የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

@aaculturearttourism1


Addis Ababa Culture, Arts & Tourism bureau

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

22 Oct, 14:41


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቢሮውን የሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ አሠጣጥ እና የቅሬታ አፈታት ስርዓት አፈፃፀም ገመገመ


ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም(ባ ኪ ቱ ቢሮ)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ አሰጣጥ እና የቅሬታ አፈታት ስርዓት አፈፃፀም የከንቲባ ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ዘርፍ ክትትልና ድጋፍ ቡድን ግምገማ አድርጓል።

የክትትልና ድጋፍ ቡድኑ በቢሮው በመገኘት የዘርፉን የ1ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ በተለይም ከመልካም አስተዳደር ምላሽ አሰጣጥ፣ ቅሬታና አቤቱታን መፍትሔ ከመስጠት አኳያ ያለውን አፈፃፀም የቢሮው ከፍተኛ  አመራሮች በተገኙበት በመገምገም ክትትልና ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፤ በቀጣይም ተጠናክረው መሰራት ስለሚገባቸው እና መሻሻል አለባቸው ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ የቃል ግብረ-መልስ ተሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

22 Oct, 13:48


የ2017 በጀት አመት የሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ውይይት ተካሄደ

ጥቅምት 12/2017 ዓ ም (ባኪቱ ቢሮ)
የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከክ/ከተማ ባህል፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት አመራሮች ጋር በ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀምና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት አካሄደ።
በመድረኩ ላይ የቢሮው የመጀመሪያ ሦስት ወራት ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት እንደ ዘርፍ ባለፉት ሶስት ወራት በተደረገው እንቅስቃሴ አበረታች ስራዎች መከናወናቸው የቀረበ ሲሆን ወደ ውይይት ከተገባ በኋላም በመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አሰተያየቶች ቀርበዋል።
በውይይቱ ላይ ተገኝተው መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንደተናገሩት አሁን የተመዘገቡት መልካም ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው በቀጣይም በከተማችን ማህበረሰብ ላይ መሰረታዊ ውጤትና የባህሪ ለውጥ በሚያመጡ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት አለብን ብለዋል።
ቢሮ ኃላፊዋ አያይዘውም በሚቀጥለው 9ወር በሦስቱም ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ገልጸው በተለይም በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ያሉ ቤተ መፅሐፍቶችን ግብዓት በማሟላት፣ ደረጃቸውን ጠብቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ትኩረት አድርገን መስራት አለብን ብለዋል።
በመጨረሻም ቢሮው ‹‹ቱሪዝም ለሰላም›› በሚል መሪ ቃል በ2017 ዓ.ም በየደረጃው የሚከበረውን የአለም የቱሪዝም ቀን አስመልክቶ ከጥቅምት 21 - 23/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጿል።

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

18 Oct, 13:34


በኢኮ ቱሪዝም ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም (ባኪቱ ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል; ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ለጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች በኢኮ ቱሪዝም ዙሪያ በማዕከሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ስልጠናው በዋናነት ትኩረት ያደረገው የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል እንደ ተቋምም ሆነ አስጎብኚ ድርጅት ምን እንደሚጠበቅበትና ቱሪስቶች ወደ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ለጉብኝት ሲመጡ ለምን እንደመጡ፣ ምን እንደሚፈልጉና ዝንባሌያቸውም ጭምር ምን እንደሆነ ማወቅ በሌላ መልኩ ደግሞ ከአስጎብኚው ምን እንደሚጠበቅ ማወቅ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ነው።
ስልጠናው ከአ/አ/ ዩኒቨርስቲ በመጡና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ባላቸው በዶ/ር ኤፍሬም አሰፋ የተሰጠ ሲሆን በገለጻው ላይ ስለ ቱሪዝም ብያኔ፣ ስለ ኢኮ ቱሪዝም ምንነትና ስለ ዕፅዋት ማዕከል አስፈላጊነት በሰፊው አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት እንደሆነ ቢሮው ገልጿል።

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

11 Oct, 13:40


በቅድሚያ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን
እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ,!

በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ የ2024 ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ ሽልማት ከ72 ሀገሮችን እና ከ115 አቻ ከተሞች አስተዳደር ከንቲባዎች መካከል ምርጥ የአመራር ሸልማት በማግኘታችን በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ይህ ያስመዘገብነው ውጤት በከተማችን በተሰሩ እና በህዝባችን ተሳትፎ እና ቅንጅት የተገኘ ውጤት በመሆኑ ለዚህ ውጤት መገኘት አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትን ሁሉ እያመሰገንኩ፣ በደቡብ ኮሪያ 2024 ሴኡል ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ የእውቅና ሸልማት ስለተበረከተልንም እናመሰግናለን።

ለህዝባችን ሰርተን በምናገኘው እውቅና ሁሉ ተመስጋኙ ሁሌም ከጎናችን በመሆን የልማቱ ዘዋሪ እና ተጠቃሚ የሆናችሁ የከተማችን ነዋሪዎች መሆናችሁን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

ይህ ሽልማት ይበልጥ እንድንሰራ ብርታት ይሆነናል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባረክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ