🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

@learn_arebic


ሰላም ሰላም ጓደኞቼ እንዴት ናችሁልኝ ይህ ቻናል የተከፈተበት ዋነኛ አላማ አረበኛን አቀላጥፈው መናገር ለሚፈልጉ የሀገራችን ልጆች አረበኛን ቀለል ባለ መንገድ ለማስተማር ታስቦ ነው!
ቻናሉን ጆይን ብላችሁ በመቀላቀል ቤተሰብ ሁኑ!
ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር በማድረግ መረጃውን ያጋሩ!

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

11 Apr, 21:08


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 20 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

30 Oct, 06:50


📚📚📚

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

12 Oct, 12:55


የግእዝ ግሶችን በአስሩ ተውላጠ ስሞች ስንዘረዝር በግሱ መጨረሻ (መድረሻ) ላይ የሚጨመሩ ባዕድ ፊደላት ወይም ቀለማት ።

1. አነ (እኔ) የግሱን መድረሻ ፊደል ወደ #ሳድስ ከቀየርን በኋላ """ኩ"" ፊደል መጨመር

2. ንሕነ (እኛ) የግሱን መድረሻ ቀለም ወደ ሳድስ ከቀየርን በኋላ ""ነ""" ፊደልን መጨመር

3. አንተ (አንተ) የግሱን መድረሻ ፊደል ወደ ሳድስ ከቀየርን በኋላ ""ከ"" ፊደል መጨመር

4. አንቲ (አንቺ) የግሱን መድረሻ ፊደል ወደ ሳድስ ከቀየርን በኋላ "" ኪ"" ፊደልን መጨመር

5. አንትሙ (እናንተ) የግሱን መድረሻ ወደ ሳድስ ከቀየርን በኋላ ""ክሙ"" ፊደልን መጨመር

6. አንትን (እናንተ) የግሱን መድረሻ ወደ ሳድስ ከቀየርን በኋላ ""ክን"" ፊደልን መጨመር

7. ውእቱ (እርሱ) ግሱ ላይ የሚጨመር የሚቀነስ የለውም።

8. ይእቲ (እርሷ) ግሱ ላይ በቀጥታ ""ት"" ፊደልን መጨመር

9. ውእቶሙ (እነርሱ) የግሱን መድረሻ ፊደል ወደ ""ካዕብ"" መቀየር

10. ውእቶን (እነርሱ) የግሱን መድረሻ ፊደል ወደ ""ራብዕ"" መቀየር

1. ግእዝ 2. ካዕብ 3. ሣልስ 4. ራብዕ 5.ኃምስ 6. ሳድስ 7. ሳብዕ ምንድናቸው????

ማስታወሻ : የሁሉም ፊደላት #መጀመሪያ ""ግእዝ "" ይባላል፤ ሁለተኛ ፊደል "" ካዕብ"" የሦስተኛ ፊደል """ ሣልስ"" አራተኛ ፊደል "" ራብዕ"" አምስተኛ ፊደል "" ኃምስ"" ስድስተኛ ፊደል "" ሳድስ"" ሰባተኛ ፊደል "" ሳብዕ"" ይባላሉ።

ለምሳሌ:- ቀተለ ===== ገደለ የሚለውን እንመልከት

1. አነ (እኔ)======== ቀተልኩ (ገደልኩ)

2. ንሕነ (እኛ) ======= ቀተልነ (ገደልን)

3. አንተ ==========ቀተልከ (ገደልክ)

4. አንቲ (አንቺ)========ቀተልኪ (ገደልሽ)

5. አንትሙ (እናንተ)=====ቀተልክሙ(ገደላችሁ)

6. አንትን (እናንተ)=======ቀለተልክን (ገደላችሁ)

7. ውእቱ (እርሱ) ========ቀተለ (ገደለ)

8. ይእቲ (እርሷ) =========ቀተለት (ገደለች)

9. ውእቶሙ (እነርሱ) =======ቀተሉ (ገደሉ)

10. ውእቶን (እነርሱ) ======= ቀተላ (ገደሉ)

https://t.me/Learn_Arebic
https://t.me/Learn_Arebic
https://t.me/Learn_Arebic

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

22 Jun, 05:14


📚አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ📚 ውድ ጓደኞቼ እንዴት ናችሁልኝ ሁላችሁም በያላችሁበት ሰላማችሁ እንደ ባህር አሸዋ ብዝት ብዝትዝት ይበል እንደሚታወቀው ላልወሰነ ጊዜ ትምህርታችን ተቋርጦ ነበር ለዛም ከልቤ ይቅርታ እጠይቃለሁ ትንሽ ችግር ገጥሞኝ ስለነበር ነው በጣም ይቅርታ ከዚህ ቡሀላ ትምህርታችንን እንደተለመደው በ አግባቡ እንቀጥላለን 📚አረብኛን እየተዝናኑ ይማሩ📚! ፡፡
#Join_Our_Telegram_Channel
🔗 @Learn_Arebic 🔗

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

13 Feb, 03:16


አረብኛ ቋንቋ ከፊደላት አጠቃቀም አንጻር እጅግ በጣም ምጥን ነው፥ በውስጡ ምንም አይነት ትርፍ ሆሄያት የሉትም። የአንዲት ፊደል ሚና በሎሎች ቋንቋዎች ውስጥ ከአንድ ቃል በላይ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፥ (يُحَارِبُونَ) የሚለው ባለ ሰባት ፊደል ቃል ወደ አማርኛ ሲመለስ “ሁለቱም እርስ በእርስ እየተገዳደሉ ነበር” በሚል ፍቺ ይተረጎማል። በሰባት ፊደላት የገነባነው አረብኛ ቃል በሶስት እጥፍ አድጎ ወደ ሀያ አንድ ፊደላት በሚጠቀም አማርኛ አረፍተነገር ይቀየራል። አረብኛ ቋንቋ አንድን መልእክት ሲያስተላልፍ ማእከላዊ ሀሳቡ ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ሌሎችን ትርፍ ቃላት ከላዩ ላይ ይሰርሳል። ቃሉንም በማእከላዊ ሀሳቡ ዙርያ ጥቂት የቅርጽ ለውጥ ብቻ እንዲያደርግ በመፍቀድ የተፈለገውን ሀሳብ ማንጸባረቅ ያስችላል። ከላይ በጠቀስነው ምሳሌ ላይ ማእከላዊ ሀሳቡ መገዳደል የሚለው ስለሆነ ሌሎቹን ቃላት (“ሁለቱም”፥”እርስ”፥”በእርስ”፥”ነበር”) በመሰረዝና መነሻ ቃሉ ላይ መጠነኛ የቅርጽ ለውጥ በማድረግ ብቻ መልእክቱን ማስተላለፍ ችሏል። ይህ ምጥንነት ዝባዝንኬ ገለጻዎችን ለማይጠቀሙ መለኮታዊ መጽሀፍት እጅግ በጣም አስፈላጊ ባህሪ ሲሆን በመልእክቶቹ ላይ በማተኮር ብቻ በርካታ ቁምነገሮችን በውስን ገጾች ላይ ማስፈር እንዲችሉ ይፈቅድላቸዋል። @Learn_Arebic

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

07 Feb, 21:45


የአረብኛ መዝገበ-ቃላት ::
- ከሰው ስናገኝ
ታዲያስ
مرحبًا
እንደምን አደሩ
صباح الخير
እንደምን ዋሉ
طاب مسائك
እንደምን አመሹ
مساء الخير
ደህና እደሩ
تصبح على خير
ስምዎ ማን ይባላል?
ما اسمك؟
ስሜ________________ይባላል
اسمي هو ___
ይቅርታ፣ አልሰማሁህም
عذرًا ، لم أسمعك
የት ነው የምትኖረው?
أين تعيش؟
ከየት ነው የመጡት?
من أي بلد أنت؟
እንዴት ነዎት?
كيف حالك؟
ደህና ነኝ፣ አመሰግናለሁ
بخير، شكرًا لك.
እርስዎስ?
وأنت؟
ስላገኘሁዎት ደስ ብሎኛል
سررت بلقائك
ስላገኘሁዎት ደስ ብሎኛል
سررت برؤيتك
መካም ቀን ይሁንልዎ
أتمنى لك نهارًا سعيدًا
በኋላ እንገናኛለን
أراك لاحقًا
ነገ እንገናኛለን
أراك غدًا
ደህና ይሁኑ
وداعًا @Learn_Arebic

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

30 Jan, 06:49


بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

አረብኛን በቀላሉ ክፍል 4

🌿ሰዋሰው(grammar)🌿

➡️በክፍል ሁለት ትምህርታችን ንግግር ከሶስት ነገሮች ማለትም ግስ፣ስምና ሀርፍ እንደሚገነባ አይተን ነበር። በዚህ ክፍል ስለ ግስ እንመለከታለን።

▶️ግስ/ፊዕል ማለት በኢንግለዘኛው verb የምንለው የንግግር ክፍል ሲሆን ተግባርን፣ ክስተትን ሁኔታንና የመሳሰሉትን ለመግለፅ የምንጠቀመው ቃል ነው።

▶️አንድ ተግባር የሚተገበርበት ጊዜ አሁናዊ፣ ያለፈ ወይም ወደፊት ነው ሊሆን የሚችለው። ከዚህም በመነሳት በአረብኛ ቋንቋ ውስጥ ተግባሩ የተከናወነበትን ግዜ በመመልከት ፊዕልን ሶስት ቦታ እንከፍለዋለን። እነሱም:
👉ማዲ(ماضي)፣
👉ሙዳሪዕ(مضارع)ና
👉 አምር(أمر) ይባላሉ።



ሀላፊ ግስ
(فعل الماضي)

👌 "ፊዕሉል ማዲ" ያለፈን ግስ የሚያመለክት የግስ ክፍል ነው። ይህን ግስ ከሌሎች ግሶች ለመለየት ትርጉሙ ወይም ድምፁ ላይ በመወሰን መለየት እንችላለን።

👉 ትርጉሙን በማየት አሁን ካለንበት ግዜ ያለፈ እንደሆነ የሚያመለክት መልእክት ካለው ግሱ ሀላፊ ግስ ወይም ፊዕሉልማዲ ነው ማለት ነው።

👉 ድምፁን በመመልከት የግሱ መጨረሻ ፈትሓ ከሆነና ግሱ የፊዕል ሙዳሪዕ ወይም አምር ምልክቶቸ ከሌሉበት ማዲ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

➡️ ምሳሌ:
አከለ(أكل): በላ
ሸሪበ(شرب): ጠጣ
ገዲበ(غضب): ተቆጣ

*⃣ ከዚህ ህግ ውጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሀላፊ ግሶች ሁሌም እንደተጠበቁ ናቸው። ጠቅላላ(general) የሆነውን ህግ በደንብ ከተረዳን ቡሃላ የተቀሩትን(exceptions) ማንሳት ይቻላል።

📒📒📒📒📒📒📒📒📒📒 @Learn_Arebic

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

27 Jan, 08:25


ሰላም ሰላም online ያላችሁ ውድ ተማሪዎቻችን ጥያቄ እና መልስ ውድድር ስላለ ግሩፓችንን ተቀላቅላችሁ እንድትሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇@Learnwithour

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

27 Jan, 05:46


🇸🇦አረብኛን🇸🇦 በአጭር ግዜ ውስጥ አቀላጥፎ መናገር የሚፈልግ ብቻ ጆይ ይበል! 👉 🇸🇦 @Learn_Arebic 🇸🇦

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

27 Jan, 05:38


ሰላም ሰላም online ያላችሁ ውድ ተማሪዎቻችን ጥያቄ እና መልስ ውድድር ስላለ ግሩፓችንን ተቀላቅላችሁ እንድትሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇@Learnwithour

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 03:11


online ያላችሁ ግሩቻችንን ተቀላቀሉ @Learnwithour

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 02:56


Channel photo updated

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 02:54


ሰላም ሰላም ጓደኞቼ እንዴት ናችሁልኝ እንግዲህ እስካሁን ከላይ በለቀቅንላችሁ መሰረት ጥያቄ እና መልስ ውድድር ስለሚኖረን በቅድሚያ ያልገባችሁን በዚህ ሊንክ 👉 @islam_bot በኩል ያጋሩን ሀሳብ አስተያየትም ካላችሁ አቅርቡ እንቀበላለን መልካም የትምህርት ጊዜ

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 02:54


بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

አረበኛን በቀላሉ ክፍል 1
🌿የአረብኛ ቃላቶች🌿

قال
👉 ሲነበብ: ቃለ

👉የቃሉ ትርጉም: አለ።

يقول

👉 ሲነበብ: የቁሉ

👉 የቃሉ ትርጉሙ: ይላል።


‘አኡዙቢላሂ ሚነሸይጣኒረጂም’ የሚለው አረፍተ ነገር ውስጥ ያሉ ቃላቶችን እንመልከት።

👈 أعوذ

👋 አንድ ላይ ሲነበብ: አዑዙ
👋 ትርጉሙ: እኔ እጠበቃለሁ

👈بالله

👋 ሲነበብ: ቢላሂ
👋 ትርጉሙ: በአላህ

👈من

👋 ሲነበብ: ሚነ
👋 ትርጉሙ: ከ

👈شيطان

👋 ሲነበብ: ሸይጣን
👋 ትርጉሙ: ሰይጣን

👈رجيم

👋 ሲነበብ: ረጂም
👋 ትርጉሙ: እርጉም

‘ቢስሚላሂረሕማኒረሂም’ የሚለው አረፍተ ነገር ውስጥ ያሉ ቃላቶችን እንመለከታለን።

👈 رحمان

👋 አንድ ላይ ሲነበብ: ረሕማን
👋 ትርጉሙ: አጅግ በጣም አዛኝ እዝነቱ ለሁሉም የሆነ

👈رحيم

👋 አንድ ላይ ሲነበብ: ረሒም
👋 ትርጉሙ: አጅግ በጣም አዛኝ እዝነቱ ለአማኞች ብቻ የሆነ

* ሁለቱም የአላህ ባህሪያቶች ሲሆኑ በምድር ላይ ለሁሉም ያዝናል ከሞት ቡሃላ ለአማኞች ብቻ ሰፊ እዝነቱን ያከናንባቸዋል።

➡️ ‘ማሊኪ የውሚዲን’ የሚለው አረፍተ ነገር ውስጥ ያሉ ቃላቶችን እንመለከታለን።

مالك

👋 ሲነበብ: ማሊኩን

👉 ትርጉሙም: ባለቤት


▶️ ይህን ቃል አረፍተ ነገር ውስጥ አስገብተን አንመልከት:

1⃣ أنا مالك هذ الكتاب
➡️ሲነበብ:አነ ማሊኩ ሃዘልኪታብ

ትርጉሙ: እኔ የዚህ መጻፍ ባለቤት ነኝ።

*⃣ አንድ አንድ ከዚህ ቃል ጋር የሚመሳሰሉ ቃላቶች አሉ:

👈 ملك

👋 ሲነበብ: መሊኩን

👉 ትርጉሙም: ንጉስ

▶️ ይህን ቃል አረፍተ ነገር ውስጥ አስገብተን አንመልከት:

1⃣ هو ملك
➡️ሲነበብ:ሁወ መሊኩን

ትርጉሙ: እሱ ንጉስ ነው

*⃣ ይህንን ቃል ሁለተኛውን ድምጽ ብቻ ብንቀይር ሌላ ትርጉም እናገኛለን:

👈ملك

👋 ሲነበብ: መለኩን

👉 ትርጉሙም: መልኣክ(አንድ መላኢካ)

▶️ ይህን ቃል አረፍተ ነገር ውስጥ አስገብተን አንመልከት:

1⃣ الجبريل ملك
➡️ሲነበብ:አልጂብሪሉ መለኩን

ትርጉሙ: ጅብሪል መልኣክ ነው

*⃣ ይህንን ቃል ሶስተኛውን ድምጽ ብቻ ብንቀይር ሌላ ትርጉም እናገኛለን:

👈ملك

👋 አንድ ላይ ሲነበብ: መለከ

👉 ትርጉሙም:የራሱ አደረገ

▶️ ይህን ቃል አረፍተ ነገር ውስጥ አስገብተን አንመልከት:

1⃣ ملك زيد السيارة
➡️ሲነበብ: መለከ ዘይዱኒ ሰያረህ

ትርጉሙ: ዘይድ መኪናውን የራሱ አደረገ

➡️ ማጠቃለያ: በዚህ ትምህርታችን አራት ተቀራራቢና የተለያዩ ቃላቶችን ተመልክተናል:
1⃣ማሊኩን
2⃣መሊኩን
3⃣መለከ
4⃣መለኩን

يوم

👋 አንድ ላይ ሲነበብ:የውሙን

👉 ትርጉሙም: ቀን


▶️ ይህን ቃል አረፍተ ነገር ውስጥ አስገብተን አንመልከት:

1⃣ والسلام علي يوم ولدت

➡️ሲነበብ: ወሰላሙ አለየ የውመ ውሊድቱ

ትርጉሙ: በተወለድኩም ቀን ሰላም በኔ ላይ ነው

*⃣ የዚህ ቃል ብዙው:
أيام

👋 አንድ ላይ ሲነበብ: አያሙን

👉 ትርጉሙም: ቀናቶች


▶️ ይህን ቃል አረፍተ ነገር ውስጥ አስገብተን አንመልከት:

1⃣ أيامك لن تعود إليك

➡️ሲነበብ:አያሙከ ለን ተዑደ ኢለይከ

ትርጉሙ: ቀናቶችህ አይመለሱልህም።

1⃣ ‘ኢያከ ነዕቡዱ ወኢያከ ነስተዒን ኢህዲነሲራጠል ሙስተቂም’ የሚሉ አረፍተ ነገሮች ውስጥ ያሉ ቃላቶችን እንመለከታለን።

إياك

ይህ ቃልአንድ ላይ ሲነበብ: ኢያከ

👉 ትርጉሙም: አንተን


▶️ ይህን ቃል አረፍተ ነገር ውስጥ አስገብተን አንመልከት:

1⃣ أريد إياك
➡️ሲነበብ:ኡሪዱ ኢያከ

ትርጉሙ: አንተን ነው የምፈልገው።

👌አስተውል:

1—‘ ኢያከ’ የሁለት የተለያዩ pronoun ስብስብ ነው። የመጀመሪያው ‘ኢያ’ ሁለተኛው ‘ከ’።
‘ኢያ’ ድርጊት የሚከናወንበትን ሌሎች pronouns ይዞ ነው የሚመጣው:
👉ኢያከ(አንተን)፣ኢያኪ(አንቺን)፣
ኢያኩም(እናንተን)፣ኢያኩማ(እናንተ ሁለታችሁን:ለሁለቱም ፆታ) .... etc

2— ባሳለፍነው አረፍተ ነገር ውስጥ ኢያከ የሚለውን ብናስቀድም(ኢያከ ኡሪዱ) የአረፍተ ነገሩ መልእክት ላይ "ብቻ" የሚል ትርጉም ይሰጠናል ምክንያቱም በአረበኛ ቋንቋ መቅደም ያለበትን ነገር አለማስቀደም ወይም በተቃራኒው ማድረግ "ብቻ" የሚል ትርጉም ይሰጠናል።


👈نعبد

👋 ይህ ቃል ሲነበብ:ነዕቡዱ

👉 ትርጉሙም:እንገዛለን

*⃣ ይህ ቃል በሌሎች ሁኔታዎቹ: አበደ(ተገዛ)፣የዕቡዱ(ይገዛል)፣ዒባደተን(መገዛትን)።

نستعين

👋 ይህ ቃል ሲነበብ:ነስተዒኑ

👉 ትርጉሙም:እገዛን እንለምናለን

መለመን የሚለውን ትርጉም ያገኘነው ኢስት ከሚሉት የመጀመሪያዎቹ ፊደሎች ነው። @Learn_Arebic

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 02:54


بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

አረበኛን በቀላሉ ክፍል 3
🌿የአረብኛ ቃላቶች🌿

ٱهۡدِنَا

ይህ ቃል ሲነበብ: ኢህዲና

👉 ትርጉሙም: ምራን(Guide us)

▶️ ይህ ቃል በሌሎች ሁኔታዎቹ :

👉ሀዳ(هدى)—መራ(ሀላፊ ግስ)

👉የህዲ(يهدي)—ይመራል

👉ኢህዲ(اهد)—ምራ

1⃣ ٱلصِّرَٰطَ
➡️ሲነበብ:አሲራጥ

ትርጉሙ: መንገድ(path)

👌 "ጠሪቅ" ማለትም መንገድ ማለት ነው።

ٱلۡمُسۡتَقِيمَ

▶️ይህ ቃል ሲነበብ: አልሙስተቂም

ትርጉሙም: ቀጥተኛ(straight)

➡️ ይህ ቃል በሌሎች ሁኔታዎቹ

👉 ኢስተቃመ(استقام) : ቀጥ አለ።

👉 የስተቂሙ(يستقيم): ቀጥ ይላል።

👉ኢስተቂም(استقم) : ቀጥ በል።


أَنۡعَمۡتَ

ይህ ቃል ሲነበብ: አንዐምተ

👉 ትርጉሙም: በጎ የዋልክላቸው(you have favored)

➡️ ይህ ቃል በሌሎች ሁኔታዎቹ:

👉አንዐመ(أنعم) : በጎ ዋለ።
👉ዩንዒሙ(ينعم) : በጎ ይውላል።
👉ኢንዓመን(إنعاما): በጎ መዋልን።
👉አንዒም(أنعم): በጎ ዋል።


عَلَيۡهِمۡ

➡️ሲነበብ:ዐለይሂም

ትርጉሙ: በእነሱ ላይ(upon them)

👌 "ዐላ" ማለት "እላይ" ማለት ሲሆን የተቀረው የቃሉ ክፍል "በእነሱ" የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል።

غَيۡرِ

▶️ሲነበብ: ገይሪ

ትርጉሙም: ያልሆነ፣ ሲቀር(other than)

*⃣ ይህ ቃል አንድ ነገር ከተናገርን ቡሃላ ከዚያ ውጭ ያለን ነገር ለመግለፅ እንጠቀምበተላን። ይህን ተግባር ያላቸው ሌሎች ቃላቶች "ሲዋ"፣"ኢላ" ና የመሳሳሉት ናቸው።

ٱلۡمَغۡضُوبِ

▶️ሲነበብ: አልመግዱብ

ትርጉሙም: ቁጣ የሰፈረባቸው

*⃣ ይህ ቃል በሌሎች ሁኔታዎቹ:

👉ገዲበ(غضب) : ተቆጣ

👉የግደቡ(يغضب) : ይቆጣል

👉ኢግደብ(اغضب) : ተቆጣ(ትእዛዝ)

وَلَا ٱلضَّآلِّينَ

▶️ሲነበብ: ወለዳሊን

ትርጉሙም: ያልጠመሙትን

*⃣ ያልሆነ የሚል መልእክት እንዲኖረው ያደረገው "ላ" የምትለዋ መጀመሪያ ላይ ያለችዋ ፊደል ነች።

ይህ ቃል በሌሎች ሁኔታዎቹ:

👉 ደለ(ضل): ጠመመ
👉 የዲሉ(يضل): ይጠማል
👉 ዲል(ضل) ብለን ወደ ጥመት ሰውን አናዝም😁

📕📗📘📙📕📗📘📙📕📗 @Learn_Arebic

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 02:54


بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

አረብኛን በቀላሉ ክፍል 2

🌿ሰዋሰው(grammar)🌿

ሰዋሰው(grammar) ማለት በቀላል ቋንቋ ስንገልፀው አንድ ቋንቋን በአግባቡ ለመጠቀምና ለመረዳት የሚያገለግሉን ህጎች ማለት ነው።

የአረብኛን ሰዋሰው እንደዚህ በሚለቀቁ አጫጭር ፅሁፎች በአግባቡ መረዳት እንደማይቻል እሙን ነው።

የአረብኛን ሰዋሰው በአግባቡ ለመረዳት ወደ ዑለሞች ቀርበን ግዜያችንን ሰጥተን በቱክረት መከታታል ይፈልጋል ምክንያቱም ቋንቋው ለጀማሪዎች እጅግ በጣም አስቸጋሪ መስሎ የሚታይና ግዜ ሰጥቶ ሀሳቦቹን በአግባቡ ለተረዳ ሰው ደግሞ እንደ መዝናኛ የሆነ ነው፤ አረብኛን በፅሁፍ ባየ ቀጥር ወይም ሲነገር በሰማ ቁጥር እነደፈለገ እያደረገው #ፈታ ይልበታል።

የዐረብኛ እውቀቶች በ 12 ተከፍለው ነው የሚሰጡት:

①—ዒልሙ ሉጋ
②—ዒልሙ ተስሪፍ
③—ዒልሙ ነሕዉ
④—ዒልሙ መዓኒ
⑤—ዒልሙ በያን
⑥—ዒልሙ በዲዕ
⑦—ዒልሙ ዐሩድ
⑧—ዒልሙ ቀዋፊ
⑨—ዒልሙ ቀዋኒኒልኪታበህ
①0—ዒልሙ ቀዋኒኒል ቂራአህ
①①—ዒልሙ ኢንሻኢረሳኢሊ ወልኹጠብ
①②—ዒልሙል ሙሓደራት

*⃣ 4ኛ፣5ኛና 6ኛው አንድ ላይ ዒልመል በላጋ በመባልም ይታወቃሉ።

😱 አረብኛ ከምናስበው በላይ በጣም ሰፊና ጥልቀት ያለው ቋንቋ ነው።

*⃣ እውቀት ስትሰጥ ይጨምራል ስለዚህ እኔም ካለችኝ ትንሽዬ እውቀት ላካፍላችሁ፤ ስለዚህም አንድ አንድ መሰረታዊና ቀለል ያሉ ሀሳቦችን እንጂ ከላይ የተጠቀሱትን አስራ ሁለቱን እዚህ ግሩፕ ላይ በጥልቀት ማየት አይጠበቅም።

*⃣ የግሩፑም አላማ ቁርኣናዊና ሀዲሳዊ የአረብኛ ቃላቶችን ማሳወቅና የሚያውቁትን ደግሞ ማስታወስ ነው ነገር ግን ቃላቶቹን በአግባቡ ለመረዳት አንድ አንድ መሰረታዊ የሆኑ የአረብኛ ህጎችን ማወቅ ያስፈልገናል። ለዚህም ሲባል ነው ትምህርታችንን "ቃላቶች ና ሰዋሰው" ብለን በሁለት ከፍለን ማየት ያስፈለገው።

➡️ በዚህ ክፍል ትምህርታችን ከ አረብኛ ንግግር(ከላም) የተወሰኑ ነጥቦችን እናንሳ:

📒 የአረብኛ ንግግር ከሶስት ነገሮች ይገነባል:

① ስም(ኢስም)
② ግስ(ፊዕል)
③ሀርፍ(ትርጉም የሚሰጥ ፊዳል)
ምሳሌ:إلى،من

👉 የአረብኛን ንግግር:

▶️ ከላይ በተጠቀሱት በሶስቱ

ወይም

▶️ በሁለት ስሞች

ወይም

▶️ከግስና ከስም

መመስረት ይቻላል።

▶️ ከሁለት ሀርፎች

ወይም

▶️ ከሁለት ግሶች

ወይም

▶️ ከግስና ከሀርፍ ብቻ

ወይም

▶️ከስምና ከሀርፍ ብቻ

መመስረት አይቻልም።

*⃣ አንድ የአረብኛ ቃልን ስናገኝ ሀርፍ ወይም ግስ አሊያም ስም መሆኑን መለየት የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ። ነገር ግን እንደዚህ አይነት ነገሮችን እያየን የምንሄድ ከሆነ በጣም በጥልቀት እየገባን ውዥንብሮችን ስለምንፈጥር መሰረታዊና ቀለል ያሉ ነገሮችን ብቻ እያነሳን እንሄዳለን።

በሚቀጥለው ክፍል ማዲ፣ ሙዳሪዕና አምር የሚባሉ የግስ አይነቶችን የምንመለከት ይሆናል፤ ኢንሻአላህ። @Learn_Arebic

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 02:54


😇😇 እዉቀት 😇😇
😇😇😇 የሚያሳጡ ነገሮች😇

👉 ራስን መናቅ: ረስህን ስትንቅ ቀላል ነገሮችን እንኳን ለመረዳት አትሞክርም።
👉 ረስን ማካበድ: ራሱን የሚያካብድ ሰው መሳሳት አይፈልግም። ካልተሳሳትክ ደግሞ እውቀት አታገኝም።
👉 ችኩልነት: ዛሬ አምብበህ ዛሬ አዋቂ መሆን አትችልም
👉 ሰውን መናቅ: ሰውን የሚንቅ ሰው በእውቀት ከሚበልጠው ሰው እንኳን መማር አይችልም።

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 02:54


ስትወለድ
👉 ሰዎች እየሳቁ😂
👉አንተ እያለቀስክ ነበር😭

ስትሞት
👉ሰዎች ያለቅሳሉ😭
👉 አንተ ደግሞ እንድትስቅ😃 በርትተህ ለኣኺራህ ስራ። 🇸🇦 @Learn_Arebic 🇸🇦

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 02:54


🇸🇦ሰላም ሰላም ውድ እና የተከበራች የሀገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ እኔ በጣም ደህና ነኝ እናንተም በያላችሁበት ሰላማችሁ እንደባህር አሸዋ ይብዛ የአረብኛ ትምህርታችንን በአዲስ መልክ በክፍል በክፍል በጥራት ለመጀመር ዝግጅታችንን ጨርሰን ብቅ ብለናል መረጃውን ሼር በማድረግ መረጃው ላልደረሳቸው ወዳጅ ዘመዶቻችሁ መረጃውን አጋሩ! ግሩፕ ስለከፈትን ከስር ባለው ሊንክ👇👇👇👇👇👇👇👇<< @Learnwithour >> ተቀላቅላችሁ Add እያጀረጋችሁ ጥያቄዎችን በመመለስ መሳተፍ ትችላላችሁ መልካም የትምህርት ግዜ ይሁንላችሁ🇸🇦

🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦

26 Jan, 02:54


🇪🇹አረበኛ መማሪያ🇸🇦
ሰላም ሰላም ጓደኞቼ እንዴት ናችሁልኝ ይህ ቻናል የተከፈተበት ዋነኛ አላማ አረበኛን አቀላጥፈው መናገር ለሚፈልጉ የሀገራችን ልጆች አረበኛን ቀለል ባለ መንገድ ለማስተማር ታስቦ ነው!
ቻናሉን ጆይን ብላችሁ በመቀላቀል ቤተሰብ ሁኑ!
ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር በማድረግ መረጃውን ያጋሩ!
https://t.me/Learn_Arebic

1,995

subscribers

2

photos

0

videos