የጥያቄዎቻችሁ መልስ

@apostolicsuccession


የዚህ ኦርቶዶክሳዊ ገጽ ዋና ዓላማ የወጣቱን ጥያቄ መመለስ ነው። ወጣቶች ማንኛውም በሕይወታቸው የገጠማቸውንም ይሁን መንፈሳዊ ጥያቄ በሚረዱት መልክ መልስ ይሰጥበታል

YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCPLJimNlqTFBnlbsh_vccgg


ለጥያቄዎችና ለአስተያየቶች
@AbuNak
@Rhripsime

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

19 Oct, 13:42


ሰላም ሰላም ተወዳጆች እንዴት ናችሁ? ለመጥፋቴ በጣም ይቅርታ ዛሬም ግን እገዛ ልጠይቃችሁ መጣሁ። ከሁለት በአንዱ እስኪ እንተጋገዝ

አንድ ወንድም አለኝ የእንጨት ስራ ባለሞያና የአንድ አመት ሴት ልጅ አባት ነው። ግን እኩያዬ በልጅነቱ ወልዶ ነውና ከልጁም ከሚስቱም ጋር አብሮ ነው ሚኖረው። የዛሬ 2 አመት እኔው ነበርኩ ከፕሮቴስታንት ያስጠመኩት። እና አሁን ላይ ስራ ስለጠፋ

አንደኛ የእንጨት ስራ(ወንበር፣ ሶፋ፣ አልጋ፣ ብፌ፣ ቁምሳጥን..) ምናምን ስራ ማግኘት ምትችሉ ካላችሁ ብትጠቁሙን

ሁለተኛ ለጊዜው ስለተቸገረ ትንሽ በቻልናት አቅም ብናግዘው? እኔም ተሳትፊያለሁ እንደ አቅሜ እናንተም አግዙት የልጁ ነገር እያስጨነቀው ስለሆነ

50427978 Abyssinia
Mesafint Hayle hancho
(የራሱ አካውንት ነው)

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

07 Oct, 14:56


የመጀመሪያው መጽሐፌን ከወንድሜ መምህር ብርሃኑ ጋር አዘጋጅተን ጨርሰናል። እግዚአብሔር ቢፈቅድና ቢወድ የፊታችን ሀሙስ ማታ ከ2:00 ጀምሮ ላይቭ በኔ ቤት የተለያዩ የተጋበዙ እንግዶች ባሉበት እናስመርቃለን። የምትችሉ በእኔ የቲክቶክ አካውንት ApostolicSuccession ላይ እንድንገናኝ ጋብዣችጓለሁ። ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

30 Sep, 07:04


የድንግል ማርያም ቅዱስ ስዕል
Full epoxy
Size = 100cm * 70 cm
💰  5000

በፈለጉት ስዕል ይዘዙን እናዘጋጃለን

ለማዘዝ @Rhripsime @Dn_bisri

@tekelepoxy
#share #share

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

21 Sep, 18:26


🎁ቴቄል epoxy and gifts 🎁


📌የወደዳችሁትን ስዕል በፈለጋችሁት መጠን          ለቤታችሁ  ፣ ለ ስጦታ   እና   ለጸሎት ቤት   የሚሆኑ ቅዱሳት ስዕላትን በጥራት  እናዘጋጃለን

🛍 አሁኑኑ ይዘዙን

📞 0945287530

     @Rhripsime

For more join our telegram channel

@tekelepoxy
@tekelepoxy
@tekelepoxy

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

10 Sep, 17:01


#መልካምአዲስ

“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።”
  — መዝሙር 65፥11

ለሁላችሁም በዓሉ የሰላም የፍቅር ይሁንላችሁ እንዲሁም ቅዱስ ቃሉ እንደሚነግረን👇 አዲሱን ዓመት ስንቀበል በአዲስ መንፈስ ይሁን ጌታም አዲስ ልብ ይሰጠናል እንዲሁም አዲሱን ዓመት ስንቀበል ኢየሱስን መልበስ ይገባናል።

“አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።”
  — ሕዝቅኤል 36፥26

በሉ እንደባህላችን ክርስቲያናዊ ምርቃን ልመርቃችሁ😁

በአዲሱ ዓመት ክርስቲያናዊ ፍሬ አፍሩ።

በአዲሱ ዓመት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የባህሪይ አባቱ የእግዚአብሔር አብ ፍቅር እንዲሁም የባህሪይ ሕይወቱ የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ፍቅር ይብዛላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን የምትወዱበት  ዓመት ይሁንላችሁ በእርግጥ አምላኩን የማይወድ ክርስቲያን የለም ነገርግን የቃሉ ባለቤት ክርስቶስ ኢየሱስ እንደነገረን እሱን መውደድ ፍቃዱን መፈፀም ነው ስለዚህ አዲሱ ዓመት የሥላሴን ፍቃድ የምትፈፅሙበት ይሁንላችሁ።

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”
  — ዮሐንስ 14፥15-16

በአዲሱ ዓመት የጌታን ስጋና ደም ለመቀበል ያብቃችሁ።

ጌታ በአዲሱ ዓመት ኃጢያትን ለመስራት የደነደነ ልብ ፅድቅን ለመስራት የበረታ የጠነከረ ልብ ያድላችሁ።

በአዲሱ ዓመት ጌታ ጸሎት ወዳድነትን፣ጥበብን፣ማስተዋልን፣ ትዕግስትን ያድላችሁ እንዲሁም ሰዉንሁሉ የሚወድ ልብ ይስጣችሁ።

አዲሱን ዓመት በማንበብ በክርስቲያናዊ ስራ እንድታሳልፉ ጌታ ይርዳችሁ።

#አሜንበሉ😁

                                  #ማሳሰቢያ
በዓሉን ስታከብሩ ክርስቲያናዊ በሆነ መንገድ አክብሩ መስከር መጨፈር ክርስቲያናዊ ትውፊት አይደለም።

"ጌታሆይ ሰላምን ስጠን እንዲሁም ከጠላታችን እጅ አድነን...ጌታሆይ በርህራሄህ ወንዞችና ምንጮችን ዛፉንና ፍራፍሬውን ባርክ ዓውደ አመቱን ባርክልን" (Doxology for the coptic new year) የአስክንድርያ ቤተክርስቲያን ምእመናንም ነገ አዲስ ዓመትን ያከብራሉ በዓሉን ሲጠሩትም በዓለ ናይሩዝ (The feast of nayrouz) ብለው ነው😊ለነገሩ በግብፅ ያለችውን ቤተክርስቲያን ለአብነት አነሳሁ እንጂ መስከረም ፩ (1) የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም አዲስ ዓመቷን የምታከብርበት ነው በዓሉንም (church new year) ብለው ያከብሩታል ለሁላችንም መልካም በዓል

@APOSTOLICsuccession

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

09 Sep, 08:47


https://youtu.be/UuRumdcDG3M?si=EE-xnoLqVd1wXGai

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

24 Aug, 18:01


"እኛምኮ እንቃወማለን አንደግፍም" ውሸት! አባባሉንማ እኔም እለዋለሁ ውስጣዊ ስሜቴ ጾታዊ ጥቃትን ሊደግፍ አይችልም ግን ምን አድርጌ አውቃለሁ? እስኪ በኢትዮጵያ ላሉ ሴቶች ሰብአዊ ነጻነት ምን አድርገህ ታውቃለህ? መቃወም ማለትኮ ውስጣዊ ስሜትህ ያን ጾታዊ ጥቃት መቃወሙ አይደለም። ያ ጥቃት እንዲቆም መስራት ነው ምን እየሰራን ነው? እንዲሁ ቁጭ ብለን የሚሰሩ ልጆች ላይ አስተያየት እንስጥ? ያ ነው መቃወም ብላችሁ የምታስቡት? የእናንተ መቃወም 0.01 እንኳን ለመፍትሄው አጋዥ ካልሆነ መቃወም አይደለም። በመንፈሳዊነት እንኳን እንሂድ እስኪ ስንቶቻችን ነው ጾታዊ ጥቃት ስለሚደርስባቸው እህቶች ጸልየን የምናውቀው? ስንቶቻችን ነን ስለተጠቃች ሴት ልጅና እግዚአብሔር መንፈሷን እንዲያጠነክር በጸሎት ያሰብናት? ስንቶቻችን ነን በክርስቲያናዊ ኅብረቶች መሀል አስተምረን የምናውቀው? ስንቶቻችን ነን መንፈሳዊ ንቅናቄን በጾታ ጥቃት ዙሪያ እንዲፈጠር አድርገን አይደለም አስበን የምናውቀው? ስንቶቻችን በዚህ ጉዳይ ጽፈናል? ስንቶቻችን በዚህ ጉዳይ ሰብከናል? ስንቶቻችን ጓደኞቻችንን አስተምረናል?

እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም አንድ ነገር እንደምንል "እያየሁ ሴት ልጅ ብትጠቃ ዝም ብዬ አላይም" For real? እያየህ ካልሆነስ? አንተ ፊት ካልሆነስ? ባንተ ዙሪያ ያሉት እህቶች ካልሆኑስ? በቃ? ዝም ነው የምንለው? ምንም አናረግም? ይሄኮ አጠገባችን ያለውን ጾታዊ ጥቃት ለማቆም እንጂ generally የሴቶች ጥቃት እንዲቆም አንዲት ፐርሰንት እንኳን ዋጋ አይኖረውም። አጠገባችን ያለችውን እሰየው ጠበቅናት። ግን ያቺ እህታችን የሆነ ቦታ፣ እኛ የሌለንበት፣ እኛ ልናድናት የማንችልበት፣ እኛ ልንደርስላት የማንችልበት ቦታ ላይስ ጥቃቷ እንዲቆም ምን እናድርግ? አይተኸዋል መቃወም ማለት ያ እንዲቆም መስራት ነው። አንተ እቃወማለሁ ያልከው አጠገብህ ጥቃት ቢፈጠር ነው ፌሚኒስቶች ግን ስራቸው በየትኛውም ስፍራ ስለምትጠቃ ሴት መቃወም ነው። ስለዚህ ከቻልን እናግዛቸው ካልቻልን አፋችንን እንዝጋ አረማመድና አነጋገራቸው ላይ አስተያየት አንስጥ።

ሴት ልጅ በሴትነቷ ምክንያት የሚገጥማትን ጾታዊ ጥቃት እንዲቆም መታገል የሁላችንም ጤነኛ ሰዎች ሰብአዊም ክርስቲያናዊም ኃላፊነት ነው። እኛ ያልተወጣነውን ኃላፊነት ግን የሚወጡ እህቶችን ቁጭ ብሎ መቃወም ለእኔ ጤነኝነት አይደለም እግዚአብሔርም ፈጽሞ አይወደውም።

ፍትህ ለህጻን ሄቨን። አሁንም ድምጻችንን እናሰማ

ወንድማችሁ አቡ ነኝ ሰላም ቆዩ
@APOSTOLICsuccession

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

24 Aug, 18:01


ጫካ መሀል ብቻሽን ሆነሽ ድንገት ቢገጥምሽ ድብ ትመርጫለሽ ወይስ የማታውቂውን ወንድ?

In real life የየትኛዋም ሴት ፍላጎቷ ባይሆንም እንኳን ደመ ነፍሷ የሚመራት ወደማታውቀው ወንድ ነው። ምክንያቱም የማታውቀው ወንድ አጥቂ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ አዳኝም ሊሆን ይችላል ስለዚህ የሕይወት ወይም የመትረፍ 50% ተስፋ አላት። ድቡጋ ግን ከመሞት ሌላ አማራጭ የለም። የማይገድል መልካም ድብ አይሆንላትም፣ ብትታገለው ልትጎዳውና ልታመልጠው የምትችለው አይደለም፣ ልታራራው ብትሞክር የሚረዳ አይደለም። ግልጽ ነው ወንዱ ሰውም አጥቂ ወንድ ከሆነ እኚህ ነገሮች ለርሱም አይሰሩም። በልመና የሚራራ ጭንቅላት ያለው ወንድ ሲጀመር ክፉ ጥቃት አያደርስም ጥቃት የሚያደርስ ከሆነ ገና ከጅምሩ ጭንቅላት የለውም።

ይሄ አባባል internationally መነጋገሪያ የሆነ ጥያቄ ሲሆን ከጥያቄው በላይ መልሱ ነው አነጋጋሪ ያደረገው። ምክንያቱም ይህን ጥያቄ የተጠየቁት ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ሴት ልጅና ታናሽ እህት ያላቸው ወንዶችም ሁሉ አብዛኛዎቹ ምርጫቸው "ድብ" የሚል ነበር። ለምን ድብን መረጡ? አብዛኛው ያስቀመጡት ምክንያት ከሁለቱም ጥቃት አንጻር ነው። ድብ ቢያጠቃ ወይ ለምግብነት ነው ወይም ራሱን ለመከላከል ነው። ወንዱ ቢያጠቃ ግን ለስጋ ስሜት ጥማቱ ነው። ድብ ቢያጠቃ ከዛ ጥቃት ሴት ልጅ ብትተርፍ እንኳን በህክምና የተጎዳ አካሏን ታክማለች ወንድ ቢያጠቃና ብትተርፍ ግን በህክምና ከማይመለስ ዘላለማዊ የህሊና ቁስል ጋር ነው። ድብ ቢያጠቃ ቢገድላት ነው። ወንድ ቢያጠቃት ግን በዝሙት እያሰቃየ ለስጋ አምሮቱ ከተጫወተባት በኋላ ለማሰብ እንኳን በሚከብድ ስቃይ አሰቃይቶ ነው። ድብ ቢያጠቃትና ብትተርፍ ሁሉም ሰው ቢያዝንላት ነው። ወንድ ቢያጠቃትና ብትተርፍ ግን በሰዎች ሁሉ አዕምሮ ውስጥ ካጠቃት ወንድ በላይ እሷ የምትሰደብ ርካሽ ተደርጋ የምትቆጠር ለነገ ሕይወቷ በማህበረሰብና በጓደኞቿ አይምሮና ንግግሮች እንዲሁም ድርጊቶች የህመሟ ቁስል እየተነካ የሚጠዘጥዛት ይሆናል። ድብ ቢያጠቃት እሷን የጥፋቱ አካል የሚያረጋት የለም ለድቡም ምክንያት የሚሰጥ አይኖርም ወንድ ቢያጠቃት ግን ምን ለብሳ ነበር? እሷ ራሱ ፈልጋ ነው፣ ሰክሮ ይሆናል፣ ወንድ አይደል አምሮት ነው..እሷንም የጥፋቱ አካል ለእሱም በርካታ excuse ይሰጠዋል። ስለዚህ ከጥቃታቸው አንጻር ድብ ወይስ የማታውቂው ወንድ ሲባል ድብን መምረጥ 100% ትክክለኛ መልስ ነው።

ከክርስትና አንጻር ይሄ አባባል እንዴት ይታያል? በእህትና ወንድሞች መሀል ያለውን ክርስቶሳዊ ፍቅር አይቀንሰውም?

Really? ስንትና ስንት ያንን ክርስቲያናዊ ፍቅር ፈጽሞ የሚያጠፉ የወንዶችን በሴቶች ላይ የሚፈጸም አሰቃቂ ጥፋት ምንም ሳንሰራበት ይሄ አባባል ወንዶችን የሚነካ ሲመስለን ያጠፋዋል ብለን እንደ ትልቅ አጀንዳ እንነጋገርበት? ክርስቲያናዊውን ፍቅርማ የሚያጠፋው ይሄ አባባል ሳይሆን ስንት ዘመን ሙሉ በወንዶች ሴቶች ላይ ሲደርስ የነበረው አሰቃቂ በደልና ጥፋት ነው። ያ በደልና ጥፋት ያላጠፋውን ፍቅር ይሄ አባባል አያጠፋውም።

"ይሄ አባባል ከአመታት በኋላ የሚፈጥረው ምንድነው?" የምር? ከስንት ዘመን ጀምሮ ያለው የወንድ ልጅ ጥቃት ምን ፈጠረ? ከወንዱ "ጥቃት" የሴቱ "አባባል" የበለጠ አስፈሪና አነጋጋሪ በምን መስፈርት ነው የሆነው? "ድብን ወይስ የማታውቂውን ወንድ" ማለትኮ ጉዳዩ ሰብዓዊነትን ከእንስሳ ጋር ማነጻጸር አይደለም የሚያደርሱትን ጥቃት ማነጻጸር እንጂ። ስለዚህ አሳሳቢው እየፈተፈጸመ ያለው ጥቃት እያለ ወርደን ስለ አባባል ልንነጋገር አይገባም። እኔ ይሄ አባባል ሰዎች ተቀበሉት አልተቀበሉት ድብ መረጡ አልመረጡ የሚፈጥረው ምንም ጉዳት አይታየኝም። የአጥቂ ወንዶችን ጭካኔ ይሄ አባባል አይደለም የፈጠረውና የሚፈጥረው። ስለዚህ አባባልን ሳይሆን ከአባባል በላይ ጥቃትን እንቃወም። አባባል ገና ለገና "እንዲህ ሊፈጥር ይችላል" በሚል ፍርሃት ነው። ጥቃቱ ግን ያለና ለዘመናት የኖረ የታቀፍነው ቆሻሻ ነው።

"ይህ አባባል ሴቶች ወንዶችን እንዲጠሉ ያደርቸዋል" ኧረ ወንድን የምትጠላ ሴት ከዚህ አባባል የበለጠ ብዙ በቂ ተግባራዊ ምክንያት አላት። ሴቶች ውስጥ "የተሳሳተ" ጥላቻ ለወንድ ልጅ ካለ ይሄንን አባባል ሳይሆን ከዚህ አባባል የሚበልጠውን እንድትጠላን ያደረገውን የዘግናኝ ወንዶች ጥቃት የበለጠ እንቃወም። ያን ጥቃት በማስቆም እንጂ አባባሉን በማስቆም ልቧን አናጠራውም። በደረሰባትና ከደረሰባቸው ሰዎች በሰማችው ጥቃቶች ምክንያት በልቧ የተፈጠረውን ጥላቻ ክርስቲያናዊነቷ ብቻውን ሊያነጻው አይችልም። የህሊናንና የአካሏን ቁስል ክርስቲያንነቷ አይፈውሰውም። እግዚአብሔር መንፈሷን አድሶላት በዛ ቁስል ውስጥ እንድትበረታና እንድትጠነክር ያግዛታል ያደርጋታል እንጂ ያን ቁስል እንዳልተፈጠረ አያጠፋውም ሊጠፋ የሚችል ቁስልም አይደለም። ስለዚህ ክርስቲያናዊውን ፍቅር የሚያጠፋውና መዝመት የሚገባን ወንድን የሚያቀል የመሰለን "ድብ ወይስ ወንድ" አባባል ላይ ሳይሆን ሰይጣናዊ የሆነውን በብዙ ወንዶች በሁሉም ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ከትንሽ እስከ ትልቅ ያሉ ጾታዊ ጥቃቶችን በመቃወምና በመከላከል እንዲሁም ባለንና በቻልነው አቅም ማኅበረሰብን ለማንቃት ከሚጥሩ እህቶች ጋር አብረን በክርስቲያናዊ መንገድ እዚህ ጉዳይ ላይ ስንሰራ ነው።

እነዚህን እህቶች (ፌሚኒስት) አስመልክቶ እኔ የኢትዮጵያን ፌሚኒዝምም ሆነ ፌሚኒስቶችን እጅግ በጣም ነው የምወዳቸውም ለእነርሱ ትልቅ ክብርም ያለኝ። እኔም እንደነርሱ ያልሆንኩት ስለማልፈልግ ሳይሆን የእነርሱን ያህል የልብና የህሊና ጥንካሬ ስለሌለኝ ነው። ለምን በዚህ ልክ አከበርኳቸው? ጤነኛ አዕምሮ ስላለኝ። (አራት ነጥብ) የሚያገናዝብና የሚሰራ ጭንቅላት ስላለኝ ሐሳባቸውንም ሆነ ትጋታቸውን በፍጹም ልቃወምና ልጠላው አልችልም። እግዚአብሔር ከዚህ በላይ አቅምና ብርታትን ይስጣቸው። የበርካታ የታፈኑ የእህቶች ድምጽ በመሆናቸው፣ ከደነዘዝንበትና ከጀዘብንበት ጉዳዮች ስለሚያነቁን፣ ትክክለኛ ወንድ እንድንሆን ስለሚቀርጹን፣ የሴትነትን ትርጉም ለሴቶች ስለሚያስተምሩ እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ያበርታቸው። ድድብናችንን ስለሚዘልፉት መሃይምነታችንን ስለሚወቅሱት እግዚአብሔር ያበርታቸው።

አገላለጻቸው? የሚጠቀሙት ቃላት? አኪያሄዳቸው..ክርስቲያናዊ ነው? Really? እነርሱ የሚያዩትንና የሚሰሙትን የሴት ልጅ ህመም እንዲሁም እነርሱ የሚገጥሟቸው በአስተሳሰብ የወረዱ ሰዎች ሁሉ እኔንም ቢገጥሙኝ ለአነጋገሬ ሳልጨነቅ ልናገራቸው እንደማልችል እርግጠኛ አይደለሁም። እኛን የሚያሳስበን ንግግራቸው ነው? እነርሱ የሚሰሩትን ቅንጣት እንኳን ሳንሰራ የእነርሱ አረማመድና አገላለጽ ላይ እጅና እግራችንን አጣጥፈን ቁጭ ብለን አስተያየት እንስጥ? ክርስቲያናዊ ካልሆነ እስኪ በክርስትያናዊ መንገድ እኛ እንስራው? እስኪ አገላለጻችንን አሳምረን እኛም እንቃወም? እስኪ አነጋገራችንን ቆንጆ አርገን እኛም የሴቶችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበር እንስራ? የሚሰሩት ላይ ቁጭ ብለን አስተያየት ከምንሰጥ ችግር የለም እነርሱን አንሁን። ፌሚኒዝም ሰይጣናዊ ነው? እሺ ይሁን እኛ ፌሚኒስት ሳንሆን የሴትን ልጅ ጥቃት እንቃወም?

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

22 Aug, 09:03


የቅድስት ድንግል ማርያም   ቅዱስ ስዕል
Full epoxy
Size = 80cm * 50 cm
💰  3500
🚕 ባሉበት እናደርሳለን

ለማዘዝ @Rhripsime

@tekelepoxy
#share #share

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

21 Aug, 18:56


https://youtu.be/skioS-VINJY

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

19 Aug, 13:07


የጥያቄዎቻችሁ መልስ pinned Deleted message

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

18 Aug, 11:15


https://youtu.be/srfLb0inmyI

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

12 Aug, 11:35


https://t.me/tekelepoxy

ሰላም ተወዳጆች ይሄ አዲስ የጀመርኩት የ epoxy ቅዱሳት ሥዕላትን ከሳይዝና ዋጋቸው ጋር የማስቀምጥላችሁ አዲስ ቻናል ነው ሁላችሁም join አድርጉትና ማዘዝ የምትፈልጉትን እየመረጣችሁ ታዙናላችሁ🙏👍

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

11 Aug, 09:09


https://youtu.be/wqm_a_GKBag

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

08 Aug, 22:13


https://youtu.be/3GooXksYCM8

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

05 Aug, 13:31


https://youtu.be/6spQWJR39jk

16,721

subscribers

338

photos

78

videos