Merega Tv = Ethio 360Media

@adawdaa


Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 07:45


አሜሪካ፤ ሶሪያ በሚገኘው የጦር ሰፈሯ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀች

አርብ አመሻሽ ላይ በሶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ የሮኬቶች ጥቃት መፈጸሙን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል፡፡

“በሶሪያ አልሻዳዲ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ጣቢያ” ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈጸም በዘጠኝ ቀናት ውስጥ ሶስተኛው መሆኑም ዕዙ ገልጿል፡፡

ቀደም ሲል እንደፈረንጆቹ ህዳር 17 በሶሪያ ትልቁ የነዳጅ ዘይት ቦታ አል ኦማር እና በኢራቅ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የጥምረቱ አረንጓዴ መንደር ጣቢያ ላይ ያነጣጠሩ ሮኬቶች ተተኩሰው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጅ በአሁኑ የሮኬቶች ጥቃት አሜሪካ የምታግዛቸው "የሶሪያ ዲሞክራቲክ ሃይሎች የሮኬት መገኛ ቦታን ጎብኝተው ሶስተኛው ያልተተኮሰ ሮኬት አግኝተዋል" ሲል ማዕከላዊ ዕዝ ባወጣው መግለጫ አመላክተዋል፡፡

በሶሪያ ውስጥ ሰፊ የመረጃ መረብ ያለውና መቀመጫውን በብሪታንያ ያደረገው የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ የሆነ የጦርነት ተቆጣጣሪ፣ ጥቃቱ የመጣው "ከኢራን ደጋፊ ታጣቂዎች" ነው ብሏል። በጥቃቱ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩም ነው የተገለጸው፡፡

የአሜሪካ ወታደሮች እንደፈረንጆቹ ከ2019 ጀምሮ የእስልምና መንግስት ቡድን (አይኤስ) ከተቆጣጠራቸው የሶሪያ ግዛቶን ጠራርጎ ለመውጣት በመፋለም ላይ የሚገኘውን የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ሃይል (ኤስዲኤፍ) በመደግፍ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።ከአይ ኤስ ቅሪቶች ጋር በሚደረገው ውጊያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች አሁንም በሶሪያ ይገኛሉ

Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 07:35


የአለም ዋንጫን ቀጥታ በቴሌግራም ማየት ከፈለጉ (live stream) ከስር ያለውን ይጫኑ
@worldcupet1277

Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 02:33


ለሚፈጠረዉ የጸጥታ ችግር ዋስትና ያጡ የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች በስጋት ከተማዋን ለቀዉ እየወጡ ነዉ ተባለ፡፡

የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ከከተማዋ ለመዉጣት ተገደዱት ሸዋሮቢት አካባቢ የተፈጠረዉ የጸጥታ ችግር ሊስፋፋ ይችላል በሚል ስጋት ነዉ፡፡

የከተማዋ ከንቲባ አቶ አሳልፍ ደርቤ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በአጣዬ ከተማ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥቃት የተፈጸመ በመሆኑ ነዋሪዉ በቀላሉ ስጋት ላይ እንዲወድቅ አድርጎታል ብለዉናል፡፡

እስካሁን በከተማዋ የተፈጠረ ነገር ባይኖርም፣ ቀደም ሲል ሲፈጸም ከነበረዉ ተደጋሚ ጥቃት አንጻር፣ ቀጣይ ምን ሊሆን እንደሚችል እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ገጠር ቤተሰቦቻቸዉ እየሄዱ ነዉ ብለዉናል፡፡

የቻልነዉን ያህል ለማረጋጋት እየሞከርን ነዉ ያሉት ከንቲባዉ፣ ሙሉ በሙሉ ምንም አትሆኑም፣ችገህርም አይፈጠርም ብለን ዋስትና ሰጥተን ከተማዋን እንዳይለቁ ለማድረግ ግን ተቸግረናል ነዉ ያሉት፡፡

ከከተማዋ የጸጥታ መዋቅር፣የክልሉ ልዩ ሃይላል የፌደራል ፖሊስ ጋር በጋራ እየሰራን ነዉ ያሉት አቶ አሳልፍ እስካሁን ሸዋሮቢት አካባቢ ከሚሰማዉ ችግር በስተቀር አጣዬ አካባቢ የተለዬ ነገር እንደሌለ አረጋግጠዉልናል፡፡

ከዚህ ቀደም ነዋሪዉ ከከተማ እንዳይፈናቀል አረጋግተን የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ ግን የሰዉ ህይወት ሲጠፋና ንብረት ሲወደም ምንም ማድረግ አለመቻላችን አሁን ሙሉ ዋስትና ለመስጠት ተቸግረናል ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሸዋሮቢት በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከ2ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው

Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 02:33


#ዜና በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ Squire Patton Boggs የተባለ የአግባቢ ኩባንያ (lobbyist) እንደቀጠረ ተሰምቷል!

የአፍሪካ ሪፖርት መፅሄት የተመድ እና ኒው ዮርክ ዘጋቢ ጁሊያን ፔክዌት ማምሻውን የተያያዘውን ዶክመንት ዋቢ አድርጎ እንደፃፈው አግባቢ ድርጅቱ በወር 60,000 ዶላር በኤምባሲው የሚከፈለው ሲሆን ውሉ ለስድስት ወር ይቆያል።

ዋና አላማው በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መሀል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ነው ተብሏል። ከዚህ በፊትም Actum እና Holland & Knight የተባሉ ድርጅቶች ለተመሳሳይ ስራ ተቀጥረው ነበር።

Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 02:33


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፋሲካ (ትንሳኤ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። መልካም በዓል

Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 01:11


"የሩሲያ ወታደሮች በዚህ በኩል አለፉ እያላችሁ ለጠላት መረጃ የምታቀብሉ አክቲቪስቶች እረፉ!" 😂
Via Grazmach Shafi

Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 01:11


ሰበር ዜና

አሜሪካ ከሩሲያ እንዲዋጋ ወደ ዩክሬን የምትልከው ጦር እንደማይኖር አስታወቀች በሩሲያ አራት ባንኮች ላይ ከባድ ያሉትን እገዳ መጣላቸውንም ነው ባይደን ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት

ለዩክሬን በአንድ ዓመት ብቻ የ650 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ወታደራዊ ድጋፍ አድርገናል ያሉት ፕሬዝዳንት ባይደን ወደ ዩክሬን የምንልከው ጦር የለም ብለዋል

አሜሪካ ለውጊያ ወደ ዩክሬን የምትልከው ወታደር እንደማይኖር ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ።

ባይደን ሩሲያ አቅዳ የፈጸመችው ነው ያሉትን የዩክሬን "ወረራ" በተመለከተ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው እንወስደዋለን ካሉት የማዕቀብ እርምጃ ጋር የተያያዙ ማብራሪያዎችንም ሰጥተዋል።

ፑቲን ወራሪ ነው፤ ጦርነትንም መርጧል" ሲሉ" በማብራሪያቸው የሩሲያን ፕሬዝዳንት የወነጀሉት ባይደን አሁን ገፈቱን መቅመስ ይጀምራል ሲሉ ተናግረዋል።

ወደ ሩሲያ ኤክስፖርት በሚደረጉ ምርቶች ላይ ከበድ ያለ ማዕቀብ መጣላቸውን ያስታወቁም ሲሆን ማዕቀቡ የሩሲያን ምጣኔ ሃብት በአጭርና በረጅም ጊዜ እንደሚያንኮታኩተው ገልፀዋል።

ሆኖም ይህ አሜሪካ በተናጠል ሳይሆን 27 የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራትን ጨምሮ ከዓለም ምጣኔ ሃብት እኩሌታውን ከያዙ አጋሮቿ ጋር የምታደርገው ነው ብለዋል።

ዛሬ ጠዋት (ሃሙስ) ከቡድን 7 አባል ሃገራት ጋር በነበረ ስብሰባ በዚሁ ጉዳይ ላይ መስማማታቸውን የገለፁም ሲሆን ሩሲያ በዶላር፣ በዩሮ ፣ በእንግሊዝ ፓውንድ እና በጃፓን የን መገበያየቷን እንገድበዋለንም ብለዋል ፕሬዝዳንት ባይደን።

በአሜሪካ በሚንቀሳቀሱ እና በጥቅሉ ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ለማካበት የቻሉ አራት የሩሲያ ባንኮች ሃብታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ እገዳ መጣሉንም ገልጸዋል።

ለፕሬዝዳንት ፑቲን ቅርበት ባላቸው አካላት የንግድ ተቋማት እና ሩሲያ ከአሜሪካ በምታስገባቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ማዕቀብ መጣሉንም ነው ይህ ወታደራዊ ብርታቷን ክፉኛ ያዳክመዋል ያሉት ባይደን ያስታወቁት።

ሆኖም የአሜሪካ ጦር ወደ ዩክሬን አቅንተው በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት እንደማይሳተፍ አልሸሸጉም።

"ወታደሮቻችን በዩክሬን ውጊያ ለመሳተፍ ወደ አውሮፓ አይሄዱም" ሲሉም ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት፤ ሃገራቸው ለዩክሬን የ650 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጓን በመጠቆም።

ይልቁንም ጦሩ የኔቶ (የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት) አባል የሆኑ የምስራቅ አውሮፓ አጋር ሃገራትን ለመጠበቅ ወደዚያው እንደሚያቀና ባይደን ተናግረዋል።

ኔቶ ለአጋሮቹ ዋስትና መስጠት በሚችልበት ጉዳይ ላይ ለመምከር ነገ አርብ አስቸኳይ ስብሰባን እንደሚያደርግም አያይዘው ገልጸዋል።

አሜሪካ ሙሉ በኔቶ ቁጥጥር ስር ያለችን እያንዳንዷን ይዞታ ኢንች እንኳን ሳታስቀር ትጠብቃለችም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 01:11


የህወሀት አለቅላቂዎች አሉ እነዚህ ናቸው ልዩ-ኃይሉ እንዳይጠናከርና ክልሉ ለጠላት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርጉት።

#Ethiopia : ከኃላፊነቴ የተነሳሁት ዋነኛ ምክንያት የአማራ ልዩ ኃይል እንዳይደራጅ የሚፈልጉ ጄኔራል መኮንኖች በመከላከያ ውስጥ በመኖራቸው ነው። አስር ቦታ የጥይት ምት እያለብኝ በዛ ክረምት በዱላ ገብቼ ያዋጋሁት ለዝና ወይም ለሌላ አይደለም "አማራን እንበቀላለን!?" ብሎ ፎክሮ የመጣውን ኃይል ለመደምሰስ ነው ተሳክቶልኛል ። እነሱ የፈለጉት መሾም እንደሚችሉ እኔም ይሄንን ኃላፊነት እንደማልቀበል ነግሪያቸዋለሁኝ። ከኃላፊነቴ የተነሳሁት ዋነኛ ምክንያት የአማራ ልዩ ኃይል እንዳይደራጅ የሚፈልጉ ጄኔራል መኮንኖች በመከላከያ ውስጥ በመኖራቸው ነው። ገና ሰናደራጅ "ይፍረስ!" ሲሉ የነበሩ አንዳንዶቹ የኛው ድርጅት የህወሀት አለቅላቂዎች አሉ እነዚህ ናቸው ልዩ-ኃይሉ እንዳይጠናከርና ክልሉ ለጠላት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርጉት።

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ለፍትህ መፅሔት

Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 01:11


ዶንባስ ክልል ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ተጀምሯል። የወታደራዊ ዘመቻው ዋነኛ ዓላማ ላለፉት 8 ዓመታት በኬይቭ በሚገኘው መንግስት የዘር ጭፍጨፋ ሲፈፀምባቸው የነበሩ ሰዎችን ነፃ ማውጣት ነው።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

Merega Tv = Ethio 360Media

20 Jan, 01:11


ሩሲያ ደም አፋሳሹን መንገድ መርጣለች፤ ቀጣይ እርምጃ ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተናል።

🇬🇧 የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን

Merega Tv = Ethio 360Media

19 Jan, 22:39


አሜሪካ ዜጎቿን ከኢትዮጵያ ውጡ ባለችበት ወቅት የአሜሪካ ዜጎች 45 የሚሆኑ አሜሪካዊ ሚስዮናውያን ኢትዮጵያ ገብተው ወደ አርባ ምንጭ ሄደዋል! ሚስዮናዊያኑ በኢንስታግራም ገጻቸው Good morning from Addis Last night we safely arrived to Addis Ababa (capital of Ethiopia). This morning we caught our last flight our final destination- Arba Minch. በማለት አሜሪካዊያንን ኩም አድርገዋል!

Merega Tv = Ethio 360Media

19 Jan, 22:14


ሰበር ዜና ‼️

#Ethiopia : በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የተጠኑና ወራሪው ሽብርተኛው ህወሓት ወያኔ መሳሪያ በማከማቸት የጦር ስልጠና የሚሰጥበት ቦታ ላይ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ለ6 ተኛ ዙር ዛሬ የአየር ጥቃት አድርሷል::