አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

@amhara_media_center


አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:25


የወሎና የጎንደር ጀብዱ

በወሎና በጎንደር ቀጠና በተካሄዱ ውጊያዎች ፋኖ በአገዛዙ ጦር ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረሱ ተገለጸ

በዋርካዉ ምሬ ወዳጆ የሚመራዉ የአማራ ፋኖ በወሎ በትላንትናው እለት ከጧቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ምሽት 4:00 ሰዓት በተደረገ አውደ ውጊያ በባለ ሽርጡ ክ/ጦር ዋና አዛዥ እንድሪስ ጉደሌ እየተመራ
ጊራና ከተማ ፣ፋፍም፣ ጊዶ በር፣ ጉቤ ፣ ውረኔ በተባሉ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ ጀብዱ ፈፅሟል ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ ገልጿል።

በዚህ በጊራና በነበረው ውጊያ በሻለቃ ደምሌ እና በፋኖ ሰለሞን ሞላ እየተመራ የልጅ እያሱ ክ/ር ጦርም ተሳትፎ ማድረጉ ታውቋል፡፡

የብልጽግናን ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ከተማውን ተቆጣጥረን በዚህ ሰዓት አሰሳ በማድረግ ላይ እንገኛለን ያለው ድርጅቱ በተጨማሪም ከሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ የአገዛዙ ቁልፍ ቦታዎች መሀል አምባ፣ሊብሶና ውርጌሳንም በመቆጣጠር እያስጨነቅነው እንገኛለን ብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአገዛዙ ሠራዊት ተጨማሪ ኃይል ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ከተማ ለማስገባት  በምድር ዙ- 23፣ BM-107፣ ዲሽቃና ሞርታርን እንዲሁም በሠማይ በሄሊኮፍተር የታገዘ ጉዞን ሢያደርግ መዋሉን የአማራ ፋኖ በጎንደር አሳውቋል።

በተመሣሣይ ከባሕር ዳር የተነሳውን ጦር ለመቀበል ከደብረ ታቦር ወደ አለም በር  የአገዛዙ ጦር በከባድ መሣሪያ ታግዞ ዘምቷል።

ሆኖም ድልን እሥትንፋሳቸው ያደረጉ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነችው ጣይቱ ሻለቃ በጥምረት የአገዛዙን ጦር የተለያዬ ቦታ ላይ ደፈጣ ጥለውበታል።

በደፈጣ የታጨደው የአገዛዙ ጦር ወደ ሁለቱም አቅጣጫ እግሬ አውጭኝ ካለ በኋላ ራሱን አደራጅቶ ተመልሷል። ድንጋጤን መለያው ያደረገው የአቢይ ጦር በምድር ውጊያ እንደተሸነፈ ሢያረጋግጥ በሠማይ በሄሊኮፍተር ታግዞ ከእንደገና ውጊያን አድርጓል።

ነገር ግን አሸናፊነት ከአባቶቻቸው የወረሱት፣ ሥነ ልቦናቸው በዕውነት የጸናው፣ ትግላቸው ሕልውናን ማሥቀጠል እንደሆነ ያመኑት የአሥቻለው ደሤ ቀኝ እጆች፣ የውባንተ አባተ ልጆችና የናሁሰናይ ወንድሞች በአገዛዙ የጦር ጋጋታ አልተረበሹም።

የአማራ ፋኖ በአለም በር ላይ የልብ ትጥቅን በደምብ ታጥቆ በውሥን ጦር አገዛዙን ሢለበልብ ውሏል። አለም በርና ዙሪያ ገባው ላይ በነበረው ውጊያ የአገዛዙ አመራሮችም ጭምር ሢደመሰሱ ደብረ ታቦር ሆሥፒታል በዚህ ሠዓት በአገዛዙ ቁሥለኞች ተሞልቷል። የአገዛዙ ከፍተኛ የጦር መሪም እንደቆሰለና ታቦር ሆሥፒታል እንደገባ አረጋግጠናል ብሏል በአርበኛ ባዬ ቀናው የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር

ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:23


ሰበር መረጃ
፨፨፨፨፨፨፨

በዛሬው ዕለት ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም የአገዛዙ ሰራዊት ከአዲስ ዘመንና ከእብናት ኃይሉን አግተልትሎ በአንቦ ሜዳና አካባቢው ወረራ ለመፈፀም በሌሊት ጀምሮ በተለያዩ አቅጣጫዎች እንቅስቃሴ ቢያደርግም በጀግናው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር አንበሳው ሊቦ ከምከም ብርጌድ ተመክቶ መመለሱን የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መልካሙ ጣሴ  ገልጿል።

ከአዲስ ዘመን አቅጣጫ የተነሳው የጠላት ሀይል በተለያየ አቅጣጫ በማስፋት ከበባ ሊፈፅም  ቢሞክርም ብራ በተባለው አካባቢ ደፈጣ ይዞ የቆየው የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር የአንበሳው ሊቦ ከምከም ብርጌድ ነበልባል ሻለቃ ሙትና ቁስለኛ አድርጎ ወደመጣበት አስፈርጥጦ ልኮታል ሲል ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለጣቢያችን ገልጿል።

የጠላት ሀይል ከላይ የጀት ሀይል በማንሳፈፍ በምድር ዲሽቃና ሞርተር አግተልትሎ ቢገባም በአናብስቶቹ የሊቦ ፋኖ ተመትቶ የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለ 251አክሎ ገልጿል።


  ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:22


★የድል ዜና

ከላይ ድሮን ከታች ታንክና ዲሽቃ ይዞ ወደ ዉጊያ ያመራው የአብይ አህመድ ሰራዊት አስከሬኑን ታቅፎ ተመለሰ።

      (ወሲል የወንዶች ወኪል)
ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በድሮን፣በታንክ፣በሞርተር እና ዲሽቃ በመታጀብ በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ ወሲል ቀበሌ በሚገኙ የፋኖ አባላት ላይ የተደራጀ ጥቃት ለመፈፀም ከቦታው የተንቀሳቀሰው የአብይ አህመድ ጥምር ጦር ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ተመልሷል።

የጠላትን ሴራ አክሽፎ የመለሰው በዋሴ ተገነ የሚመራው የተስፋ ብርጌድ ሻለቃ አራት የፋኖ አባላት የጠላትን ሴራ ቀድሞ በመገንዘብ በወታደራዊ ቋንቋ አገላለፅ ገዥ ቦታ ቀድሞ በመያዝ እስካፍንጫው ታጥቆ የመጣን የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርጎ መልሶታል።

ወቅቱ የደረሱ ሰብሎች መሰብሰቢያ ወቅት ስለሆነ አርሶአደሩ ሰብሉን እንዳይሰበስብ እንቅፋት እንሆናለን ሰብሉንም በከባድ መሳሪያ እናቃጥላለን በሚል ሰይጣናዊ ተልዕኮ አማራን ለማጥፋት የሚጋጋጠው ቡድን በተስፋገብረስላሴ  ብርጌድ የፋኖ አባላት እየተደመሰሰ ሲሆን ለበረኸት ወረዳ ማህበረሰብ የእናቶች አገልግሎት መዋል ያለባቸው አምቡላንሶች የጠላትን ጥምር ጦር ሙትና ቁስለኛ ማመላለሱን ቀጥለውበታል።

    ድል ለአማራ ህዝብ!
ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ክፍል
ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:22


ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም

★የድል ዜና

ከላይ ድሮን ከታች ታንክና ዲሽቃ ይዞ ወደ ዉጊያ ያመራው የአብይ አህመድ ሰራዊት አስከሬኑን ታቅፎ ተመለሰ።

     
ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በድሮን፣በታንክ፣በሞርተር እና ዲሽቃ በመታጀብ በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ ወሲል ቀበሌ በሚገኙ የፋኖ አባላት ላይ የተደራጀ ጥቃት ለመፈፀም ከቦታው የተንቀሳቀሰው የአብይ አህመድ ጥምር ጦር ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ተመልሷል።

የጠላትን ሴራ አክሽፎ የመለሰው በዋሴ ተገነ የሚመራው የተስፋ ብርጌድ ሻለቃ አራት የፋኖ አባላት የጠላትን ሴራ ቀድሞ በመገንዘብ በወታደራዊ ቋንቋ አገላለፅ ገዥ ቦታ ቀድሞ በመያዝ እስካፍንጫው ታጥቆ የመጣን የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርጎ መልሶታል።

ወቅቱ የደረሱ ሰብሎች መሰብሰቢያ ወቅት ስለሆነ አርሶአደሩ ሰብሉን እንዳይሰበስብ እንቅፋት እንሆናለን ሰብሉንም በከባድ መሳሪያ እናቃጥላለን በሚል ሰይጣናዊ ተልዕኮ አማራን ለማጥፋት የሚጋጋጠው ቡድን በተስፋገብረስላሴ  ብርጌድ የፋኖ አባላት እየተደመሰሰ ሲሆን ለበረኸት ወረዳ ማህበረሰብ የእናቶች አገልግሎት መዋል ያለባቸው አምቡላንሶች የጠላትን ጥምር ጦር ሙትና ቁስለኛ ማመላለሱን ቀጥለውበታል።

    ድል ለአማራ ህዝብ!
ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ክፍል
    

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:22


በጦርነት ላይ ትንታኔ የሚሰራው አለም አቀፉ ተቋም “ፋኖ የሰለጠኑ ተዋጊዎች ያሉት ሃይል ነው” ሲል ገለጸ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አለም አቀፉ የጦርነት እንቅስቃሴዎችን አጥኚ ተቋም “Institute for the study of war” /ISW/ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል በአማራ ፋኖ እና በልጽግናው አገዛዝ መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በሚመለከት ትንታኔያዊ ሪፖርት አቅርቧል፡፡በሪፖርቱም የፋኖ ሃይሎች ከሃምሌ ወር ጀምሮ ባደረጉት አዲስ የማጥቃት ዘመቻ በርካታ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ገልጿል፡፡

በአለማችን ላይ የሚካሄዱ ጦርነቶችን እየተከታተለ በባለሞያዎች የሚያስተነትነው ይህ ተቋም የፋኖ ሃይሎች በተበታተነ ሁኔታ ያሉና የየራሳቸው አመራር ያላቸው ቢሆኑም ሁሉም በሚገባ የሰለጠኑና ተመሳሳይ አላማ ያላቸው ናቸው ብሏል፡፡ከቀድሞ የክልል ልዩ ሃይልና የፌደራል የጸጥታ ሃይሎች ጭምር የተካተቱባቸው እንደሆኑ ያመለከተው ሪፖርቱ በክልሉ ህዝብም ድጋፍ እንዳላቸው አስረድቷል፡፡


እንደሪፖርቱ ከሆነ ከ2015 ሰኔ ወር ጀምሮ እስከ 2016 መጋቢት ወር ድረስ በየወሩ የፋኖ ሃይሎች በአማካኝ በወር 25 ጥቃቶችን ፈጽመዋል፡፡ይህ አሃዝ ባለፉት ጥቂት ወራት ግን በሶስት እጥፍ ማደጉን ገልጿል፡፡ በቻርት ፣ በካርታና በግራፍ ተደግፎ

የቀረበው ሪፖርቱ በርካታ ጉዳዮችን በስፋት ዳሷል፡፡በመሆኑምእስከዛሬ ፋኖን እና እንቅስቃሴውንበሚመለከት ከቀረቡ አለም አቀፍ ሳይንሳዊ ትንታኔዎች የተሻለና የተብራራ እንዲሁም መረጃዎችን ያካተተ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል፡፡

ይህ ተቋም በአለማችን ላይ ያሉ ትላልቅ ጦርነቶችን በመተንተን እና የዳሰሳ ጥናት በመስራት የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል እየተካሄደ ስላለው ጦርነት የሚሰራቸውን ትንታኔዎች አለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደምንጭነት ሲጠቅሱት ይሰማል፡፡

 ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለአማራ ፋኖ

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:17


የድሮን ጥቃት!

ዛሬ በጠዋቱ በረኸት ወረዳ 04 ቀበሌ ላይ የብልፅግና አገዛዝ ድሮን ተጠቅሞ የንፁሀን ቤት ላይ ጥቃት አድርሷል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:16


5/2/17 ዓ.ም

🔥ወሎ ቤተ-አምሃራ የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው ተጋድሎ‼️

ጥቅምት 4 እና 5 ዞብል አምባ ክፍለጦር ታጠቅ ልዩ ዘመቻና ዲቢና ወርቄ ባለ ሽርጡ ብርጌድ ከሙጃ አቦሆይ ጋሪያና በቅሎ ማነቂያ በኩል የመጣዉን ጠላት ተኩለሽና አካባቢው ላይ እንዲገባ በማድረግ ከበባ ዉስጥ አስገብተው እየቀጠቀጡት ይገኛሉ:: ከወልድያ ዙሪያ ቃሊምና ሮቢት አካባቢ በአዋስ በኩል ዉጊያ የጀመረው ጠላት የወልድያ ዙሪያው ዉጊያ ተበላሽቶበት ግራ ተጋብቶ የሚገኝ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ዉጊያ የጀመረዉና በአቦሆይ ጋሪያና በበቅሎ ማነቂያ ወደ ተኩለሽ የወረደው ጠላት ከበባ ዉስጥ ይገኛል::

በዚህ ዉጊያ ዞብል አምባ ክፍለጦር ሰፊ ቀጠና ሸፍና የአምበሳዉን ድርሻ ወስዳ ተጋድሎ እያደረገች ያለች ሲሆን ዲቢና ወርቄ ባለሽርጡ ብርጌድ ታጠቅና ልዩ ዘመቻም የገባዉን ጠላት ከበባ ፈፅመዉ ተጨማሪ ስንቅና ጥትቅ እንዳይደርሰው አድርገዉ ዘግተዉ ይገኛሉ::

በሌላኛው ቀጠና ሃውጃኖ ክፍለጦር ከራያ ቆቦ በዋ ሚካኤል እስከ ራያ አላማጣ ዋጃ ከተማ ድረስ ሰፊ ቀጠና በመሸፈን ተጋድሎ እያደረገች ትገኛለች:: ጮቢ በር ተራራ ላይ ያለው የጠላት ሃይል ከሃውጃኖ ክፍለጦር መካናይዝድ በኩል የሚወረወርበትን ሞርታር መቁዋቁዋም አቅቶት ያለበት ሁኔታ ነው ያለው:: ከዚህ በተጨማሪም ሃውጃኖ ክፍለጦር በተኩለሽና በአቦሆይ ጋሪያ አካባቢ ተከቦ ያለው ጠላት ከራያ ቆቦ ከተማና ከራያ አላማጣ አካባቢ ተጨማሪ ሃይል እንዳይደርስለት ቀጠናዉን ዘግታ ትገኛለች::

በዚሁ በወሎ ቤተ-አምሃራ አማራ ሳይንት
ከ10 በላይ የጥምር ጦር አባላት ሲደመሰሱ ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛም ተጫነ!
ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ መቅደላ ወረዳ ውስጥ ኮሬብ ታዳጊ ከተማ አቅራቢያ የረንዛ የሚባል ስፍራ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ/ም የአማራ ፋኖ በወሎ አምሓራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ፋኖዎች ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ጉርቦ ለጉርቦ ሲተናነቁ የዋሉ ሲሆን በድምሩ ከ10 በላይ ጠላት ሲደመሰስ በውጊያው የቆሰሉትም ወደ ሆስፒታል ሲጋዙ ውለዋል::
የሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ በለጠ ምትክ በመራው በዛሬው ኦፕሬሽን ጠላት ላይ የከፋ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን ለማረጋገጥ ተችሏል::

አሳምነው ክፍለጦር የሰሜን ወሎ ዞን መቀመጫ ወልድያ ከተማና አካባቢው ላይ ባለፉት ሶስት ቀናቶች ታላቅ ተጋድሎዎችን በማድረግ በርካታ ድሎችን የተጎናፀፈች ሲሆን በክፍለጦሩ መካናይዝድ በኩል የሞርተር ጥቃት በመፈፀምም ወልድያ ከተማ መድፍ ማቃጠላቸዉና ማውደማቸው የሚታወቅ ነው::

በዚሁ በወሎ ቤተ-አምሃራ የአማራ ፋኖ በወሎ  እያደረገው ባለው ከፍተኛ ተጋድሎ አገዛዙ ሽንፈቱንና የቁልቁለት ጉዞዉን የተያያዘው ሲሆን የብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊትም በአውደ ዉጊያ እየደረሰበት ያለዉን ሽንፈት ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ በመጨፍጨፍ እየተበቀለ ይገኛል:: ምንም እንኩዋን የኦነግ ብልፅግና ቡድን የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ ዘር ማጥፋት እየፈፀመበት ያለ ቢሆንም በሰሞኑ ዉጊያ ከወልድያ ስታዲየም በሚወነጨፍ መድፍ ቃሊምና አካባቢው ላይ የንፁሃንን ህይወት ቀጥፎዋል:: ቆቦ ከተማ ሆርማትና ጠዘጠዛ የሚወነጨፍ መድፍ በዋ ሚካኤል እና አካባቢው ላይ በተመሳሳይ የንፁሃን ህይወት ተቀጥፎዋል:: ባለፉት ጊዜያት በርካታ አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ንፁሃኖች በአገዛዙ ጭፍጨፋ እንደተፈፀመባቸው የሚታወቅ ነው::


#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:16


ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም


#ደጋዳሞት !

# በደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ የድሮ ጥቃት ተፈፅሟል። የድሮን ጥቃቱ በወረዳው አስተዳደር ግቢ ውስጥ የተፈፀመ ሲሆን ፍርድ ቤቱ መውደሙን የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ዮሀንስ ዓለማየሁ ተናግሯል።

በዛሬው እለት ከቀኑ 6፡15 ላይ አገዛዙ  ደጋዳሞት ወረዳ  ፈረስቤት ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ላይ ጥቃት ፈጽሟል፡፡ በዚህ ጥቃት በካባቢው የነበረ አንድ ህጻን የተጎዳ ሲሆን ወረዳ ጽህፈት ቤቱም ጉዳት ደርሶበታል፡፡ በዚህ ሰዓትም ተጨማሪ ድሮን አሰሳ እያደረገች ነው፡፡

የአማራን ህዝብ ለማጥፋ* ት  እና  ወደ ኋላ ለማስቀረት የሚታትረው አገዛዙ፡ ተቋማትን እና የህዝብ መገልገያ ቁሳቁሶችን በድሮን እና ከባድ መሳሪያ እያወደመ ቀጥሏል፡፡  በመውደቅ ላይ የሚገኘው የአብይ አህመድ  አገዛዝ  መሰል ዘግናኝ ጸረ_ህዝብ ጥቃት ይፈጽም እንጂ፡  ከመውደቅ ወይም ከመገርሰስ የሚታደገው አንዳች ሀይል አይኖርም!

ድል ለፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:16


5/2/17 ዓ.ም


🔥#ኮሬብ_ወሎ‼️

የአማራፋኖ በወሎ አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ትናንት ጀምሮ እያደረገ ባለው እልህ አሥጨራሽ ትግል የብልጽግና ሚኒሻና አድማ ብተና
#በኮሬብ ከተማ የረንዛ በተባለ ቦታ እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል  የሸህ ሁሴን ልጆች ግንባርን ለይተው በመምታት የሚታወቁት ጀግኖቹ የህዝብ ልጆች እየለበለቡት ይገኛሉ።
ይህ ብርጌድ በበለጠ ምትክ (ድሮን)እየተመራ አሥደማሚ ቀዶጥገና ሠርቶ የአገዛዙን አሽከር ከአፈር ደባልቆታል ከአሥር በላይ የተደመሠሠ ሲሆን ከዚሁቁጥር ያላነሠ ሆስፒታልእደገቡ አረጋግጠናል። በቀጣይ ጠላትን ሙሉ በሙሉ ከወረዳው ለማሥለቀቅ አሥፈላጊውን ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል ሲል መቅደላ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ለንስር አማራ ገልፀዎል‼️


#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:16


🔥#የቦንብ_ጥቃት‼️

የደሴ ከተማ አስተዳድር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በሆነው ሳሙኤል ሞላልኝ መኖሪያ ቤት አካባቢ 2 የቦንብ ጥቃት ተፈፅሟል💪
3/2/17 ዓ.ም



#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:15


4/2/17 ዓ.ም

#ወልድያ

የሰሜን ወሎ ዞን መናገሻ በሆነችው ወልድያ ከተማ ዙሪያ አፍሪኬር፣ ጥቁር ውሃ፣ ጦጣ ማደሪያ እና ጉቦ በተባሉ አከባቢዎች ትናንት ምሽት ከባድ ውጊያ ተካሂዷል።

በከተማዋ ዙሪያ በተለይ ከጎንደር በር ኬላ በቅርብ ርቀት በሚገኘው በተለምዶ ጉቦ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ምሽቱን ሁለት ጊዜ ከባድ ውጊያ እንደተደረገበት የመረብ ሚዲያ የወሎ ቅርንጫፍ ማሰራጫ ጣቢያ ዘጋቢዎች አረጋግጠዋል።

ጉቦ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ምሽት 01 ሰዓት እና ምሽት 04 ሰዓት ላይ እልህ አስጨራሽ ውጊያ የተደረገ ሲሆን በዚህም በርካታ የመከላከያ ሰራዊትና የአድማ ብተና አባላት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው ታውቋል።

ጎንደር በር የሚገኘው የወልድያ ከተማ 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለሁለተኛ ጊዜ ትናንት ምሽት ጥቃት እንደተፈመበት የአከባቢው ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።

400 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎበት በተሰራው በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስቴዲየም ማዘዣ ጣቢያውን ያደረገው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄኔራል አሰፋ ቸኮል በትናንት ምሽቱ ውጊያ እንዴት ሆኖ ወደ አፋር እንደሸሸ መረብ ሚዲያ ዘግቧል፡፡



#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:15


3/2/17 ዓ.ም

🔥#ነጎድጓድ_ክፈለ_ጦር💪

የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ደብረብርሃን ከተማ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ተከማችቶ በነበረ የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ኃይል ላይ በምሞርተር የታገዘ መብረቃዊ ጥቃት ሰነዘረ‼️

ከሰሞኑ የአማራን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠፋለሁ በሚል ፉከራ ያለ የሌለ ሀይሉን አግተልትሎ  ወደ አማራ ክልል የገባው የብልፅግናው ዙፋን አስጠባቂ ቅጥረኛ አራዊት ሰራዊት ባሰበው ልክ ሳይሆን በግልባጩ እየተቀጠቀጠ ይገኛል።
በትናንትናው አመሻ እለትም የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ኃይል  ደብረብርሃን ከተማን ለመጠበቅ በሚል ከደብረብርሃን ከ5ኪሎሜትር በላይ በማትርቀው ወሻውሽኝ ቀበሌ መሽጎ ህዝብን ለማሰቃየት በተቀመጠ ባንዳ አድማ ብተናና ቅጥረኛ ሚሊሻ  በአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ በካምፑ ላይ በተወሰደ በሞርተር የታገዘ መብረቃዊ ጥቃት ብትንትኑ ወጥቶ ወደ መሀል ደብረብርሃን ፈርጥጧል።
በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽ ሻለቃ ዓለሙ ሀብቱ እና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ ምኒልክ ሻለቃ መሪ ፊትአውሪሪ ደሳለኝ ሽፈራ በተመራ በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን በርካታ የጠላት ሀይል ሰብዐዊ እና ቁሳዊ ሀብቱን አጥቶ ወደመጣበት የፈረጠጠ ሲሆን የወገን ሀይልም ግዳጁን በሰላም አጠናቆ ወደ መጣበት በሰላም ተመልሷል።
       "ድላችን በክንዳችን"

©የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኘነት ክፍል



#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:15


3/2/17 ዓ.ም


🔥#ቤተ_አማራ_ወልድያ አሁን | ምድር አንቀጥቅጥ ውጊያ‼️

በሰሜን ወሎ ዞን መቀመጫ ወልድያ ከተማ ከፍተኛ የሆነ የመድፍ ፍንዳታ እየተሰማ ሲሆን ወደ ቃሊም አቅጣጫ ነው የመከላከያ ሜካናይዝድ አባላት መድፍ አዙረው የሚተኩሱት:: ከሼሁ ስታዲየም የሚተኮሰው መድፍ በቃሊም ግንባር የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ክፍለ ጦር የቆረጠውን የመከላከያ ሰራዊት ቅሪት ለማስወጣት ነው:: አሳምነው ክፍለ ጦር ግን  አልሰማም አላስወጣም ብሎ ይዞት ምድር ቀውጢ ሆናለች በተየያዘ
#ወልድያ ቆንጆዎች ገብተዎል።

የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ጽጌ ክፍለ ጦር ፋኖዎች በዛሬው ዕለት የ801ኛ ኮር ሰራዊትን ጥሰው ወልዲያ ከተማ ገብተዋል:: ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ትንቅንቅ ላይ ናቸው:: የከባድ መሳሪያ ተኩስ አሁንም አልቆመም! መከላከያ በጨበጣ ሲያቅተው በርቀት መድፍ እየተኮሰ ሲሆን ቅንቡላው የሚያርፍበት አልታወቀም:: ንፁሀንን የመፍጀት ውሳኔ ነው:: የወልዲያ ህዝብ ከፋኖ ጎን እንድትቆሙ ጥሪ እናቀርባለን!   ወልድያ አካባቢ ያላቹህ መረጃ በዉስጥ መስመር እንድታደርሱንም እንጠይቃለን።



#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:13


ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም

በከባድ መሣሪያ ታጅቦ ከአጣዬ እና ከኬሚሴ ከተማዎች በመነሳት ካራ ቆሬ አካባቢ የሚገኘውን የፋኖ አባላት ለመደምሰስ አስቦ የተነሳው የመከላከያ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ተመለሰ።

ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም የካራ ቆሬ ከተማን ለመቆጣጠር መድፍና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን በመያዝ የክፋት ሴራውን ሰንቆ ከኬሚሴ እና አጣዬ አቅጣጫዎች በመነሳት ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሰራዊት ያሰበው ሳይሳካ ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ተመልሷል።

ከኬሚሴ እና ከአጣዬ የተንቀሳቀሰው የጠላት ሃይልን አስመልክቶ መረጃው ቀድሞ የደረሰው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ አፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለጦር በሻለቃ ልመነው ዘውዴ የሚመራው የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብርጌድ በጠላት ሀይል ላይ ባደረገው የደፈጣ ጥቃት አማራን ለማጥፋት አቅዶ የመጣው የአገዛዙ ወታደር ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት ወደየመጣበት አቅጣጫ ፈርጥጦ ተመልሷል።

   ድል ለአማራ ፋኖ

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ
ህዝብ ግንኙነት ክፍል
 

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:13


2/2/17 ዓ.ም

🔥#የድል_ዜና_በላስታ_ሰማይ_ስር‼️

ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል
ዘመቻ አርበኛ ሻለቃ ሰማኝ
አማራ ፋኖ በወሎ ጀነራል አሳመነው ጽጌ ኮር
በትናንቱ ዕለት ማለትም 1/2/17 ጀግኖች በደፈጣ ታሪክ ሰርተዋል ከወደ ወልደያ  ወደ ላሊበላ እየተግተለተለ ሲጓዝ የነበረው ሶስት ኦራል ሙሉ  የብራኑ ጁላ ግፋፎት ድብኮ ላይ በደፈጣ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ በጀግኖቹ ድባቅ ተመቷል።

ይህን ድል የተጎናጸፈውም የኮሩ ሰባተኛ ክፍለጦር ሆኖ ከወር በፊት በኮሩ እውቅናን ያገኘው  እሸት ክፍለጦር ነው የክፍለጦሩ መሪ እደተናገረው
የተለያዩ የሬሽል ግብዓቶችም የወገን ጦር ተረክቧል የቡድን መሳሪያና የነስወከፍ መሳሪያም ለመቁጥር በሚያዳክት መልኩ መረከባቸውን ገልጾልናል 💪

ዛሬም ከጧቱ 4:00 ጀምሮ በአዚላ እና አምደወርቅ ሀይሉ ከበደ ክፍለጦር አናብስቶች ሲፋለሙ መዎላቸውን መረጃውን አድርሰውናል የዛሬውን ውሎ ሙሉ መረጃ ሲደርሰኝ አደርሳለሁ።




#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:12


የድል ዜና

ዘመቻ አርበኛ ሻለቃ ሰማኝ

አማራ ፋኖ በወሎ ጀነራል አሳመነው ጽጌ ኮር
በትናንቱ ዕለት ማለትም ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም በደፈጣ ታሪክ ሰርተዋል።

ከሰሜን ወሎ ወልደያ  ወደ ላሊበላ እየተግተለተለ ሲጓዝ የነበረውን ሶስት ኦራል ሙሉ  የብርሀኑ ጁላ ግፋፎት ድብኮ ላይ በደፈጣ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ድባቅ ተመቷል።

ይህን ድል የተጎናጸፈውም የኮሩ ሰባተኛ ክፍለጦር ሆኖ ከወር በፊት በኮሩ እውቅናን ያገኘው  እሸት ክፍለጦር ሲሆን በርካታ የተለያዩ የሬሽን ግብዓቶችን : የነስወከፍና የቡድን መሳሪያዎችን  መማረካቸውንም የክፍለጦሩ መሪ ገልጿል።

ዛሬም ከጧቱ 4:00 ጀምሮ በአዚላ እና አምደወርቅ ሀይሉ ከበደ ክፍለጦር አናብስቶች እየተፋለሙ መሆኑን መረጃውን አድርሰውናል።

ድል ለአማራ ፋኖ
ላስታ ጄነራል አሳምነው ፅጌ ኮር

ንሥር ብሮድካስት መረጃ
ቅዳሜ ጥቅምት 02 ቀን 2017 ዓ.ም

=====================
ቤተሰብ ይሁኑ! ትግላችን በጋራ!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:11


1/2/17 ዓ.ም

🔥#የድል_ዜና_አማራ_ሳይንት‼️

የአማራ ፋኖ በወሎ አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር  የአገዛዙን  አራዊት ሰራዊት እያርበደበዱት ይገኛሉ።

የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር  ክንፍ የሆነው በአማራ ሳይንት (አጅባር)  ወረዳ የሚንቀሳቀሰው በፋኖ ደሳለው ስጦታ የሚመራው #ታቦር_ተራራ_ብርጌድ ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም የጀግኖቹን ክንድ መቋቋም ያቃተው አማራ ሳይንት ወረዳ የገባው የአብይ የግል ወንበር አስጠባቂ ግሪሳ ሰራዊት ከጎረቤት ወረዳ ማለትም ከመሐል ሳይንት ወረዳ እገዛ ጠይቆ ከመሃል ሳይንት ወረዳም ለማገዝ መንገድ የጀመረ ቢሆኑም ጀግኖች የአትሮንስ ብርጌድ ፋኖዎች የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው የመንፈስ ልጆች ወደየት ነው እምትሄደው በማለት #ቀበሮ_ሜዳ ላይ ጠብቀው አፈር ከድሜ ሲያበሉት ውለዋል።


#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:10


ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ሁለት ክፍለ ጦሮች በጋራ በሻለቃ ዓለሙ ሀብቱ የነጎድጓድ ክፍ ለጦር ምክትል  አዛዥ በተመራ ልዩ ኦፕሬሽን በሁለት የተለያዩ ቦታዎች በተመሳሳይ ሰዓት ድል ተቀዳጁ።
        
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ ነብሮ ሻለቃ እና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ፊትአውራሪ አስማረ ዳኜ ብርጌድ በሻለቃ ዓለሙ ሀብቱ የቀድሞው ጋተው ብርጌድ ዋና አዛዥና በአሁኑ ነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን መሪነት በተሰራ  በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን ከደብረብርሃን ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘው አንጎለላና ጠራ ወረዳ  "ጠገጎ ቀበሌ"*ተከማችቶ የነበረውን የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ባንዳ ሚሊሻ በመበታተን ከተለያዩ ቦታዎች የፋኖ ቤተሰብና ደጋፊ ናቸው በሚል የተዘረፋ በርካታ የቀንድ ከብቶች ፣ በጎችና የጋማ ከብቶችን በማስመለስ ለባለቤቶቹ ለማስረከብ የመለየትና የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
 
ላለፈው አንድ አመት ደብረብርሃን ከተማ ተከማችቶ የህዝባችንን ሰላም ሲያናውጥ የከረመው ይህ አጥፊ እና ወራሪ የኦሮሙማ ቡድን የቀድሞው አማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ጋተው ብርጌድ ዋና አዛዥ የአሁኑ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽንን በተደጋጋሚ የሚወስደውን እርምጃ መቋቋም ስላቃተውና መውጫ መግቢ በመቸገሩ የተነሳ ከሰሞኑ የተለያዩ አካላትን የይተወን ሽምግልና ማቅረቡን ለማወቅ ተችሏል።

ይህ የተጠናና ድንቅ ኦፕሬሽ ከሀሳብ ጀምሮ እስከ ተግባራዊነቱ ድረስ በንቃት በመሳተፍና በመተግበር  የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ፊትአውራሪ አስማረ ዳኜ ብርጌ ሻለቃ አንድ መሪ ፋኖ ሀይሉ ተፈራ እንዲሁም የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር  ጋተው  ብርጌ ነብሮ ሻለቃ መሪ ፋኖ መንገሻ አዲሴና የጋተው  ብርጌድ ዘመቻ መሪ የሆነው ፋኖ ነገሰ አስበ በጋራ  የፈፀሙት ጀብዱ በታሪክ የሚመዘገብ ሆኖ አልፏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተመሳሳይ ሰዓት በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ በተሰራ ልዩ ኦፕሬሽን በደብረብርሃን ከተማ ጫጫ ክፍለ ከተማ ለአርሶ አደሩ መከፋፈል የነበረበትን የአፈር ማዳበሪያ ለአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ባንዳ ሚሊሻዎች በዝቅተኛ ዋጋ በማስረከብ እንዲቸረችሩ በመሰጠቱ ሰው በማይኖርበት አሳቻ ሰዓት በከባድ መኪና ተሳቢዎች ሲያንቀሳቅሱ በጀግናው ሻለቃ ዓለሙ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን እና በጋተው ብርጌድ ነብሮ ሻለቃ እይታ ውስጥ በመግባቱ ከነ ከባድ ተሽከርካሪዎቹ በቁጥጥር ስር በማስገባት ለማህበረሰቡ በዝቅተኛ ዋጋ ማከፋፈል ተችሏል ሲል የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኘነት ክፍል  አስታውቋል።

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለ ፋኖ

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:10


🔥#ባንዳ_መጨረሻችሁን_ከደጋዳሞት_ተማሩ‼️

ደጋ ዳሞት የሆነው እንዲህ ነው

        ሰራዊቱ ከደጋዳሞት ለቆ ሲወጣ አብሮት የነበረውን ሚሊሺያ ፖሊስና አድማ ብተና እንዳትከተለኝ ብሎ ጥሏቸው ነው የሄደው። ለመከተል የሞከሩት የብአዴን ሰራዊተቶች ተገድለዎል። ለምሳሌ የወረዳው ፖሊስ ሀለፊ በራሱ መኪና ሲከተላቸው ገለውታል። ፋኖ ደጋ ዳሞትን ሲይዝ ተራግፈው የቀሩትን የወረዳው አመራሮች አስተዳዳሪውን ጨምሮ አንቆ እስር ቤት ከቶታል። ሌሎች ፖሊስና አድማ ብተና እየተፈለጉ ነው። ብዙዎቹን ከተደበቁበትን አውጥተዋቸዋል።

       ሌላው ሰራዊቱ ሲወጣ አስሯቸው የነብሩ ሰዎችን በውጭ ቁልፎባቸው ነበር የሄደው። ፋኖ ከተማውን ሲይዝ ቁልፉን ሰብሮ እስረኞችን እንዲወጡ አድርጓል።

የፖሊስ፣ አድማ ብተናና የሚሊሺያ አባላት ከዚህ ምን ትማራላችሁ

#ንቁ...‼️

#ማሳሰቢያ_ለወገን_ሀይል‼️

ህዝብን ከጠላት ነፃ በማድረግ እያስተዳደራችሁ ያላችሁ የፋኖ ሀይሎች ‼️

1ኛ. እንቅስቃሴያችሁ በህዝባችን ፍላጎት መሰረት ይሁን ማለትም እያንዳንዷ ህግ የማስከበር እርምጃ በግል ጥላቻና ቂም ላይ የተመሰረተ እንዳይሆን እያንዳንዱ ከፍተኛ ውሳኔ በህዝብ ድምፅ ይሁን!!

2ኛ. ከጠላተ ነፃ የሆኑ ቀጠናዎች በማንኛውም ሰዓትና ቦታ የአየር ድብደባ ሲለሚኖር የህዝብ መሰባሰብ እንዳይኖር በማድረግ ህዝቡን ከጉዳት ጠብቁ!!

3ኛ. ነፃ ቦታዎችን በመጠቀም ለአየር ሀይል በማያጋልጥ መልኩ ስልጠናዎችና አደረጃጄቶች ይቀጥሉ ዘንድ በርትታችሁ ስሩ!!!

በመጨረሻም የወጣነው ለአማራ ህዝብ ነውና የህዝባችንን ባህል፣ዕምነት እና የአኗኗር አሴት ወዘተ እንጠብቅ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን‼️


©ንስር አማራ - ሀገሬ ሚዲያ

#ወጥር‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

1/2/17 ዓ.ም

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:09


30/1/17 ዓ.ም

🔥#መረጃ‼️

#ጎንደር
በዛሬው ዕለት ማለትም መስከረም 30/2017 አም በታች አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ቦታው በበው ከተማ በአርበኞች የጎቤ መልኬ፣የሰጠኝ ባብል እናም የማሃቤ ትንፋሽ የሆኑት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የጎቤ ክፍለ ጦር ፋኖዎች ከኦሮሙማው ግሪሳ ጋር እልህ አስጨራሽ ውግያ እያደረጉ ይገኛሉ‼️

በተየያዘ መረጃ ጎንደር ከደቢያ በለሳ እሰከ ወገራ
#የሂሊኮፕተር ቅኝት እየተደረገ ሲሆን ከትግራይ በሸሬ ወደ ደባርቅ ከባህርዳር ወደ ጎንደር ከወልቃይት ወደ ጎንደር  እንዲሁም በአየር ቀጥታ ወደ ደብረታቦር ተጨማሪ በርካታ ሀይል እየገባ ነው‼️

#ጎጃም

የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክ/ጦ በባህር ዳር ዙሪያ በአንዳሳና በጢስ አባይ አካባቢ የባህር ዳር ብርጌድ ከጠላት ጋር እየተፋለመ ነው ሲሉ ምንጮች ገልፀዎል‼️


#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:08


29/1/17 ዓ.ም


ወሎ ቤተ-አምሃራ

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው ተጋድሎ

ከአምቡላንስ ዉጭ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴን ለአንድ ሳምንት አካባቢ በመገደብ የጠላትን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በመግታት ስንቅና ንብረትም ይሁን የሰው ሃይል ከቦታ ቦታ እንዳያንቀሳቅስ በማድረግ የጠላት ተሽከርካሪዎች በብቸኝነት የሚገኙበትን ሁኔታ በመፍጠር ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚፈጠር የህዝባችንን ሞት በመቀነስ ብዙ ድሎችን ተጎናፅፈናል::

ጠላት ከሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ ወደ ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ዋናዉን መስመር ተጠቅሞ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ካቆመና በሃራ ጭፍራ ባቲ መስመርን መጠቀም ከጀመረና አመራሩም ከወልድያ ከተማ ወጥቶ ሃራ ከተማ ከመሸገ ወራቶች የተቆጠሩ ሲሁን ይህንን አሁንም በተሻለ ሁኔታ አጠናክረን ቀጥለናል:: መስመሩ ዛሬም ድረስ በፋኖ ቁጥጥር መሆኑ የሚታወቅ ነው:: ጊራና ከተማና አካባቢዉም በፋኖ ቁጥጥር ስር መሆኑ የሚታወቅ ነው::

አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦርና ንጉስ ሚካኤል ክፍለጦር የኦነግ ብልፅግናን ሰራዊት እና ባንዳን እያፀዱ እየማረኩ እየታጠቁ በድል የታጀበ ጉዞዋቸው ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎዋል:: በደላንታ ፀሃይ መውጫና ዳዉንት አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የአማራ ፋኖ በወሎ አደረጃጀቶችም ቀጠናዉን እስከመቆጣጠር የደረሰ ተጋድሎ በማድረግ ብዙ ድሎችን ተጎናፅፈዋል::

ላስታ ብ/ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ባለፈው አንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ከላሊበላ ከተማ የተነሳዉንና በጎንደር እብናት በኩል የመጠዉን የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ሁሉንም ወደመጣበት ሸኝተው በንብረትና በሰው ሃይል ብዙ ኪሳራ በማድረስ ድል አድርገዉታል:: ላስታ እሳምነው ኮር ዉስጥ የሚገኙት ሰባት ክፍለጦሮች ታላቅ ተጋድሎ እያደረጉ ያሉ ሲሆን ወደ ቀጠናው የገባዉን ጠላት ሙሉ ለሙሉ የማፅዳቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::
በዚሁ ቀጠና የጥራሪ ጀግኖችም ሙጃ ከተማ በመግባት በርካታ ባንዳ በመደምሰስ ብዙ ጦር መሳሪያዎችን ማርከው ታጥቀዋል::

በራያና በየጁ በኩል የሚገኙ ሁሉም የአማራ ፋኖ በወሎ ክፍለጦሮች ቆቦ ከተማንና ወልድያ ከተማን ከበው የሚገኙ ሲሆን በሰሞኑ ተጋድሎም ብዙ ድሎችን የተጎናፀፉ ሲሆን ሰሞኑን በሚደረጉ ተጋድሎዎችም የተለመዱ ጀብዶችን በመፈፀም ቀጠናው ላይ ያለን ጠላት መማረክና መታጠቅ ብሎም ማፅዳት ተጠናክሮ ይቀጥላል::

በቀጣይም ደሴንና ኮምቦልቻ ከተማን ጭምር ማእከል ያደረጉ ተጋድሎዎች አጠናክረን የምናደርግ ሲሆን በአማራ ፋኖ በወሎ ድርጅትን መጠበቅና ስዉር ድርጊያ በኩል የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ባንዳን የመመንጠርና አካባቢዉን ለትግል ምቹ የማድረግ የቅድመ ሁኔታ ስራዎችም ተጠናክረው ይቀጥላሉ::

#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:08


ዛሬ መስከረም 29-2017 አም በዘመቻ መቶ ተራሮች ሰባተኛ ቀን ላይ እንገኛለን!! አስቀድመን ቃል በገባነው መሰረት ለታሪክ ገፆች እንኳን የሚከብዱና  የሚገርሙ ድሎችን አስመዝግበናል፣እያስመዘገብንም ነው።

ዘመቻ መቶ ተራሮች ይቀጥላል። በትግላችን የሚመጣው ዋናውና ሙሉው ድልም ከፊታችን ይጠብቀናል።

-“ይህን ዘመቻ በትግሉ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነገር እናሳያለን ብለን ጀመርነው  “እግዚአብሄር ይመስገን! በተመኘነው ባቀድነውና ባሰብነው ፍጥነትና ግዝፈት እየተከወነ ነው።
-እንግዲህ የዛሬው ልዩ ክስተት
በጥብቅ ዲሲፕሊን የጠበቅነው የህዝብ ተቋም ባንክ! ዛሬ ውጊያ መሀል ቆሞ ሲተኩስ ተገኝቶ ከበርካታ
የአብይ ወራሪ ሰራዊት አባላት ጋር ምርኮኛ ሆኗል። እናመሰግናለን።

ወንድምና እህቶቼ!
ይህ ድል በፍፁም ወንድማማችነት፣ትብብር እና ፍቅር እየተገኘ ያለ ድል ነው።በጥቅሻ መግባባት የወንድሞች ቅንጂት የወለደው ነው።

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:08


ሰበር ዜና
ከሁለት ሰዓታት ባነሰ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሃያ የኮማንዶ አባላት በበረኸት ወረዳ መጥተህ ብላ ከተማ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፀመ።
መስከረም 28/2017 ዓ.ም
ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ
የአማራን ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ከነ ብርሀኑ ጁላ ሰይጣናዊ ተልዕኮ ተቀብሎ ወደ አማራ ክልል ያመራው የብልፅግናው አሽከር ባለ ቀይ ቦኔቱ ኮማንዶ ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ የፋኖ አባላት ጋር መስከረም 28/2017 ዓ.ም ለሁለት ሰዓታት ባደረገው ውጊያ ሃያ(20) የኮማንዶ አባላት ይቺን አለም እስከወዲያኛው ሲሰናበቱ ለቁጥር የሚስቸግሩት ደግሞ ቁስለኛ ሆነው ሲቃይ ላይ ናቸው።
በፋኖ ጌታው ሻረው ብርጌድ መሪነት የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ክንደ ብርቱው የተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ ከመጥተህ ብላ ከተማ ተነስቶ በተለያዩ አቅጣጫዎች በተለይ በተለምዶ ዋንሴ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ ላይ ትንኮሳ ለማድረግ በሞከረው የየአገዛዙ ወታደር ላይ በፈፀመው አስደማሚ የደፈጣ ውጊያ አብይ አህመድ የሚመካበት ባለ ቀይ ቦኔቱ የኮማንዶ ሳይቀር የብልፅግናውን ወንበር ለማስጠበቅ ውድ ህይወቱን ገብሯል።የፋኖን ምዕታታዊ ጥቃት መቋቋም የተሳነው የአገዛዙ መንጋ ቡድን ለንዴቱ ማብረጃ ይሆን ዘንድ በተለምዶ ዋንሴ አካባቢ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ የአንድን ፋኖ መኖሪያ ቤት በእሳት አቃጥሎ አማራዊ ጠላትነቱን በግልፅ አሳይቶ ተመልሷል።
"ድላችን በክንዳችን"
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል

ፋኖነት የጀግንነት መገለጫ ነው።

አማራነት ፋኖነት ይለምልም!!!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:08


🔥#የበረኸትና_ምንጃር_የዛሬ_ዉሎ‼️

📌 ሸዋ በረኸት ላይ በተደረ ውጊያ በጠላት በኩል ምክትል ሻለቃ መሪውን ጨምሮ 13 ሙት 9 ቁስለኛ አስተናግዷል።

📌 ሸዋ ምንጃር ላይ በተመሳሳይ ጠላት ከባድ ኪሳራ አስተናግዶ ወደጎሬዉ ገብቷል።ይህ ሁሉ ሲሆን በወገን በኩል አንድ አባል እጁ ላይ ከገጠመው አነስተኛ የመቁሰል አደጋ ዉጭ የደረሰ አደጋ የለም።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ🔥

©ያሬድ አላዩ ወልደዬስ


#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

21 Jan, 00:06


28/1/17 ዓ.ም

🔥#ሸዋ‼️

በሸዋ ምድር ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ መሽጎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ፀረ አማራ ቡድን በጀግናው የነበልባል ብርጌድ የፋኖ አባላት በአራት አቅጣጫ እየተገረፈ ይገኛል።

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የነበልባል ብርጌድ መስከረም 27/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአራት አቅጣጫ ማለትም በጨሌ መስመር፣አዳማና ድሬ ፣ሸንኮራ እና ቦሎ አካባቢ አሰፍስፎ የመጣን የብርሀኑ ጁላ ፍዝ ምንጋ ሠራዊት እየገረፉ በርካቶች ተገድለው ፣በርካቶች ቆስለው እድለኛ የሆኑት ደግሞ የያዙትን መሳሪያ በየጫካው እየጣሉ ፈርጥጠዋል።

ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እስከምሽቱ 2:30 ድረስ በቆየው የ12 ሰዓታት እልህ አስጨራሽ ውጊያ ጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የነበልባል ብርጌድ ፋኖዎች ዙ-23 እና ዲሽቃ እስካፍንጫው የታጠቀ የአብይ አህመድን ግሪሳ ቡድን እየገረፉ ታላቋን የባልጪ ከተማን ተቆጣጥረው ያደሩ ሲሆን ፀረ አማራው የአብይ አህመድ ቡድን በየቤተክርስቲያኑ ተበታትኖ ነፍሴ አውጪኝ እያለ የድኩላ ፀሎት ሲያደርስ አድሮ ለማንሳት ያልቻለውን አስከሬን በየጫካው እየጣለ ሔዶ በአካባቢው ማህበሰሰብ ወግና ባህል ስርዓተ ቀብራቸው በክብር ተፈፅሞላቸዋል።

ታላቅ አማራዊ ስነልቦና በተሞላበት ወኔው አማራን አጠፋለሁ ብሎ ተማምሎ የመጣን ወንበዴ ቡድን ከህዝባቸው ጋር በመሆን አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ እንደሆነና አሁንም በፀና ወታደራዊ አቋማቸው ተገደን የጀመርነውን የህልውና ትግል በቅርቡ ቋጭተን የአማራን ህዝብ ከተደቀነበት የሞት ድግስ እንደሚያላቅቁት በልበ ሙሉነት ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና የሸዋን ምድር በስህተት የረገጠው የአብይ አህመድ መንበር አስጠባቂ ቡድን በተስፋ ብርጌድ የፋኖ አባላት እንደ ጌሾ እየተወቀጠ ይገኛል።ከመስከረም 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት እለት ማለትም 28/01/2017 ዓም ድረስ በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚፈራገጠውን የአገዛዙ አሽከር በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ የፋኖ አባላት የበረታ ክንድ በተሬ፣በወሲል እና በዋኒሴ አካባቢዎች እየተገረፈ የአሞራ ቀለብ ሆኖ ይገኛል።

አምባገነኑና ፀረ አማራው የብልፅግና ቡድን በረኸት ወረዳ መጥተህ ብላ ከተማ ላይ ያሰራቸውን ንፁሀን ዜጎች ወደ ሌላ ቦታ ለማንቀሳቀስ ለበርካታ ጊዜ ሙከራ ቢያደርግም ከላይ ድሮን ከታች ዙ እና ዲሽቃ የማይበግራቸው የተስፋ ልጆች እስካሉ ድረስ አንድም የወረዳችንን ህዝብ ወደ ሌላ ቦታ ሊጭን እንደማይችል በአቋምም በአቅማቸውም አገዛዙን ልክ ማስገባት ችለዋል።

ድል ለተካደው የአማራ ህዝብ
መስከረም 28/2017 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል



#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪