Последние посты Sheger Times Media️ (@shegrtimesmedia) в Telegram

Посты канала Sheger Times Media️

Sheger Times Media️
በማትሪክስ ኢንተርቴይመንትና የፕሬስ ስራዎች ኃ.የተ.የግ.ማ እየታተመ በየ15 ቀኑ ለአንባቢያን የሚደርሰው የ #ሸገር_ታይምስ መፅሄት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
4,614 подписчиков
6,689 фото
112 видео
Последнее обновление 01.03.2025 03:50

Похожие каналы

AL JAZEERA ENGLISH
18,235 подписчиков
Addis Ababa Police Official
12,731 подписчиков
Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
9,056 подписчиков

Последний контент, опубликованный в Sheger Times Media️ на Telegram


🆕" የሀገር ችግር የሚፈታው በእድሜ አይደለም!"

➡️“ቃሉን በተግባር ኖሮ ራሱንም፤ ሃገሩንም ያስከበረው መሪ!
********

በአፍሪካ በእድሜ ትንሹ የሆነው የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ወደ ስልጣን መጥቶ ቃለ መሀላ በፈፀመ ጊዜ “ቃሉን ወደ ተግባር የመለወጥ አቅምና በቂ ተሞክሮ አለው ወይ?” የሚል የጥርጣሬ አስተያየት ይሰጡ የነበሩ ጥቂት አልነበሩም፡፡

ከእነዚህ መካከል ለመፈንቅለ መንግስት የቋመጡ ወታደራዊ መኮንኖች ይገኙበት ነበር፡፡

ይህን ቀድሞ ከግንዛቤ ያስገባው የነበረው ትራዎሬ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችንና የካቢኔ አባላትን ሰብስቦ “እድሜ ቁጥር ነው፤ የቡርኪናፋሶን ችግር መፍታት የሚቻለው በእድሜ መብዛትና ማነስ አይደለም…” ብሎአቸው ነበር፡፡

ይህን ቃሉንም ቢሆን አምነው ያልተቀበሉና ቦታው ይገባናል የሚል ስሜት አድሮባቸው የነበሩ የቀድሞው ብልሹ ስርዓት አሸርጋጅ የነበሩ አዛውንት መኮንኖች ወደ ስልጣን ከመጣ ጥቂት ወራት እንዳስቆጠረ መፈንቅለ መንግስት ሞከሩበት…

ሙሉ ታሪኩን ይመልከቱት…
⬇️⬇️⬇️
https://youtu.be/IBnfhza0gBk?si=1GhtSBPxfhn9ufAz

‼️ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ተጨማሪ ጦር አስጠጋች

የኬንያ መንግስት በደቡብ ኢትዮጵያ በኩል ወደሚያዋስነው ድንበር ነው ተጨማሪ ጦር እንዲሰማራ ያዘዘው፡፡

እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ ባሳለፍነው አርብ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ እና በጎረቤት አገር ኬንያ ቱርካና ካውንቲ ማኅበረሰቦች መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካቶች ከተገደሉ በኋላ ነው ተጨማሪ ጦር እንዲሰማራ የተወሰነው፡፡

የኬንያ ካቢኔ ጉዳዮች ሚንስትር ኪፕቹምባ ሙርኮሜን እንዳሉት ከሆነ “በአካባቢው አሁን ላይ ሰላም ሰፍኗል፡፡ የኬንያ ፖሊሲ አመራሮችም ውጥረቱን ለማርገብ እና ዘላቂ መረጋጋት ለማስፈን ሀላፊነቱን ወስደው እየተሰሩ ነው፡፡”

ሙርኮሜ አክለውም “ሁለቱን ማህበረሰቦች ለማስታረቅ የኬንያ መንግስት ከኢትዮጵያ አቻው ጋር ምክክር አደርጓል” በማለት “ህዝባችን ሁልጊዜም ደህንነቱ እንዲጠበቅ ማናቸውንም ነገር እናደርጋለን” ነው ያሉት፡፡

ሮይተርስ የኬንያ ቱርካና ካውንቲን ፖሊስ ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ በኦሞ ወንዝ አቅራቢያ በተቀሰቀሰው የሁለቱ ማህበረሰብ ግጭት ሳቢያ እስካሁን 22 ኬንያዊያን የገቡበት አልታወቀም፡፡
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

🆕“ማንም አያቆመንም!” አሲሚ ጎይታ
*********
የማሊው አብዮተኛ መሪ አሲሚ ጎይታ በሁለት ዓመት ውስጥ በሀገሪቷ ውስጥ ተዓምር የሚባሉ ለውጦችን አሳይቷል፡፡


አሁን ደግሞ ከሩሲያ ጋር በሀገሪቱ የኒውክሌር ማመንጫ ግንባታን ማስጀመሩ የዓለም ትኩረት የሳበ መነጋጋሪያ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ሮዛተም የተሰኘውና የሩሲያን ከፍተኛ የኒውክሌር ፕሮጀክቶችን የሚያስተዳድረውና ደህንነታቸውን የሚቆጣጠረው ተቋምም ወደ ማሊ በመግባት በዚህ የኒውክሌር ፕሮጀክት ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎችና ሰራተኞች ከወዲሁ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት በገዛ ሀገራቸው የበይ ተመልካች ሆነውና አንገታቸውን ደፍተው የነበሩ ማሊያውያን አሁን በመሪያቸውና በሀገራቸው ተስፋ አድርገው ቀና ብለው መራመድም ጀምረዋል….

👀ሙሉ ቪዲዮውን ይመልከቱት..
⬇️
https://youtu.be/f4YYZv7bF0U?si=SFQFxHsqO57crntV

🆕መቻል 21 ሚሊየን ብር ሲዳማ ቡና 18 ሚሊየን ብር ተቀጡ
🥾🥾🥾
የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ተሳታፊ የሆነው መቻል እግር ኳስ ክለብ የ21 ሚሊየን ብር እንዲሁም ሲዳማ ቡና የ18 ሚሊየን ብር ቅጣት የተላለፈባቸው መሆኑን የሊጉ የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ÷በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች የክፍያ ሥርዓት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2016 አንቀጽ 7 በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት በ4 ክለቦች እና በ15 ተጫዋቾች ላይ ምርመራ አካሂዷል፡፡

በምርመራውም ክለቦቹ የቅድመ ክፍያ (በሶስተኛ ወገን) በመክፈላቸው እና ተጫዋቾቹ በመቀበላቸው በአንቀጽ 5 የተከለከሉ ተግባራት ስር የተቀመጡትን ድንጋጌዎች የጣሱ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በመቻል እግር ኳስ ክለብ በተደረገው ምርመራ የክለቡ 7 ተጫዋቾች የቅደመ ክፍያ ገንዘብ መቀበላቸው የተረጋገጠ ሲሆን÷በዚህም ክለቡ በእያንዳንዱ ተጫዋች የ3 ሚሊየን ብር በአጠቃላይ የ21 ሚሊየን ብር ቅጣት ተላልፎበታል፡፡

ከክለቡ በተጨማሪ ተጫዋቾች የ200 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍሉ እና የከፈሉበትን ደረሰኝ በሰባት ቀናት ውስጥ ለአክሲዮን ማህበሩ እንዲያሳውቁ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

በተመሳሳይ በሲዳማ ቡና እግር ኳስ ቡድን በተደረገው ምርመራ 6 ተጫዋቾች የቅድመ ክፍያ ገንዘብ ከአክሲዮን ማህበሩ መመሪያ ውጭ መቀበላቸው የተረጋገጠ ሲሆን÷ ክለቡ በአጠቃላይ የ18 ሚሊየን ብር ቅጣት ተላልፎበታል፡፡

በተጨማሪ ስድስቱ ተጫዋቾች የ200 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍሉ እና የከፈሉበትን ደረሰኝ በሰባት ቀናት ውስጥ ለአክሲዮን ማህበሩ እንዲያሳውቁ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡

በሌላ በኩል የመቐለ 70 እንደርታ እና ሃዋሳ ከተማ አንድ አንድ ተጫዋቾች የቅድመ ክፍያ ገንዘብ በመቀበላቸው እያንዳንዳቸው የ3 ሚሊየን ብር የገንዘብ ቅጣት የተላለፈባቸው ሲሆን÷በተጫዋቾቹ ላይም የ200 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፏል፡፡

በኮሚቴው ቅጣት የተጣለባቸው ቡድኖች ቅጣታቸውን ጨርሰው የክፍያ ደረሰኛቸውን ለአክሲዮን ማህበሩ እስከሚያሳውቁ ድረስ ከውድድር ታግደው እንደሚቆዩ የአክሲዮን ማህበሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

🆕“ማንም አያቆመንም!” አሲሚ ጎይታ
*************
የማሊው አብዮተኛ መሪ አሲሚ ጎይታ በሁለት ዓመት ውስጥ በሀገሪቷ ውስጥ ተዓምር የሚባሉ ለውጦችን አሳይቷል፡፡

አሁን ደግሞ ከሩሲያ ጋር በሀገሪቱ የኒውክሌር ማመንጫ ግንባታን ማስጀመሩ የዓለም ትኩረት የሳበ መነጋጋሪያ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ሮዛተም የተሰኘውና የሩሲያን ከፍተኛ የኒውክሌር ፕሮጀክቶችን የሚያስተዳድረውና ደህንነታቸውን የሚቆጣጠረው ተቋምም ወደ ማሊ በመግባት በዚህ የኒውክሌር ፕሮጀክት ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎችና ሰራተኞች ከወዲሁ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት በገዛ ሀገራቸው የበይ ተመልካች ሆነውና አንገታቸውን ደፍተው የነበሩ ማሊያውያን አሁን በመሪያቸውና በሀገራቸው ተስፋ አድርገው ቀና ብለው መራመድም ጀምረዋል….

👀ሙሉ ቪዲዮውን ይመልከቱት..
⬇️
https://youtu.be/f4YYZv7bF0U?si=SFQFxHsqO57crntV

💯ባሲሩ ዲዮማ ኒፋዬ ይሰኛል… 44 ዓመቱ ነው፡፡

ከእስር ቤት በወጣ በማግስቱ በሀገሪቱ በሚከናወነው ምርጫ ለመወዳደር በግሉ ተመዘገበ፡፡


ከቀናት በኋላ በተከናወነው ምርጫም በከፍተኛ ድምፅ አሸነፈ፡፡ ከእስር ቤት ከወጣ ከ15 ቀን በኋላም የሀገሪቱ መሪ ሆኖ ተመረጠ፡፡ራዕዩ ትልቅ ነው፣ ተግባሮቹ ጠንካራ ናቸው፡፡

አፍሪካ የምዕራባውያን ሰለባ የመሆኗ ነገር ቆራጥ መሪ ባላቸው ሀገራት ዘንድ እየቀረና እያከተመ ነው፡፡ በነትራዎሬ የተጀመረው የባርነት ቀንበርን አሸቀንጥሮ የመጣል ተግባር አሁን እሱ የሚመራት ሀገር ላይ ደርሷል፡፡

እሱም እንደ ነትራዎሬ ፈረንሳይንና በሀገሪቷ ያላትን ጦር በቀጭን ትዕዛዝ ከሀገሩ ጠራርጎ አባሯል…
ሙሉ ታሪኩን ይመልከቱት
⬇️⬇️
https://youtu.be/PapcJpMbH58?si=GfjQPAkq3laN_rL7

🟢44 ዓመቱ ነው፡፡ ከእስር ቤት በወጣ በማግስቱ በሀገሪቱ በሚከናወነው ምርጫ ለመወዳደር በግሉ ተመዘገበ፡፡

ከቀናት በኋላ በተከናወነው ምርጫም በከፍተኛ ድምፅ አሸነፈ፡፡ ከእስር ቤት ከወጣ ከ15 ቀን በኋላም የሀገሪቱ መሪ ሆኖ ተመረጠ፡፡ራዕዩ ትልቅ ነው፣ ተግባሮቹ ጠንካራ ናቸው፡፡

አፍሪካ የምዕራባውያን ሰለባ የመሆኗ ነገር ቆራጥ መሪ ባላቸው ሀገራት ዘንድ እየቀረና እያከተመ ነው፡፡ በነትራዎሬ የተጀመረው የባርነት ቀንበርን አሸቀንጥሮ የመጣል ተግባር አሁን እሱ የሚመራት ሀገር ላይ ደርሷል፡፡

እሱም እንደ ነትራዎሬ ፈረንሳይንና በሀገሪቷ ያላትን ጦር በቀጭን ትዕዛዝ ከሀገሩ ጠራርጎ አባሯል…ባሲሩ ዲዮማ ኒፋዬ!

ሙሉ ታሪኩን ይመልከቱት
⬇️⬇️
https://youtu.be/PapcJpMbH58?si=GfjQPAkq3laN_rL7

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የጣሪያና ግድግዳ ግብር ለማስከፈል ተግባራዊ ያደረገው መመርያ “የሕግ መሠረት የለውም” ብሎ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላሳለፈው ውሳኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “በሚገባ ሥልጣን አለው” ሲል ምላሽ ሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ በከተማው ፋይናንስ ቢሮ በኩል ተግባራዊ የተደረገው፣ የጣሪያና የግድግዳ ግብር መመርያ አወጣጥ “መርሆዎችን ያልተከተለ ነው” ተብሎ በፍርድ ቤት መሻሩን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት “ከሕጉ አንፃር ፍርድ ቤት ወስኗል፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤት ሁሌ ትክክል ቢወስን ኖሮ፣ ይግባኝም ቀጥሎ ያሉ ክርክሮችም ባልኖሩ። ነገር ግን የከተማ አስተዳደሩ በሚገባ ሥልጣን አለው፤” በማለት ማብራሪያ መስጠታቸውን ሪፖርተር በዛሬ ዕትሙ አስነብቧል፡፡

የጣሪያና ግድግዳ ግብር ተግባራዊ በመደረጉ ምክንያት እናት ፓርቲ “ሕጋዊ መሠረት የሌለው ነው” በማለት በከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ ላይ ክስ መሥርቶ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ጉዳዩን ሲመለከተው የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጣሪያና የግድግዳ ግብር ተግባራዊ እንዳይደረግ ቢወስንም፣ የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ ማክሰኞ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ግብር ከፋዮችን ያለ ቅጣትና ወለድ የሚያስከፍልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ መሆኑን በመጥቀስ፣ ግብሩን እንዲከፍሉ ማሳሰቢያ ማውጣቱንና በዚህም መነሻነት ነዋሪው ”መፈጸም ያለበት የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ወይስ የገቢዎች ቢሮ ማሳሰቢያ?” የሚል ጥያቄ እያነሳ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል ።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ረቡዕ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም. አራተኛ የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት፣ የምክር ቤቱ አባል ሲሳይ መንግሥቴ (ዶ/ር) ጉዳዩን አስመልክቶ ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም “ከቤት፣ የጣሪያና ግድግዳ ግብር ጋር ተያይዞ ምጣኔ (Rate) አልጨመርንም፣ ሠንጠረዡም በአንድ ካሬ ሜትር ተሠልቶ የሚሰጠው ምጣኔ ያው ነው። ለምክር ቤቱም ይህንን ጥያቄ ለሚጠይቁ የከተማችን ነዋሪዎችም ግልጽ እንዲሆን የተቀየረው የኪራይ መጠኑ ነው፤”ብለዋል።

በተጨማሪም ከንቲባዋ በ1968 ዓ.ም. ይህ ሕግ ሲወጣ አንድ ካሬ ይከራይበት የነበረው ዋጋ ዛሬ ላይ አይከራይበትም ብለው፣ ‹‹”ያኔ አሥር ብር የነበረው ዛሬ 300 ወይም አምስት መቶ ወይም አንድ ሺሕ ብር ደርሷል። የአንድ ካሬ ግብር ክፍያ የሚሰላበት መጠን ያው ነው፣ ነገር ግን ቤቱ የሚከራይበት ገንዘብ መጠን ስለተቀየረ ሥሌቱን አሁን በተቀየረው የገንዘብ መጠን ብቻ ነው ያደረግነው። ይኼ ነው ለውጡ ሌላ ለውጥ የለም፤”ሲሉ ተናግረዋል።

ወ/ሮ አዳነች፣ “በየጊዜው የማይከፍሉ የግብር ሥርዓቱ ውስጥ ያልነበሩ ብዙ ናቸው” ያሉ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ወደ 800,000 የሚጠጉ ሕንፃዎችና ቤቶች እንዳሉ ጠቅሰው፣ ግብር የሚከፍሉት ግን 120,000 ብቻ ነበሩ ሲሉ ወቅሰዋል።
ሙሉ ዘገባውን በሊንኩ ያገኙታል።
ℹ️https://www.ethiopianreporter.com/138636/
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

‼️በአዋሽ ፈንታሌ እየጨመረ የመጣው የሚቴን ጋዝ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ሊያስከትል ይችላል ተባለ
*******
በአዋሽ ፈንታሌ ከጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የወጣው የሚቴን ጋዝ መጠን እየጨመረ መሆኑንና ይህም እሳተ ገሞራ ሊያስከትል እንደሚችል ጤናዓለም አየነው (ፕ/ር) ገለጹ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነምድር መምህር ጤናዓለም አየነው እንደገለጹት፤ ላለፉት ሁለት ወራት በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ዙሪያ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ የሚታወስ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጥ እና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የተያያዙ ናቸው ያሉት ፕሮፌሰር ጤናዓለም፤ በኢትዮጵያ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ፍንዳታ ከመከሰቱ በፊት የሚፈጠሩ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ነው ብለዋል።

በአብዛኛው ሙቅ ውሃ ከመሬት አየገነፈለ የሚወጣ ሲሆን፤ አልፎ አልፎ ደግሞ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ እንደተከሰተው የሚተኑ ጋዞች እንደሚወጡ አስታውቀዋል።

በአዋሽ ፈንታሌ ከጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚቲን ጋዝ እየወጣ መሆኑን ገልጸው፤ የሚወጣው የጋዝ መጠን ከጊዜ ወደ ጌዜ እየጨመረ መሆኑን አመላክተዋል።

የሚቲን ጋዝ የሚከሰተው ከመሬት ውስጥ የቀለጠው አለት ከውሃ ጋር ሲገናኝ፣ ጥልቅ ከሆነ ቦታ የኬሚካል እንቅስቃሴ ሲኖርና በሌሎች መንገዶች መሆኑን አስረድተዋል።

የሚቲን ጋዝ ከእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ከሚወጡ የጋዝ አይነቶች አንዱ መሆኑን ማስታወቃቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

🟢አትሌት አንችንአሉ ደሴ ሲቪላ የሴቶች ማራቶን ውድድር አሸነፈች
***
በስፔን ሲቪላ በተካሄደው የሴቶች ማራቶን አትሌት አንችንአሉ ደሴ ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ በማጠናቀቅ በአንደኝነት አሸንፋለች።

👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia