ከሞት በኋላ ቀባሪዎች የሚጠይቁት የተለመደ ጥያቄ ነው። ኦርቶዶክስ፣ ሙስሊም፣ ወንጌላውያን፣ ካቶሊክ ወዘተ በየስማቸው በተዘጋጀ መቃብር በሃይማኖቱ ስርዓት ለመሸኘት ይሯሯጣሉ። ነገር ግን አሸኛኘት ምን ቢለያየም ዘላለም ግን አንድ ነው፤ የዘላለም ህይወት ወይንም ሞት።
ታዲያ ለሰዎች ከዘላለም ርዕሰ ጉዳይ በላይ ምን የከበደ ነገር ሊኖር ይችላል? የምድሩ ቆይታማ ከአንቀልባ እስከ ሽምግልና ዕድሜ እንዴት ባለ ፍጥነት እንደሚንደረደር ትላንት የአራስ መጠየቂያ ይዘን የሄድንበትን ህጻን ዛሬ አንቱ ተብሎ ሲጠራ ማየት በራሱ በቂ ማስረጃ ነው።
ስለዚህም የቀበር ሽኝትህ እንዴትም ያለ ቢሆን ዋናው ጥያቄ ነፍስህ የት ታርፋለች የሚለው ነው። ምክንያቱም ሰው ሁሉ 'የዘላለም አምላክ' ተብሎ በተጠራው አንድ አምላክ ፊት ይቆማል እንጂ ስንሞት እንደየእምነታችን የሚቀበሉን የተለያየ እምነት ያላቸው አምላኮች የሉም።
"ሰው አንድ ጊዜ ሊሞት ከዚያም በኋላ በፍርድ ፊት ሊቆም ተወስኖበታል።" ዕብራውያን 9:27
እናም የእርስዎ ተራ መቼ እንደሚሆን ባይታወቅም በዘመንዎ ፍጻሜ ማወቅ የሚፈልጉት ዋና ጉዳይ የትና እንዴት ባለ ስርዓት እንደሚቀበሩ ሳይሆን ነፍስዎ የትኛው ዘላለም እንደምታርፍ ነው።
"እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።" ዮሐንስ ወን 17:3
ጥያቄ ቢኖርዎ ይላኩልን!
Share @Bruh_Tesfa