የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@ethiopian_orthodox


በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡

ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot

Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:26


@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:26


ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡ በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡

በመጨረሻም
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የሥራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኀላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን የጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑ እናበስራለን፡፡

እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን::
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:26


የቅዱስ ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ መልእክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጐጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዓመቱን ጠብቆ ስለ አጠቃላይ ተልእኮአችን ለመወያየት በዚህ ጉባኤ የሰበሰበን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡

“ወይእዜኒ ግብኡ ኀበ ኖላዊሃ ወዓቃቢሃ ለነፍስክሙ፤ አሁንም ወደ እረኛችሁና ወደ ነፍሳችሁ ጠባቂ ተመለሱ” (1 ጴጥ 2÷!5)

ሁሉን የሚችል አምላካችን እግዚአብሔር በፍቅሩና በፍቅሩ መነሻነት ብቻ ፍጥረታትን በሙሉ እንደፈጠረ ቅዱስ መጽሐፍ ያስተምረናል፤ ከፈጠረም በኋላ የክብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ወዶ ክብሩን አድሏቸዋል፡፡እግዚአብሔር ለፍጡራኑ ካደላቸው ነገሮች አንዱ በየዓይነታቸው ጠባቂና መሪ እያደረገ በፍጡራን ላይ ፍጡራንን መሾሙ ነው፤ ይህ ስጦታ በሰማይም ሆነ በምድር ላሉ ፍጥረታት የተሰጠ የሱታፌ መለኮት ስጦታ ነው፡፡

ይህም በመሆኑ ሁሉም ፍጡራን አራዊትም ሆኑ እንስሳት ይብዛም ይነስ ጠባቂና መሪ እንዳላቸው እናስተውላለን፤ በተለይም የፍጥረታት ቁንጮ የሆኑ መላእክትና ሰዎች መሪና ሹም እንዳሏቸው የማንክደው ሃቅ ነው፡፡ ቅዱስ መጽሓፍም ይህንን ደጋግሞ ያስረዳል፤ የነዚህ ሁሉ ላዕላዊ ጠባቂና መሪ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በፍጡራን ላይ ፍጡራንን ጠባቂዎች አድርጎ ሲሾም ፍጡራንን የክብሩ ተሳታፊ ለማድረግ እንጂ የእሱ ጥበቃ አንሶ ወይም ድጋፍ ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ፍጹምና ላዕላዊ የሆነ ጥበቃው ሁሉንም ያካለለ ነውና ከእሱ ቊጥጥርና ጥበቃ ውጭ አንድም ነገር እንደሌለ የምንስተው አይደለም ፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!

በአምሳለ እግዚአብሔር በተፈጠረውና በክብር መልዕልተ ፍጡራን በሆነው ሰው ላይ በዚህ ዓለም የተሾሙ ሁለት አካላት አሉ፤ እነሱም የመንፈስና የዓለም መሪዎች ናቸው፡፡ በተለይም የመንፈስ መሪዎችና ጠባቂዎች የተባሉት በመንፈስ ቅዱስ ተሹመን በዚህ ክርስቶሳዊ ጉባኤ የተሰበሰብነው እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ነን፡፡

ይህ ጉባኤ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መሪና ጠባቂ ነው፤ ከዚያም ባሻገር እንደ ቃሉ እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ቃሉን በመስበክ ፍጥረተ ሰብእን በሙሉ የመጥራት ተልእኮ ለእኛ የተሰጠ የቤት ሥራ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የተሰጠን ኀላፊነት እጅግ በጣም ታላቅ እንደመሆኑ የሚጠበቅብን ውጤትም በዚያው ልክ ትልቅ ነው፤ ብዙ ከተሰጠው ብዙ ይፈለግበታል ያለው የጌታችን አስተምህሮም ይህንን ያስታውሰናል፡፡

ሁላችን እንደምንገነዘበው አሁን የምንገኝበት ዘመን የጸላኤ ሠናያት መንፈስ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ከምንም ጊዜ በበለጠ ጦሩን ሰብቆ የተነሣበት ጊዜ ነው፤ አሁን ያለው ዓለም በሀገራችንም ሆነ በሌላው ክፍለ ዓለም ላሉ ኦርቶዶክሳውያን ከባድ ፈተና ደቅኖብናል፡፡

ክፉው መንፈስ የሰውን አእምሮ በማዛባት ምእመናንን በቅዱስ መጽሐፍና በሕገ ተፈጥሮ ከተመደበላቸው የጋብቻ ሕግ በማስወጣት እንስሳት እንኳ የማይፈጽሙት ነውረ ኃጢአት እንዲፈጽሙ በመገፋፋት ላይ ይገኛል፡፡ በአማንያን ልጆቻችን ላይም በረቀቀ ስልት ግድያ፣ እገታ፣ አፈና፣ የመብት ተጽዕኖ እና አድልዎ በማድረግ እንደዚሁም በአስመሳይ ስብከትና አምልኮ ጣዖትን በማለማመድ ሕዝቡ ሳይገባውና ሳይጠነቀቅ ከእግዚአብሔር መንግሥት እንዲወጣ እያደረገ ነው፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!

ክፉው መንፈስ በተራቀቀና በተራዘመ ስልት ሊውጠን በተነሣ ልክ እኛም ከእሱ እጥፍ በሆነ መለኮታዊ ኃይል ልንመክተው ካልቻልን በፈጣሪም ሆነ በትውልድ እንደዚሁም በታሪክ ፊት በኀላፊነት መጠየቃችን አይቀርም፡፡ መከላከል የምንችለውም ችግሩን በውል ከመረዳት አንሥቶ ሕዝቡን በደምብ በማስተማርና በመጠበቅ እንደዚሁም ለመሪነታችን ዕንቅፋት ከሚሆኑን ዓለማዊ ነገሮች ራሳችንን በማራቅ ነው፡፡

ሕዝቡም በዚህ ዙሪያ ሊያደምጠንና ሊከተለን የሚችለው መስለን ሳይሆን ሆነን ስንገኝለት ነው፡፡ ሕዝቡ ሊከተለን የሚችለው እሱን በብቃት ለመጠበቅ ዓቅሙም ተነሣሽነቱም ቁርጠኝነቱም እንዳለን ሲመለከት፣ እንደዚሁም ከዕለት ተዕለት ተግባራችንና አኗኗራችን የሚያየው ተጨባጭ እውነታ ኅሊናውን ሲረታ እንደሆነ አንርሳ፡፡

የምናስተምረው ሌላ የምንሠራው ሌላ ከሆነ ግን ከሕዝቡ አእምሮ መውጣታችን እንደማይቀር መገንዘብ አለብን፤ በመሆኑም በሰብእናችን፣ በአስተዳደራችን፣ በአመራራችንና በጥበቃችን ሁሉ እንደቃሉና እንደቃሉ ብቻ ለመፈጸም መትጋትና በቁርጥ መነሣት ጊዜው አሁን ነው እንላለን፡፡ ይህ ሲሆን በምእመናንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት አስተማማኝና እንከን የለሽ ይሆናል፤ ይህ ከሆነ እውነትም የመሪነት፣ የእረኝነትና የመልካም ተምሳሌነት ኀላፊነታችንን በትክክል ተወጥተናል ማለት እንችላለን፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!

የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሯቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡ ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክልል መምራት ይጠበቅበታል፡፡ ምንም ቢሆን የተቀበለው ኀላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሠራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡

እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኀላፊነት አለብን፡፡ ይህ የሁለታችን ኀላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኩረፍና መቀያየም ሰፍቷል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡

ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡

በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሠራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:23


ደጅሽ ላይ ቆሟል

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:23


🌹 ልጅሽ ደጅ ላይ ቆሟል 💧
-------------------------------
ከመስከረም 26-እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደየካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው . . . መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ
‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡
‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤
‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ
‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት . . . ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡
‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ
ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡
ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው . . . በሲጋራና በመጠጥ ሽታ የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤
‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ
መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት
‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት . . . ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን . . . ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት . . . ለረጅም ዓመታት . . . አክሊለ ጽጌ ብዬ . . . ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ
‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ . . . በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ. . . አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ . . . ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ. . . ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል
‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም . . . ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ. . . መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣ . . . የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ . . . ማልቀስ እጀምራለሁ . . . ፍቅሯን አስባለሁ . . . የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው . . . ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል . . . በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ›› አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤
‹‹ወደውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ
‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤
‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣
‹‹ማን . . . እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ . . . እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ
ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ
ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ›› አልኩ አምላኬን፣
በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት
‹‹በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ›› ነህ 6፡10

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:22


ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም፤
ዘወለደት ጽጌ(፫) ወፀሐየ ዓለም።

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:22


ስርዓተ ማኅሌት ዘሣልሳይ ጽጌ በዓለ መስቀል
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀

ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
........................................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

ዚቅ
ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤ ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ህይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።

ማኅሌተ ጽጌ
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤ ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤ ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል።

ወረብ፦
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል/፪/
ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ያሬድ ወይብል ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል/፪/

ዚቅ፦
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ በውስተ አህዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይዕቲ

ማኅሌተ ጽጌ
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።

ወረብ፦
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/
 
ዚቅ
እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ

ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤ ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።

ዓዲ ዚቅ
ወይቤላ ንዒ ንሑር፤ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ አውግረ ስኂን፤ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤  ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ በትምህርተ መስቀል

ዓዲ ዚቅ፦
በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት

ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።

ወረብ፦
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/

ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ

ወረብ፦
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/2/
እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/2/

ሰቆቃወ ድንግል(ሌላ)
ኀበ አዕረፍኪ እግዝዕትየ ማርያም ታሕተ ጽላሎተ ዕፅ እምፃማ፤ፈያት ክልኤቱ ሶበ በጽሑኪ በግርማ፤እምትሕዝብተ ሞቱ ማሕየዊ ለወልድኪ ንጉሠ ራማ፤እፎኑ አዕይንትኪ ማያተ አንብዕ አዝንማ፤አዕይትየ ለገብርኪ ክልኤሆን ይጽለማ

ዚቅ
ሐፃቤ ርስሐትየ ይኩን አንብዕኪ ዘአንፀፍፀፈ ዲበ ምድር አመ ወልድኪ ይፄዓር በመልዕልተ

መዝሙር፦
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፣ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀይል መላትሒሁ፤ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ሰማይ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ  በከዋክብት ሠማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤ማ፦ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፥ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ።

አመላለስ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/፪/
ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ/፪/

©ያሬዳውያን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:19


# ቅድስት ሥላሴ

በ ‹‹ምሥጢረ ሥላሴ›› ትምህርት እንደምንረዳው ቅድስት ሥላሴ አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ ‹‹ሥላሴ›› የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ፤ ሦስት አደረገ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ (መጽሐፍ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ገጽ ፮፻፷፱)

ቅድስት ሥላሴ ስንልም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡ ‹‹ቅድስት›› ተብሎ ደግሞ በሴት አንቀጽ /ቅድስት ሥላሴ/ ይጠራል፤ ‹‹ቅድስት›› እና ‹‹ልዩ ሦስት›› የሚባልበትም ሃይማኖታዊ ምሥጢር፡-

፩. ቅድስት

ሥላሴ ‹‹ቅድስት›› ተብለው በሴት አንቀጽ መጠራታቸው ሴት /እናት/ ልጅዋን መውለዷን እንደማትጠረጥረው ሁሉ ሥላሴም ይህን ዓለም መፍጠራቸውን ስለማይጠረጥሩ ነው፡፡ ሁሉም ከእነርሱ፣ ለእነርሱ፣ በእነርሱ ሆኗልና፡፡ ሴት ወይንም እናት ልጅዋ ቢታመምባት እንዲሞትባት አትሻም፤ ሥላሴም ከፍጥረታቸው አንዱ እንኳን በጠላት ዲያብሎስ እንዲገዛባቸው አይፈቅዱም፡፡ ሴት ፈጭታ ጋግራ ቤተሰቦቿን እንደምትመግበው ሥላሴም በዝናም አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረቱን ሁሉ ስለሚመግቡ ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እያልን እንጠራቸዋለን፡፡

፪. ልዩ ሦስትነት

በትምህርተ ሃይማኖት ሥላሴ በቅድምና፣ በፈጣሪነት፣ በሥልጣን፣ በመመስገን፣ በክብር፣ በፈቃድ አንድ /እግዚአብሔር/ ሲሆኑ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት መሆናቸውን ይገልጻል፡፡

ሀ. በስም

የቅድስት ሥላሴ የስም ሦስነትነት አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ተብለው መጠራታቸው ነው፡፡ አብ በራሱ ስም አብ ይባላል እንጂ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አይባልም፡፡ ወልድም ወልድ ይባላል እንጂ አብ ወይንም መንፈስ ቅዱስ አይባልም፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ቢባል እንጂ አብ ወይንም ወልድ አይባልም፤ ስማቸው ፈጽሞ የማይፋለስ ነውና፡፡

ከቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ በሦስተኛነት በአንጾኪያ ተሹሞ የነበረው ቅዱስ አግናጥዮስ ‹‹አብሂ ውእቱ አብ ወኢኮነ ወልደ ወኢ መንፈሰ ቅዱሰ፣ ወልድሂ ውእቱ ወልድ ወኢኮነ አበ ወኢ መንፈሰ ቅዱሰ፣ ወመንፈስ ቅዱስሂ መንፈስ ቅዱስ ውእቱ ኢኮነ አበ ወኢ ወልደ፣ ኢይፈልስ አብ ለከዊነ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፣ ወኢ ወልድ ለከዊነ አብ ወወልድ፤ ወኢ መንፈስ ቅዱስ ለከዊነ አብ ወወልድ፤ አብም አብ ነው እንጂ ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም፤ ወልድም ወልድ ነው እንጂ አብን መንፈስ ቅዱስንም አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ አብን ወልድን አይደለም፤ አብ ወልድን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም፤ ወልድም አብን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም፤ መንፈስ ቅዱስም አብን ወልድን ወደመሆን አይለወጥም›› ብሏል፡፡ (ሃይ. አበው ዘቅዱስ አግናጥዮስ ምዕ. ፲፩. ገጽ. ፴፯)

የቅድስት ሥላሴ ስማቸው ከአካላቸው፣ አካላቸው ከስማቸው ሳይቀድም ቅድመ ዓለም የነበረ ስም ነው እንጂ ድኅረ ዘመን የተገኘ አይደለም፡፡ ቅድምናቸው ዘመኑን ቢወስነው እንጂ ዘመኑ ቅድምናቸውን አይወስነውምና፡፡ (መንገደ ሰማይ-በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ገጽ. ፴፪)

ስለዚህም ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ‹‹ወናሁ ንቤ ካዕበ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወአኮ እሉ አስማት ዘቦኡ ላዕሌሆሙ ድኅረ አላ እሙንቱ እስመ አካላት፡፡ ወብሂለ ሰብእሂ አኮ ውእቱ ስም ዳዕሙ ፍጥረት ውእቱ… ወአካሎሙኒ ለሥሉስ ቅዱስ ወአስማቲሆሙ አልቦ ውስቴቶሙ ዘይዴኀር አላ እሉ እሙንቱ ብሉያነ መዋዕል እምቀዲሙ ዘእንበለ ጥንት ወዘመን፤ አሁን ደግሞ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንላለን ግን አካላት ተቀድመው ተገኝተው እሊህ ስሞች ኋላ የተጠሩባቸው አይደለም፤ ሰው ማለት ኋላ የወጣ ስም አይደለም፡፡ ባሕርዩ ነው እንጂ የሥላሴ አካላቸውም ቀድሞ ስማቸው ከአካላቸው በኋላ የተገኘ አይደለም፡፡ ጥንት ሳይኖራቸው ዘመን ሳይቀድማቸው የነበሩ ናቸው እንጂ›› ብሎ ተናግሯል፡፡ (ሃይ-አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ፲፫፥፬-፰ ገጽ ፵)

ለ. በአካል

የቅድስት ሥላሴ የአካል ሦስትነታቸው ደግሞ አብ ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው፡፡ ወልድም ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው፡፡ ሊቁ አቡሊዲስ ስለ ሥላሴ የአካል ሦስትነት ሲገልጽ ‹‹ነአምን በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ከመ ሠለስቱ ገጻት ፍጹማነ መልክእ ወአካል እሙንቱ እንዘ አሐዱ መለኮቶሙ ዘበአማን፤ ባሕርያቸው በእውነት አንድ ሲሆን በመልክ፣ በአካል ፍጹማን እንደሆኑ ሦስት ገጻት እንደሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን›› ብሏል፡፡ (ሃይ. አበ. ዘአቡሊዲስ ምዕ. ፴፱፥፫ ገጽ ፻፴፯)

ሐ. በግብር

የቅድስት ሥላሴ የግብር ሦስትነታቸው ሲተረጎም የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረፅ ነው፤ ወልድን ወልዷል፣ መንፈስ ቅዱስንም አሥርፇልና፡፡ የወልድ ግብሩ መወለድ ነው፤ ከአብ ተወልዷልና፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረፅ ነው፤ ከአብ ሠርፇልና፡፡

አብ ወልድን ቢወልድ፣ መንፈስ ቅዱስንም ቢያሠርፅ እንጂ አይወለድም፣ አይሠርፅም፡፡ ወልድ ቢወለድ እንጂ አይወልድም፤ አይሠርፅም፤ አያሠርፅም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አይወለድም፤ አያሠርፅም፤ በመሆኑም ቅድስት ሥላሴ በዚህ ግብራቸው አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ ተብለው ይጠራሉ፡፡

በእርግጥ ምሥጢረ ሥላሴን በሚገባ መርምሮ መረዳት ለማንም ቢሆን አይቻለውም፡፡ እርሱ ባወቀ ግን ምሥጢረ ሥላሴ በምሥጢረ ጥምቀት ተገልጧል፡፡ እንግዲህ እምነታችንን በቅድስት ሥላሴ ላይ በማድረግ በቀናች ሃይማኖት ልንጸና ይገባል፡

©Mahibere kidusan

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:19


ሥላሴ ትትረመም

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:16


"የአምላክ አቃቤ ሕግ"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:16


@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:16


ጥቅምት ፭

የታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት) የዕረፍታቸው መታሰቢያ

ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሏቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አንደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ፭፻፷፪(562) ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ፭፻፷፪ ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮጵያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊዮን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።

ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለ'የ'ት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው፤ ከዕልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።

የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ፻(100) ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።

ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ፳፻(2,000) በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ፰(8)ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ፲፬(14)ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዝዘው መጋቢት ፭(5) ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።

ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ። "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ።" እንዲል።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት ፭(5) ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው። ፍትሃ ነገስት አንቀጽ ፲፭(15) ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ :የመጋቢት ፳፯(27) ስቅለት ጥቅምት ፳፯ ቀን እንደሚከበረው ሁሉ የአባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው ወደ ጥቅምት ፭ ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው በእኛ በምናምን ላይ ይደርብን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:14


"ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ"
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:14


✝️ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ ! 🔔

በጥንቱ ዘመን ሰማዕትነት ከዓላዊያን ነገሥታት ጋር ነበር። ዓላዊያን ነገሥታት ክርስቲያኖችን ያሳድድዋቸዋል። ክርስቲያኖችም ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ይሰደዳሉ። ስለ ሃብት ንብረታቸው፣ ስለ ምድራዊ ክብራቸው፣ ስለ ሚስቶቻቸው፣ ስለ ልጆቻቸው፣ ስለ ምድራዊት ኑሮአቸው ብዙም አይጨነቁም። ዋናው ጭንቀታቸው ነፍሳቸው ከአምላክዋ ከወዳጅዋ ከሞተላት አፍቃሪዋ ርቃ እንዳትሰደድ ነበር። ታዲያ ለዚህ ብለው የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ግማሾቻቸው ዱር ለዱር፣ ግማሾቻቸው ተራራ ለተራራ፣ ግማሾቻቸው ዋሻ ለዋሻ፣ ግማሾቻቸው ፍርክታ ለፍርክታ ተቅበዘበዙ። ብዙ የብዙም ብዙ መከራ ተቀበሉ። ነፍሳቸውን ለማትረፍ ብለው ራሳቸውን በየመቃብሩ፣ በየበረሃው ይደብቁ ነበር። በጣም የሚያስደንቀኝ ግን ይህን ያደረጉት በጣም ብዙ እናቶችም መኖራቸው ነው።
ልጆቼ የእኛ ሰማዕትነት ግን እንዲህ አይደለም። የእኛ ሰማዕትነትና ውጊያ በላያችን ላይ ካሉት ነገሥታት ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት ከምኞቶቻችን ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት ከስግብግብነት፣ ከእንቅልፍ፣ ከዋዛ ፈዛዛ፣ ከስንፍና፣ ከውሸት፣ ከሐሜት ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት በጠዋት ተነሥቶ ለጫወታ መሮጥ ሳይሆን ለጸሎት፣ ለስግደት ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ነው። የእኛ ሰማዕትነት ወንበራችን እስኪጎደጉድ ድረስ ፊልም ማየት ሳይሆን ቃለ እግዚአብሔርን ማንበብ ነው።
ስለዚህ ልጆቼ! ከምኞቶቻችን ጋር ተጋድሎ እንግጠም። ነፍሳችንን ከአምላክዋ ጋር ከሚያጣሉ ደግሞም ለጊዜው ሳይሆን ለዘለዓለም ከሚለይዋት ፍላጎቶቻችን ጋር እንጋደል። ስለ ምድራዊ ሃብት፣ ስለ ምድራዊ ዝና፣ ስለ ጊዜአዊ ደስታ ብለን ነፍሳችንን ለዓላውያን ነገሥታት (ለምኞቶቻችን) ትንበረከክ ዘንድ አሳልፈን አንስጣት።
ነፍሳችንን ከእነዚህ ነገሥታት መከራ እናድናት። እነዚህን ነገሥታት ድል አድርገን ከአምላክዋ ጋር እናገናኛት። ከእንቅልፍ ጋር ተዋግተን ድልም አድርገን ጠዋት ለጸሎት ፣ ለስግደት እናበርታት። የእኛ ዘመን ሰማዕትነት ይህ ነውና። ........ ✞ ✞ ✞ ..........
☞ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ[ትርጉም-ገብረ እግዚአብሔር ኪደ] ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:12


በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ዘኮንኪ ለእረፍት ትእምርተ ኪዳን፤
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን።

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:12


ስርዓተ ማኅሌት ዘካልዕ ጽጌ በዓለ በዓታ ለማርያም
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀

ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
.....................................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከተ፤ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ።

ማኅሌተ ጽጌ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ(ጽላተ) ኪዳን፤ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡

ወረብ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ዘኮንኪ ለዕረፍት ትእምርተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/

ዚቅ
ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ኅቡረ ንትፈሳሕ ዮም በዛቲ ዕለት፡፡

ማኅሌተ ፅጌ፦
ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ፤በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ

ወረብ፦
እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ  ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ/፪/
ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ/፪/

ዚቅ
አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን ድንግል ኅሪት ዘነበረኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ሥርግው በወርቅ ንጡፍ ወልቡጥ በዕንቍ ባሕርይ ዘየኃቱ ዘብዙኅ ሤጡ ከመዝ ነበርኪ በቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽሑ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ አሠርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ

ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/

ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎሕ ሠናይት ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጣስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት

ዓዲ ዚቅ
ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።

ወቦ ዘይቤ ዚቅ
ይዌድስዋ ትጉሃን፤ይቄድስዋ ቅዱሳን፤ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርይዪ ወአጽምዒ ዕዝንኪ

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/

ዚቅ
ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤መራኁቱ ለጴጥሮስ፤አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ

ሰቆቃወ ድንግል
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ሥሩዓ፣ ኅብስተ ኅቡዓ ወጽዋዓ ወይን ምሉዓ፤እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ዘኃጥአ፤ተአገሠት በብሔረ ግብጽ ረኃበ ወጽምዓ፤አልቦ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ

ወረብ፦
እፎ ከመ ነዳይ ዘኃጥአ ሲሳየ ዕለት/፪/
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ኅብስተ መና ኅቡዓ/፪/

ዚቅ
እሴብሕ ጸጋኪ ኦ ዑጽፍተ ልብሰ ወርቅ እግዝዕትየ ወለተ ዳዊት ንጉሥ ዘተሐፀንኪ በቤተ መቅደስ ወተዓንገድኪ በፈሊስ እምሀገር ለሀገር እንዘ ተዓውዲ በተፅናስ

መዝሙር፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።

አመላለስ፦
መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/
ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/

©ያሬዳውያን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:09


"ተይ ተመከሪ"
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

21 Jan, 00:06


"በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች" | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox