Tikvah_University @tikevah_university Channel on Telegram

Tikvah_University

@tikevah_university


Tikvah_University (English)

Welcome to Tikvah_University! Are you looking to expand your knowledge and learn something new every day? Look no further, as Tikvah_University is here to provide you with a virtual platform for learning and growth. Our channel offers a wide range of educational content, including lectures, workshops, and resources on various subjects. Whether you're interested in history, science, literature, or any other topic, Tikvah_University has something to offer for everyone. Who is it? Tikvah_University is a community of curious minds looking to engage in lifelong learning and intellectual development. What is it? Tikvah_University is a Telegram channel dedicated to providing educational content and resources to its subscribers. Join us today and embark on a journey of continuous learning and discovery. Expand your horizons with Tikvah_University and unlock the doors to a world of knowledge waiting to be explored.

Tikvah_University

22 Oct, 05:12


#ማስታወቂያ

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጻል።

በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ስለሚገለጽ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን።


(ትምህርት ሚኒስቴር)

Tikvah_University

18 Oct, 04:52


የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የመማር ብቃት ምዘና ሊያካሒድ ነው፡፡

የመማር ብቃት ምዘናው የሚካሔደው በናሙና በተመረጡ 110 በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ ነው፡፡

የመማር ብቃት ምዘናው በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ የማስተማርያ ቋንቋ በሦስት የትምህርት አይነቶች አርብ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

በመማር ብቃት ምዘና ጥናት የሚገኘው ውጤት በቀጣይ በመማር ማስተማሩ ሒደት ለሚሰሩ ሥራዎች በግብዓትነት የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

Tikvah_University

18 Oct, 04:51


ማስታወቂያ

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና ቱሪዝም ሙያ ዘርፎች ስልጠና በመስጠት የረጅም ዓመታት ልምድ ያለው ብቁ አሰልጣኞችና ደረጃቸውን የጠበቁ የስልጠና ወርክሾፖች ያሉት፤ ብዙዎችን በሥራው ዓለም ስኬታማ እና በቱሪዝምና በሆቴል ሙያ ብቁ ያደረገ አንጋፋ ተቋም ነው።

ኢንስቲትዩቱ ልዩ እና ተመራጭ የሚያደርገው፤

በዘርፉ የበቁና ከፍተኛ ልምድ ያላቸው አሰልጣኞች መኖራቸው፤

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው የሆቴል ሶፍትዌር ማሰልጠናችን፤

ብቁ የሆኑና በገበያው ተፈላጊ የሆኑ ሰልጣኞች ማፍራታችን፤

የስልጠና አሰጣጣችን በተግባር የተደገፈ መሆኑ፤

ሰልጣኞቻችን ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት እንዲኖራቸውና የተግባቦት ክህሎታቸው እንዲጨምር በእንግሊዘኛ፤ በፈረንሳይኛ፤ በአረብኛ ማስልጠናችን፤

በ2017 ዓ.ም በቀን እና በማታ እንዲሁም በቅዳሜና እሁድ ለማሰልጠን ዝግጅቱን አጠናቋል፤ የምንሰጣቸው የስልጠና ዓይነቶች ለቀን መርሃ ግብር ሰልጣኞች በ2015 እና 2016 የ12ኛ መልቀቂያ ፈተና ውጤት የቲክኒክና ሙያ

በደረጃ ሦስት እና አራት

በእንግዳ አቀባበል፣ በቤት አያያዝ፣ በምግብና መጠጥ ቁጥጥር፣ በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ በቱሪስት አስጎብኚ፣ በኬክ እና ዳቦ አሰራር

በደረጃ አምስት

• ክሉናሪ አርት
• በቱር ኦፕሬሽን

በዲግሪ

• ሆቴል ማኔጅመንት
• ቱሪዝም ማኔጅመንት

በማታ እና ቅዳሜና እሁድ ስልጠና ፈላጊዎች

• የትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርስቲ መግቢያ ያወጣውን መስፈርት ያሟሉ፤
• በቴክኒክ ሙያ በደረጃ 4 ሰልጥኖ በሲኦሲ የበቃና በሙያው አንድ ዓመት
• የሥራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
• በማንኛውም ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው፤
• የ8ኛ እና የ12 ክፍል ሰርትፍኬት ዋና እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
• ኢንስቲትዩቱ የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና መውሰድ አለባቸው

የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት

[ለበለጠ መረጃ: ስልክ 0115308121]

Tikvah_University

18 Oct, 04:51


ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታቸውን በተቋሙ ሲከታተሉ የነበሩና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ኦንላይን ማየት እንደሚችሉ ገልጿል፡፡

ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም በዩኒቨርሲቲው የተሰጣቹሁን Username በማስገባት ውጤታቹሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ውጤት ለማየት፦
https://www.slu.edu.et/remedial/index.php?fbclid=IwY2xjawF87TpleHRuA2FlbQIxMQABHRy6t7Qm6QrjVX6dWQXP2Tf7T0FetYe0oQW43itxh_NZSJnmtaVJjTZgQA_aem_MBlSF0PfU8yugqnKRa6sRQ

Tikvah_University

18 Oct, 04:50


ማስታወቂያ ለግል አቅም ማሻሻያ (Private Remedial) ትምህርት ፈላጊዎች:-

ደባርቅ ዩኒቨርስቲ በ2016 ዓ.ም በተሰጠው ሃገር አቀፍ ፈተና 155 ከ 500፣ 186 ከ600፣ 2017 ከ700 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ አመልካቾን በተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች የአቅም መሻሻያ ፕሮገራም ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከጥቅምት 11-29/ 2017 ዓ.ም ማመልከት እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል።

Tikvah_University

12 Oct, 16:36


#AAU

ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ውጪ የምትመጡ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6/2017 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የማደሪያ አገልግሎት ለተሰጣችሁ ብርድ ልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ አለባችሁ፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል https://portal.aau.edu.et/NewStudent/DormitoryPlacement በመግባት ማየት ትችላላችሁ።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በመርካቶ፣ በላምበረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን ገልጿል።

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች እና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን፤ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ማክሰኞ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

Tikvah_University

11 Oct, 16:59


#TVET

ለኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ነባር የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ የመደበኛ መርሀ ግብር ሰልጣኞች በሙሉ

የ2017 ዓ.ም ስልጠና ምዝገባ የሚካሄደው ጥቅምት 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተቋሙ ሪጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ክፍል በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

[የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት]

Tikvah_University

11 Oct, 16:58


#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ከነገ ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ያከናውናል።

ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ለተማሪዎች ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በአዲስ አበባ መርካቶ እና ቃሊቲ መናኸርያዎች እንዲሁም በአዳማ ፍራንኮ አካባቢ (ፖስታ ቤት) እና በሚጊራ መናኸርያ በመገኘት የትራንስፖርት አገልግሎቱን መጠቀም ትችላላችሁ ተብሏል።

@tikevah_university

Tikvah_University

10 Oct, 08:55


HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ለመከታተል የአመልካቾች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

በዚህም የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ መስከረም 30/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

https://application.haramaya.edu.et በመጠቀም የማመልከቻ ቅፁን ኦንላይን መሙላት ይቻላል ተብሏል።

አመልካቾች ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፋችሁና በሚያመለክቱበት ትምህርት ክፍል የሚሰጥን ፈተና ማለፍ ይጠበቅባችሀኋል።

Tikvah_University

09 Oct, 08:26


በፀጥታ ችግር ምክንያት በአማራ ክልል የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ነባር መደበኛ ተማሪዎችን የሚቀበሉበትን ጊዜ ማራዘማቸው ተሰማ፡፡

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢው ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎችን በተፈለገው ጊዜ መቀበል አለመቻሉን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚ ፕሮግራም ዳይሬክተር ሰዋለም ሙሌ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በደባርቅ አካባቢ ከመስረከም 1 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የፀጥታ ችግር እንደነበረና በዚህም ምክንያት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን የሚበቀልበት ጊዜ መራዘሙን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተለይ የጎንደር እና የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ቅበላ ጊዜን ታሳቢ አድርጎ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የገለፁት ኃላፊው፤ ከሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2017 የትምህርት ዘመን 2,500 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል ዕቅድ መያዙን አስረድተዋል፡፡

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ምዝገባ ከመስከረም 28 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ለማከናወን ጥሪ ያደረገ ቢሆንም፤ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ባለመጠናቃቸው የቅበላ ጊዜው መራዘሙን ገልጿል፡፡

ሪፖርተር የተማሪዎችን ቅበላ በተመለከተ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎችን በስልክ ለማነጋገር ጥረት ቢያደረግም ምላሽ አላገኘም፡፡

የወልድያ እና የወሎ ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊዎች በአካባቢው የፀጥታ ችግር ባለመኖሩ፣ መደበኛ ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተማር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ #ሪፖርተር

Tikvah_University

07 Oct, 10:46


#ጥቆማ

በሁዋዌ የተማሪዎች የICT ውድድር 2024-2025 ይሳተፉ!

በሁዋዌ ተማሪዎች የICT ውድድር (Huawei ICT Competition 2024-2025 for Northern Africa) ለመሳተፍ በቅድሚያ የሁዋዌ ICT አካዳሚ አባል ይሁኑ።

የአካዳሚው አባል ለመሆን ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👇
https://e.huawei.com/en/talent/portal/#/

በሁዋዌ የICT ውድድር 2024-2025 ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👇
https://e.huawei.com/en/talent/#/ict-academy/ict-competition/regional-competition?zoneCode=026902&zoneId=98269642&compId=85131998&divisionName=North%20Africa&type=C001&isCollectGender=N&enrollmentDeadline=undefined&compTotalApplicantCount=209

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦
ኅዳር 1/2017 ዓ.ም

የማጣሪያ ፈተና የሚሰጠው፦
ኅዳር 6/2017 ዓ.ም

የፍፃሜ ውድድር፦
ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም

Tikvah_University

07 Oct, 10:30


#BoranaUniversity

ቦረና ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዘርፎች በመደበኛው እና በተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚህም መንግስት ያስቀመጣቸውን የመመዝገቢያ መስፈርቶች የምታሟሉ በሙሉ እስከ ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም ድረስ በተቋሙ ዋና ሬጅስትራር በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

@tikevah_university

Tikvah_University

23 Sep, 16:59


#DebreBerhanUniversity

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 29 እና 30/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

በቅጣት የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ሲሆን፤ ትምህርት ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

Tikvah_University

11 Sep, 20:20


#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናት መስከረም 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀመርበት ቀን መስከረም 23/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቅጣት ለመመዝገብ 👇
መስከረም 23 እና 24/2017 ዓ.ም

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikevah_university

Tikvah_University

11 Sep, 20:19


#HarariEducationBureau

በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተሻለ ውጤት በሀረሪ ክልል መመዝገቡን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

በሀረሪ ክልል ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪ ማሳለፍ መቻላቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ነገዎ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በክልሉ ሁለት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ሳያሳልፉ መቅረታቸውን ያስታወሱት የቢሮው ኃላፊ፤ ዘንድሮ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን አሳልፈዋል።

በ2015 ዓ.ም 7.1 በመቶ ተማሪዎች ማለፊያ ውጤት አስመዝግበው የነበረ ሲሆን፤ በ2016 ዓ.ም 13.3 በመቶ ተማሪዎች በክልሉ ማለፍ መቻላቸውን ጠቁመዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡ ከፍተኛ ውጤቶች መካከል አራቱ በሀረሪ ክልል የተመዘገቡ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ የተመዘገበው ውጤት አጥጋቢ አይደለም ያሉት ኃላፊው፤ በ2017 የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የበለጠ ይሠራል ብለዋል።

@tikevah_university

Tikvah_University

11 Sep, 20:19


#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ለቅድመ ምረቃ ትምህርት በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ እና በግል ከፍለዉ ለሚማሩ እንዲሁም በማታ በተከታታይ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲዉ ድረ ገጾች (https://aau.edu.et ወይም https://portal.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

• የመመዝገቢያ ቀናት ከማክሰኞ ጳጉሜ 05/ 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 08/ 2017 ዓ.ም ድረስ
• የዩኒቨርሲቲዉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት በዩኒቨርሲቲዉ ማህበራዊ ሚዲያ እና ድረ ገጾች ላይ ይገለጻል ።

(አ.አ.ዩ ሬጅስትራር)

🗝 @tikevah_university

Tikvah_University

10 Sep, 21:29


#ኢትዮጵያ2017

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን !

🌼🌼🌼🌼🌼

Tikvah_University

10 Sep, 04:57


ይህን step ተከትላቹህ ውጤት መመልከት ትችላላችሁ 👇

https://Verify.eaes.et/temporary/FNLNMN=ID

🎯 FN ማለት ከራሳችሁ ስም ላይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ፊደል
🎯 LNከአያታችሁ ስም ላይ የመጀመሪያው ሁለት ፊደል
🎯 MN ከአባታችሁ ስም ላይ የመጀመሪያ ሁለት ፊደል አድርጋችሁ iD ላይ reg number መፃፍ

ማሳሰቢያ 🔥

1 ቅም ተከተል እንዳትሳሳቱ ከስማችሁ ከአያታችሁ ስም ከዛ ከአባታችሁ ሁለት ፊደል
2 ሁሉ በcapital መሆኑን እንዳትረሱ


Use #VPN

Tikvah_University

10 Sep, 04:56


Name: Yonas nuguse
Total: 675/700

Bravo 👏🏾

Tikvah_University

09 Sep, 17:13


ውጤት : የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል።

በሚከተሉት አማራጮች ውጤታችሁን ተመልከቱ፦

► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

► በቴሌግራም ቦት 👉 https://t.me/EAESbot

ከውጤት መግለጫ ፖርታል እና ቴሌግራም ቦት ላይ ጊዜያዊ ሰርቲፊኬት ማውረድና ማተም እንደምትችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በውጤት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ካላቸው ወደ አገልግሎቱ ቢሮ በአካል መሔድ ሳያስፈልጋችሁ ከSMS በስተቀር በውጤት መግለጫ አማራጮቹ ላይ Compliant የሚለውን በመጫን የቅሬታቸውን ዓይነት በተዘጋጀ የቅሬታ ፎርም ላይ በትክክል በመሙላት ማቅረብ ትችላላችሁ።

አገልግሎቱ በቅሬታችሁ ላይ ምላሽ ቅሬታቸውን ባቀረቡበት ተመሳሳይ አድራሻ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።


Via Tikvah