Ethiopian Electric Utility

@eeuethiopia


EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ethiopian Electric Utility

22 Oct, 17:35


ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎቱ ተመልሷል

በመሬት ውስጥ ተቀባሪ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በየካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 440 እና 447፣ አርሴማ አካባቢ፣ ወጋገን ባንክ ጀርባ፣ ሸገር ዳቦ መሸጫ፣ አባዶ መስቀለኛ እና ፒያሳ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ ወደ አገልግሎቱ ተመልሷል ፡፡

የጥገና ስራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁ ደንበኞቻችን ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

22 Oct, 12:46


በመሬት ውስጥ ተቀባሪ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል

በመሬት ውስጥ ተቀባሪ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 440 እና 447፣ አርሴማ አካባቢ፣ ወጋገን ባንክ ጀርባ፣ ሸገር ዳቦ መሸጫ፣ አባዶ መስቀለኛ እና ፒያሳ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል ፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ያጋጠመውን ብልሽት ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

22 Oct, 09:03


715 አዳዲስ ደንበኞች በአንድ ቀን የኤሌክትሪከ ተጠቃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን "ኤሌክትሪክ በአንድ ቀን" በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ በሚገኘው የስራ ዘመቻ 715 አዳዲስ ደንበኞች በአንድ ቀን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

በሪጅኑ እየተከናወነ በሚገኘው የስራ ዘመቻ ከተስተናገዱ አዳዲስ ደንበኞች ውስጥ 266 የሚሆኑት በሐምሌና በነሐሴ ወራት ሃይል በጠየቁ በ24 ስዓት ውስጥ የኤሌክትሪክ ሃይል የገባላቸው ሲሆኑ 314 የሚሆኑ ደግሞ በመስከረም ወር ብቻ የሃይል ተጠቃሚ የሆኑ ናቸው፡፡

በመስከረም ወር ኤሌክተሪክ ከገባላቸው አዳዲስ ደንበኞች ውስጥ 147 የሚሆኑት በመስከረም 27 ቀን የተገናኘላቸው ሲሆኑ 136 የሚሆኑት ደግሞ በአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የተገናኙ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሪጅኑ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ያልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ በጀመረው የስራ ዘመቻ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም 135 አዳዲስ ደንበኞችን የሃይል ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

በሪጅኑ የሚገኙ አዲስ ሃይል ፈላጊ ደንበኞችን በአንድ ቀን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያደረገው በጋሸና፣ በመርሳ፣ በወልድያና በሰቆጣ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ሲሆን አሁን የጀመረውን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የማድረግ ተግባር በማጠናከር የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞችን ቁጥር ለማሳድግ እየሰራ ነው፡፡

ተቋሙ በተያዘው የ2017 በጀት አመት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን "ኤሌክትሪክ በአንድ ቀን" በሚል መሪ ቃል በሃገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወነ ይገኛል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

22 Oct, 08:24


በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች የቅድመ ጥገና የመልሶ ግንባታ ስራ ለማከናዎን ሲባል በዕቅድ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸውን አካባቢዎችን ለማየት ይህ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ:-http://www.eeu.gov.et/power-interruption?lang=am
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

22 Oct, 07:37


ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያን በቀላሉ፣ የትም ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ካሻዎ በቴሌ ብር፣ በሲቢኢ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በአዋሽ ብር ፕሮ ወይም በኤም ፔሳ በኩል ይፈፅሙ፡፡

ፍጆታዎ በስልክዎ!
ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ በመምረጥ ኑሮዎን ያቅሉ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

21 Oct, 16:26


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ ከአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን #ነፃ_ሐሳብ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ረቡዕ ምሽት 3፡00 ይጠብቁ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

21 Oct, 13:24


ለክቡራን ደንበኞቻችን በሙሉ

ከአገልግሎት አሰጣጣችን ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎችና ጥቆማዎችን ለመቀበልና ለመፍታት ነፃ የጥሪ ማዕከል መዘረጋታችን ይታወቃል፡፡ በአሁን ወቅት ይህ የጥሪ ማዕከል ይበልጥ ለደንበኞቻችን ተደራሽ ለማድረግና አገልግሎቱንም ለማስፋት የዲጅታል አማራጭ በመጨመር ወደ ደንበኞች ኮንታክት ሴንትር ለማሳደግ እየሰራን እንገኛለን፡፡

ለዚህም እንዲያግዝ 905 እና 904 ነፃ ስልክ መስመሮች የምናስተናግድበት የጥሪ ማእከላችን አሁን ከሚገኝበት አድራሻ ወደ ሌላ የተሻለ ቢሮ ከትላንት ጥቅምት 10 ቀን 2017 ጀምሮ የማዛወር ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ሥራው ዛሬም ባለመጠናቀቁ በአዲስ አበባ የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን በአቅራቢያችሁ የሚገኝ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ቀጥታ ስልክ ቁጥር በመደወል በጊዜያዊነት መገልገል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ እየጠየቅን፤ የጥሪ ማዕከሉ ወደ መደበኛ አገልግሎት እንደተመለሰ ወዲያው የምናሳውቅ መሆኑንም እንገልፃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

21 Oct, 12:00


ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ተመልሷል

በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በትላንትናው ዕለት የኃይል አቅርቦቱ ያልተመለሰላቸው የለገጣፎ ከተማ፣ 44 እና ኢንዱስትሪ መንደር እንዲሁም አባዶ ኮንድምኒየም አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የኃይል አቅርቦቱ ተመልሶላቸዋል፡፡

ስለሆነም የጥገና ስራው ሙሉ በሙለ ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁ ደንበኞቻችን ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

21 Oct, 07:42


ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት በከፊል ተመልሷል

በለገጣፎ ከፍተኛ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት አምባሳደር ሪል ስቴት፣ አያት ዞን 1፣ ዞን 2 እና ዞን 8፣ መሪ 40/60 ኮንድምኒየም፣ ሰባ ሁለት፣ ከሸገር ዳቦ ወደ ጥሩ መናፈሻ፣ ሳራ አምፖል ፋብሪካ፣ ካራ ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት የተመለሰ ሲሆን፤ በቀሪዎቹ አካባቢዎች ማለትም በለገጣፎ ከተማ፣ 44 ማዞሪያ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ ገዋሳ እንዲሁም የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል ኃይል ለማገናኘት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

ኤሌክትሪክ ለተመለሰላችሁ ደንበኞቻችን በትዕግስት ስለጠበቃችሁ ምስጋና እያቀረብን፤ አሁንም የኃይል አቅርቦቱ ባልተመለሰባቸው አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ጥገናው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አቅርቦቱ ወደቦታው እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

21 Oct, 07:05


ሪጅኑ ለ6ሺህ 96 አዳዲስ ደንበኞች ኃይል አገናኘ

የአዳማ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2017 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለ6 ሺህ 96 አዳዲስ ደንበኞች ኃይል የማገኛኘት ሥራ አከናውኗል፡፡

ሪጅኑ በሩብ ዓመቱ 7 ሺህ 384 ለሚሆኑ ደንበኞች አዲስ ኃይል ለማገናኘት አቅዶ 6ሺህ 96 ለሚሆኑ ደንበኞች በማገናኘት የእቅዱን 83 በመቶ ማሳካት ችሏል።

አዲስ ኃይል ከተገናኘላቸው ደንበኞች መካከል በ በቆጂ፣ አሰላ፣ መተሀራ፣ ዝዋይ፣ ሞጆ፣ መቂ እና ሌሎች ከተሞች ይገኙበታል፡፡

የአዲስ ኃይል አቅርቦቱ ተጠቃሚ ከሆኑት ደንበኞች መካከል 4ሺህ 548 የሚሆኑት በተቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት ማለትም በ10 ቀናት ውስጥ የተስተናገዱ ናቸው።

በተጨማሪም ሪጅኑ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት መልሶ ግንባታና ማሻሻያ ሥራ 39 ነጥብ 22 ኪሎ ሜትር ሥራ በማከናወን የእቅዱን 94 በመቶ ማሳካት ችሏል።

በመልሶ ግንባታ ሥራው ከተከናወኑ ተግባራት መካከል 784 የኮንክሪት እና የእንጨት ምሰሶ ተከላ ስራ የተሰራ ሲሆን፤ የመልሶ ግንባታ ሥራው የተከናወነው በአዳማ ሪጅን ዴክሲስ፣ ዴራ እና መተሀራ አካባቢዎች ነው።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

19 Oct, 14:34


የጥሪ ማዕከል ቦታ ማዛወር ስራ ስለሚከናወን ማዕከሎቻችን አገልግሎት አይሰጡም

ነገ እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም እና ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሙሉ ቀን የጥሪ ማዕከል ቦታ ማዛወር ስራ ስለሚከናወን የ905 እና 904 ነጻ የጥሪ ማዕከሎቻችን አገልግሎት አይሰጡም፡፡

ስለሆነም የቦታ ማዛወር ስራው ተከናውኖ የጥሪ ማዕከሎቻችን ወደ አገልግሎት እስኪመለሱ ድረስ በአዲስ አበባ የምትገኙ ደንበኞቻችን ከስር ባያያዝነው ስልክ ቁጥር በመደወል ወይም በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመሄድ አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

19 Oct, 11:34


በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች የቅድመ ጥገና የመልሶ ግንባታ ስራ ለማከናዎን ሲባል በዕቅድ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸውን አካባቢዎችን ለማየት ይህ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ http://www.eeu.gov.et/power-interruption?lang=am

Ethiopian Electric Utility

19 Oct, 06:15


የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ሥራ እጅግ ፈታኝና ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፡፡ ባለሞያዎቻችን የኤሌክትሪክ ኃይል ሲቋረጥ መልሶ ለማገናኘት በሚያደርጉት ጥረት አካላቸውን አልፎም ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ህዝብን ማገልገል ቀዳሚው ሥራችን በመሆኑ፤ በብዙ መስዋቶች ውስጥም ሆነን እናንተን ውድ ደንበኞቻችን ለማገልግል ሁሌም ተግተን እንሰራለን፡፡ ያሉብንን ክፍተቶች በማረም ከእናንተ ጋር በጋራ በመስራት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በቀርጠኝነት እንተጋለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ዋልታ ቴሌቪዥን ከኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ጀረባ ያሉ እውነቶችን አስመልክቶ የሰራውን ፕሮግራም እንዲመለከቱ እንጋብዛለን፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=NsmxJlQ1xsg

Ethiopian Electric Utility

18 Oct, 13:47


በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

በለገጣፎ የኃይል ማከፋያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በለገጣፎ ከተማ፣ ለገጣፎ አዲሱ መንገድ፣ አምባሳደር ሪል ስቴት፣ አያት ዞን 1፣ ዞን 2፣ እና ዞን 8፣ መሪ 40/60 ኮንድምኒየም፣ ሰባ ሁለት፣ ከሸገር ዳቦ ወደ ጥሩ መናፈሻ፣ ሳራ አምፖል ፋብሪካ፣ ካራ እና አባዶ ኮንድምኒየም ሙሉ በሙሉና በከፊል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ብልሽቱን ለመጠገን ርብርብ እያደረገ መሆኑን በመገንዘብ ጥገናው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Ethiopian Electric Utility

18 Oct, 08:16


በአዲስ አበባ ከተማ ከጥቅምት 9 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ኃይል ለማገናኘትና በመልሶ ግንባታ ምክንያት በዕቅድ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸውን አካባቢዎችን ለማየት ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡-http://www.eeu.gov.et/power-interruption?lang=am

Ethiopian Electric Utility

18 Oct, 06:56


በክልሉ 11 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ግንባታ በመካሄድ ላይ ነው

ተቋሙ ግንባታቸው የተጠናቀቁት ማዕከላት በ ደ/ታቦር፣ ተንታ እና ወራታ እንዲሁም በዳንግላ አንድ የሰብስቴሽን መቆጣጠሪያን ጨምሮ አሁን ላይ ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን እና የደንበኞቹን ዕርካታ ለመጨመር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት፡-http://www.eeu.gov.et/news/detail/981?lang=am

#የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት