በመልካም እዘዝ ከመጥፎ ከልክል አሷሐቡል የሚን ሁን!
وَأَصْحَابُ الْيَمِينِ مَا أَصْحَابُ الْيَمِينِ
【ሱረቱ አል-ዋቂዓህ - 27】
የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!
« የመልካም ጓደኛ (ጀሊስ፣አቀማማጭ) እና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌው ምስክ እንደያዘና (እንደሚነግድና) ወናፍ እንደሚነፋ ሰው ብጤ ነው። »
#ጥሩ ጠረን ያለው ነገር የያዘ ሰው ዘንድ ከተቀመጥክ ያንኑ ጥሩ ሽታ ትላበሳለህ።
መልካሞቹ ፈሪሃ አላህ የሆኑ ጓደኞች ካለን መቸም ቢሆን ያቅማቸውን ያህል ከጎናችን ይሰለፋሉ።
قال تعالى: { الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِين. }
َ {الزخرف:67}
« ወዳጆች በዚያን ቀን ከፊሎች ለከፊሎች ጠላት ናቸው። አላህን ፈሪዎች የሆኑት ሲቀሩ።
ኢማሙ አል ሻፊዒ【 ረሂሙሁሏህ 】እንዳሉት ፦
#የጀነት ሰዎች ጀነት በገቡ ጊዜ በዱንያ ላይ በመልካም ነገር ላይ የነበሩ ጎደኞቻቸውን ጀነት ውስጥ ሲያጧቸው አሏህን እንዲህ ሲሉ ይጠይቃሉ
" #ጌታችን ሆይ ከኛ ጋር ሲሰግዱ እና ሲፆሙ የነበሩ ጎደኞች ነበሩ ጀነት ላይ አጣናቸው " ብለው ይጠይቃሉ ፡ አሏህም እንዲህ ይላቸዋል ፡ ወደ እሳት ሂዱና ከቀልቡ የዘር ፍሬ የምታክል ኢማን ያለውን ሰው አውጡ ይላቸዋል ,
#ሀሰን አል በስሪ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ ፦
【 ሙእሚን የሆኑ ጎደኞችን አብዙ 、 የቂያም ቀን አሏህ በፈቃዱ መሸምገልን ይሰጣቸዋል እና】,
#ኢብኑ አል ጀውዚ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ
#በጀነት ውስጥ በመካከላችሁ ካጣችሁኝ , ስለኔ ጠይቁ ፡ ጌታችን ሆይ ያ ባሪያ በዱንያ ላይ ስላንተ ያስታውሰን ነበር የት አለ በሉ ከዛም አለቀሱ።
#ወዳጆቼ በጀነት ውስጥ ካጣችሁኝ ስለኔ ጠይቁ ምናልባትም በአሏህ መንገድ ላይ አንድ ጊዜም ቢሆን ስለሱ ታላቅነት ፣ ፈጣሪነት አስታውሻችሃለሁና።
وَأَصْحَابُ الْيَمِينِ مَا أَصْحَابُ الْيَمِينِ
【ሱረቱ አል-ዋቂዓህ - 27】
የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!
አሏህ ሆይ ! ያንተን ትእዛዝ በመፈፀም ላይ የሚያበረታቱን መልካም ጎደኞች አብዛልን ወዳጆቻችንም ጋር በጀነት አል ፊርደውስ አንድ ላይ ሰብስበን ...አሚንንንንን
┏━━━ ◌༄ ━━━━🌸━━┓
彡🌸@Remedan_tube☜join us
┗━━━ ◌༄ ━━━━🌸━━