Dire Dawa Administration Education Office communication

@diredawa_14


DDAEOc Telegram Channel

Dire Dawa Administration Education Office communication

20 Oct, 15:21


Dear , we are pleased to inform that, result for the summer teacher's capacity building training have been officially released.
Trainees can check their result by visiting  https://result.ethernet.edu.et and selecting the TDP option from the available list.

Note:
Candidates must use their registration number to access their result (e.g.: TDP0000016)
All candidates who sat for the exam can see their result
Only candidates who scored 70 and above will get an authorized certificate.

ውዶች የክረምት መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና ውጤት በይፋ መለቀቁን ስንገልጽ በደስታ ነው።

ሰልጣኞች ውጤታቸውን https://result.ethernet.edu.et በመጎብኘት እና ካለው ዝርዝር ውስጥ የTDP ምርጫን በመምረጥ ማረጋገጥ ይችላሉ።


ማስታወሻ፡-

እጩዎች ውጤታቸውን ለማግኘት የምዝገባ ቁጥራቸውን መጠቀም አለባቸው (ለምሳሌ፡ TDP0000016)

ለፈተና የተቀመጡ እጩዎች በሙሉ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

70 እና ከዚያ በላይ ያመጡ እጩዎች ብቻ የተፈቀደ የምስክር ወረቀት ያገኛሉ።

Dire Dawa Administration Education Office communication

19 Oct, 19:51


ጥቅምት 9/ 2017ዓም
አፈተ ኢሳ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 2017 ትምህርት ዘመንን አስመልክቶ የተማሪዎች ውጤት ማሻሻል ዙሪያ ከተማሪ ወላጅ ጋር ውይይት አካሄደ ።

የ2016 ዓ.ም የ6፤ የ8 እና የ12 ክፍል የተማሪዎች ውጤት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል ።

አፈተ ኢሳ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዘንድሮ 2017 ዓ.ም የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በሚሰራው ስራ የወላጅ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ወላጆች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Facebook፡- https://www.facebook.com/dire.educ?mibextid=ZbWKwL
Telegram፦ https://t.me/DireDawa_14
Tiktok፡- https://www.tiktok.com/@diredawaeducationbureau
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Dire Dawa Administration Education Office communication

19 Oct, 14:54


ጥቅምት 9/ 2017ዓም

በድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይና አካቶ ተግባር ክፍል ከUNICEF ጋር በመተባበር በዋሂል ወረዳ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ አመራሮችና የስርዓተ ጾታ ተጠሪ መምህራን ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።
========================

በድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይና አካቶ ተግባር ክፍልከUNICEF ጋር በመተባበር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብሎም ፆታዊ ጥቃትን የሚፀየፍና የሚታገል ትውልድን መፍጠር በሚቻልበት አግባብ በዋሂል ወረዳ ከሚገኙ ትምህርት ቤት ለተውጣጡ አመራሮችና የስርዓተ ጾታ ተጠሪዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት የተጠናቀቀ ሲሆን በዋናነትም የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትን አስፈላጊነት እና ሴቶች የማኅበረሰባቸውንና የአገራቸውን የወደፊት እጣ ፈንታ በመወሰን ረገድ ያላቸውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን በሚፈለገው መጠን ለመተግበር ብሎም በየደረጃው የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል በትምህርት ቤቶች ሊሰሩ የሚገባቸው ተግባራትን በተመለከተ ለትምህርት ቤት አመራሮችና ባለሞያዎች ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ስልጠና ነበር።

ስልጠናው በጀንደር(ስርዓተ ፆታ) ሚኒስትሪሚንግ፣ በትምህርት ቤት አካባቢ ጾታዊ ጥቃትን መከላከል እና ያለ እድሜ ጋብቻን መከላከል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች የተሰጠ ሲሆን በስልጠና መድረኩ ማጠቃለያ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ እንደገለፁት ሰልጣኞች በቆይታቸው ያገኙትን ተጨማሪ እውቀት ወደየ ትምህርት ቤታቸው ሲመለሱ ፆታዊ ጥቃትን በጋራ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ፍሬ እንዲያፈራ በሚያስችል አግባብ የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎቻቸው ላይ በአግባቡ እንዲሰሩም መልዕክት አስተላልፈዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Facebook፡- https://www.facebook.com/dire.educ?mibextid=ZbWKwL
Telegram፦ https://t.me/DireDawa_14
Tiktok፡- https://www.tiktok.com/@diredawaeducationbureau
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!