ጳጉሜን ለቸቸላ
ውድ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች፤ አጋፔ የቤተሰብ በጎ አድራጎት ማህበር ከግቢያችን አቅራቢያ ለሚገኘው የቸቸላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱ የሚጠቅማቸውን የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ከእናንተ ከተማሪዎች በመሰብሰብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ለማድረስ አስቧል።
ለተማሪዎች ከሚያስፈልጉ መማሪያ ቁሳቁሶች በዋናነት፣ ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ እርሳስ፣ ላፒስ፣ ከለር፣ ማስመሪያ ወዘተ… ይገኙበታል። ከነዚህ መካከል ለመስጠት ፍቃደኛ የሆናችሁ ተማሪዎች ግቢያችን ውሰጥ ባዘጋጀናቸው ልዩ ልዩ ቦታዎች እንድታስቀምጡልን በአክብሮት እንጠየቃለን።
# መሰብሰቢያ ቀን ከጳጉሜ 1 እሰከ ጳጉሜ 4
የተዘጋጁ ቦታዎች
# የወርቁ ሱቅ
# ተማሪ ሕብረት
# ፔንታ በራፎች ጋር
# የተለመደ ትብብራችሁን እንዳይለየን ስንል በአክብሮት እንጠየቃለን።
ለበለጠ መረጃ 0929177427 በመደወል ያናግሩን
[email protected]!! ኑ በበጎ ፈቃድ ቤተሰብ እንመስርት !!