membership applications, and all applicants were approved as members of the organization.

This year's assembly aimed to foster greater connection and collaboration among its members, creating a more engaging and inclusive environment for the community.

Abrham Yohanes Law Corner

19 Sep, 05:16


https://youtu.be/N_sTstWvunI?si=ehhbu6n79t-JBO32

Abrham Yohanes Law Corner

18 Sep, 16:58


https://youtu.be/MsOOvdmYnMg

Abrham Yohanes Law Corner

16 Sep, 16:22


ከ meme ጎን ለጎን Status update ለማሳወቅ ያክል:

1- ስመ ብዙ የሆነው በአማርኛ "የግለሰብ ዓለም ዓቀፍ ህግ' አንዳንዴም 'የህጎች ግጭት' እየተባለ የሚጠራውን ህግ በሶስት ዋነኛ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ይኸውም:
1--መሠረታዊ መርሆዎች (የውጭ አገር ህግ የሚረጋገጥበት መንገድ: Characterization, Renvoi,) እንዲሁም በኢትዮጵያ የህጉ አጸጻጸም ላይ የሚነሱ ቁልፍ ጉዳዮች

2- የዳኝነት ሴልጣን

3- የውጭ አገር ፍርዶች እና የግልግል ውሳኔዎች ዕውቅና እና አፈጻጸም
በአጠቃላይ የህግ መረጣ ደንቦችን (Choice of law rules) ሳያካትት
ወደ 50 የሚጠጉ የሰበር ውሳኔዎችን በማጣቀስ አጭር መግቢያ መፅሐፍ ፅፈን አጠናቀናል።

#2 ደሞ 'የኢትዮጵያ የስፖርት ህግ' አጭር መግቢያ መፅሐፍ ጀምረን ጥቅምት መጀመሪያ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ይዘናል።
ይህን መፅሐፍ ለየት የሚያደርገው ለመጀመሪያ ጊዜ ስፖርት በማይሰራ እንዲሁም የእንግሊዝን እግር ኳስ በማይከታተል የህግ ሰው የተጻፈ (ሲጠናቀቅ) መሆኑ ነው።

Abrham Yohanes Law Corner

16 Sep, 16:11


https://youtu.be/g3xXtfCve2Y