kewser Media_ከውሰር ሚድያ

@kewsertubeofficial


You Tube ላይ እንገኛለን👉👉https://youtube.com/@am2media1?si=r-fGZbnW47oDUtHA

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

23 Oct, 00:54


ሄዝቦላህ አምርሮ የቆረጠ ይመስላል እስራኤል በበኩሏ እንደ ዋዛ ዘላ የገባችበት የወረራ ጦርነት ጨቀጨቅ እየዋጣት እያስጨነቃት ይመስላል …ተመልሳ አትወጣ ነገር አርፍዳለች …ህዝቧን የፍርሃትና ጭንቀት እጣ እያደለችው ትገኛለች ሰላማዊ ኑሮ ከራቀ ከራርሟል 😅

ትላንት ምሽቱን ጀምሮ የእስራኤል በርካታ ከተሞች በሄዝቦላህ ሮኬቶች እየተመቱ ነው …ዋና ከተማዋ ቴላቪቭን ጨምሮ ሃይፋና ሌሎችም ከ60 በላይ ከተሞች የአደጋ ግዜ ደውል ደውለው …ህዝቤ ሆይ ምሽግ ያዝ …መሬት ያዝ …ተደበቅ… ራስህን ከሄዝቦላህ ጥቃት ጠብቅ ሲሉ በጩኸት ምድር ሰማዩን አናውጠውታል የሄዝቦላህ ሮኬት ፍንዳታ ድምጽ ጋር ተዳምሮም እራኤላውያንን የምጽዓት ቀን የተቃረበ ያህል በሽብርና ጭንቀት አራውጠዋቸዋል

ከሄዝቦላህ ጥቃት እጅግ አስገራሚው አለፍ ሲልም አስቂኙ ነገር ደግሞ😄 እስራኤላውያንን ከሚሳኤልና ሮኬት ጥቃት ይመክታል ተብሎ ብዙ ሲወራለት የነበረው …አይረን ዶም …የተሰኘው የሚሳኤል መከላከያ ምድብ በሄዝቦላህ የሮኬት ጥቃት ኢላማ መሆኑ ነው 😅

የጎላን ተራራን ተጠግተው የተመሰረቱት የዋቭና ኪላ ከተሞችም የሄዝቦላህን ሮኬት ከሰማይ አንጋጠው እያዩ ምሽቱን በፍርሃትና ጭንቀት አሳልፈዋል …

ብዙ የተባለለት የእስራኤል ጸረ ሚሳኤል መከላከያ ነሁልሎና ጀልፎ እንኳን ሌላውን ሊጠብቅ ራሱንም እያዳነ እንዳልሆነ የታዘበችው ወዳጇ አሜሪካ ታሃድ የተሰኘ እጅግ ዘመናዊ ሚሳኤልና ሮኬት መመከቻ ዘመናዊ መሳሪያን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል አስገብታለች ዘዋሪና ኻዳም 100 ወታደሮች ጋር

😅 አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒዮ ብሊንከንም እዚያው ናቸው ፈጣን በራሪ ጀታቸውን አክንፈው ቴላቪቭ ገብተዋል …ዋና የጉዟቸው ምክንያት የእስራኤል ደጋግሞ መጠቃት የፈጠረው ጭንቀትና ምጥ ነው …ቢባልም እሳቸው ግን ግዴላችሁም ጎበዝ ስለ ሰላም እና ተኩስ አቁም ብንመካከር ይበጃል ሲሉ ተደምጠዋል …

በአንድ በኩል ግፋ በለው እያሉ ትጥቅ አግዘው ስንቅ ቋጥረው እያታኮሱ ወዳጃቸው እስራኤል ዱላው ሲበረታባት ስለ ሰላም እንማከር እንጅ ጃል ! …ማለታቸው ጭንቀትና ተንኮል የወለደው ሴራ ለበስ ጥሪ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው
  ሲፋጅ በማንኪያ ሲበርድ በእጅ …ማለት አሁን አይደል 😅

ወዳጆቼ ሆይ …ፌስ ቡኬ ተወስዶብኛል እስካሁን አላስመለስኩ 😐

እናም
ከቢቢሲ ከcnn ከአልጀዚራ ከስካይ ኒውስና ከሮይተርስ ወዘተ የመረጃ ምንጮች አሰባስቤ ያዘጋጀሁት የእለቱ ዝርዝር መረጃ በተለመደው ሰአት እዚህ ቴሌግራሜ ላይና You Tube ላይ ይቀርባል ኢንሻ አሏህ ሼር በማድረግ አግዙኝ የፌስ ቡኩን ክፍተት በመሙላት አግዙኝ ቤተሰብ🙏

https://youtube.com/live/sTLmicF6-Sg?feature=share
  የkewser Mediaን ሰብስክራይብ ሼር በማድረግ ቤተሰኛ ወዳጅ ይሁኑ 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

22 Oct, 22:13


https://youtube.com/live/sTLmicF6-Sg?feature=share

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

22 Oct, 19:15


ከመርካቶው የምሽቱ ቃጠሎ ጀርባ ምንድነው ያለው ሴራ?? የጉዳቱ መጠን ምን ያህል ነው ምን ያህል ሰው ተጎዳ ……
በተመሳሳይ ሰአትና ቀን ባህር ዳርና ጎንደር ላይ በተመሳሳይ የገበያ ማዕከል ቃጠሎ ለምን? እንዴት??

የሚሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ከጥቂት ቆይታ ቡሃላ kewser Media ላይ Live እገባለሁ ጠብቁኝ 🙏

https://youtu.be/-gJUEQnZRAQ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

22 Oct, 11:06


በርካታ ወንድም እና እህቶች በአንድ ቀን ጀንበር ድንገተኛ ቅጽበት የአመታት ልፋታቸውን በሙሉ ያጡበት የመርካቶ ሸማ ተራ ቃጠሎ😥😥

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

22 Oct, 03:21


https://youtu.be/-gJUEQnZRAQ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Oct, 21:30


ሰበር መረጃ
እስራኤል ISO2 በተባለ ወታደራዊ ሚስጥራዊ ኮድ ስምሪቷ ኢራንን በድንገት ለመደብደብ አቅዳ የተዘጋጀችበት ሰነድ በአጋሯ አሜሪካ በኩል ሾልኮ እንዲወጣ እና እንዲጋለጥ በመደረጉ በአሜሪካና እስራኤል መካከል ከባድ ቅራኔ መፍጠሩ ተሰማ

ከባድ ጦርነት ውስጥ የተዘፈቀችው እና አስጨናቂ ውጥረት ውስጥ የወደቀችው እስራኤል ከሲቪሉ አስተዳደር ጎን ለጎን በወታደራዊ ኮማንድ ካቢኔ ጭምርም ለመመራት ግድ ብሏታል

ዛሬ በወጡ መረጃዎች ይሄው ከሲቪሉ ካቢኔ ጎን ለጎን የእስራኤልን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲወስን የተዋቀረው ወታደራዊ ኮማንድ ዛሬ ያደረገውን ስብሰባውን ያለ ውጤትና በከፍተኛ ሃሳብ ግጭት ያለ ስምምነት በትኗል

እስራኤል በኮድ ISO2 ሚስጥራዊ ኮድ ስምሪት የጥቃት እቅዷ 16 ያክል ጎልደን ሆራይዘን እና ከ40 በላይ ሮክስ የተሰኙ ከአየር ላይ የሚወነጨፉ ባላስቲክ ሚሳኤሎችን ለኢራኑ ጥቃት ያዘጋጀት ሲሆን …አየር ላይ ነዳጅ የሚቀበሉ በርካታ የውጊያ ጀቶችን እና ግዙፍ የነዳጅ ታንከር ያላቸው ለተዋጊ ጀቶቹ አየር ላይ ነዳጅ መውላት የሚችሉ KC-707 ግዙፍ ቦይንግ አውሮፕላኖችን እና ለተጨማሪ ሎጀአቲክ ስራ የሚውሉ G-550 ገልፍ ስትሪም ጀቶችን በተጠንቀቅ ላይ ማድረጓ ነው የተጋለጠባት

ተጨማሪ ትንታኔና ዝርዝሩን አሁን ከቆይታ ቡሃላ በሚለቀቀው የዛሬ ምሽት መረጃ መሰናዶ ይዘን እንቀርባለን ኢንሻ አሏህ

https://youtu.be/DL5zv-EouFQ

ከውሰር ሚድያን ሰብስክራይብ ላይክና ሼር በማድረግ ወዳጅ ቤተኛ ሆነው አለም አቀፍ መረጃዎችን ይከታተሉ 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Oct, 20:34


እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የቤካም ሸለቆ መንደሮችና የደሂየ ግዛቶች ላይ ከባድና ተከታታይ የአየር ላይ ጥቃት ሰንዝራለች …የጥቃቱ ኢላማ የንግድ ማዕከላትና ባንኮች መሆናቸውም ተጨምሮ ታውቋል …
https://youtu.be/DL5zv-EouFQ
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን በዛሬው ምሽት የkewser Media ላይ ይጠብቁን

24,904

subscribers

674

photos

144

videos