أحدث المنشورات من Sheger Times Media️ (@shegrtimesmedia) على Telegram

منشورات Sheger Times Media️ على Telegram

Sheger Times Media️
በማትሪክስ ኢንተርቴይመንትና የፕሬስ ስራዎች ኃ.የተ.የግ.ማ እየታተመ በየ15 ቀኑ ለአንባቢያን የሚደርሰው የ #ሸገር_ታይምስ መፅሄት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
4,614 مشترك
6,689 صورة
112 فيديو
آخر تحديث 01.03.2025 03:50

قنوات مشابهة

Ethiopian News Agency
19,843 مشترك
ትንግርቱ
10,919 مشترك

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة Sheger Times Media️ على Telegram


“ሩቅ አስበን በትንሹ ጀምረናል.!”
**********
ይህ ምስል ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና የሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሀሴን ሼክ ሞሀመድ በሞቋዲሹ ባሀረ ገብ መሬት የህንድ ውቂያኖስን ሲጎበኙ የሚያሳይ ነው፡፡

ዛሬ በሶማሊያ መዲና ሞጋዲሹ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉት አብይ - ከጎበኟቸው ስፍራዎች መካከል በተለምዶ “Somalia Beach” እየተባለ የሚጠራው የባህር ዳርቻ ይገኝበታል፡፡

በቀይ ባህር አሊያም በህንድ ውቂያኖስ ለኢትዮጵያ ወደብ ብቻ ሳይሆን የባህር በር ለማጎናፀፍ እየሰሩ እንደሆነ የሚናገሩት አብይ - ውቡን ህንድ ውቂያኖስ በቅርበት ጎብኝተውታል - በሶማሊያው መሪ ሼክ ሞሀመድ አማካኝነት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለአንድ ዓመት የቆየውን ውዝግባቸውን በድርድር ከፈቱ በኋላ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ለይፋዊ ጉብኝት ሞቋዲሾ የተገኙት፡፡

ሶማሊያ ከአንደ አመት በፊት ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የባህር በር አጠቃቀም ስምምነት ሉአላዊነቴን የሚጥስ ነው በማለት ስትቃም እና የጦርነት ነጋሪት ስትመታ ቆይታለች፡፡ “የአንካራው ዲክላሬሽን” ግን ሞቃዲሾ እና አዲስ አበባ በዚህ መልኩ ወዳጅነታቸው እንዲታደስ ምክንያት ሆኗል፡፡

ለዚህም ይመስላል የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊው ሳንዶካን ደበበ “እሩቅ አስበን ጀምረናል - የኢትዮጵያ መፃኢ ዘመን ብሩህ ነው” ሲሉ በኤክስ ገፃቸው የፃፉት፡፡
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

‼️የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 7 ተከሳሾች በሙስና ወንጀል ጥፍተኛ ተባሉ

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጫላ ዋታን (ዶ/ር) ጨምሮ ሰባት ተከሳሾች በቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል ጥፍተኛ ተባሉ።

ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተከሳሾች በቀረበባቸው ሁለት ከባድ የሙስና ወንጀል ጥፍተኛ የተባሉ ሲሆን÷ 7ኛ ተከሳሽ ደግሞ በቀረበበት አንድ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ መባሉ ተመላክቷል፡፡

ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጫላ ዋታ (ዶ/ር)፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ታምሩ ኦኖሌ (ዶ/ር)፣ የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ሮባ ደንቢ (ዶ/ር)፣ የቢዝነስና ተቋማዊ ልማት ም/ፕሬዚዳንት አብርሐም ባያብል (ኢ/ር)፣ የግዢ ዳይሬክተር አቶ ሊበይ ገልገሎ፣ የፋይናንስ ዳይሬክተር አቶ ቦሩ ህርቦዬ፣ የዩኒቨርሲቲው መምህርና የቢኤች ዩ አማካሪ ለታ ድሪባን ናቸው፡፡

በዚህም ከ1ኛ እስከ 6ኛ ተራ ቁጥር ያሉት ተከሳሾች የዩኒቨርሲቲው አመራርና የማኔጅመንት አባል በመሆን ሲሰሩ የመንግስት ግዢ አዋጅን በመተላለፍ በ2012 ዓ.ም በያዙት ቃለ ጉባዔ መሰረት ሕግን ባልተከተለ መልኩ ያለአግባብ ቢኤች ዩ ለተባለ አማካሪ ግዢው በቀጥታ እንዲፈጸም በማኔጅመንት ውሳኔ ማስተላለፋቸው ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ውል ሲዋዋል ዩኒቨርሲቲውን በመወከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት 1ኛ ተከሳሽ ውል ሰጪ ሆነው 7ኛ ተከሳሽ ውሉን በመፈረም በ5ኛ ተከሳሽ ትዕዛዝ መሰረት በ1ኛ ተከሳሽ ስም ለተመዘገበው አማካሪ ድርጅት ያለአግባብ ክፍያ እንዲፈጸም ማድረጉን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል።

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በመንግስት ላይ ከ196 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ ከባድ የሙስና ክስ ቀርቦባቸው ነበር፡፡

በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ከሕግ ውጭ በሚሊየን በሚቆጠር ከደረሰው ጉዳት ውስጥ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው ተመላክቷል፡፡

2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በተመሳሳይ ከ500 ሺህ ብር በላይ ለግል ጥቅም ማዋላቸው የተመላከተ ሲሆን÷ 4ኛ ተከሳሽ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ፣ 5ኛ ተከሳሽ ከ99 ሺህ ብር በላይ፣ 6ኛ ተከሳሽ ከ400 ሺህ ብር በላይ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ በአጠቃላይ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው በክሱ ተብራርቷል።

ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ ክደው በመከራከራቸው ዐቃቤ ሕግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተከሳሾች በሁለት ክሶች የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በተጨማሪም 7ኛ ተከሳሽ በአንድ ክስ ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን÷ ፍርድ ቤቱ ከ8ኛ እስከ 17ኛ ያሉ ተከሳሾች ላይ ደግሞ በሌሉበት የጥፋተኝነት ውሳኔ በማስተላለፍ የቅጣት አስተያየት ለመቀበል ለመጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ኤፍቢሲ
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

👀🆕አነጋጋሪዎቹ የሳውዲ ስቴዲየሞች!
*********
ለወትሮው በሃይማኖታዊ ጉዞ መዳረሻነትና የእስልምና እምነት ቅዱስ ከተማ መቀመጫ በመሆኗ የምትታወቀው ሳውዲ በየግዜው ማስገረምና ማነጋገሯን ቀጥላለች፡፡

ከወረቀት አያልፉም የተባሉና ህልም የመሰሉ ፕሮጀክቶችን እያቀላጠፈች የምትገኘው ሳውዲ “አይሆኑም አይሳኩም” የተባለላቸው ግዙፍ ግንባታዎች መልክ እየያዙ ከሰፊው የበረሃ አሸዋ ውስጥ በግርማ አንገታቸውን ቀና ሲያደርጉ እየታዩ ነው፡፡

ሀገሪቱ የአለም ዋንጫን እንደምታስተናግድ ከታወቀ በኋላ በስፖርቱ ዘርፍ አጃኢብ የሚያሰኙ፣አስደማሚ፣ ህልም የሚመስሉ የስቴዲየም ፕሮጀክቶችን ይፋ አርጋለች፡፡

አስገራሚው ነገር የተመደበላቸው ገንዘብ አስደንጋጭ ከሆኑት ተዓምረኛ የስቴዲየም ግንባታዎች በተጨማሪ ዓለም ዋንጫውን ለመታደም ለሚመጡ እንግዶች አገልግሎት የሚሰጡ ከ128 ሺ በላይ ቅንጡ የሆኑ ሆቴሎች ለመገንባት ሽር ጉድ እያለች ትገኛለች፡፡
⬇️⬇️⬇️
https://youtu.be/BlHKdPTnV6Q?si=9c67yOsnKmNev7Hq

🔴ከመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ ኑሮውን በዋሻ ያደረገው…

🟢ግለሰቡ 50 ሺህ ዜጎችን ከጨረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለጥቂት የተረፈ ነው
**************
ከሁለት ዓመት በፊት በቱርክ ባጋጠመ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት 50 ሺህ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በደቡባዊ ቱርክ ባጋጠመው በዚህ አደጋ ምክንያት ከነቤተሰቡ በተዓምር የተረፈው አሊ ቦዞግላን አንዱ ነበር።

ይህ ሰው ይህን ሰቅጣጭ አደጋ ካየሁ በኋላ ዳግም ወደ መኖሪያ ቤት አልገባም ብሎ በዋሻ ውስጥ እየኖረ ይገኛል።

በዋሻ ውስጥ ኑሮ ተመችቶኛል የሚለው ይህ ሰው እየኖረበት ያለው ዋሻ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎችን ተቋቁሞ ቆይቷል ብሏል።

የሶስት ልጆች አባት የሆነው አሊ ከእንግዲህ ሰው ሰራሽ ቤት ውስጥ የመኖር ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል።

ሚስት እና ልጆቹ እሱን ተከትለው ወደ ዋሻው የመምጣት ፍላጎት ስለሌላቸው ብቻውን በዋሻ ውስጥ እየኖረ መሆኑን ተናግሯል።

በዋሻ ውስጥ ለብቻ መኖር ከባድ ቢሆንም ደስተኛ ህይወት ስመራ ሁለት ዓመት ሆኖኛል ማለቱን የቱርኩ ሀበር ሚዲያን ዋቢ አርጎ አል አይን አስነብቧል።

ከሁለት ዓመት በፊት የካቲት ወር ላይ ያጋጠመው ይህ አደጋ ደቡባዊ ቱርክን እና ሰሜናዊ ሶሪያ አካባቢዎችን ጎድቷል።

ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ደረጃውን ያልጠበቁ ህንጻዎች እንዲገነቡ አድርገዋል ያለቻቸውን ባለ ንብረቶች እና ባለሙያዎችን ማሰሯ ይታወሳል።

በ20 ዓመት ታሪክ ውስጥ በገዳይነቱ አንደኛ ነው የተባለው ይህ አደጋ ከ55 ሺህ በላይ ሶሪያዊያንን እና ቱርካዊያንን ገድሏል።
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

አገልጋዮች በቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።

ሀገረ ስብከቱ የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ አገልግሎቱ እንዴት መከናወን እንዳለበት ከሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ቄሰ ገበዞች ጋር ባደረገው ውይይትና ስምምነት መነሻነት የተለያዩ መመሪያዎች መተላለፋቸውን የሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ገልጿል።

ከመመሪያዎች አንዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከተለ መሆኑን ለሁሉም ገዳማትና አድባራት በተላከው የመመሪያ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።

“በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ቅዳሴ የሁሉም ጸሎታት ማጠናቀቂያ ፣ ቀራንዮ ላይ ምንገኝበት፣ የበጉ ሠርግ ላይ የምንታደምበት፣የጌታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በአንድነት ለሓጢአት ሥርየት፣ ለነፍስ ሕይወት፣ ለሃይማኖት ጽንዐትና ለመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ይሆነን ዘንድ የምቀበልበት ታላቅ የጸሎት ሰዓት ነው” ያለው ዘገባው በመሆኑም አላስፈላጊ የእጅ ስልክ አጠቃቀም ጎልጎታን ከሚያስረሱ ፣በረከትን ከሚያሳጡና ጸጋን ከሚያስወስዱ ድርጊቶች መካከል አንዱ በመሆኑ እንደተከለከለም ተገልጿል።

ይህንን መመሪያም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲያስፈጽሙ መታዘዛቸውን ጠቁሟል፡፡
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

🔖ነዳጅ በሊትር 900 ብር!!!!

በኦሮሚያ ክልል መቱ ከተማ ነዳጅ በሊትር እስከ 900 ብር እየተሸጠ መሆኑ በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ አስነሳ፡፡

የነዳጅ አቅርቦት በማደያዎች ባለመኖሩ በጥቁር ገበያ እየተሸጠ እንደሚገኝ ያነሱት ነዋሪዎቹ፤ በተለይ በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፉ ላይ ጫናው ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ በበኩሉ "በዚህ መልኩ የተጋነነ የጥቁር ገበያ የለም" ሲል ቅሬታውን ያስተባበለ ሲሆን ሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድን ለመቆጣጠር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

እንደ አሐዱ ሬዲዮ ዘገባ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም ተመሳሳይ የሕገ-ወጥ ነዳጅ ሽያጭ መኖሩ ተጠቁሟል።

#እስኪ በየአከባቢያችሁ ያለውን የነዳጅ ዋጋ በተከታዩ ሊንክ አስቀምጡልን፡፡
➡️https://web.facebook.com/shegerTimesMedia/

ከዚህ ቀደም መነሻቸውን ከደቡብ ሱዳን ያደረጉ ታጣቂዎች ድንበር ተሻግረው በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ይታወሳል።

አሁን ግን በአመዛኙ ካለፉት ዓመታት አኳያ ጥቃቱ እየቀነሰ መጥቷል ሲል ክልሉ መግለጹን ሸገር ኤፍም ዘግቧል፡፡

የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሚዮኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ጌሌጅሎ ባለፉት ዓመታት በድንበር አዋሳኝ ባሉ ቀበሌዎች በርካታ ህጻናትና የቁም እንስሳት በታጣቂዎች እንደሚወሰዱ እና ጥቃት እንደሚደርስ አንስተው አሁን ላይ ግን ጥቃቱ ቀንሷል ብለዋል ያለው ዘገባው አቶ ኡጁሉ ጥቃቱ ቀንሷል ይበሉ እንጂ አሁንም ቢሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ እያደረጉ ስለመሆኑም ነግረውኛል ብሏል፡፡

ግን ይሄ እንቅስቃሴ ያን ያህል ስጋት ላይ አይጥልም፡፡ ከዚህ ቀደም በክልሉ በእነዚህ ታጣቂዎች ምክንያት በርካታ ጉዳት ደርሷል።

ክልሉን እና አካባቢውን የሚጠብቁ የፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት አሉ፡፡ ሆኖም እነሱ ባሉበት ሁኔታ ህፃናትና እንስሳት በታጣቂዎቹ ሲጋዙ እና ጉዳት ሲደርስባቸው ነበር ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? ተብሎ ለኃላፊው ለቀረበላቸው ጥያቄ ታጣቂዎቹ በትናንሽ ቡድኖች ተበታትነው በተለያዩ አቅጣጫዎች ስለሚንቀሳቀሱ እንደሆነ መናገራቸውን ገልጾአል፡፡
የድምፅ ዘገባውን በተከታዩ ሊንክ ያድምጡት
➡️https://tinyurl.com/ye3sfd86
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

‼️የከሰም የስኳር ፋብሪካ ከ3 ሺህ በላይ ሰራተኞቹን አሰናበተ ⵑⵑ
*******
በአፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው ከሰም የስኳር ፋብሪካ፣ በክልሉ እየተከሰተ ባለው ለወራት የቀጠለ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይፋ ባደረገ በወሩ፣ ከ3,700 በላይ ሠራተኞቹን ከሥራ ማሰናበቱ ታወቀ።

እንደሪፖርተር ዘገባ በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመጣው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ተፈናቅለው በካምፕ የተጠለሉ 3,750 ቋሚና ጊዜያዊ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች፣ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባልጠበቁት ሁኔታ ከሥራ መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡

ጋዜጣው አገኘሁት ያለው የሰነድ ማስረጃ እንደሚያስረዳው፣ ከሥራ ገበታቸው የተገለሉት 1,250 ቋሚ ሠራተኞች ሲሆኑ፣ የተቀሩት 2,500 ሠራተኞች ደግሞ በሸንኮራ እርሻና በፋብሪካው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ላይ አስተዋፅኦ የነበራቸው ጊዜያዊ የሥራ ቅጥር ውል የነበራቸው ሠራተኞች ናቸው።
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

🔖ካናዳውያን የኢለን መስክ ዜግነት እንዲነጠቅ የሚጠይቅ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመሩ

እስካሁን ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ፊርማውን መፈረማቸው ታውቋል

ካናዳ 51ኛው የአሜሪካ ግዛት እንድትሆን ሀሳብ ያቀረቡት ትራምፕ የቅርብ ሰው የሆነው ቢሊየነሩ በካናዳ ዙሪያ በሚሰነዝረው ሀሳብ ነው ዜግነቱ እንዲቀማ የተጠየቀው

የአለማችን ቁጥር አንድ ባለሀብት ኢለን መስክ የካናዳ ዜግነት እንዲነጠቅ የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡

በካናዳ የምክር ቤት አባል ካዋሊያ ሬድ እና በሌሎች ዜጎች የተጀመረው የፊርማ ማሰባሰብ ሂደት ከ200 ሺህ በላይ ካናዳውያን ፊርማ እንዳረፈበት ታውቋል፡፡

የፊርማ ማሰባሰብ ሂደቱ የተጀመረው መስክ ካናዳን 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት አደርጋታለሁ ከሚሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ባለው ቅርበት እና በሀገሪቱ ፖለቲካ ዙሪያ በሚሰነዝረው ሀሳብ ነው ተብሏል፡፡

ከአምስት ቀናት በፊት በበይነ መረብ ብቅ ያለው የፊርማ ማሰባሰቢያ መስክ የካናዳን ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረር ሁኔታን ደግፎ ቆማል በሚል ከሷል፡፡

ከዚህ ባለፈም መስክ ከትራምፕ ጋር ያለው ወዳጅነት የሀገሪቱን ሉዐላዊነት ለመገርሰስ ከሚሰራ የውጭ መንግስት ጋር በግልጽ እየተባባረ መሆኑን የሚያመላክት ስለመሆኑ አብራርቷል፡፡

እነዚህ ጉዳዮች የፈጠሩት የካናዳውን ቁጣ የባለሀብቱ ዜግነት እንዲነጠቅ ለመጠየቅ አደባባይ እንዲወጡ አድርጓቸዋል፡፡

ትውልደ ደቡብ አፍሪካዊው ኢለን መስክ የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹን ቴስላ፣ የጠፈር ኩባንያውን ስፔስ ኤክስ እና የማህበራዊ ትስስር ገጹን ኤክስ (ትዊተርን) ጨምሮ የተለያዩ የአሜሪካ ኩባንያዎችን የሚመራ ሲሆን በእናቱ በኩል የካናዳ ዜግነት እንዳለው የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ካናዳን ወደ አሜሪካ ለማጠቃለል ያቀረቡት ሀሳብ 40 ሚሊየን ካናዳውያንን አስቆጥቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዝዳንቱ ከሀገሪቱ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ተግባራዊ ማድረጋቸው በጎረቤታሞቹ መካከል ውጥረትን አስከትሏል፡፡

መሰል የፊርማ ማሰባሰብ ጥያቄዎች በፓርላማው ቀርበው ይፋዊ ምላሽ ወይም ውሳኔ ያገኙ ዘንድ 500 እና ከዛ በላይ ፈራሚዎችን ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ነገር ግን በ5 ቀናት ውስጥ በ100 ሺዎች ፊርማዎችን ያገኘው እና እስከ ሰኔ 20 ድረስ ይቆያል የተባለው የኢለን መስክ ዜግነት እንዲነጠቅ የሚጠይቀው ፊርማ ከሚያስፈልገው በላይ በርካታ ፈራሚዎችን ማግኘት ችሏል፡፡[ አል አይን]
👀https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

➡️
በአፍሪካ በእድሜ ትንሹ የሆነው የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ወደ ስልጣን መጥቶ ቃለ መሀላ በፈፀመ ጊዜ “ቃሉን ወደ ተግባር የመለወጥ አቅምና በቂ ተሞክሮ አለው ወይ?” የሚል የጥርጣሬ አስተያየት ይሰጡ የነበሩ ጥቂት አልነበሩም፡፡


ከእነዚህ መካከል ለመፈንቅለ መንግስት የቋመጡ ወታደራዊ መኮንኖች ይገኙበት ነበር፡፡

ይህን ቀድሞ ከግንዛቤ ያስገባው የነበረው ትራዎሬ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችንና የካቢኔ አባላትን ሰብስቦ “እድሜ ቁጥር ነው፤ የቡርኪናፋሶን ችግር መፍታት የሚቻለው በእድሜ መብዛትና ማነስ አይደለም…” ብሎአቸው ነበር፡፡

ይህን ቃሉንም ቢሆን አምነው ያልተቀበሉና ቦታው ይገባናል የሚል ስሜት አድሮባቸው የነበሩ የቀድሞው ብልሹ ስርዓት አሸርጋጅ የነበሩ አዛውንት መኮንኖች ወደ ስልጣን ከመጣ ጥቂት ወራት እንዳስቆጠረ መፈንቅለ መንግስት ሞከሩበት…

ሙሉ ታሪኩን ይመልከቱት…
⬇️⬇️⬇️
https://youtu.be/IBnfhza0gBk?si=1GhtSBPxfhn9ufAz