Latest Posts from School of Aygoda(High School) (@schoolofaygoda01) on Telegram

School of Aygoda(High School) Telegram Posts

School of Aygoda(High School)
The official channel for all Highschool students #0916925592(Saris) #0916139929(Bulbula) #SchoolofAygoda
3,783 Subscribers
2,813 Photos
104 Videos
Last Updated 09.03.2025 05:16

Similar Channels

Light Pictures Asella
4,523 Subscribers
FIX JODI VEER BHAI Ji
2,737 Subscribers

The latest content shared by School of Aygoda(High School) on Telegram

School of Aygoda(High School)

04 Mar, 19:35

1,450

Grade 12 gabi(cultural cloth) day celebrated today!
School of Aygoda(High School)

04 Mar, 19:30

1,465

First semester top acheiver students recognition ceremony
School of Aygoda(High School)

28 Feb, 12:20

2,663

ለስኩል ኦፍ አይጎዳ የሳሪስ ቅርንጫፍ ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ

ነገ ማለትም የካቲት 22/2017ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ ዓመት አማካይ ውጤታችሁ ከ70 በታች ያመጣችሁ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች በውጤቱ ዙሪያ ለመመካከር ወላጅ ይዛችሁ በመምጣት ከጥዋቱ 2:30-6:00 ድረስ ካርድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።


ማሳሰቢያ
👉አማካይ ውጤቱ ከ70 በታች የሆነ ማንኛውም ተማሪ ወላጅ ማምጣት አለበት።

👉አማካይ ውጤታችሁ ከ70 በላይ የሆናችሁ ተማሪዎች አጠቃላይ የውጤት መረጃችሁን ከትምህርት ቤቱ በይነ መረብ(website) ላይ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን


website👉
www.schoolofaygodaethiopia.com
School of Aygoda(High School)

21 Feb, 08:11

2,359

ማስታወቂያ
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡


የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው። ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው፡፡ በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ አሉ፡፡ በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የፈተና ዝግጅቱ፡-
1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣
2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።


ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ ይሆናል።

በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ስለሆነም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት!
የካቲት 2017 ዓ.ም
School of Aygoda(High School)

08 Feb, 16:26

5,153

🥢🥢በኢትዮ ፓረንት ትምህርት ቤት አዘጋጅነት በ16 ትምህርት ቤቶች መካከል እየተደረገ በሚገኘው የእግርኳስ ዉድድር ስኩል ኦፍ አይጎዳ ሳሪስ ቅርጫፍ   ስኩል ኦፍ ቱሞሮን በተማሪ ኤልናታን ወንደሰን እና በተማሪ ዳንኤል ከበደ አማካኝነት በተገኙ ሁለት ግቦች 2 ለ1 በማሸነፍ  ወደ ሩብ ፍጻሜ በመቀላቀል በቀጣይ ከ ብሪቲሽ ትምህርት ቤት ጋር የምንጫወት ይሆናል።
School of Aygoda(High School)

07 Feb, 18:00

4,527

የሶስተኛው ሩብ ዓመት የትምህርት ዘመን ሰኞ የካቲት 3/2017 ዓ.ም ይጀምራል ።

የሶስተኛው ሩብ ዓመት ሰኞ ማለትም የካቲት 3/2017 ዓ.ም የሚጀምር ሲሆን ሁላችሁም በትምህርት ቤት በሰዓቱ በመገኘት መደበኛ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።


ማሳሰቢያ:👉 ትምህርት ሙሉ ቀን ይሆናል።
               👉 ማርፈድ ወይም መቅረት አይቻልም
        
                                                    ት/ቤቱ

#schoolofaygoda
#allbranches
School of Aygoda(High School)

07 Feb, 17:23

3,900

ለስኩል ኦፍ አይጎዳ ቡልቡላ ቅርንጫፍ  ወላጆች በሙሉ

የተከበሩ የተማሪ ወላጆች በቅድሚያ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን የሶስተኛዉ ሩብ ዓመት ክፍያ የሚከፈልበት ቀን ከየካቲት 1-15 ብቻ ሲሆን ከተጠቀሠው ቀን አሳልፈው ለሚከፍሉ ወላጆች ቅጣት ያለው መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

                     የት/ቤቱ ፍይናንስ አስተዳደር
School of Aygoda(High School)

18 Jan, 15:45

7,486

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራና ለአየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ!


ኢየሱስ ክርስቶስ የጠፋውን ሰው አዳምን ለመፈለግ በመጣ ጊዜ እከብር አይል ክቡር የባሕርይ አምላክ ሆኖ ሳለ በዮርዳኖስ ወንዝ በአገልጋዩ (በፍጡሩ) በዮሐንስ ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ ያንን የዕዳ ደብዳቤ መደምሰሱን ወደሲኦል ተጥሎ የነበረዉን ደግሞ በእዕለተ ዐርብ በአካለ ነፍስ ወደሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ባወጣ ጊዜ ማጥፋቱን እንዲሁም በእርሱ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት መቀደሱን ከሀይማኖታዊ አስተምረቶች እንረዳለን፡፡


በአለም መድረክ የኢትዮጵያን ከፍታን ከሚያሳዩና አይን ከሚስቡ በሀገራችን በአደባባይ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቱባ ባህላዊ ትእይንቶቻቸዉን አጎልተዉ ከሚያሳዮባቸዉ እንዲሁም በአልበሳትና በብዝሃ ቋንቋቸዉም ፈክተዉ ከሚታዩባቸው በዓላት መካከል አንዱ የጥምቀት በዓል ሲሆን በአለም በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ ቅርሶች መካከልም ተመዝግቦ የሚገኝ ነው፡፡

በመጨረሻም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራና ለአየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡


     #Schoolofaygoda
     #allbranches
     Shapping  Generation Since 1956
School of Aygoda(High School)

06 Jan, 16:31

5,367

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ!


(ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም)  የገና ፆም  ከቤተ ክርስቲያን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው  ነብያት የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የሚፆሙት ታላቅ ፆም ነው። ዛሬም  ክርስቲያኖች ይህንን  ፈለግ ተከትለው በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የሚያስቡበት ነው።


ይህንንም ታላቅ የፆም ወቅት በማጠናቀቅ ለዛሬ ው የገና በዓል ዋዜማና በነገው እለት ለሚከበረው የገና በዓል ላደረሳችሁ ላደረሰን ለፈጣሪ  ክብር ምስጋና ይድረሰው።


ውድ የስኩል ኦፍ አይጎዳ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በዓሉን ስናከብር ያለንን ተካፍለን ፣ አቅመ ደካምችንና አረጋዊያንን አግዘን እንዲሁም ለሌሎች ብርሀን በመሆን፣ ወንድማማችነትን በማጎልበት ፣ ፍቅርን በማብዛት እና እርስ በእርስ በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል።


በመጨረሻም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን  ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን !  እያልኩ  በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የመረዳዳት፣ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆን ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡



አመሰግናለሁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  የቴሌግራም ገፅ የተወሠ
School of Aygoda(High School)

06 Jan, 16:31

4,188

የ 2071ዓ .ም የ ገና በዓል የአብሮነት  ጊዜ በሳሪስ ስኩል ኦፍ አይጎዳ  2ኛ ደረጃ የበጎ አድራጎት ክበብ አስተባባሪነት የተካሔደ የምሳ ግብዣ ፕሮግራም።