Diredawa Adminstration Electric Utility

@eeudiredawa


Officail Telegram channel of EEU Diredawa Region.

Diredawa Adminstration Electric Utility

16 Oct, 17:22


ከሁለት ሳምንት በኋላ መስመሩ ዳግም ተገናኝቷል
………///……….
በስርቆት ምክንያት ላለፉት ሁለት ሳምንታት አገልግሎቱ ተስተጓጉሎ የነበረው የቆቃ-ሁርሶ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ማምሻውን አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የኃይል ማስተላለፊያዎችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት የተቋረጠውን መስመር መልሶ ለማገናኘት ከፍተኛ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል።

ከሪጅኑ በተጨማሪ የሦስት ሪጅኖች ባለሙያዎችን በቅንጅት በማሳተፍ የተከናወነው የጥገና ሥራ የምስራቅ ኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ከፈረቃ ወጥተው ኃይል እንዲያገኙ ማስቻሉን ዳይሬከረተሩ ገልፀዋል።

በጥገና ሥራው ላይ የተሳተፉ ሁሉንም ባለሙያዎችና የአዋሽ 7 ኪሎ ከተማ አስተዳደርን አመስግነዋል።

የአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ተደጋጋሚ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ስርቆት ከሚፈፀምባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ ነው።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Diredawa Adminstration Electric Utility

14 Oct, 10:45


ተቋርጦ የነበረው ነፃ የጥሪ ማዕከል ወደ አገልግሎት ተመልሷል

ከጥቅምት 02 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ የመረጃ ማዕከል ማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል ተቋርጦ የነበረው ነፃ የጥሪ ማዕከል ወደ አገልግሎት ተመልሷል፡፡

በመሆኑም ውድ ደንበኞቻችን በነፃ የጥሪ ማዕከሎቻችን በመደወል እንደተለመደው ማንኛውም መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በዚህ አጋጣሚ በተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Diredawa Adminstration Electric Utility

13 Oct, 06:10


ከቆቃ- ሁርሶ በተዘረጋው መስመር ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ርብርብ እየተደረገ ነው
………///……….
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ የወደቀውን ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመጠገን ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የኃይል ማስተላለፊያዎችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጎሣዬ ደምሴ እንደገለፁት ከቆቃ ሁርሶ በተዘረጋው የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የተፈፀመው ስርቆት በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የኃይል መቋረጥ ምክንያት ሆኗል።

ጉዳት የደረሰበትን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ መልሶ ለማቆም የወደቀውን ምሰሶ የመፈታታት ሥራ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ጎሳዬ ምሰሶውን መልሶ በማቆም በቀጣይ ሳምንት የመጀመሪያዎቹ ቀናት አካባቢዎቹ ኃይል እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሪጅኑ 12 ባለሙያዎች በጥገና ሥራው ላይ እየተሳተፉ ቢሆንም ሥራውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ከማዕከላዊ አንድ እና ሦስት ሪጅን እንዲሁም ከምስራቅ አንድ ሪጅን ተጨማሪ ባለሙያዎች ቡድኑን እንዲቀላቀሉ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የጥገና ሥራው ሙሉ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ከመስመሩ ኃይል ሲያገኙ የነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች በፈረቃ ኤሌክትሪክ የማድረግ ሥራው እንደሚቀጥል ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ለጥገና ሥራው የቅርብ ድጋፍ እያደረገ ያለውን የአዋሽ 7 ኪሎ ከተማ አስተዳደር እና ከንቲባውን በሪጅኑ ስም አመስግነዋል፡፡

በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በኃይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶ አካላት ላይ እየተፈፀሙ የሚገኙ የስርቆት ወንጀሎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የመስተዳድር እና የፀጥታ አካላት ለመሰረተ ልማቶቹ ተገቢውን ጥበቃና ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Diredawa Adminstration Electric Utility

11 Oct, 13:58


የጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እሑድ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከ ማለዳ 12፡00 እስከ ምሽት 12፡00 ድረስ ጥገና ስራ ስለሚያከናውን በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ፊቅ፣ ጅግጂጋ፣ ደገሐቡርና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጦ ይቆያል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Diredawa Adminstration Electric Utility

10 Oct, 08:13


በጥሪ ማዕከሎቻችን ይሰጥ የነበረው አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል

ከትላንት መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 1 ስዓት ጀምሮ ባጋጠመ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት 905 እና 904 ነፃ የጥሪ ማዕከሎቻችን አገልግሎት መስጠት አቁመዋል፡፡

ውድ ደንበኞቻችን ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እየጠየቅን፤ ችግሩ ተፈትቶ የተቋረጠው አገልግሎት እስከሚመለስ ድረስ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ ዲስትሪክቶች ወይም አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በአካል ወይም በቀጥታ ስልክ በመደወል ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

Diredawa Adminstration Electric Utility

07 Oct, 14:53


በኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ መውደቅ ምክንያት አገልግሎት መቋረጡን ስለማሳወቅ

*******************

ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም በመልካ ጀብዱ አካባቢ የኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች በመውደቃቸው ምክንያት መልካ ጀብዱ ሙሉ በሙሉ፣ ገንደ ሪጌ፣ አዲሱ ባቡር ጣቢያ፣ ደረቅ ወደብ እና አካባቢዎቸቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥገና ቡድን አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን እየገለፅን፤ ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞች የጥገና ስራው ተጠናቆ አገልግሎቱ ወደ ነበረበት እስከሚመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡



#የድሬዳዋአስተዳደርኤሌክትሪክአገልግሎት



ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የትስስር ገፆቻችን ቤተሰብ ይሁኑ:-

ፌስ ቡክ፡https://www.facebook.com/diredawaelectric2011
ቴሌግራም፡ https://t.me/eeudiredawa

Diredawa Adminstration Electric Utility

07 Oct, 06:31


ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያን በቀላሉ፣ የትም ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ካሻዎ በቴሌ ብር፣ በሲቢኢ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በአዋሽ ብር ፕሮ ወይም በኤም ፔሳ በኩል ይፈፅሙ፡፡

ፍጆታዎ በስልክዎ!
ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ በመምረጥ ኑሮዎን ያቅሉ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Diredawa Adminstration Electric Utility

03 Oct, 09:11


ከቆቃ- ሁርሶ በተዘረጋው ከፍተኛ መስመር ላይ በደረሰ ጉዳት በአካባቢው ኃይል ተቋርጧል

ከቆቃ-ሁርሶ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አዋሽ ፓርክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በተፈፀመ ስርቆት ኃይል መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

በዚህም በምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል በሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች፣ ለአዲስ አበባ- ጅቡቲ የባቡር መስመር እንዲሁም ለጅቡቲ የሚሄደው የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋጧል።

ስርቆት የተፈፀመበት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ጥምር የኤሌክትሪክ መስመሮችን የያዘ በመሆኑ የጥገና ሥራው ከ20 ቀን ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል የተጠቀሰ ሲሆን ፤ የጥገና ሥራው ሙሉ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ከመስመሩ ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች በፈረቃ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረቶች ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመተሃራ - አዋሽ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የባቡር መስመር ላይ በሚገኙ ዘጠኝ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ታውቋል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡሯን ደንበኖቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ ጥገናው እስኪጠናቀቅ ድተስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Diredawa Adminstration Electric Utility

02 Oct, 17:44


ለስራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

*******

የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርብ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ኃይል የማገናኘት ስራ ለማከናወን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 7:00 ድረስ አዲስ ከተማ፣ ለገሀሬ፣ ቀፊራ፣ ግንፍሌ እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

#የድሬዳዋአስተዳደርኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የትስስር ገፆቻችን ቤተሰብ ይሁኑ:-

ፌስ ቡክ፡https://www.facebook.com/diredawaelectric2011
ቴሌግራም፡ https://t.me/eeudiredawa

Diredawa Adminstration Electric Utility

02 Oct, 10:49


ቆጣሪ በወቅቱ አለመነበብ በደንበኞች ላይ ምን ያህል ጫና እንደሚያሳድር ያውቃሉ? እንግዲያውስ እናሳውቅዎ የሚጠቀሙበት ቆጣሪ ካልተነበበ ቢል ስለማይዘጋጅልዎ ለተጨማሪ ወጪ ይዳረጋሉ፡፡ ስለሆነም ወድ #የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞችን የሚጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በተቀመጠለት የማንበቢያ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በየወሩ መነበቡን ይከታተሉ፤ካልተነበበልዎትም ወዲያውኑ አገልሎት ወደሚያገሀኙበት ማዕከል በመሄድ ያሳውቁ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Diredawa Adminstration Electric Utility

26 Sep, 08:33


የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለክቡራን ደንበኞቹ እንኳን ለመስቀልና ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

የቅድመ ክፍያ ደንበኞች የመስቀል በዓል ቀን በካርድ ማለቅ ምክንያት አገልግሎት እንዳይቋረጥባቸው በማሰብ ኮኔል እና ሳቢያን በሚገኙ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ የካርድ ማስሞላት አገልግሎት የምንሰጥና የድህረ ክፍያ ደንበኞቻችንም የተጠቀሙበትን የፍጆታ ሂሳብ የምንቀበል በመሆኑ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህን አውቃችሁ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

መልካም በዓል!!!!



#የድሬዳዋአስተዳደርኤሌክትሪክአገልግሎት



ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የትስስር ገፆቻችን ቤተሰብ ይሁኑ:-

ፌስ ቡክ፡https://www.facebook.com/diredawaelectric2011
ቴሌግራም፡ https://t.me/eeudiredawa

Diredawa Adminstration Electric Utility

26 Sep, 08:02


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!! በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Diredawa Adminstration Electric Utility

21 Sep, 07:37


ውድ #የድህረ_ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ይፈፅሙ! ከዚህ በተጨማሪም ወርሃዊ የቆጣሪ ንባብ እየተወሰደ መሆኑን ያረጋግጡ! የቆጣሪ ንባብ ካልተወሰደ ለተጨማሪ ውዝፍ እዳ የሚዳርግ በመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ንባብ መወሰዱን ያረጋግጡ፤አለመነበቡን እርግጠኛ ከሆኑ በአቅራቢዎ ለሚገኙ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ ያሳውቁ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Diredawa Adminstration Electric Utility

18 Sep, 18:46


አዲሱ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ አተገባበር በምሳሌ ሲቃኝ

ከመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ ለቀጣይ 4 ዓመታት በየሶስት ወር ተከፋፍሎ በ16 ጊዜ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡ ይህም አነስተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን የሚጠቀሙ ደንበኞችን እንዳይጎዳ፣ አሁናዊ የኑሮ ደረጃን ያገናዘበና ድጎማን መሰረት ያደረገ ማስተካከያ መሆኑ ነው፡፡

ይህ የታሪፍ ማስተካከያ የመኖሪያ ቤት፣ ንግድ ተቋማት፣ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ፣ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራት ተጠቃሚ ደንበኞች በሚል የተከፋፈለ ነው፡፡

የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎችን በተመለከተ ሰባት እርከኖች ያሉት ሲሆን፤ እንደ አጠቃቀማቸው መሰረት ያደረገ ድጎማ ተደርጎበታል፡፡ በዚህም ከ0 እስከ 200 ኪሎዋት ሰዓት የሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች የድጎማው ተጠቃሚ ናቸው፡፡

ለአብነት በአገራችን ካሉ የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎች ውስጥ 75 በመቶ የሚደርሱት ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ካሉት አጠቃላይ ደንበኞች ደግሞ ግማሽ የሚሆኑት በወር 50 ኪሎዋት ሰዓት እና ከዚያ በታች የሚጠቀሙ ናቸው፡፡

እንደ አጠቃቀም ደረጃ ካየነው በወር እስከ 100 ኪሎዋት ሰዓት የሚጠቀመው ደግሞ ቁጥሩ 65 በመቶ ድርሻ አለው፡፡ ከፍ አድርገን እስከ 200 ኪሎዋት ሰዓት በወር ኤሌክትሪክ የሚጠቀመውን ብንመለከት ከአጠቃላይ የተቋሙ ደንበኛ እስከ 80 በመቶ ይደርሳል፡፡

በተሻሻለው ታሪፍ ለምሳሌ የመጀመሪያው እርከን ማለትም እስከ 50 ኪሎዋት ሰዓት በወር የሚጠቀሙ የተቋሙ ግማሽ የሚሆኑ ደንበኞች 75 በመቶ የተደጎመ ታሪፍ ነው አሁንም እንዲከፍሉ የሚደረጉት፡፡

በወር እስከ 50 ኪዋሰ የሚጠቀሙ ደንበኞች ድጎማ ሳይደረግላቸው በትክክለኛው የታሪፍ ቀመር እንዲከፍሉ ቢደረግ ለአንድ ኪሎዋት ሰዓት 6.01 ብር ይከፍሉ ነበር፡፡ ድጎማ በመደረጉ ለአንድ ኪሎዋት ሰዓት በዚህ በያዝነው መስከረም ወር 0.35 ብር እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡ ይህም ከነባሩ 0.27 ታሪፍ ያለው 12 ሳንቲም ብልጫ ብቻ ነው፡፡

በተመሳሳይ ከ51 እስከ 100 ኪሎዋት ሰዓት ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች ቀድሞ ይከፍሉት ከነበረው 0.77 ብር ታሪፍ በዚህ ወር በ1 ኪሎዋት ሰዓት የሚከፍሉት 0.95 ብር ነው፡፡ ይህም ጭማሪው 2 ሳንቲም ነው፡፡ ከ101 እስከ 200 ኪሎዋት ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞች ደግሞ 1.63 ብር የነበረው፤ አሁን 1.89 ብር በመክፈል 26 ሳንቲም ጭማሪ ብቻ ይከፍላሉ፡፡

ተጨማሪ ማሳያ ለመጥቀስ በአንድ ወር ውስጥ 50 ኪሎዋት ሰዓት የሚጠቀም አንድ ደንበኛ ድጎማ ባይደረግለት ኖሮ በአጠቃላይ ትግበራው በአማካይ ይከፍል የነበረው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሒሳብ የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ ብር 311 (50 ኪዋሰ *6.01+10.24=310.74) ይሆን ነበር፡፡ ሆኖም ድጎማ በመደረጉ 59.74 ይከፍላል ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ደንበኛው ለተጠቀመው 50 ኪዋሰ ብር 251 በተቋሙ ይሸፈናል ማለት ነው፡፡

የያዝነው የመስከረም ወር ወርሃዊ ፍጆታ እንኳን በምሳሌ እንመልከት፡-

👉 50 ኪሎዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሆነ አንድ ደንበኛ በነሃሴ ወር ይከፍለው የነበረው 24 ብር ታሪፍ፤ በአዲሱ መስተካከያ ሚከፍለው 28 ብር ይሆናል፡፡ ጭማሪውም 4 ብር ነው፡፡

👉 በተመሳሳይ አንድ 200 ኪሎዋት ሰዓት በወር የሚጠቀም ደንበኛ በቀድሞ ታሪፍ (200*1.63+42 = 368 ብር) ይከፍል የነበረ፤ በዚህ ወር (200*1.89x42.95 = 420.95 ብር) ይከፍላል፡፡ ልዩነቱም 52.95 ብር ብቻ ነው፡፡

በዚህ ማሳያ መሰረት ማንኛውም የተቋማችን የመኖሪያ ቤት ደንበኛ በሚያርፍበት እርከን ውስጥ የሚገኘውን የታሪፍ መጠን በተጠቀመው ኪሎዋት ሰዓት መሰረት በማስላት ወርሃዊ የፍጆታ መጠኑን ማወቅ ይችላል፡፡ የዚህ ወር የአገልግሎት ክፍያ (ለድህረ ክፍያ) ከ50 ኪሎዋት ሰዓት በታች 10.24 ብር እንዲሁም ከዚያ በላይ ለሚጠቀሙት ደግሞ 42.95 ብር ነው፡፡

ሆኖም ሰሞኑ ይህንን እውነታ ባፈነገጠ መልኩ የተዛባ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ጥቂት መገናኛ ብዙናንና የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች ተጠቃሚውን እያሳሳቱ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉና ትክክለኛውን መረጃ ከተቋማችን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Diredawa Adminstration Electric Utility

14 Sep, 10:13


ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቻችን በሙሉ እንኳን ለ1499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!

በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

ኢድ-ሙባረክ

Diredawa Adminstration Electric Utility

10 Sep, 12:29


የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለክቡራን ደንበኞቹ እንኳን ለ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

የቅድመ ክፍያ ደንበኞች በበዓሉ ቀን በካርድ ማለቅ ምክንያት አገልግሎት እንዳይቋረጥባቸው በማሰብ ኮኔል እና ሳቢያን በሚገኙ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ የካርድ ማስሞላት አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን ክቡራን ደንበኞቻችን ይህን አውቃችሁ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

መልካም በዓል!!!!



#የድሬዳዋአስተዳደርኤሌክትሪክአገልግሎት



ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የትስስር ገፆቻችን ቤተሰብ ይሁኑ:-

ፌስ ቡክ፡https://www.facebook.com/diredawaelectric2011
ቴሌግራም፡ https://t.me/eeudiredawa

Diredawa Adminstration Electric Utility

10 Sep, 11:57


የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለክቡራን ደንበኞቹ፣ ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለመላው የተቋማችን ሰራተኞች እንኳን ለ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅርና የብልፅግና እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡
ፍቅረማርያም አለማየሁ
የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ስራ አሰፈጻሚ


#የድሬዳዋአስተዳደርኤሌክትሪክአገልግሎት



ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የትስስር ገፆቻችን ቤተሰብ ይሁኑ:-

ፌስ ቡክ፡https://www.facebook.com/diredawaelectric2011
ቴሌግራም፡ https://t.me/eeudiredawa

Diredawa Adminstration Electric Utility

10 Sep, 11:45


ለቅድመ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ

ተቋማችን የዘመን መለዋጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የቅድመ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በበዓሉ ዕለት በመላው አገሪቱ በሚገኙ በተመረጡ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ካርድ መሙላት እንዲችሉ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ በመጫን በበዓሉ ዕለት የካርድ መሙላት አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላትን ዝርዝር መመልክትና አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
http://www.eeu.gov.et/contents/prepaid?lang=am

Diredawa Adminstration Electric Utility

09 Sep, 07:56


የተቋማችን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ሽፈራው ተሊላ ያስተላለፉት #የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት