አማራ ሚድያ

@amhara_3


የመላው አማራ ድምፅ!!ለአማራ ድሚድያ በውስጥ መረጃ ለመስጠት 👉 @belachew07
ዩቲብ:- https://m.youtube.com/results?sp=mAEA&search_query=%40Amhara_3

አማራ ሚድያ

28 Aug, 12:39


የኤርትራና የትህነግ ጉዳይ ግራ ላጋባችሁ!

በትህነግና ኤርትራ ጉዳይ ላይ አልፎ አልፎ የሚነገሩ ጉዳዮች አሉ። ብዙዎቹ በቁማሮች መክሸፍ የተጀመሩ፣ በቁማርነትም የቀጠሉ ናቸው። ግራ የገባችሁ ካላችሁ አንዳንዶቹን እንሆ!

1) የደቡብ አፍሪካው ስምምነት ለትህነግ ምቹ አልነበረም። ትጥቅ በወር ውስጥ እንዲፈታ የሚያዘውን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮች ነበሩት። ይሁንና ከደቡብ አፍሪካ ፈራሚዎች ውጭ ብርሃኑ ጁላና ታደሰ ወረደ ዋና ተዋናይ ሆነው የወጡበት የናይሮቢ ስብሰባ ሌላ የጓዳ እርቅ ይዞ መጣ። የደቡብ አፍሪካውን ስምምነት ወደ ጎን ትተው ትህነግን አትርፈው በቀጣይ ስለሚሰሩት በዋነኛነት ኤርትራንና አማራን ስለመምታት ትኩረት አደረጉ።

2) በናይሮቢው የጓዳ ስምምነት መሰረት የአማራን ልዩ ኃይል ቀጥሎም ፋኖን ትጥቅ በማስፈታት የአማራን ግዛቶች ለትህነግ አሳልፎ መስጠት ላይ ገቡበት። በዚህ ወቅት ዋና አማካሪዎቹ የትህነግ ጀኔራሎች ነበሩ። ቀጣይ ኤርትራ ነው ተባለ። በዚህ መሰረት አብይ ለሚኒስትሮቹ "ወጭ ቀንሱ ከህወሓት ጋር ከነበረው የባሰ ቀጠናዊ ጦርነት አለብን" ብሎ ትዕዛዝ እስከመስጠት ደርሷል። ቀስ እየተባለ አሰብን ስለመያዝ አጀንዳ ሆነ። አጫፋሪዎቹ ደግሞ የትህነግ ደጋፊዎች ነበሩ።

3) አብይ አህመድና ትህነግ ኤርትራን ስለማጥቃት አጀንዳ አድርገው የመከላከያ ጀኔራሎቹ ጋር  ቤተ መንግስት ውስጥ ክርክር ጭምር ተደርጎበታል። የትህነግ ጀኔራሎች ስለ ኤርትራ ግምገማ ሲያደርጉ በዋነኛነት "የኤርትራ ወጣት ተሰድዶ አልቋል። ኤርትራ ወጣት የለውም። እኛ ብዙ የሰው ኃይል አለን። ሻቢያን እናውቀዋለን። እንመታዋለን" ብለዋል። ያው በሰው ማዕበል መሆኑ ነው። አብይ አህመድም የትህነግን ታጣቂ ትጥቅ ያላስፈታው ለዚህ አላማ ጭምር ነው። "እናንተ በእግረኛ፣ እኔ በከባድ መሳሪያና ድሮን ተቀናጅተን" ተባብለው መክረዋል። ለኤርትራ  ቀናኢነት አላቸው የተባሉ የመከላከያ ጀኔራሎች በትህነግ ጀኔራሎች ተተክተው ጦርነቱን የሚመሩበት መንገድ ሁሉ ተወርቶበታል።

አብይ አሰብን እይዛለሁ ብሎ ከሁለት የአውሮፓ አገራት ቀጥተኛ ድጋፍ ማግኘቱን ተናግሯል። አሜሪካም ትህነግና አብይ ከተስማሙ ኢሳያስን ማስወገድን እንደምትፈልግ አስበዋል።  በዚህ መሃል ግን ችግሮች ተፈጠሩ። ፋኖን በሶስት ቀን ትጥቅ አስፈትቸ የአማራን ርስት  አሳልፌ እሰጣችኋለሁ ያለው አብይ ችግር ገጠመው። ጦርነቱ እንዳሰበው ሳይሄድ ቀረ።

4) ኤርትራን ስለመምታት ሲታሰብ ትህነግ ያሰበው "ኤርትራ ከተመታች ሌላው እዳው ገብስ ነው" የሚል ጭምር ነው። ለምሳሌ ኤርትራ ሳትመታ አማራ ጋር ብገጥም ኤርትራም ስለምታግዝ መጀመሪያ ከአብይ ጋር ሆኘ እመታታለሁ የሚል እሳቤ ነው። ከሶስተኛው የትህነግ ወረራ በፊት ወደ አዲስ አበባ ከመዝመታችን በፊት አስመራን እንምታ የሚሉ ነበሩ። አሰብን ይዘን ከበባውን እንስበር የሚል ክርክርም ነበር። ተሸንፈው ሲመለሱም "ኤርትራን ብንመታ ኖሮ" የሚሉት ሌላ ጊዜ አግኝተዋል።

አማራው የቆመው በኤርትራ ድጋፍ ስለሆነ ቀጥለን በይፋ ወደ አማራ እንዘምታለን የሚል የተሳሳተና የንቀት ግምገማቸውም ለውሳኔነት ውሏል። ከዚህ ባሻገር አሰብን ከያዝን በኋላም ቢሆን ምናደርገውን እናደርጋለን ብለው ከአብይ ጋርም ሌላ ቁማር ጀምረው ነበር። ኤርትራን ከአብይ ጋር ሆኖ መውጋት ግን በሙሉ ድጋፍ ያለፈ አይደለም። የአማራ ክልሉ ጦርነትና ግዛት አሳልፎ መስጠት ጉዳይ ቃል በተገባላቸው መሰረት ባለመሄዱ "አብይ የራሱን የቤት ስራ ሳይሰራ እኛን መጠቀሚያ ሊያደርግ ነው" የሚል  ስጋትም እንደነበር ተሰምቷል። ከዚህ ባሻገር የኤርትራ ተቃዋሚዎች ከኢሳያስ ጋር ያብራሉ፣ ከአዲሱ የኤርትራ ትውልድ ጋር እንቀያየማለን የሚሉ ጥቂት ሰዎች አልጠፉም።

5) ታዲያ ኢሳያስ ምኑ ሞኝ ነው? አብይ የትህነግን ግሪሳ አፈስበታለሁ ብሎ ሲያስብ ፣ ወደ አሰብና አስመራ ፊቱን ያዞራል የተባለውን የትህነግ ኃይል "ወደ አዲስ አበባም መዞር ይችላልኮ!" የሚል ሀሳብ ብቅ አለ። በአጭሩ ኢሳያስ የትህነግ ሰዎችን "ግሪሳውን" ወደ አዲስ አበባ አዙሩት አላቸው። የትህነግ ሰዎች አብይ በተናገረው ፍጥነት አልፈፀመም ያሉትን ሁሉ አዲስ አበባን ይዘንም ሆነ ሳንይዝ እንፈፅመዋለን የሚል አማራጭ ያዙ። አብይ ከኢሳያስ ጋር ከሚያብሩብኝ ብሎ የበለጠ እንዲሰራላቸውም ይፈልጉ ነበር። በዚህ ወቅት ትህነግ በመደበኛውም በጥቁር ገበያም ዋጋዋ ከፍ ያለ መሰላት።

6) ትህነግ ኤርትራ ጋር ግንኙነት ሲጀምር ቢያንስ በአማራ ጉዳይ ገለልተኛ እንዲሆን የሚል ነው። ከዛም አብይ ፈጥኖ አልፈፀመልንም የሚሉትን የግዛት ወረራ ፈፅመው መደራደሪያ ከፍ ማድረግ ነበር። በዱባዩ የኤርትራና የትህነግ ውይይት ቁርጡ ተነገራቸው። "እንዲህ አይነት አካሄድ አይጠቅምም" ተባሉ። "የፈለጋችሁት  ስልታዊ እንጅ ስትራቴጅካዊ ወዳጅነት አይደለም። የምር ሰላም ከፈለጋችሁ ከአማራ ጋር ተነጋገሩ" ተባሉ። ትህነግ ባያምንበትም ለይምሰል በሚዲያም ከሚዲያ አለፍ ካለም በምናምናቸው ሰዎች በኩል ከአማራ ጋር እየተነጋገር እንደሆነ እናሳያቸው አለ። ይህ በተነገራቸው ማግስት የትህነግ ሚዲያዎች ስለ አማራና ትግራይ ህዝብ ሰላምና ውይይት በተደጋጋሚ አወሩ።  በጦርነቱ ወቅት ከትህነግ ጎን የነበሩ ትህነግ የአማራ ተወካይ ያደረጋቸው ስለ  ሁለቱ ህዝብ ውይይት ፃፉ። ተናገሩ። ከዚህ ያለፈ ግን ብዙ አልተሄደበትም።

7) ኢሳያስ አብይ የትህነግን ግሪሳ ከሚያዘምትብኝ እኔ አዘምትበታለሁ ብሎ ከትህነግ ሰዎች ጋር ሲነጋገር ትህነግን ለሁለት ከፈለው። ኤርትራን እንውረር ያሉት እነ ፃድቃን ጎን በ1993 ከትህነግ የተባረሩት የድሮዎቹ አመራሮች ጭምር ተቀላቀሉ። የእነ ደብረፅዮን ትህነግ ለአብይ ሽምግልና ልኮ ወጥቶ ወርዶ ስልጣን ሲነሳው አማራ ላይ የታወጀው በፈለጉት መልኩ አልሄድ ሲል ኤርትራ ትሻለናለች አለ።

8/ኤርትራን የመረጠው ትህነግ ግን ሌላ ተስፋ ጨምሮ ነው። ባለፈው ኤርትራ ወጣት የላትም ብሎ ያቀረበ ቡድን አሁን ደግሞ "ትንሽ ከታገስን ኢሳያስ አርጅቷል። ይሞታል። ወጣቱ ጋር መግባባትም የበላይነት መውሰድም እንችላለን" ብሎ አስቦ ነው። ብዙ በተስፋ የሚያወሩት አለ።

9) አብይ አህመድ ኬንያ ላይ በብርሃኑ ጁላ በኩል፣ ሀላላ ኬላና አዲስ አበባ ራሱ በነገራቸው መሰረት የአማራ ክልል ጦርነትን ማስኬድ ሲያቅተው ደግሞ ትህነግ ሌላ አማራጮችን አስበው ነበር። የትህነግ ዩቱዩበሮች ፋኖን ደገፍን ያሉት መጨረሻ ላይ በትግሉ ነበርን ለማለት ጭምር ነው። ሌሎች ጉዳዮችም አሉ።



ቁማሩ ነገም ከነገ ወዲያም ይቀጥላል። አብይ አህመድ አማራውን መትቶ ቃል የገባላቸውን ቢፈፅም ወደ ኤርትራም አብረው መዞራቸው አይቀርም ነበር። ነገም  ትንሽ ክስተት አሰላለፉን ሁሉ ትቀይራለች።

ቁማሮቹ የተሳሳቱ ቁማሮች፣ የጓዳ ስምምነት ውጤቶች ናቸው። አንተ እዘምትበታለሁ ስትል አፈሙዙ በአፍታ ወደአንተ ይዞራል። ሌላ ትጀምራለህ! የቁማር አቁሪት ነው!

የጌታቸው ሽፈራው ፁሁፍ ነው

ባለኝ ግምትና መለስተኛ መረጃ ትክክለኛም ነው::

አማራ ሚድያ

28 Aug, 12:38


የጭካኔ ጥግ ተመልከቱ!

ይህንን እየፈፀመ ያለው "አገው" ሸንጎ ነው። የሰራዊቱን ሬንጀር ለብሶ ልጁ ላይ የጭካኔ ድርጊት የሚፈፅመው ወንበዴ ደግሞ የቀድሞው አዊ ዞን አስተዳዳሪ እና የአገው ሸንጎ የጀርባ አጥንት የሆነው የእንግዳው ዳኜው አጃቢ ነው።

የጭካኔ ተግባር እየተፈፀመበት ያለው ምስኪን ልጅ ደግሞ እቁብ በደረሰው በማግስቱ የታፈነ አብዲ ፈንታው የሚባል ሙስሊም አማራ የባጃጅ ሾፌር ነው።

ይህ ቪዲዮ በአጋጣሚ አንዱ የሸንጎ አባል በድንገት በወገን እጅ ወድቆ እንደ ማስረጃነት ተገኘ እንጅ፣ እነ እንግዳው ዳኘውና መዝገቡ ቦጋለ ያደረጃጁት ጭራቅ የወንበዴ ቡድን በህዝብ ላይ ከዚህም የከፋ ወንጀሎችንና ጭካኔዎችን እየፈፀመ ይገኛል።

እንግዲህ በዚህ የጭራቅ ስብስብ እርምጃ ወስዶ ፍትህን ማስፈንና ለህዝብ ሰላምን ማምጣት ለነገ የሚባል ተግባር አይደለም።

አማራ ሚድያ

12 Aug, 15:51


የአፈና አዜና

የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቬ ሃይማኖት ቆሞስ አባ ኪነ ጥበብ ገብረ ኢየሱስ ታፍነው ተወስደዋል።
@Amhara_3

አማራ ሚድያ

10 Aug, 11:49


የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ድብ ጠለምት ተከዜ ክ/ጦር ሁመራ ብርጌድ እና ወፍ አርግፍ ኩሊታ ብርጌድ በጥምረት በጠላት ላይ ድል ተቀዳጁ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አማራ ሚዲያ
ነሀሴ 04/13/2016ዓ.ም


የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለ ጦር ሁመራ ብርጌድ እና ወፍ አርግፍ ኩሊታ ብርጌድ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት ጠላትን ሲረፈረፉት ውለዋል።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ  ድብ ጠለምት ክ/ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ አላምረው በሰጠው አስተያየት ከትግራይ ማዶ ወደ ወልቃይት ጠገዴ በአዲጎሹ አካባቢም ሲሻግር የነበረውን የመከላከያ ልብስ የለበሰ የትግራይን ታጣቂ ሰባቱን መኪና ሙትና ቁስለኛ አድርጎ 10 ክላሽ 1 ስናይፐር በመማረክ አስደናቂ ጀብድ ተቀናጅቶ የአማራነት ክብሩን አስጠብቆ ድል በድል የታጨቀ ምሸትን ማሳለፍ ተችሏል።
✍️አማራ ሚድያ ( @Amhara_3 )

አማራ ሚድያ

09 Aug, 18:08


ከአማራ ፍኖ በጎጃም የተሰጠ  መግለጫ
—————————————————————
ነሐሴ 03/2016 ዓ/ም
—————————————————————
ለአንድ ዓመት ያክል በጽናት የተመከተው እና ፍርክስክሱ የወጣው የብልጽግና ሰራዊት የአማራን ሕዝብ የማጥፋት የዘወትር ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሎበታል::በአውደ ውጊያ ሲመታ እናቶችን፣ አዛውንቶችን እና ህፃናትን ጨምሮ በንፁሃን ላይ የበቀል ርምጃ የሚወስደው እና የከተማውን ሕዝብ እንደ ሰብአዊ ጋሻ በመጠቀም ኃላፊነት የማይሰማው መሆኑን በተግባር ያረጋገጠው ይህ ወራሪ ሰራዊት ሀገርን ቃብድ አስይዘው በፈረሙት ውል ያገኙትን ዶላር የተማመኑ ጌቶቹ የሰጡትን አዲስ ስምሪት ለመተግበር እየተንደፋደፈ ነው:: በተለይም ስርዓቱ በአሉባልታ ማሽኖቹ በሚረጨው መርዛማ ፕሮጋንዳ የፋኖ ሰራዊት እና አመራሩ የተከፋፈለ ነው፣እርስ በእርሱ እየተታኮሰ ነው የሚለውን የማደናገሪያ አጀንዳ ለወራሪው ሰራዊት በማሰራጨት የሰራዊቱን ሞራል ከፍ ለማድረግ እየሞከረ ይገኛል:: በአንድ በኩል የሰላም መሐላ እየደረደረ የሰላም ኃይል መስሎ ለመታዬት ጥረት ሲያደርግ በሌላ በኩል ደግሞ በብድር እና በስጦታ እንዲሁም ከአማራ ሕዝብ ጠላቶች በሚያገኘው የመሳሪያ እና የሙያ ድጋፍ በመታገዝ በመከላከያ ስም የሰበሰበውን ሰራዊት በገፍ ወደ ቀጠናችን በማስገባት ሕዝባችንን አንገት ሊያስደፋ ቆርጦ መነሳቱ ተረጋግጧል:: የፋኖው ሰራዊታችን ለተከታታይ ፩ ዓመት ባደረጋቸው ተደጋጋሚ ውጊያዎች የብልጽግናን ሰራዊት ለቁጥር በሚታክቱ አውደ ውጊያዎች አሳምሮ ያሸነፈ፤ ኮሎኔሎችን ጨምሮ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩትን የወራሪው ኃይል አመራር እና አባላት የማረከ፤ ከጠላት እጅ ባገኘው ተተኳሽ እና መሳሪያ ጠላትን በርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ  በተደጋጋሚ የማረከ በመሆኑ የአሸናፊነት ፀጋን በስራው የተላበሰ ግዙፍ ኃይል ነው:: በእርግጥ በፋኖ ስራዊታችን ወታደራዊ ቁመና፣ ሞራል እና ወኔ ብቻ ተኩራርተን የሕዝባችንን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ደጀንነት የምንዘነጋ አይደለንም:: በመሆኑም በአጭር ቀናት ውስጥ በምናደርገው በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመቻ ሕዝቡ ከወራሪው ሰራዊት የበቀል እርምጃ ራሱን እንዲጠብቅ እያሳሰብን የአማራ ሕዝብ ነጻነት እና ህልውና የሚያሳስበው ሁሉ ከጎናችን በመሰለፍ በየቀየው የገባውን የጠላት ኃይል በመዋጥ ወራሪውን ሰራዊት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመጥረግ የሚደረገውን ተጋድሎ በመቀላቀል በትውልድ ፊት የሚኮራበት ደማቅ ታሪክ እንዲጽፍ ጥሪ እናቀርባለን::

ለዚህ ዘመቻ ተፈጻሚነት ሲባልም ከነሐሴ 07/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከአምቡላንሶች በስተቀር ለሁሉም ተሽከርካሪዎች መንገዶች ዝግ መደረጋቸውን እናሳውቃለን::

👉 አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
       [ ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!]

@Amhara_3

አማራ ሚድያ

07 Aug, 20:58


ሸዋ ላይ ወንድም በወንድሙ ላይ አነሳስተዉ የሰማችሁትን ተፈጥሯል።
የምኒልክ ልጆች ወንድማማቾች ተነጋገሩ ታሪካዊ ስተት እንዳትሰሩ


@Amhara_3

አማራ ሚድያ

28 Jul, 17:28


ሰበር መረጃ
–––––––
ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም
————————————
ከመርዓዊ፣ ዳንግላ እና ዱርቤቴ ተሰባስቦ የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀጠናው የጀመረውን አደረጃጀቱን የማጠናከር ስራ ለማስተጓጎል ወደ ሰሜን አቸፈር ሊበን ከተማ ተንቀሳቅሶ የነበረው የጠላት ሰራዊት ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከሊበን ወደ ዱርቤቴ ሲመለስ አዘና ማርያም ልዩ ቦታው ክልቲ የተባለ አካባቢ በወገን ኃይል ተደቁሷል።

በ3ኛ አገው ምድር ጎጃም ክፍለ ጦር ስር የሚገኘው የአቸፈር ወንድዬ ብርጌድ ብቻ በተሳተፈበት እና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ ምሽት 12:30 በተካሄደው በዚህ የደፈጣ ውጊያ ከ75 -80 የሚሆን የጠላት ሰራዊት ሲደመሰስ ጠላት ቁስለኛውን በአራት ተሽከርካሪወች ጭኖ ወደ ዱር ቤቴ ፈርጥጧል።

በየዕለቱ መስዋዕትነት የሚከፈልበትን ተጋድሎ ለድል የሚያበቃ ስራዊት ተገንብቷል፤ ተጋድሎው ይቀጥላል!!!

© አስረስ ማረ ዳምጤ
@Amhara_3

አማራ ሚድያ

28 Jul, 17:17


የአማራ#ፋኖ በጎጃም በተድላ ጓሉ ዕርሰ መዲና በሆነችዉ
ደብረ ማርቆስ ዙሪያ ሀዲስ አለማየሁ #ክፋለ ጦር የቦቅላ
ዓባይ ብርጌድ በዛሬዉ ዕለት አዲስ ሰልጣኝ ፋኖወችን አስመርቋል።
ጎጄ የዘምየ አገር ጥላቱ በበዛ ቁጥር እንደ ብረት እየጠነከረነዉ እሚሄደዉ!!!
ድል ለአማራ ፋኖ!!
ፋኖየ የኔዋስ ጠበቃ💪💪💙💙

አማራ ሚድያ

15 Jul, 07:55


መረጃ ፓዊ መተከል
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በሆዳሙ ሚሊሻ እና አድማ ብተና አማካኝነት ፓዊ ከተማ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች አማራ በመሆናቸው ብቻ ድብደባ እና እስራት እየተፈፀመባቸው መሆኑን ነው የደረሰን መረጃ የሚጠቁመው።
ከቀናት በፊት የወርቁ አይተነው እርሻ ስራ ሃላፊ የነበረ እና አንድ መምህር በአድማ ብተና እና ሚሊሻ ቡድኖች ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ነው የታወቀው።

#በተለምዶ ስሙ መንደር 14 እና 24 እንዲህውም 26 በሚባሉ የአማራ አርሶ አደሮች መኖሪያ አካባቢዎች የብርሀኑ ጁላ ገዳይ ቡድን እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ አድማ ብተና በጋራ በመሆን በርካታ አማራዎችን በመደብደብ አካለ ጎደሎ መደረጋቸውን ነው ኗሪዎች የገለጹልን።

በተመሳሳይ ግልገል በለስ እና ቻግኒ አማራ በመሆናቸው ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው ሲሆን በርካቶች ወደ ማጎሪያ ቤቶች እንደሚወስዷቸው ነው ለማወቅ የተቻለው።


@Amhara_3

አማራ ሚድያ

15 Jul, 07:43


የባህርዳርን ጉዳይ ከእንግዲህ ይዘነዋል!

የከተማችን ነዋሪዎች አገዛዙ ባደራጀው የወንበዴ መንጋ የሚፈፀምበትን ወንጀል ልንቋጨው የግድ ነው።

እነዚህ በፎቶው የሚታዮት ዘራፊ ወንበዴ የዘረ ወንበዴ ልጆች - በአገዛዙ የኮማንድ ፖስት አመራሮች ስምሪት ተሰጥቷቸው በባህርዳር ከተማ ዘረፋና እገታ ሲፈፅሙ የነበሩ ናቸው። ከዛም ሰኔ የመጀመሪያ ሳምንት አካባቢ በፖሊሶችና ጉዳዮን ባላወቁ ወታደሮች ይያዛሉ፤ ሳይውሉ ሳያድሩ ተለቀዋል። ይህንን የወንበዴ ቡድን የሚመሩ እነማን እንደሆኑም በፎቶ ሳይቀር አውቀናል። ይህንን አንድ ብላችሁ መዝግቡልን።

እንቀጥል… አሁንም ሌላ በአገዛዙ ስምሪት የተሰጠው ነዋሪውን እያገተ ሚሊዮን ብሮችን ተቀብሎ ለአገዛዙ አመራሮች የሚያከፋፍል የዘራፊ ወንበዴ ቡድን ኔትወርክን ደርሰንበታል። መታወቂያቸውን ሳይቀር አግኝተነዋል። ይህንን ደግሞ ሁለት ብላችሁ መዝግቡልን።

የሁሉም አናት ምስራቅና ምዕራብ ሳይሆን እረፍት አናገኝም፤ ጉዳዮን ይዘነዋል።

ወንድሞቻችን እነ ኢንጅነር ማንችሎት እነ አማኑኤል (ደጉ በላይ ሻለቃ) ልታግዙን ተዘጋጁ። ሌላ መንግሥት የለም እኮ መንግሥት እናንተው ናችሁ፤ እንደ መንግሥት ደግሞ ህግ ማስፈፀም የግድ ይላል።

የከተማችን ነዋሪዎች አሁንም ተጨማሪ መረጃና ጥቆማ በማድረስ ታግዙናላችሁ።
@Amhara_3

አማራ ሚድያ

15 Jul, 07:42


ሰበር ዜና!

በወልድያ ከተማ በሚገኝ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በተፈፀመ ጥቃት ስድስት የፖሊስ አባላት ሲገደሉ አምስቱ ተማርከው መወሰዳቸው ተሰማ!

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነችው ወልድያ ከተማ 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ላይ አዳሩን በተፈፀመ ጥቃት በቁጥር ስድስት የፖሊስና የአድማ ብተና አባላት ሲገደሉ አምስቱ ደግሞ ተማርከው መወሰዳቸውን የአማራ ድምፅ ሚዲያ ጥቃቱን የፈፀሙ የፋኖ አባላትና አመራሮችን እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎችን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል።

ሙት እና ምርኮኛ ከሆኑት የአድማ ብተናና የፖሊስ አባላት በተጨማሪ ሰባት የጣቢያው አባላት ቆስለው ወደ ሕክምና የተወሰዱ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሦስቱ በጠና ታመው ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ነው የአይን እማኞች ለጣቢያችን የገለፁት።

ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ሐምሌ 07/2016 ዓ/ም ለዛሬ አጥቢያ ለሊት 7:00 ጀምሮ እስከ 9 ሰዓት ባለው ነው የተባለ ሲሆን ጥቃቱን የፈፀሙት የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብርጌድ ፋኖዎች መሆናቸውንም ለማረጋገጥ ተችሏል።

በከተማዋ ራስ አሊ ክ/ከተማ ስር የሚገኘው 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በተፈፀመው ጥቃት ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ ከሆኑ የአድማ ብተናና ፖሊስ አባላት በተጨማሪ አንድ የፖሊስ ጣቢያው ተሽከርካሪ መውደሙንም  የራስ አሊ ክ/ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በዚህ ጥቃት አራት ስታር ሽጉጥን ጨምሮ 25 የሚደርስ ክላሽንኮቭ መሣሪያና በርካታ ቁጥር ያለው ተተኳሽ የማረኩት የፋኖ አባላቱ፡ የማረኩትን መሣሪያ በማረኳቸው የፖሊስ አባላት አሸክመው ከተማዋን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል።

ከቆሰሉት ሰባት የፖሊስ አባላት መካከል ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር የተባሉት ሦስቱ የፖሊስ አባላት ክፉኛ በመጎዳታቸው የመትረፍ እድላቸው አነስተኛ ነው ሲሉ ሁኔታውን በቅርብ ርቀት ሁነው ሲከታተሉ የነበሩ የክ/ከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

"በፖሊስ ጣቢያው ላይ ጥቃቱ ሲፈፀም ዝም ብላችሁ ተመልክታችኋል፡ ለምን አባሎቻችንን አላገዛችሁም?" በሚል ዛሬ እረፋዱን ለእስር የተዳረጉ በርካታ የራስ አሊ ክ/ከተማ ነዋሪዎች መኖራቸውም ታውቋል።
የአማራ ድምፅ ሚዲያ
@Amhara_3

አማራ ሚድያ

11 Jul, 04:03


ነበልባሎቹ ኦፕሬሽን በደብረ ማርቆስ

ሐምሌ 02/2016 ዓ.ም ሌሊት 3:00 ላይ የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ በደብረ ማርቆስ ከተማ ኮሌጅ ሰፈር በአገዛዙ የጦር ካምፕ ላይ በአስገራሚ ኦፕሬሽን ከፍተኛ ጥቃት አድርሶበታል።

4 የፋሽስቱን ታጣቂዎች ከነመሳሪያቸው ነበልባሎቻችን ማርከው የወሰዱ ሲሆን በውል ያልታዎቁ የአገዛዙ ኃይሎችም ጉዳት መድረሱ ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም የ2 የካድሬዎች ቤት ላይ የድንች ጥቃትን የጨመረ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀሙ ታውቋል። የካድሬዎቹ ሁኔታ እስካሁን አልታወቀም።

በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ በደብረማርቆስ ከተማ
የጨነቀው ፋሽስታዊው አገዛዝ ሁሉም የከተማዋ ባጃጆች በዚህ ክረምት ሸራቸውን እንዲያነሱ ማዘዙ ተነግሯል 🤣🤣 ይህ ድርጊት የአገዛዙ ጭንቀት በውል የሚያስረዳ አስገራሚ ነገር ሆኗል።

@Amhara_3

አማራ ሚድያ

09 Jul, 11:47


ጎንደር ከተማ ላይ እየተሰራ ያለው አስነዋሪ ስራ

አገዛዙም ያደራጀው፣ ይሄን ግርግር ተጠቅሞ ሀብት ማካበት የፈለገው ሁሉም በፋኖ ስምና በራሱ መንገድ በከፍተኛ ዘረፋ፣ እገታ ፣ ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ ተበራክቷል።

እገታው ከህፃን እስከ አዛውንት ያካለለ ነው። ሀብት አላቸው፣ መክፈል ይችላሉ ተብለው የታመኑትን ያጠኑና ህፃናትን ወይም ሽማግሌዎችን አፍነው እንደታፋኙ ቤተሰብ የአቅም ደረጃ ገንዘብ አምጡ ይባላሉ። መክፈል የማይችል ተገድሎ ተጥሎ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ወረቀት ተፅፎ አለያም በስልክ በቴክስትና በቀጥታ ስልክ ተደውሎ ይሄን ያህል ማዕቀብ ተጥሎብሃል አስገባ ካላስገባህ እርምጃ ይጠብቅሃል ይባላል። አሁን ያለው ሀቅ ይህ ነው።

ለእኔ ጥቆማ በመጣልኝ መሠረት አባ ሳሙኤል ሪል ስቴት ከደንቢያ የመጣች እናት፣ ሸዋ ዳቦ አካባቢ አንድ ሽማግሌ አባት ታፍነው በገንዘብ ተለቀዋል። በርካታ ነው። አሁን ሰው ቢጨንቀው ወደ አዲስ አበባ እየተሰደደ ነው። አዘዞ ኤርፖርቱን ሂዶ ማየት ይቻላል።

አገዘዛዙ ምንጊዜም ጠላት ነው። እንዴት አማራ ነኝ፣ ጎንደሬነኝ አንዳንዱ ደግሞ ታጋይ ነኝ እያለ ህዝብን ይበድላል። ህዝብን በበደለበት ግብሩ ደግሞ የህዝብ ተቆርቋሪ ነኝ ይላል። አረ ነውር ነው። ትግሉ ህዝባዊ ሁኗል። ለትግሉም የሚገባውን ዋጋ እየከፈለ ነው። ከዚህ ውጭ እንዴት በግዴታ አምጣ ይባላል። በትግል ስም የምታጭበረብር ይሄ ጊዜ ሲያልፍ እዳው አይለቅህም። ዛሬ ላይታይህ ይችላል። ህዝብ ግን ስንዴና እንክርዳዱን መዝግቦ ያቆያል።  ስለዚህ ይሄን ግርግር ተጠቅመህ ሞራልህን አዝግጠክ ሀብት አሰበስባለው የምትል ስትሰበስብ የነበርክ ይቅርብህ ሳትበላው ትበላለህ ከመበላት ብትተርፍም በአደባባይ ህዝብ ያዋርድሃል። በዚህ አላቆምም መረጃን መሠረት አድርጌ ለህዝብ ይፋ አደርጋለሁ።

ድል ለፋኖ የፈራ ይመለስ

አማራ ሚድያ

31 May, 11:20


ላስታ አውራጃን ከመንግስት እየተረከቡት ነው፤
የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ የጄኔራል አሳምነው ፅጌ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የሆነው 50 አለቃ ወንድሙ ማሩ እና የክፍለ ጦሩ ስራ አስኪያጅ ፋኖ አለምነው መብራቱ የሲቪል አስተዳደር ስራን ለማሳለጥ በማሰብ ከዘመቻ መልስ ወደ ቢሮ አቅንተው አንዳንድ ስራዎችን ሲያከናውኑ የሚያሳይ ምስል ይፋ ሆኗል።
የአሳምነው ልጆች ትግላቸው ከልብ ነው። የአማራነት ስሜታቸው እና የአንድነት ፍላጎታቸውም ከማንም የበለጠ ነው። ሲታገሉ ተራራ ለተራራ ሳይሆን ኤርፓርት አፍንጫ ስር ጀምረው የመንገደኞች ጌት ላይ ቆመው ነው።
በምን ቃል እንደምገልፃቸው እቸገራለሁ። የአሳምነው ልጅ እያለ እንደ አንበሳ እያገሳ የጠላትን እሬሳ የሚረማመድ ጀግና ትውልድ ተፈጥሯል።

አሳምነው ብለው ስሙን ከመጥራት ባሻገር በተግባር አሳምነውነትን እየኖሩት ነው።
ኤርፓርቱን የካቲት ላይ እንደተቆጣጠሩት ድጋሜ ደግሞ ሰሞኑን ገብተው እንደዘየሩት ይታወቃል። ታዲያ የትኛው የፋኖ ሀይል ነው በተደጋጋሚ እንዲህ ያለ ስትራቴጅክ እና አለም አቀፍ ትኩረት የሚገዛ ቦታን በተደጋጋሚ የያዘው? የአሳምነው ልጆች ብቻ ናቸው ይህን ማሳካት የቻሉት።
ስለ ሀምሳ አለቃ ወንድሙ ማሩ እና ፋኖ አለምነው መብራቱ እንድሁም ኮማንዶ ፍቅሩ እና ፋኖ ታዘበው ሻምበል ወንድማዊ ፍቅር እና መከባበር ሳስብ ጭምር አሳምነውነት መሬት እንደነካ አረጋግጣለሁ።
ላስታ ላይ ጀግንነት ብቻ ሳይሆን ወንድምነት እና አሳምነውነት ነግሷል።
ለወንድም መሳሳት፣ ለጓድ መታመን፤ ከአንተ በፊት እኔ ማለት አሳምነውነት ነው። የአማራን አንድነት ለማጥበቅ መስራት አሳምነውነት ነው። መከበብን አውቆ ከበባን መበጣጠስ አሳምነውነት ነው። መሬት የነካ ስራ መስራት አሳምነውነት ነው።
አሳምነው ፅጌ ሺህ ሆኖ በላስታ ምድር ላይ በቅሏል። ለእዚህ ደግሞ ምስክር የሚሆኑን የክፍለ ጦሩ አመራሮች እና አባላት ናቸው።
አማራን ማሸነፍ አይቻልም

@Amhara_3

አማራ ሚድያ

31 May, 11:19


የድል ዜና

ፀረ አማራው የአብይ አህመድ ሰራዊት በሸዋ ምድር በረኸት፣ባልጪና ቀይት ላይ እንደ እባብ ተቀጠቀጠ።

የእምዬ ምኒሊክ አድባር ፣የነገስታቶች ቀዬ፣የጀግኖች መፍለቂያ ምድር ሸዋ ለአብይ አህመድ ስልጣን ጠባቂ ባለሟሎች ሲዘሉ ገደል ሲረግጡ ረመጥ ሆኖባቸዋል።

ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር በነበልባል ብርጌድ የተለያዩ ሻለቆች በተካሔደ ኩታ ገጠም የማጥቃት ኦፕሬሽን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መዲና ከሆነችው አረርቲ ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው የባልጪ ከተማ በአብይ አህመድ ሰራዊት አስከሬን ተጨንቃለች።

ሀምሳ አለቃ ፈቃዱ ጥላሁን ከፊት ሆኖ የሚመራው ተወርዋሪው ኮከብ የነበልባል ብርጌድ የአማራው ልጅ ፋኖ በነ ሽመልስ ባለአደራ ፣በነ አብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ቡድን ላይ በወሰደው ስትራቴጂካዊ የተቀናጀ የማጥቃት ኦፕሬሽን በመከላከያ ጭምብል አማራን ለማጥፋት የተነሳው የጠላት ሀይል የተሸኘው ተሸኝቶ የተረፈው ደግሞ ከባልጪ ከተማ ሻይ ቤትና መፀዳጃ ቤቶች ከተደበቀበት ተፈልጎ እጁን ለጀግኖች አስረክቧል።

በሌላ ዜና የፊደላት አባት የተስፋ ገብረስላሴ ምድር የሆነችው የበረኸት ወረዳ በጠላት ሀይል በብልፅግናው አሽከር አስከሬን ተጨናንቃለች።

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በከሰም ክፍለጦር በወንድማማቾቹ ተስፋ ገብረስላሴ ፣ሀይለማርያም ማሞ እና በአስማረ ዳኜ በተለያዩ ሻለቆች አማካኝነት በጠላት ሀይል ላይ በተወሰደ መብረቃዊ የተናበበ የወንድማማቾች የማጥቃት ኦፕሬሽን አማራን በአስር ቀን ውስጥ ለማጥፋት ከአምቦ እስከ ሰምቦ፣ከጅማ እስከ አዳማ ተሰባስቦ የመጣው የብርሀኑ ጁላ ጦር አስር ደቂቃ እንኳን መመከት ሳይችል የተወለደበትን ቀን እየረገመ ይችን አለም ሸዋ ምድር ላይ ተሰናብቷል።

ሺ ሆነው እንደ አንድ አንድ ሆነው እንደ ሺ ጠላትን ድል ማድረግ ከአባቶቻቸው የወረሱት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የከሰም ክፍለ ጦር አናብስቶች የበረኸት ወረዳ መጥተህ ብላ ከተማን አንቆ ሙጥኝ ያለውን የነብርሀኑ ጁላ ጦር ከበው በከፈቱት የማጥቃት ኦፕሬሽን በርካቶች ተሸኝተው በርካቶች ደግሞ ቆስለው በየጉራንጉሩ ከመደበቃቸው ባሻገር ጀግናው ፋኖ የበረኸት ወረዳን ፖሊስ ጣቢያን አመድ አድርጎት አድሯል ጦርነቱም ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት ሰዓት ድረስ እንደቀጠለ ነው።

በተያየዘ ዜና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ  የዕዙ ተወርዋሪ ውስን ሰራዊት በጠላት ሀይል ላይ ታላቅ ጀብዱን ተጎናፅፏል።

ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ደብረብርሀን ከተማ ቀይት አካባቢ ከሌሊቱ 10:30 ጀምሮ በጠላት ሀይል ላይ በተወሰደ የቆረጣና የደፈጣ ውጊያ የፋኖን ምት መቋቋም የተሳነው የአገዛዙ ቡድን እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ደብረብርሀን ከተማ ፈርጥጧል።

የአብይ አህመድ ሰራዊት መጠቀም ያለበትን ሞርተር ፣ዲሽቃና ዙ-23 ለረጅም ሰዓት ለመጠቀም ቢሞክርም እውነትን ይዘው የሚታገሉት የአማራ ልጆች ግን ድልን ከመጎናፀፍ አላገዳቸውም።

        ድል ለአማራ ፋኖ
    የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ክፍል
              ግንቦት 23/2016 ዓ.ም

@Amhara_3

አማራ ሚድያ

31 May, 08:38


የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፅህፈት ቤት ኃላፊ መኖሪያ ቤት በቦንብ መደብደቡን ተከትሎ ለሰዓታት የቆየ ውጊያ መካሄዱ ተሰማ!

የዞኑ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ መኖሪያ ቤት በአሁን ሰዓት በአድማ ብተና አባላት ተከቦ ማንም እንዳይገባና እንዳይወጣ እየተጠበቀ ሲሆን፡ ኃላፊው በጥቃቱ ሳይገደል እንዳልቀረ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

ትናንት ግንቦት 21/2016 ዓ/ም ምሽት አንድ ሰዓት ገደማ በወልድያ ከተማ ልዩ ስሙ ጎማጣ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘው የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ የአቶ ከድር ሙስጠፌ መኖሪያ ቤት በቦንብ መደብደቡን ተከትሎ በኃላፊው አጃቢዎችና በሌሎች የዞኑ ፖሊስ አባላት መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ማምሸቱን የአማራ ድምፅ ዜና አገልግሎት የወሎ ግንባር ዘጋቢዎች የአከባቢው ነዋሪዎችን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችለዋል።

ምሽት አንድ ሰዓት ገደማ የፋኖ አባላት ወደ ኃላፊው መኖሪያ ቤት በመዝለቅ የቦንብ ጥቃት ከፈፀሙ በኋላ የቦንብ ፍንዳታውን ተከትሎ ከኃላፊው መኖሪያ ቤት በቅርብ ርቀት የሚገኘው የጎማጣ ፖሊስ ጣቢያ አባላት ወደ ሰማይ እየተኮሱ ጣቢያውን ለቀው መሸሻቸው ነው የታወቀው።

በጨለማው ምክኒያት አንዱን ከአንዱ መለየት ስላልተቻለ የኃላፊው አጃቢዎች ወደ ሰማይ እየተኮሱ የሚሸሹ ፖሊሶች ፋኖ ይሆናሉ በሚል ወደ ፖሊሶቹ ሲተኩሱ፡ በተመሣሣይ የፖሊስ አባላቱም ፋኖ ተኮሰብን በሚል አፀፋዊ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በዚህ መካከል ሰባት የፖሊስ አባላት ክፉኛ መቁሰላቸውን የወሎ ግንባር ዘጋቢዎቻችን ለማረጋገጥ ችለዋል።

የአማራ ድምፅ ሚድያ ያነጋገራቸው በዞኑ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃቱን የፈፀሙት የፋኖ አባላቱ፡ "እኛ ሁለት ቦንብ በተከታታይ በመወርወር የኃላፊውን መኖሪያ ቤት ከደበደብን በኋላ ጥግ ይዘን በመቀመጥ በኃላፊው አጃቢዎች እና በፖሊስ አባላቱ መካከል ሲደረግ የነበረንው የተኩስ ልውውውጥ እየተመለከትን ስንስቅ ነበር" ሲሉ ስለ ሁኔታው ተናግረዋል።

በተጨማሪም የፋኖ አባላቱ፡ በአቶ ከድር መኖሪያ ቤት ጥቃቱን ከፈፀምን በኋላ በዚህ የተደናገጡት የጎማጣ ፖሊስ ጣቢያ አባላት ጣቢያውን ለቀው በመሸሻቸው እኛ ወደ ፖሊስ ጣቢያው በመግባት በቁጥር ሰባት ክላሽንኮቭ መሣሪያና ስታር ሽጉጥ እንዲሁም በርካታ ሳጥን ተተኳሽ ጥይት ይዘን መውጣት ችለናል ብለዋል።

የፋኖ አባላቱ አክለውም፡ አከታትለን በወረወርነው ቦንብ የዞኑ ብልፅግና ኃላፊ ተመቶ ወድቋል ያሉ ሲሆን በመኖሪያ ቤቱ ላይም ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ምሽቱን ጥቃት የተፈፀመበት የዞኑ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ሙስጠፌ ህይወቱ አልፏል ወይንስ አላለፈም የሚለውን እስካሁን ማረጋገጥ ያልተቻለ ሲሆን፡ ጣቢያችን ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች አቶ ከድር በጥቃቱ ቆስሎ ቢሆን ለህክምና ወደ ሆስፒታል ይወሰድ ነበር ብለው፡ ነገር ግን እስከ አሁን ወደ ሕክምና አለመወሰዱን በመግለፅ ምናልባትም ሳይሞት አይቀርም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል።

ዛሬ ከንጋት ጀምሮ የኃላፊው መኖሪያ ቤት ዙሪያ ገባውን ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው በአድማ ብተናና መከላከያ ሰራዊት አባላት እየተጠበቀ ሲሆን፡ ከተፈቀደለት የዞኑ አመራር ውጭ ማንም ወደ ቤት መግባትና መውጣት እንዳይችል ታግዷል ሲሉ ቃላቸውን  የሰጡ የጎማጣ አከባቢ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

አቶ ከድር ሙስጠፌ ትውልድና እድገቱ ራያ ቆቦ ዋጃ አከባቢ ሲሆን የተፈፀመበትን ጥቃት የሰሙ ቤተሰቦቹና ሌሎች ዘመድ ወዳጆቹ ከዋጃ ተነስተው የመጡ ቢሆንም ነገር ግን ወደ ከድር ቤት እንዳይገቡና ከድርንም እንዳያገኙ በፀጥታ ኃሎች መታገዳቸውም ታውቋል።

ከዋጃ ተነስተው ወደ ወልድያ ከመጡ የኃላፊው ቤተሰቦች መካከል አንዳንዶች ነጠላቸውን ዘቅዝቀው እያለቀሱ ነበር ያሉት የአይን እማኞቻችን፡ ነገር ግን የፀጥታ ኃይሎቹ ወዲያውኑ ዝም እንዳስባሉዋቸው ገልፀዋል።

ከኃላፊው ጋር እድርተኛ የሆኑ የአከባቢው ነዋሪዎች ሁኔታውን ለማጣራትና ሞቶም ከሆነ እድርተኛው እንዲሰባሰብ እንናገር ለማለት ወደ መኖሪያ ቤቱ ያቀኑ ቢሆንም የፀጥታ አመራሮች "ተረጋጉ፡መሆን ያለበትን እኛ እናውቃለን" የሚል ምላሽ ከመስጠት ውጪ ዝርዝር ጉዳይ ሳይነግሯቸው በአስቸኳይ መኖሪያ ቤቱን ለቀው እንዲወጡ አድርገዋቸዋል ነው የተባለው።

የዞኑ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃቱን በተፈፀመበት ተመሣሣይ ሰዓት በከተማዋ ፒያሳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ አንድ የትራፊክ ፖሊስ አባል ግድያ እንደተፈፀመበት ታውቋል።

ከአማራ ድምፅ ሚድያ ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት በወልድያ ዙሪያ የሚንቀሳቀሰው የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብርጌድ ፋኖ አመራሮች፡ በዞኑ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ በሆነው በአቶ ከድር ሙስጠፌ ላይ ጥቃቱን የፈፀምነው እኛ ነን ያሉ ሲሆን: ነገር ግን ስለ ትራፊክ ፖሊስ አባሉ ግድያ የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል።

ምን አልባት በሰዓቱ የነበረውን ግርግር ተጠቅሞ የግል ቂመኛ ይሆናል በትራፊክ ፖሊስ አባሉ ላይ ግድያ የፈፀመው ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል።

በወልድያ ከተማ ስር ከሚገኙ ስድስት በላይ ክ/ከተሞች አንዱ የሆነው ጎማጣ ተብሎ የሚጠራው አከባቢ "ጎልማሶች ማሰልጠኛ ጣቢያ"የሚለው በምህፃረ ቃት ሲጠራ መሆኑንም ጣቢያችን ለማወቅ ችሏል።
@Amhara_3

አማራ ሚድያ

31 May, 08:36


ሰበር መረጃ ❗️

አገዛዙ የሚተማመንበት የሰራዊቱ ኮማንዶ አዛዥ በጀግኖች ተሞሸረ !

ሰሞኑን ሰሜን ሸዋ ላይ በተደረገው ኦፕሬሽን አንድ ከፍተኛ የአገዛዙ ኮማንዶ አዛዥ ከእነ ግብረአበሮቹ መደምሰሱን አረጋግጠናል።

በዚህ ኦፕሬሽን የተደመሰሰው ተራ ወታደር ቁጥር ስፍር እንደሌለው ገልፀው ሰራዊቱ እንዲሁ በጅምላ ተቆፍሮ ሲቀበር ተመልክተናል ሲሉ የጃዊሳ ሚዲያ አይን እማኞች ገልፀዋል።

ግባ ግን መውጣት የለም !


@Amhara_3

አማራ ሚድያ

30 May, 14:31


ሰበር ዜና!

ነበልባሉን የአማራ ፋኖ ከበባ አድርጎ ጥቃት ለመፈፀም ያቀደው የአብይ አህመድ ወታደር እንደእባብ ተቀጥቅጦ ተመልሰ።

      የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ

ከደብረብርሀን 13 ኪ.ሜ ርቀት ላይበእምዬ ምኒልክ ቀዬ በአንኮበር መስመር ልዩ ቦታው ዲቡት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ጀግኖች ላይ የህልም እንጀራ ለመብላት ከአንኮበር እና ከደብረብርሀን ከተማ ተሰባስቦ ያለውን ሁሉ ሜካናይዝድ የጦር መሳሪያ በመያዝ ጥቃት ለመፈፀም እሳቱን የሸዋ ምድር የረገጠው የብርሀኑ ጁላ ፀረ አማራ ፍዝ መንጋ ቡድን በጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በተለያዩ የብርጌድ ሻለቆች በደረሰበት መብረቃዊ የመልሶ ማጥቃት ምት አስከሬኑን ሳይሰበስብ እግሬን በሰበረኝ እያለ ወደ መጣበት ፈርጥጧል።

ግንቦት 21/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:00 ጀምሮ ጥቃት እንዲፈፀምበት በሸዋ ባንዳዎች ሴራ የተሸረበት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ለልዩ ኦፕሬሽን የተዘጋጁ የተለያየ የብርጌድ ሻለቆች በየአቅጣጫው ዲሽቃና ዙ-23 ተሸክሞ በሁለት አቅጣጫ የመጣውን የአብይ አህመድ አሽከር ባደረጉት አስደማሚ እና ተወርዋሪ የማጥቃት ኦፕሬሽን ፀረ አማራው የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ የጠላት ሀይል ጥቁር አስፓልቱን ተከትሎ ወደ ደብረብርሃን ከተማ ፈርጥጦ የተመለሰ ሲሆን ሀቅን ከህዝባቸው፣ ጀግንነትን ከአባታቸው የወረሱት የአማራ ፋኖ የሸዋ አናብስቶችም ታላቅ ጀብዱ በመጎናፀፍ የጠላትን ሀይል እግር በእግር እየተከተሉ ወደ ደብረብርሃን እየገሰገሱ  ይገኛሉ።
ድል ለአማራ ፋኖ
    @Amhara_3

1,655

subscribers

156

photos

6

videos