22/05/2017ዓ.ም
ለመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና የተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ እያልን የሚከተሉትን መልዕክቶች እናስተላልፋለን ።
1ኛ. ነገ ታርመው የደረሱ የፈተና የመልስ ወረቀቶችን ከ4፡00 እስከ 6፡30 ለተማሪዎች እንመልሳለን ስለሆነም ተማሪዎች ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የፈተና ወረቀቶቹን በማየት ያመጡትን ውጤት እንድታዩ እናሳስባለን :: 11ኛ ክፍሎች ጠዋት ፈተና ስለሌላቸው የፈተና ወረቀቶችን ለመቀበል 4፡00 ላይ እንዲመጡ እናሳስባለን ::
2ኛ. ዛሬ የተፈተኗቸውን እና ነገ የሚፈተኗቸውን ( ታርመው ያልደረሱትን ) ሰኞ በ26 / 05 /2017 እስከ 6፡ 00 እንመልሳለን አጠቃላይ ከ100 ያመጡትን ውጤት መምህራን የሚያሳዩ ስለሆነ ተከታትሎ ማየትና የውጤት ስህተትና ችግሮች ካሉ ማስተካከል ስላለባቸው ተማሪዎች እንዲገኙ ስንል መልእክታችንን
እናስተላልፍለን :: በእነዚህ ቀናት ሳይገኙ ቀርተው ውጤቴ ስህተት አለበት የሚል አቤቱታ አናስተናግድም ::
3ኛ. ወላጆች የልጆቻችሁን ውጤት Ethio SchoolS . et በማለት ጎግል ላይ በመግባት ከተማሪዎች መታወቂያ ላይ በተቀመጠው student Id በመግባት ኦን ላይን ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን ።
ት/ቤቱ