ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

@nisirrmedia


ስለ አማራ ፋኖ መረጃ ይቀርብበታል! የህልውና ትግሉን የምትደግፉ ተቀላቀሉን!!
ፋኖ ያሸንፋል!
አማራውም ነፃ ይወጣል!!

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

19 Oct, 07:32


አብይ አህመድ እና ግብረ አብሮቹ በህፃናት ላይ ለምን ጨከኑ፥ ሲቪሊያንን በድሮን መጨፍጨፍስ ለምን ወደዱ:-

ለ15 ወራት በተደረገው ጦርነት የፋኖ ኃይሎች ወታደራዊ ጡንቻ በእጅጉ የፈረጠመበት፣ ፋኖ የስነ ልቦና የበላይነት የያዘበት፣ የብልፅግናን ሰራዊት መማረክም ሆነ መሳሪያውን መረከብ የፋኖ የዘወትር ተግባር የሆነበት ሁኔታ ተፈጥሯል። አልተሳካለትም እንጅ አብይ ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ ብዙ ሚሊዬን ዶላሮች አፍስሷል ፥ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን መከላከያውን የእሳት ራት አድርጓል።

ይህ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ብልፅግናን አማራ ክልል ውስጥ መልሶ ለመትከል ነበር። ይህም ቅዥት ብቻ ሆኖ ቀርቷል። እግር ትከል የተባለው ካድሬም "የትኛውን እግሬን?፥ እግር ሳይኖረኝ?" የሚል ምክንያታዊ ጥያቄን ማቅረብ ጀምሯል።
ይህ ጉዳይ በእነ አብይ ቤት ሙሉ በሙሉ የመሸነፍን ፍርሃት ፈጥሯል።

እግረኛው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ንፁሃንን መግደሉ የተለመደ ቢሆንም የአሁኑ የሚለዬው በራሱ በአብይ አህመድ ፊርማ በሚተኮሱ ድሮኖች ታስቦበት ህዝብ መጨፍጨፍ በመጀመራቸዉ ነው።
በሌላ በኩል አብይ ፋኖን አሸንፎ አገሩን መቆጣጠር ካልቻለ በስተቀር የዓለም ባንክ እና የIMF የዶላር ብድር ውል እና የፕሪቶሪያው ስምምነትም ሊተገበር እንደማይችል ተገንዝቧል።

በዚህ ወቅት የሚያደርገው የድሮን ጭፍጨፋ ዓለም አቀፋዊ ውግዘት እና ማዕቀብ ያስከትልብኛል ብሎ እንዳይሰጋ ደግሞ ምዕራባውያን በአሜሪካ ምርጫ፥ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት፥ በራሽያ ዩክሬን ጦርነት፥ በማይናማር ጉዳይ ትኩረታቸው መያዙን እንደ መልካም አጋጣሚ ወስዶታል።

የሚደረገው ጭፍጨፋ እነኝህን ነባራዊ  ሁኔታወች መነሻ ያደረገ ሲሆን የአጭር ግዜ ግቡ ብልፅግና አየር ኃይልን በመጠቀሙ ከፋኖ የተሻለ ጉልበት እና መንግስታዊ ሞገስ ያለው መሆኑን በማሳዬት የካሬወችን ስነ ልቦና መጠገን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ህዝቡ "መንግስትን" ማሸነፍ ለማትችሉት እኛን አስጨፈጨፋችሁን የሚል ጫና በፋኖ ላይ እንዲያሳድር ተፈልጎም ነው። ውጤቱ ግን በተቃራኒው ነው።

ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ከህዝብ ልብ መውጣቱን ስላረጋገጠ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል እንኳን ሲቪሊያንን መግደል እንደሌለበት በራሱ ካድሬ ሳይቀር የሚቀርበውን ጥያቄም መስማት አልፈለገም።

በአጭር አገላለፅ መንግስት መሆን እንደማይችል ያወቀው ብልፅግና የአሸባሪነት ሚናን እየተጫወተ እድሜውን ማራዘም ምርጫው አድርጓል።

አንዳንዶች የድሮን ጭፍጨፋውን ጉዳይ ደጋግመን ስንገልፅ ወታደራዊ ብልጫ ስለተወሰደብን አልያም ለተራ የጦርነት ፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሚመስላቸው አሉ። ዋነኛ  ምክንያታችን ህዝብ የእነኝህን ሰወች ብልግና ማወቅ እና መታገልም ስላለበት ነው።

ከዚህ በተረፈ ብልፅግና ከፖለቲካዊ ሽንፈቱ ባሻገር ከተቆጣጠርነው ቀጠና ውስጥ አንድ ኢንች እንኳን ሊነጥቀን አልቻለም፥ አይችልምም። ይልቁንም ወሳኝ ኮሪደሮችን ተረክበነዋል። ገና በድሎችም እንደምቃለን!

ጠበቃና አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

20 Sep, 10:06


አስቸኳይ!!

1. ከ 20  ደቂቃ  በፊት ሶስት  ድሮኖች  ከደብረ ዘይት ተነስተው  ወደ  አማራ  ክልል  አምርተዋል።

2. ዛሬ ማለዳ ከ40 እስከ 50 የሚደርሱ የአገዛዙ ወታደር የያዙ አይሱሪ መኪናዎች ከባህር ዳር በላይ ዘለቀ አየር ማረፊያ ወደ ጎንደር ቀጠና መሄዳቸውን ምንጮች ገልፀዋል::

ለፋኖዎች  ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በአስቸኳይ  ይድረስ!!

ሞገሴ ሽፈራው

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

20 Sep, 10:06


ከምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ካሉ አዛዦች ለመረብ ሚዲያ የደረሰው መረጃ!

በአማራ ክልል በሁሉም ቀጠና ጀትን ጨምሮ በድሮን እና በግረኛ መጠነሰፊ ጥቃት ለመሰንዘር  አዲስ እቅድ ወጥቷል።

ለዚህም ሲባል የምስራቅ ዕዝ 303ኛ ኮር ሙሉ ኃይል ወደ አማራ ክልል እንዲገባ ታዞ እንቅስቃሴ ጀምሯል።

በርካታ የሕዝብ ማመላለሻ ባሶች ግዳጅ ተይዘው ጎዴ ከተማ ላይ የ303ኛ ኮር ወታደርንና ወታደራዊ ንብረትን እየጫኑ ነው። የኮሩ አዛዥ ብ/ጄነራል ተሾመ ይመር ይባላል።

ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተላከ ትዕዛዝ መሠረት የምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች  ከ303ኛ ኮር የበላይ አዛዦች ጋር በእቅዱ አፈፃፀም ዙሪያ በነበራቸው ውይይት፡ አሁን ላይ በፋኖዎች ዘንድ የሚስተዋሉ የአደረጃጀት ልዩነቶችን በመጠቀም እርስ በራሳቸው የሚታኮሱበትን መንገድ ማስፋት።ልዩነቶችን ተጠቅሞ ሰርጎ በመግባት አመራሮችን መግደል የሚሉ ሃሳቦች ተነስተው ወደ ትግበራ እንዲገባ ውሳኔ ላይ መደረሱን በዕዙ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ያሉ ምንጭች ለመረብ ሚዲያ መረጃውን አድርሰዋል።

ለሁሉም የፋኖ አመራሮችና አደረጃጀቶች እንዲደርስ ባስቸኳይ ሼር#ሼርMerebMedia2

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

20 Sep, 10:06


#ለሸዋ,ለጎንደር,ወሎና ጎጃም ፋኖ ይድረስ:-
#ከድሮን ጭፍጨፋ ለመዳን የሚከተሉትን ያድርጉ?
1ኛ በአንድ  ወይም በቡድን ሁኖ አለመጓዝ!
2ኛ ከ5 ሰው በላይ ሁኖ አለመጓዝ!
3ኛ ራሱን በቅጠል/በጫካ መሸፈን!
4ኛ ከ25ሜትር  በታች ባለ የጎንዮሽ ርቀት አለመጓዝ!
5ኛ ሲቀመጡ በዛፍ ጥላ ስር መሆን አለብን (ድሮን በጥላ ስር ያለን ብዙ ጊዜ ማበብ አይችልም)!
6ኛ የሚያፀባረቁ ምንጣፍ/አንሶላ አለመጠቀም!
7ኛ ሲቀሳቀሱ በጨለማ/ጧት/በደመና ይጓዙ!
8ኛ ካሉበት ቦታ ጋ የሚመሳሰሉ ልብስ ይልበሱ!
9ኛ በአንድ መንገድ ሁሌም አለመጓዝ!
10ኛ ከመሄዳችን/ከመጓዛችን በፊት ጫካ የሆኑ ቦታወችን መምረጥ!
11ኛ በአንዴ ብዛት የወታደር ስቅ መጫንና መጓጓዝ የለበትም!
12ኛ ከድሮውን እይታ ውጭ መሆን!
13ኛ በገቢያ, ሰበት ቀን,እቁብ,በመኪና, በጋራ ,በሀዘንና በሌሎች የማህበር አኗኗር አብሮ አለመገኘት(መበትን ያስፈልጋል)!
14ኛ ሲራመዱና ሲቀሳቀሱ በዝግታ ይሁን ም/ቱም ሲፈጥኑ በቀላሉ ድሮውን ሰለሚያየን!
15ኛ ወደ አዲስ ቦታ ሲሄዱ በጥንቃቄ ይሂዱ!
16ኛ በእንቅስቃሴ ወቅት በደንብ መረጃ መለዋወጥ!
17ኛ አካባቢውን መቃኘት!
18ኛ የድሮን እቆስቃሴ መኖሩን ወደ ሰማይ በማየት በደንብ ማረጋገጥና መዘጋጀት ቦታ ለመያዝ!
19ኛ አንዴ በድሮን ከመታን በኋላ እኛ ቁስለኛ ወይም አስክሬን ለማሳት አለመሄዴ ም/ቱም ከዛው ላይ እኛን ድጋሜ ሊመታን ስለሚችል!

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

20 Sep, 09:24


መርጦለማርያም ከትናንት የቀጠለ...!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 9ኛ ክፍለጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድ ትናንት ጨለማ ያቋረጠውን ውጊያ ዛሬ በጠዋት ቀጥሎበታል። በመርጡ ለማርያም ከተማ ዙሪያውን ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ሲሆን ጀግናው አርሶ አደር ወራሪውን በጠዋት እጅ በእጅ ገጥሞታል።

ትናንት አመሻሹን የወራሪው 71ኛ ክፍለጦር አመራሮች መደምሰሳቸውን ገልፀን ነበር። ዛሬ ደግሞ በርከት ያለ የወራሪው ኃይል እጅ በእጅ እየተቀጠቀጠ ነው። 

      © አሻራ ሚዲያ

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

19 Sep, 16:58


ውድ የንስር ሚዲያ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰቦች በቴክኒክ ችግር ምክንያት መረጃዎችን ማድረስ አልቻልንም።ችግሩን በቅርቡ እናስተካክለዋለን።

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

10 Sep, 07:02


ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ   ለዕዛችን እና ለመላው የአማራ ፋኖ አባላት፣ለዞናችን እና ለመላው የአማራ ህዝብ እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን "እንኳን ከ2016 ወደ 2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ማለት ይወዳል።

አዲሱ ዓመት የሰላም ፣የአንድነት ፣የነፃነት የእኩልነት የፍቅር ዘመን እንዲሆን እየተመኘን በዓሉን ስናከብር በፍፁም አማራዊ ለጋስነት ፣ኢትዮጵያዊ መተሳሰብ የተቸገሩትን በመርዳት፣የታመሙትን በመጠየቅ ፣አቅመ ደካሞችን በማገዝ እንድናሳልፍ እዛችን ጥብቅ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

አዲስ አመት :-ያንን ሁሉ ድቅድቅ ጨለማ የክረምት ጊዜ አሳልፈን በአደይ አበባ ፍካት ቀዬው ሁሉ ድምቅ ብሎ አዳዳዲስ ተስፋዎችና እቅዶች የሚሰነቁበት ወቅት ነው።የአማራ ህዝብም ከተጫነበት ዓብይ መራሽ የባርነት ቀንበር ተላቆ በአብራኩ ልጆች ብርቱ ክንድ የባርነት ቀንበሩ ሊንኮታኮት ዋዜማው ላይ ደርሷል ለዚህም የአማራ ፋኖ በደማቅ ብዕር የሚፃፍ አይረሴ አሻራውን አስቀምጧል።

በእርግጥ እንቅፋት ሲመታ ወደፊት እንደሚያንደረድር ሁሉ የአማራ ህዝብም የደረሰበት ሞትና ስደት፣ግፍና መከራ፣ሰቆቃና ሲቃይ፣ርሀብና ጥም አንድ ሆኖ እንዲደራጅና በተናጥል ከመታረድም አልፎ ለማንም የማታዳላ ኢትዮጵያን ለመገንባት ከጥንት አባቶቹ ከነ እምዬ ምኒሊክ የመሪነት ጥበብን በመውረስ ታላቋን ሀገር "ኢትዮጵያን"ለመረከብ ጥቂት ጊዜያት ብቻ ቀርተውታል።

የተከበርከው የአማራ ህዝብና የዕዛችን ደጋፊዎች ሆይ ትናንት ስንደራጅ ጀምሮ ሲርበን እያጎረስክ ፣ሲጠማን እያጠጣህ፣ስናጠፋ እየገሰጥክ፣ስንደሰት ተደስተህ ስንከፋ ተክዘህ እዚህ አድርሰኸናል ።እኛም የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ አመራሮችና አባላት የህዝብ ልጆች እንደመሆናችን መጠን ለወጣንለት አላማ ፀንተን የአማራ ህዝብ ነፃነት በነጋሪት እስኪታወጅ ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ልንከፍል ቃል እንገባልሀለን።በአዲሱ ዓመት አዲስ አሰራር፣አዲስ የምስራች ይዘንም ብቅ እንላለን።

                መልካም አዲስ ዓመት!
               ክብር ለተሰው ፋኖዎች
                ድል ለአማራ ህዝብ
        የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ
                 ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም

5/13/16 ዓ.ም

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

10 Sep, 06:37


ታላቅ ድል በወሎ ..‼️‼️

የአማራ ፋኖ በወሎ የአሳምነው ክፍል ጦር ጳጉሜ 2 እና 3 ቀን በሰራው ኦፕሬሽን በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት እንደተማረከና የቡድንና የነብስ ወከፍ መሳሪያ ተማርኳል ።

4/13/16 ዓ.ም

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

07 Sep, 17:49


#መተማ_ኮኪት_ገንደውሃ..‼️

በጎንደር #መተማና አካባቢው የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ፋኖዎች በቅንጅት ዛሬም ጠላትን ሲያደባዩት ውለዋል:: የአጣናው ዋሴ ክፍለጦር  አርበኛች ክፍለጦርና ካራማራ ክፍለጦር ነበልባል ፋኖዎች በቅንጅት ጠላትን ሲለበልቡት ውለዋል::

6ኛ ቀኑን በያዘው የዛሬ የውጊያ ውሎ  የሱዳን ድንበር ከተማዋ መተማ ዮሐንስን ጨምሮ #የኮኪትና መተማ ከተማዎችን ለመያዝ የሞከረው የኦሮሙማው መከላከያና የባዳው ስብስብ በነበልባሎቹ በደረሰበት ምት ሙትና ቁስለኛ የተደርገ ሲሆን #ከገንደውሃ ተጨማሪ ሀይል በሚል የተላከው አራዊት ሰራዊትም በደረሰበት የደፈጣ ጥቃት ከ100 በላይ ሙትና ቁስለኛ ተደርጎ ከሞት የተረፈው ጎመን ወደመጣበት ፈርጥጧል::  ሽንፈትን የተከናነበው ኦነግ ብልጽግና በነዚህ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎቶችን አቋርጧል::

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

07 Sep, 17:48


የተከበቡት የብልጽግና ባለስልጣናት

በርካታ የብልጽግና የዞን ባለስልጣናት በፋኖ ከበባ ውስጥ በመግባታቸው እጅ እንዲሰጡ ተጠየቁ
ከሰሞኑ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በሚገኙ አካባቢዎች በፋኖ እና በአገዛዙ ጦር መካከል ከፍተኛ የፋኖ ተጋድሎ የታየበት ውጊያ እየተካሄደ ነው፡፡በዚህ ውጊያም የፋኖ ሃይሎች ወሳኟን የድንበር ከተማ መተማ ዮሃንስን ጨምሮ ሽንፋና ኮኪትን መቆጣጠራቸው ይታወቃል፡፡

የአገዛዙ ጦርም ከእነዚህ አካባቢዎች ሸሽቶ ወደ ሱዳን ማቅናቱን ሌላውም ሙትና ቁስለኛ መሆኑ ተነግሯል፡፡ይህ ጉዳይም ሰሞንኛ መነጋገሪያ ጉዳይ ሲሆን የብልጽግናው መንደርም ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባበት ሁኔታ ነው፡፡

በአርበኛ ባዬ ቀናው የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር እና በአርበኛ ሃብቴ ወልዴ የሚመራው የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ በጋራ እየሰሩት ባለው ጀብዱም አካባቢው ከብልጽግና መዋቅር ሙሉ በሙሉ እየጸዳ ነው፡፡

አገዛዙ ከተሞቹን መልሶ ለማስለቀቅ ያለ የሌለ ሃይሉን ቢጠቀምም ሊሳካለት አልቻለም፡፡ ይባሱኑም በዋናነት ሰፍሮ በተቀመጠባት የዞኑ መቀመጫ ገንደውሃ ከተማ ላይ ከበባ ተፈጽሞበታል፡፡ይህን ከበባ ተከትሎም በከተማዋ የሚገኙ የዞኑ የብልጽግና አመራሮች ለፋኖ ሽምግልና ቢልኩም ፣ የፋኖ ሃይሎች ግን አመራሮች እጃቸውን እንዲሰጡ እየጠየቁ ነው፡፡

ዋነኛ የብልጽግና ተላላኪዎች የሆኑት እነዚህ ከሽሽት የተረፉ የዞን አመራሮችም ከከተማዋ እንዳይወጡ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል፡፡

የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ የአርበኞች ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ብርሃኑ ነጋ “ ዞኑን ሙሉ በሙሉ ነጻ ለማድረግ ተዘጋጅተናል” ሲል ገልጿል፡፡

የብልጽግና ጦርና ካድሬዎች አሁን ላይ አንድ አካባቢ የመሸጉ መሆናቸውን ያነሳው ሻለቃ ብርሃኑ ፣ ፋኖም እነዚህ ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል ብሏል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን የአገዛዙ  መዋቅር ሙሉ በሙሉ ፈርሷል ያለ ሲሆን በእግር ጉዞ ጭምር የሚሸሹ ካድሬዎችን እያሳደድን ነው ብሏል፡፡ የተቀሩትም የብልጽግና የዞን ካድሬዎች እጅ እንዲሰጡ ተጠይቋል።
rohatv

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

07 Sep, 17:34


የአማራ ፋኖ በወሎ በድል የታጀቡት ውሎዎች...‼️

በድል የታጀበው ዘመቻ ይታገሱ የቀጠለ ሲሆን #በአማራ_ሳይንት የአማራ ፋኖ በወሎ መቅደላ ክፍለጦር አትሮንስ ብርጌድ አናብስት ከታቦር ተራራ ብርጌድ ነበልባሎች ጋር በመቀናጀት ከትላንት በስተያ ባደረሱት ጥቃት በርካታ የኦነግ ብልጽግና አራዊት ወደ አስክሬንነት ተቀይረዋል:: በርካታ መንገድ ጠቋሚ ባንዳ ሚሊሻዎች የተሸኙ ሲሆን  የሳይንት የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ክፉኛ ተመቶ በሆስፒታል ነፍስ ውጪ ነፍስ ጊቢ ላይ ይገኛል ሲሉ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል::

በተመሳሳይ በትላንትናው ዕለት በቤተ አማራ ወሎ #ወልድያ እና ራያ #ቆቦ ዙሪያ በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ከተማዎቹን #ቀለበት ውስጥ በማስገባት ጠላትን ድባቅ መተዋል::

በወልድያ ከጎብዬ እስከ ሲሪንቃ ድረስ በተደረጉ ውጊያዎች በርካታ የኦነግ ብልጽግና መከላከያ የፋኖ ጥይት ሲሳይ ሆኗል :: የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ክፍለጦር ፣ የጊራናው ባለሽርጡ ክፍለጦር እና ታጠቅ ብርጌድ ጎብየ ከተማና ጥቁር ዉሃንን ጨሮ በወልድያ ዙሪያ ገዢ ቦታዎችን ተቆጣጥረዋል:: ፀረ አማራው የኦነግ ብልጽግና አራዊት የ13አመት ታዳጊን ጨምሮ ንፁሀን አማራዎችን ገድሏል::

ከአራዱም እስከ ቆቦ ከተማ ዙሪያ በነበረው ውጊያ የጠላት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ገዢ መሬቶች በአማራ ፋኖ በወሎ ዞብል አምባ ክፍለጦር፣ ሃውጃኖ ክፍለጦርና ዲቢና ወርቄ ባለሽርጡ ብርጌድ ነበልባሎች እጅ ገብተዋል::  የካላኮርማ ክፍለጦር ከአሚድ ዉሃ ሮቢት ከተማ እስከ መንጀሎ ድረስ የተለያዩ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል::

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

07 Sep, 07:20


ጎንደር የጀግኖች ማኅደር ነው። ጥርጥርም የለውም።  
የሚያሸንፈው ግን ከሸዋ፣ ከወሎ እና ከጎጃም አንድ ሲኾን ነው።

ወሎ ስለጀግንነቱ አይደለም የሀገር ሰው ይናገራል መሬቱ። የሚያሸንፈው ግን ከሸዋ፣ ከጎጃም እና ከጎንደር አንድ ሲኾን ነው።

ሸዋ ከልብም ነጥሎ የደም ሥር የሚበጥስ አነጣጥሮ ተኳሽ የጀግና መፍለቂያ ነው። የሚያሸንፈው ግን ከወንድሞቹ ከወሎ፣ ከሸዋ እና ከጎጃም ሲያብር ነው።

ጎጃም ከታገለ ሳይጥል የማይመለስ ከተኮሰ ዝሃ የሚበጥስ የጀግንነት ራስ ነው። እርሱም ቅሉ የሚያሸንፈው ከክንዶቹ፣ ከጋሻዎቹ ከጎንደር ከሸዋ እና ከወሎ ሲተባበር ነው።

አንዱ ያለ ሌላው ጦርነት ሊያሸንፍ ይችላል። የሚጨብጠው ድል ግን የለም።
ስለዚህ ወደ ድሉ ተራራ ከፍ ለማለት ከፋፋዮችን ገለል እናድርግ !!

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

06 Sep, 05:57


የኮሚቴው መግለጫ

ህወሃት ከ20 ሺህ በላይ ወታደራዊና የመረጃ ደህንነት ሰራተኞችን ወደ ጠለምት ማስገባቱ ተገለፀ
የጠለምት አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ 
በወቅታዊ ጉዳዩች ላይ በሰጠው መግለጫ" ከፍተኛ መጠን ያለው ህገወጥ ገንዘብ ከትግራይ ወደ ጠለምት እየገባ ነው" ሲል ገልጿል። የኮሚቴው

ኮሚቴው በመግለጫው " በሦስቱም ወረዳዎች ይኖሩ ከነበሩ በጦርነቱ ወቅት ከተፈናቀሉ 422  እውነተኛ ተፈናቃይ የትግራይ ተወላጆች ውጭ፣ በተፈናቃይ  ስም ከ20,000  በላይ የወታደራዊ፣ የመረጃና የፖለቲካ ተልዕኮ የመፈፀም ልምድ ያላቸው፣ በጦርነቱም ተሰልፈው የነበሩ ሰዎች እንዲገቡ ተደርጓል" ብሏል

"ከእነዚህ ውስጥ የጦር መሳሪያ የታጠቁ፣ የራሳቸው ውስብስብና ረቂቅ የግንኙነት ሰንሰለትና ጥርነፋ እንዳላቸው ከእንቅስቃሴዎች መታየቱ፣ ድርጅቱ አሁንም በመጣበት የጥፋት መንገድ የመቀጠል ዝግጁነት ላይ እንደሆነ ተጨባጭ ስጋት አድሮብናል፡" ሲልም ይቀጥላል።  

ህወሃት በውስጥ ጉዳዩ የተወጠረ ቢመስልም ወታደራዊ፣ መረጃና የፖለቲካ ኃይሉ የየራሱን ስምሪት ወስዶ የሚሰራ በመሆኑ በሰሞነኛ መረጃዎች በ ‹‹አክሱም››፣ ‹‹ውቅሮ›› ‹‹ማራይና›› ‹‹ሰለክላካ›› በሚባሉ የትግራይ አካባቢዎች ከተራ ተዋጊ ሰራዊት እስከ ኮማንዶ ድረስ ወታደራዊ ስልጠና እየሰጠ፣ ሰልጣኞችንም ለማይታወቅ ተልዕኮ እያዘጋጀ ነው" ብሏል፡፡ 

በተጨማሪም ህወሃት በርካታ ሚሊዮን ብሮችን በድጋፍ ስም ወደ አካባቢው እያስገባ መሆኑ ተነግሯል።
"ችግሩ በዘላቂነት መፈታት አለበት በተባለበት መንገድ እስከሚፈታ ድረስ፣ በሦስቱም ወረዳ የሚገኘው ሕዝብ ጊዜዊ ሕዝባዊ አስተዳደር በማዋቀር፣ የአካባቢው የመልማትና የፍትህ ጥያቄ እንዲቀላጠፍ አገዛዙም አምኖ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸው ይታወቃል" ሲል መግለጫው አስታውሷል፡፡  "ይህን ተግባር ለማስፈፀምም አስፈፃሚ ኮሚቴ ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም. ልኮ ወደ ተግባር ለመግባት በተጀመረበት ሁኔታ፣ ህወሃት ግን የጠለምትን ሕዝብ እንዳሻው ረግጦ ለመግዛት፣ የራሱን ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅም ለማሳደግ ጊዜ ለመግዛት የ ‹‹ይራዘምልን›› ጥያቄ አቅርቧል" ብሏል ኮሚቴው፡፡

የብልፅግና ተወካዮችም ጥያቄያቸውን ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም ተቀብለው ወደማዕከል ተመልሰው ሄደዋል ያለው ኮሚዬው ይህ በምንም ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው አሰራር ነው በሚል ኮንኗል፡፡ ህወሃት‹‹የጊዜዊ ሕዝባዊ አስተዳደር ምስረታው ይራዘምልን›› ያለው አንድም በሦስቱም የጠለምት ወረዳ የሚኖረው የአማራ ሕዝብ ቁጥር ከ 240,000 በላይ መሆኑን ስተረዳ በሕገወጥ መንገድ ካስገባቸው ተፈናቃዮች ጋር የሚጣጣም በላመሆኑ የጉልበት አማራጭን በማሰብ ነው ሲልም ያክላል፡፡

እውነተኛ ተፈናቃይ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በሚኖሩባቸው ቀበሌዎች በቁጥር ድርሻቸው ልክ የሚሳተፉበት ሕዝባዊ አስተዳደር እንዲቋቋምና ከሕዝባችን የማንነትና ወሰን ጥያቄ ጎን ለጎን የመልማት ጥያቄዎቹ፣ በኢትዮጵያዊ ዜግነቱ ሊያገኘው የሚገባ የበጀትና የልማት ማካካሻዎች እንዲሰጡት ሲልም  ኮሚቴው ጠይቋል። ምንም እንኳን ጥያቄው የቀረበው የአማራን አንገት ለማስደፋትና ማንነቱን ለማጥፋት ለሚተጋው ለብልፅግናው አገዛዝ ቢሆንም።

roha tv

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

06 Sep, 05:56


🔥#አቸፈር‼️

በጎጃም አቸፈር ዱርቤቴ ከተማ ከትላንት በስተያ የኦነግ ብልጽግና መከላከያና የባንዳው ስብስብ ‘ሚሊሻ ለማደራጀት’ በሚል #ስብሰባ እያደረጉ በነበረበት በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት ጠላት ድባቅ ተመቷል::  የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገው ምድር (ሶስተኛ) ክፍለጦር የአቤ ጉበኛ ብርጌድ አናብስት የኦነግ ብልጽግና አገልጋዮች ስብሰባ እያደረጉ በነበረበት ሰዓት ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት ከ25 በላይ ጎመን የተሸኘ ሲሆን ከ15 በላይ ጠላት ቁድለኛ ተደርጏል::

1/13/16 ዓ.ም

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

06 Sep, 05:55


🔥#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️

ስለ እነ “#እያገባህም”!

በየቲክቶክ ፌስቡክና ዩቱብ ተቀምጦ አንተ ከጎንደር/ጎጃም/ሸዋ/ወሎ አካባቢ ስለሆንክ ሌላ አካባቢ ስለሚኖረው አማራ አያገባህም የሚል ሁሉ 100/100 በሚባል ደረጃ ከአማራ ስም ጀርባ የተደበቀ ነገር ግን ከአማራ ብሔር ያልተወለደ #የኦነግና #ወያኔ ኤጀንት መሆኑ ይታወቅ::

#ሁሉም_ነገደ_አማራ በየትኛውም አካባቢ ስለሚኖር አማራ ያገባዋል:: ያንንም እውነታ ከአማራ ነገድ የተወለደ ሁሉ ጠንቅቆ ያውቀዋል::

ስለዚህ "አያገባህም" የሚለው አስመሳይ ሾተላይ የኦሮሙማው ፣ ትግሩማውና መሰሎቻቸው ኤጀንቶች እንደሆኑ ይታወቅ!

"አያገባህም" የምትለዋ ጨዋታ እነሱን ለማወቅ እንደ #ምልክት ትወሰድ‼️

ይህ መልዕክት ይዛመት‼️

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

06 Sep, 05:54


የፋኖ ሀይሎች በሰሜን ወሎ ዞን ለሚገኙ ሁለት ወረዳዎች አስተዳዳሪ መሾማቸዉ ተገለፀ

በሰሜን ወሎ ዞን ስር ባሉት የቡግና እና ላስታ ወረዳ ህዝብ አዳዲስ አስተዳዳሪዎች በፋኖዎች ተመድበዋል፡፡

አስር አለቃ ነጋ የቡግና አስተዳዳሪ ሆኖ ሲሾም ፋኖ ተመስገን ደግሞ የላስታ ዋና አስተዳዳሪ በመሆን መሾማቸዉ ተገልፆል፡፡

የካቢኒ አስተዳደራዊ  መዋቅርን በቅርቡ ዘርግተዉ ወደ ስራ እንደሚገቡ ታዉቋል፡፡

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

06 Sep, 05:52


አስቸኳይ መረጃ ጎንደር መተማ

በአውሮፕላን ተጓጉዞ በሱዳን በኩል የገባ ወራሪና ተበትኖ የነበረው በመሰባሰብ በመተማ ዮሐንስና በድል _በር ውጊያ ከፍቷል።
ድል ለፋኖ

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

05 Sep, 16:59


#ኦነጉ ብልጽግና በመብራት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንደሚያደርግ አስታውቋል..‼️

ኦነግ ብልጽግና ከመጪው መስከረም 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2020 ዓ.ም. ድረስ በየአራት ወሩ በኤሌክትሪክ ታሪፍ ላይ ጭማሪ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ መሰረት የመኖሪያ ቤት ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች በአራት ዓመት ውስጥ ከ256 እስከ 477 በመቶ የሚደርስ የክፍያ ጭማሪ ይደረግባቸዋል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሰጠው መግለጫው ገልጿል::

ከሳምንታት በፊት ከውጪ ሀይሎች ገንዘብ ተቀብሎ የውጪ ምንዛሬ ተመን ለውጥ በማድረግ #የኑሮ_ውድነትን በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው የኦሮሙማው ብልጽግና በተጨማሪ ህዝብን ወደ የባሰ ድህነት የሚወስዱ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል::

የራበው ህዝብ መሪውን ይበላል!

30/12/16 ዓ.ም

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

05 Sep, 16:57


#ወንበርማ‼️

የአማራ ፋኖ በጎጃም ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም (5ኛ) ክፍለጦር ወንበርማ ብርጌድ ስበር ወንበርማ ሻለቃ ነበልባሎች በትላንትናው ዕለት #በወንበርማ የተንቀሳቀሰውን የኦነግ ብልጽግና አራዊት ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ሲቀጡት ቆይተዋል::

በባንዳ ሚሊሻ እየተመራ ከወገዳድ ወደ ጎመር የተንቀሳቀሰው የኦሮሙማው ጎመን  ሲጠባቀበቁት በነበሩት የስበር ወንበርማ ሻለቃ ፋኖዎች ሙትና ቁስለኛ ተደርጏ ከሞት የተረፈው ጠላት ወደ ወገዳድ ፈርጥጧል:: ከሽንዲ ከተማ ተጨማሪ ሀይል አሰባስቦ ከእንደገና የተንቀሳቀሰው ጠላት መንገድ ላይ እንዳለ በደረሰበት የደፈጣ ጥቃት ድባቅ ተመቷል:: ነበልባሎቹ ፋኖዎች ባደረሷቸው ጥቃቶች ከ45 በላይ የኦነግ ብልጽግና አራዊት ሰራዊት ረግፎ ሙትና ቁስለኛ ተደርጏል::

ንስር ሚዲያ-(Nisir Media)

04 Sep, 22:28


ሸዋ!!

በጤና ጣቢያ እና ትምህርት ቤቶችን መሽጎ የተቀመጠው የአገዛዙ ጦር እርምጃ እንደተወሰደበት ተነግሯል።

በሜዳ ወረዳ ሬና ከተማ በትምህርት ቤቶች እና በጤና ጣቢያዎች  ውስጥ መሽጎ የተቀመጠው የስርዓቱ አገልጋይ ወታደር መደሰሱ ተሰምቷል።

በዛሬው እለት የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር በሜዳ ወረዳ ሬና ከተማ መሽጉ የተቀመጠውው የአገዛዙ ጦር ከበባ ውስጥ በማስገባት  ከተማዋን መቆጣጠር መቻላውን ገልፀዋል ።

ከጥዋቱ 12: ሰዓት ጀምሮ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ውጊያ ጠላት በትምህርት ቤት እና ጤና ጣቢዎች የመሸገው የአገዛዙ ጦር ሙት እና ቁስለኛ በመሆን ሬና ከተማን የአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር መቆጣጠር መቻሉን ቃል አቀባዩ ገልጿል።

ሞገሴ ሽፈራው!!