REMEDAN Tube @remedantube Channel on Telegram

REMEDAN Tube

@remedantube


📡 በቻናሉ ውስጥ 📡

🖱 Entertainment
🖱 ጥናታዊ ጽሁፎች
🖱 ቪዲዎች
🖱 ጥቆማዎች
🖱 አስተማሪ የሆኑ ትረካዎች እና
🖱 ሌሎች ትምህርቶችንም ያገኛሉ።


Fσ૨ αɳყ CØΜΜ€ŇŦ
°°°°°°°°°°°°•••••••°°°°°°°°°°°°°°
          👇🏾
@Remedantubebot
️ 

REMEDAN Tube (Amharic)

ለዚህ ቻናል ቱቢ ከአማርኛ ማህበረሰብ እና አማርኛ ትግሪዋይ በአንድ ቦታ ህመም ላይ ማብራሪያ እና ጥናት ነው። REMEDAN Tube ለምሳሌ አንድ መልእወቅና ከእንግሊዝ ሰማይ የሚጋለጥ ሃገርን ለፊት ለመሀበሙ የሚከብሩ ታሪኮችን እና ትምህርቶችን ዋናው ማወቅ ያጣሉ። የፍቅርና እንጨት የማውቀው የሚጠለፍ ትምህር አዳራሻ ለመነፅህ እንደሚረግፈው አሰልጣኞቹ ከሌሎች ትምህርቶች የሆኑ ጥቆማዎች ጋር እንዲሼከል የሚያሳቅርው ነው። በጣም ሌላው ትምህርት መፈጠሩን ከታች እና እንደሆነ በመሆን እንሸልፍል። ሌሎች አዳዲስ ቻናሉዎችን እንድናገኙ ይቀላቀሉ።

REMEDAN Tube

05 Dec, 07:40


     ┏━━━ ◌‌༄ ━━━━💞━━┓
💞@Remedantube☜join us
     ┗━━━ ◌‌༄ ━━━━💞━━┛

❍✰✰ የትኛውም " የነፃነት ትግላቹ" እስልምናን በነፃነት የመተግበር ዓላማን ከፊቱ እስካላስቀደመ ድረስ ከንቱ ነው ። ዲን የተዋረደበት የትኛውም ምድራዊ "ነፃነት" ከንቱና ጎደሎ ነው።
⁩✿┈┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿
📮•〔➣ T.me/Remedantube 〕•

REMEDAN Tube

05 Dec, 06:06


Share Share Share

ለሁሉም እንዲደርስ ሼር እናድርገው። ልሳኑ መዘጋት አለበት።

በረሱላችን ﷺ ድርድር የለም
||

REMEDAN Tube

05 Dec, 06:05


አንድ የሚገርመኝ ነገር አለ። በፊት ረሱል ﷺ በህይዎት ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የርሳቸውን ክብር ለመንካት የሞከሩ ግለሰቦች ሁሉ፤ የዚህች ዱንያ መጨረሻቸው ያልተጠበቀና በጣም አሰቃቂ የሆነ መጥፎ ፍጻሜ መሆኑ ነው።

በቅርቡ ካርቱን ፊልም ለመሥራት የሞከረውን ግለሰብ ፍጻሜ ራሱ እናስታውሳለን።


አላህ እንዲህ ብሏላ፦

(إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ!)

«ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡»
[አል-ሒጅር: 95]

እንዲህም ብሏል፦

(إِنَّ شَانِئَكَ هُوَ الْأَبْتَرُ")

«ጠይህ (የሚጠላህ) እርሱ በእርግጥ (ዘሩ) የተቆረጠው ነው፡፡»
[አል-ከውሠር: 3]


አላህ ይህን ግለሰብ ወይ እስልምናን ይወፍቀው፤ አሊያ መጥፎ ፍጻሜውን አሳይቶ አንጀታችንን ቅቤ ያጠጣው።
እንዲህ አይነት ሰዎች የርሳቸውን ክብር ለማጉደፍ በመሞከር ሰዎችን ከእስልምና የሚያስወጡ እየመሰላቸው፤ ጭራሽ ስለርሳቸው በመረጃ ሳያውቅ በሩቅ የሚጠላቸው ሁላ ታሪካቸውን ለማንበብ ሲሞክር በዛው ተማርኮ እየቀረ እስልምናን ይቀባላል።

ፊዳከ አቢ ወ ኡሚ ወ ነፍሲ ወ ደሚ ያ ረሱ-ል'ሏህ ﷺ

REMEDAN Tube

29 Nov, 17:42


«ከሰዎች ይደበቃሉ፡፡ ከአላህ ግን መደበቅ አይቻላቸውም፡፡»
.
© ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
.
አማኞች በምንም ምክንያት ለእኩያን ወግነው ሊሟገቱላቸው እንደማይገባ አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣን በግልፅ ተናግሯል። ለፖለቲካ አሰላለፍ፥ለብሄር ወገንተኝነት፥ ለጥቅማቸው ወይም ሌላ ምክንያት በዚህ ዓለም ሳሉ ለእኩያን ቢከራከሩላቸውና ጥብቅና ቢቆሙላቸው እነኝህ ምድራዊ ነገሮች ሁሉ ቅንጣት በማይፈይዱበት በእለተ ትንሳኤስ አላህ ፊት ማን ይሟገትላቸዋል? ሁላችንም በጥሞና ቀጣዩን የቁርአን አንቀጽ እንመልከት።አላህ እንዲህ ይላል፦

“ለነዚያ ነፍቦቻቸውን ለሚያታልሉት (ጥብቅና በመቆም) አትሟገት፡፡ አላህ አጭበርባሪና ኃጢአተኛ (የሆነን ሰው) አይወድምና፡፡ ከሰዎች ይደበቃሉ፡፡ ከአላህ ግን መደበቅ አይቻላቸውም፡፡ በሌሊት እርሱ የማይወደውን ቃል በሚነጋገሩበት ወቅት አብሯቸው ነበር፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ያካበበ÷ (ሁሉንም ዓዋቂና ተቆጣጣሪ) ነው፡፡ እነሆ ከዚህች ዓለም ላይ እናንተ ተከራከራችሁላቸው፡፡ በዕለተ ትንሳኤ ከአላህ ዘንድ ማን ይሟገትላቸዋል ማንስ ጠበቃ ይሆናቸዋል?” (ቁርኣን፥4÷107-109)

የዚህ አንቀፅ መልዕክት ለሕዝቡ ሁሉ ቢሆንም አንቀጹ በምክንያትነት ሊወቅስ የወረደው መልዕክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ) አስመልክቶ ነበር፡፡ ታሪኩን ቲርሚዚ÷ ኢብኑ ጀሪር÷ ኢብኑ አቢሃቲም÷ አቡሻይ እና ሓኪም ቀታዳ ኢብኑ ኑዕማንን አጣቅሰው ዘግበዋል፡፡

ታሪኩ እንዲህ ነበር። የበኑ ኡበይረቅ ጐሣ አባላት የሆኑ ቢሽር÷ቢሽር እና ሙበሽር የተሰኙ እኩያን ግለሰቦች ነበሩ፡፡ “ቢሽር” ግን ሙናፊቅ ነበር፡፡ ግጥም በመግጠም ሰሀቦችን ያጥላላ ነበር፡፡ በዚሁም በሰዎች ዘንድ ታወቀ፡፡ የርሱን ግጥሞች የሰሙት ሰሀቦች “ይህንን ግጥም ይህ እኩይ ግለሰብ እንጂ ማንም አይገጥመውም” ይሉ ነበር፡፡ ይህንንም የሰሀቦችን ንግግር ቢሽር ሲሰማ ስንኝ በመቋጠር “አንድ ግጥም በሰሙ ቁጥር ሳያጣሩ ጆሮአቸውን ደፍነው እርሱ ነው” ይላሉን? የሚል ይዘት ያለው መልዕክት አሰራጨ፡፡

ይህ በእንዲህም እያለ እነኚሁ የበኒ ኡበይሪቅ ሰዎች በሌሊት የቀታዳ ኢብኑ ኑዕማን አጐት የሆነውን የሪፋአን ሠይፍ÷ ጋሻ ፣ ጦር፣ ምግብና ሌሎች ንብረቶችን ቤት ሰብረው ወሰዱ፡፡ ይህን ጊዜም ሪፋአና ቀታዳ ጋር ሆነው ሌባውን ለማፈላለግ ተንቀሳቀሱ፡፡ በኒ ኡበይሪቆች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ የሚያመለክት መረጃ አገኙ፡፡ ሄደውም ጠየቋቸው እነርሱም “እኛ አልሠረቅንም፡፡ የሰረቀውም ሊበድ ኢብኑ ሰህለ ይመስለናል “ሲሉ መለሱ፡፡ ይህ ግለሰብ ግን ምጡቅ ስብእና የነበረውና በዚህ በፍፁም ሊጠረጠር የማይችል ነው፡፡ በርሱ ያላከኩት ጥርጣሬን ከራሳቸው ለማስወገድ ነበር፡፡ በስርቆት የታማው ሊበድ ኢብኑ ሰህል ሰይፉን መዞ ወደ በኒ ኡበይሪቅ ሰዎች ዘንድ ሄደ፡፡ “እኔ ሌባ ነኝን? በአላህ እምላለሁ ይህንን ሰይፍ አንገታችሁ ላይ ሳላሳርፍ የሰረቀውን ግልፅ አድርጉ፡፡” አላቸው። እነርሱም “ከኛ ዞር በልልን! የሰረቅከው አንተ አይደለህም፡፡” አሉት፡፡ እርሱም ተዋቸው፡፡

ንብረቱ የተሰረቀበት ሪፋአ ያሰባሰበው መረጃ ሁሉ ጥርጣሬውን ወደበኑ ኡበይረቅ ሰዎች አነጣጠሩ፡፡ በዚህን ጊዜም ሪፋ እና ቃታዳ ተነጋግረው ጉዳዩን ወደ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ አቀረቡ፡፡ የበኑ ኡባይሪቅ ጐሣ አባላት የሆኑትን ግለሰቦች ከሰሱ፡፡ ንብረቱን የሰረቁት የበኑ ኡበይሪቅ ሰዎችም በተራቸው «ስማችንን በስርቆት አጠፋ» በማለት ሪፋአንና ቀታዳን መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ “ያለምንም ማስረጃና ምስክርም ሰማችንን አጠፉ” ሲሉም ከሰሱ፡፡ ጉዳዩንም መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ተመለከቱ፡፡

እነሪፋእና ቀታዳ የተጨበጠ ማስረጃና ምስክር እንዲያቀርቡ ተጠየቁ፡፡ እነርሱ ያላቸው ማስረጃ ቀጥተኛ ሳይሆን የአከባቢ ማስረጃ ነበር፡፡ መልዕክተኛውም (ሰ.ዐ.ወ) ለበኒ ኡበይሪቆች በመወሰን እነቀታዳን ወቀሱ፡፡ ምስክርና ቀጥተኛ ምስክር ሳይይዙ የግለሰቦችን ስም ማጥፋታቸው በመጥቀስ ተከራከሯቸው፡፡ በድርጊታቸውም ወቀሷቸው፡፡ እነ ቢሽር ጨለማን ተገን አድርገው መስረቃቸው ሳያንስ የተሰረቀባቸውን ሰዎች በስም ማጥፋት ከሰው አስወቀሱ፡፡ እነ ሪፋእና ቀታዳ ግን ንብረታቸውም ተሰርቆም ዳግም ስም በማጥፋትም ተወቀሱ፡፡

ይህን ሁሉ ነገር ይመለከት የነበረው አላህ (ሱወ) የእኩያንና መናፍቃኑን ጥፋተኝነት አረጋገጠ፡፡ መልዕክተኛውም ምስክርና ግልፅ ማስረጃ ባለመኖሩ ለእኩያኑ በመከራከራቸው ተወቀሱ፡፡ እንዲህም አለ፡-

“እኛ ሰዎችን አላህ ባመላከተህ (ፍትህ) ትዳኝ ዘንድ መጽሐፉን በአንተ ላይ በእውነት አወረድን፡፡ (ስለሆነም) ለከዳተኞች ተሟጋች (ጠበቃ) አትሁን፡፡ አላህን ምህረት ጠይቅ፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ ለነዚያ ነፍሶቻቸውን ለሚያታልሉት (ጥብቅና በመቆም) አትሟገት፡፡ አላህ አጭበርባሪና ሃጢአተኛ (የሆነን ሰው) አይወድምና፡፡ ከሰዎች ይደበቃሉ፡፡ ከአላህ ግን መደበቅ አይቻላቸውም፡፡ በሌሊት እርሱ የማይወደውን ቃል በሚነጋገሩበት ወቅት አብሯቸው ነበር፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ያካበበ÷ (ሁሉንም ዐዋቂና ተቆጣጣሪ) ነው፡፡ እነሆ ከዚህች ዓለም ላይ እናንተ ተከራከራችሁላቸው፡፡ በዕለተ ትንሳኤ ከአላህ ዘንድ ማን ይሟገትላቸዋል? ማንስ ጠበቃ ይሆናቸዋል?” (ቁርኣን።4÷105-109)

ይህ የቁርኣን አንቀፅ ለመናፍቃን መሟገትን አስመልክቶ ጠንከር ያለችን መልዕክትን ያዘለ ነው፡፡ አንቀፁ የወረደበት ምክንያት ደግሞ መናፍቃኑን ይታገሉ በነበሩት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መሆናቸው ጉዳዩን ይበልጥ ጥብቅ ያደርገዋል፡፡ በስርቆቱ ጉዳይ ምስክርና ቀጥተኛ ማስረጃ በሌለበት ነገር ግን ግለሰቦቹ ቀደም ብለው በእኩይነታቸው የታወቁ ነበር፡፡ ቢሽር ደግሞ ሙናፊቅ ከመሆኑም በተጨማሪ የሰሀቦችን ስም ያጠፋ የነበረ ግለሰብ ነው፡፡ በመሆኑም ምስክርና ቀጥተኛ ማስረጃ ቢጠፋም መልዕክተኛው ለእኩያኑ ወግነው በመከራከራቸው ተወቀሱ፡፡

ከዚህ ታሪክ እኩያን ራሳቸው በደል ፈጽመው ንጹሓንን መልሰው ሊከሱ እንደሚችሉ፥ ያለ ተጨባጭ ማስረጃ ሌሎችን መወንጀልና መፍረድ፥እንዲሁም ለእኩያን ጥብቅና ቆመን መሟገት እንደማይገባን እንረዳለን።

በመጨረሻም በጥላቻ፥ለፖለቲካ ትርፍና ሴራም ሆነ ሌላ በምክንያት መስጂዶቻችንና ንጹሓንን ላይ ጥቃት የፈጸመና የሚፈጽም፥ ራሱ ጥቃት ፈጽሞ በሌላው ያላከከና የሚያላክክ፥ እንዲሁም እውነቱን እያወቀ ለመሸፋፈን የሚተጋም ጭምር ማንም ይሁን ማን አላህ የክፉ ሥራውን ዋጋ ይስጠው።

REMEDAN Tube

07 Nov, 13:15


     ┏━━━ ◌͜͡༄ ━━━━💞━━┓
💞@Remedantube☜join us
     ┗━━━ ◌͜͡༄ ━━━━💞━━┛

❍✰✰“በምድር የአንድን አማኝ ችግር የቀረፈ በፍርዱ ቀን አላህ የርሱን ችግር ይቀርፍለታል፤ በምድር ችግርን (ተቋቁሞ) ያለፈ በፍርዱ ቀን አላህ ከችግሩ ያሳልፈዋል፤ የሙስሊምን (ገመና) የሸፈነ አላህ በፍርዱ ቀን ከሚያጋጥመው ገመና ይሸፍነዋል፤ ባሪያ ወንድሙን እስከረዳ ድረስ አላህ ባሪያውን ይረዳል፤ . . .” ሰሂህ ሙስሊም (7028)

⁩✿┈┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿
📮•〔➣ T.me/Remedantube 〕•

REMEDAN Tube

07 Nov, 13:15


REMEDAN Tube:
«ልጄ ሆይ! ይህች ዓለም ጥልቀት ያላት ባህር ናት ። በርካታ ሰዎች በውስጧ ሰጥመዋል ። በርሷ ላይ ስትጓዝ የአላህን ፍራቻ ሰፊናህ አድርግ። ነዳጇ ኢማንህ ይሁን ። በአላህ መመካትን (ተወኩልን) መንገድህ አድርግ ። ከመስመጥ ትድናለህና » (ሉቅማን)

♡•.¸¸.•♥️•.¸¸.•♡

⁩✿┈┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿
📮•〔➣ T.me/Remedantube 〕•

REMEDAN Tube

06 Nov, 19:59


የት በደረስን ነበር ?
┏━━━ ◌͜͡༄ ━━━━💞━━┓
💞@Remedantube☜join us
     ┗━━━ ◌͜͡༄ ━━━━💞━━┛


"ሁልጊዜም እራሳችንን ለመረዳት በቀን ውስጥ የተወሰኑ ሰዓታትን ብንመድብ ከተራራዎች በላይ መዋል የምንችል ፍጡሮች እንሆን ነበር ። ነገር ግን ስለራሳችን ከማሰብ ይልቅ ስለሰዎች በማሰብ እራሳችንን ጠምደን አሰርነው ። የራሳችንን ነውሮች ረስተን የሰዎችን ነውር እያሳደድን አእምሮአችንን በነገር ጠምደን ከንቱዎች ስለሆን እንጂ የራሳችንን ነውሮች ፈትሸን ራሳችንን መመርመር ብንችል ኖሮ የት መድረስ በቻልን ነበር ። "


⁩✿┈┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿
📮•〔➣ T.me/Remedantube〕

REMEDAN Tube

04 Nov, 05:23


ሰበር ዜና❗️❗️

ቀደም ሲል በዩቲዩብ "innocent prophet"የሚል የ 13 ደቂቃ ኢስላም ጠል ፊልም ተለቆ ነበር። አሁን ግን ሙሉ የ 74 ደቂቃ ጸረ ኢስላም ፊልም “innocent prophet” በዩቲዩብ የተለቀቀ ሲሆን በዓለም ዙሪያ 2 ቢሊዮን ሙስሊሞች ተቃውሞ ቢያሰሙም ዩቲዩብ አላጠፋም በማለት በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን አድርጓል።

ማስጠንቀቂያ አሰላሙ አለይኩም ወንድሞች እና እህቶች ኡለማዎች (ምሁራን) በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሁሉም ሙስሊሞች ጉግል እና ዩቲዩብን ዛሬ እና ለ 3 ቀናት እንዳይጠቀሙ አስጠንቅቀዋል ምክንያቱም ጉግል ሙሐመድን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የሚሳደብ ፊልምን እንደማያግድ አስታውቋል፡፡

ይህ ከ 210 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ ያደርስባቸዋል፣ ምክንያቱም ዓለም ላይ 1.5 ቢሊዮን ያህል ሙስሊም ተጠቃሚዎች አሉት ፡፡ ሙስሊም ነኝ እና የመሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተከታይ ነኝ ብለው የሚያስቡ ከሆነ
ይህን ሚሴጅ ያጋሩ።ይህንን ሚሴጅ ለማጋራት ወይም ለማስተላለፍ ከ 2 ደቂቃ በታች ነው የሚወስድቦት። አላህ የቂያም ቀን ነብዩ ሲሰደቡ ምን እንደሰራን ሲጠይቀን ምናልባት መልስ ሊሆነን ይችላል። (አሜሪካ ትከስራለች)

ይህ ትንሽ ጥረት ብቻ ነው ፣ ትንሽ እንቅስቃሴ ከባዶ ይሻላል። ስለዚህ እባክዎን ይህንን ያጋሩ

REMEDAN Tube

28 Oct, 19:25


#አስተማሪ__የሆነ__ቂሷ

አንዲት እናት ለአንድ ሼኽ ልጆቼን ከበድ ያለ #እንቅልፍ ስለሚተኙ #ለሶላተል ፈጅር ማስነሳት አልቻልኩም ምን ይሻላል ብላ ትጠይቃችዋለች??

ሼኹም፦ አያርገውና ልጆችሽ ተኝተው ቤቱ ላይ #እሳት ቢነሳ ምን ታደርጊያለሽ አሏት ?

እናት፦ እቀሰቅሰቸዋለው.

ሼኹም፦ ከበድ ያለ እንቅልፍ ላይ ከሆኑስ?

እናት፦ወሏሂ በግድም ቢሆን አንገታቸውን ይዤ እቀሰቅሳቸዋለሁ

ሼኹም፦ #ከዱንያ እሳት ልታድኛቸው ይሄን ያህል ከታገልሽ #ከአኼራ ለማዳን ከዚህ በላይ መታገል አለብሽ አሎት ይባላል።

#አሏሁ ተዓላ ከጀሀነም እሳት ይጠብቀን!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞👇 𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 👇𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

@Remedantube👈

መልካም ውሎ ውዶችየ 😍

REMEDAN Tube

28 Oct, 19:25


በህይወት እያለህ
ከአላህ ጋር ንፁህ በሆነ ልብ
መገናኘትን ግብህ አድርገው
⇨ ከሺርክ, ኩራት, ጥላቻ,
ሀሜትና ከምቀኝነት ነፃ ሆነህ አላህን
ስትገናኘው ከውርደትም ሆነ
ከቂያም ቀን ጭንቀት ነፃ ትወጣለህ ።

 وَلَا تُخْزِنِى يَوْمَ يُبْعَثُونَ
" በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ ፡፡"
 يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌۭ وَلَا بَنُونَ
" ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን ፡፡"
 إِلَّا مَنْ أَتَى ٱللَّهَ بِقَلْبٍۢ سَلِيمٍۢ
"ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጂ ፡፡"

አላህ ሆይ ቀልባችንን ንፁህ አድርገህ
ከኛም ወደህ እንድንገናኝህ አድርገን ።

...........
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. t.me/Remedantube
•════•••🍃🌺🍃•••════•

REMEDAN Tube

28 Oct, 19:25


ከመጥፎ ሰዎች ጋር ጣፋጭ ነገር ከምትበላ ከደጋግ ሰዎች ጋር ድንጋይ ብትሸከም ላንተ የተሻለ ነው!
#ኢብኑ_ቀይም

@Remedantube

REMEDAN Tube

24 Oct, 16:28


የረበና ሰላም በናንተ ላይ ይሁን👋

የግጥም ውድድራችን ተጠናቋል!! አሸናፊዎቻችንም የሚከተሉት ናቸው።

🥇ሱመያ ሀሪስ
#code 30 ከጅዳ በዳኞች 50 ነጥብ በአጠቃላይ 75 ነጥብ በማምጣት (1 GB)

🥈ፈትያ ሁሴን ከጅማ
#code 2 በዳኞች 50 ነጥብ በማግኘት በአጠቃላይ 72 በማምጣት (500 MB)

🥉ሙኒር ሁሴን ከአዲስ አበባ
#code 9 በዳኞች 50 ነጥብ በማግኘት በአጠቃላይ 70 ነጥብ (250 MB)

❹ ሪሀና ከባህርዳር
#code 18 በዳኞች 32 ነጥብ በአጠቃላይ 62 ነጥብ በማምጣት (100 MB)

❺ሰሚራ ሸረፋ ከሀዋሳ በዳኞች 50 ነጥብ በአጠቃላይ 60 ነጥብ በማምጣት (100 MB)

➏ዘምዘም ከሸዋሮቢት በዳኞች 50 ነጥብ ባጠቃላይ 58 ነጥብ በማምጣት (100 MB)

➐ነኢማ ከገርጂ በዳኞች 33 በአጠቃላይ 53 ነጥብ በማምጣት (100 MB)

➑ መንሱር ሱልጣን ከአዳማ በዳኞች 40 በአጠቃላይ 50 ነጥብ በማምጣት (100 MB)

➒ተምኪን ሙላቱ ከባህርዳር በዳኞች 29 በአጠቃላይ 49 በማምጣት (100 MB)
➒ ሀሰን ኤልያስ ከመደወላቡ በዳኞች 30 በአጠቃላይ 49 በማምጣት(100 MB)

የመጨረሻ ሁለቶቹ እኩል ስላመጡ ነው አስረኛ የሌለን በቃላችን መሰረት ካርዱን እንልካለን፣ አንደኛ ተሸላሚያችን ሱመያም ሙሉ አባያ ተሸላሚ ሆነሻል። ለተሳተፋችሁ በሙሉ ጀዛኩሙላህ ኸይር አላህ ያክብርልን። ኢንሻአላህ ከወራት ቆይታ በኋል የተለየ ውድድር ይኖረናል ከዚ የበለጠ አሸላሚና አጓጊ የሆነ እስከዛው መልካም ቆይታ።

ተሸላሚዎች ስልካችሁን @sEKIYEEBOT ላይ ላኩልን።


ረመዳን ቲውብ || @Remedantube

REMEDAN Tube

23 Oct, 07:54


አላህዬ❤️

የወደደኝ ወዶ የጠላ ቢጠላኝ
አላህዬ ካለኝ እኔ ምንአገባኝ
እሱ የወደደው ማረፊያው ጀነት ነው
ሰው ግን የወደደው አፈር ነው ማለቂያው
ታዲያ ለምን ብዬ በሰው ለመወደድ ልጣርና ልልፋ
ሙሉነት የሞላው አላህዬ ኖሮኝ ገፍቶ የማይገፋ!!

አላህን ምትወዱ ላይክ አርጉልኝ

ሱመያ ሀሪስ ከጅዳ

code 30

Like አድርጉልኝ 👍👍

እርሶም መወዳደር ከፈለጉ @Remedantube

REMEDAN Tube

23 Oct, 06:42


የረበና ሰላም በናንተ ላይ ይሁን👋

የግጥም ማስገቢያ ሰአት ሊያልቅ ሰአታት ይቀሩታል!! ግጥም ያላስገባችሁ እስከ መግሪብ ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ!!

🎁እስካሁን ባለው የውድድር ሂደት በላይክ ብዛት እየመሩ ያሉ ተወዳዳሪዎች የሚከተሉት ናቸው:-

🥇ሙሀመድ አሊ ከደቡብ ወሎ 72 ላይክ
🥈ከድር ሲራጅ ከቢቸና 62 ላይክ
🥉ነስራ ከትግራይ 45 ላይክ
❹ ነሱሀ አወል ከአዲስአበባ 32 ላይክ
➎ ኢክራም ከአዳማ 28 ላይክ
➏ ፈሲሊሀ ከአሰላ 27 ላይክ
➐ ሪሀና ከባህርዳር 23ላይክ
➑አንዋር አህመድ ከጂንካ 21 ላይክ
➒ ነሀራ ከሻሸመኔ 19 ላይክ
ሰኢድ ከሚዛን ተፈሪ 19 ላይክ


‼️ልብ በሉ ከላይክ ይልቅ ጥራት ያሸልማል‼️
ለሁላችሁም መልካም እድል!!

🎁ሙሀ የሙስሊም አልባሳት መሸጫም አንደኛ ለወጣች / ለወጣ ተወዳዳሪ ሙሉ አባያ / ጀለቢያ ለመሸለም ቃል ገብቶልናል🎁

ውድድሩ መች ይለቅ የሚለው የብዙዎቻችሁ ሀሳብ ቅዳሜ ወይ እሁድ ነው!! ተወዳዳሪዎች የሚመቻችሁን ቀን አሳውቁንና ያበቃል!!

@Remedantube