Pharo School - Assosa @pharo_primary_school_assosa Channel on Telegram

Pharo School - Assosa

@pharo_primary_school_assosa


Dear all,
Welcome to Pharo School - Assosa Telegram channel. We will be able to reach you through this telegram channel, and share messages and update you with important information.
Thank you!
The school.

Pharo School - Assosa (English)

Welcome to Pharo School - Assosa Telegram channel! If you are looking for a reliable source of information and updates regarding Pharo Primary School in Assosa, then you have come to the right place. Through this channel, we aim to keep parents, students, and the community informed about important news, events, and announcements from the school. Whether it's details about upcoming school activities, exam schedules, or any changes in school policies, you can find it all here. Stay connected with us and never miss out on any important information. Join our channel today and be a part of the Pharo School - Assosa community. Thank you for your support! The school.

Pharo School - Assosa

03 Feb, 05:01


ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የሁለተኛ  ሩብ አመት ማጠቃለያ  ፈተና ውጤት ዛሬ እና ነገ ማለትም ጥር 26 እና 27 ይሰጣል። እንዲሁም ከሁሉም የፈተና ወረቀት ላይ ከ100 ይገለፃል።

ስለዚህ የልጆቻችሁን ውጤት እንድታዩ እያሳሰብን የውጤት ማስተካከያ ካለ እስከ ረቡዕ ት/ቤት በመምጣት ማስተካከል ትችላላችሁ።

ት/ቤቱ

Pharo School - Assosa

24 Jan, 16:30


የ2017 የትምህርት ዘመን የአንደኛው መንፈቀ ዓመት የሁለተኛ ሩብ ዓመት የማጠቃለያ ፈተና ወቅት እየደረሰ እንደመሆኑ መጠን  ተማሪዎች ሊተገብሯቸው የሚገቡ ጠቃሚ የጥናት ምክሮች

1. የክፍለ ጊዜ ማስታወሻ መጠቀም
በሁሉም የት/ት ክፍለ ጊዜያት መገኘት፣ ንግግሮቹ ላይ በትኩረት መከታተል፣ እና ትርጉም በሚሰጥ መንገድ ማስታወሻ መያዝ

2. ከክፍል ጓደኞች ጋር ማጥናት
ጓደኞችን ከማፍራት በተጨማሪ፣ በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ የጥናት ቡድኖችን መፍጠር እና አብሮ መስራት ጥሩ የጥናት ልምዶችን ለማዳበር ይረዳል፤ በቡድን ፕሮጀክቶች ላይ ትብብርን ይጨምራል ፤ በራስ መተማመንንም ይጨምራል። "አብሮ መስራት፣ ማጥናት፣ መረዳዳት የተሻለ ለመሆን ይረዳል ።"

3. መምህራችን ነፃ የሚሆኑባቸውን ሰዓቶች መጠቀም
በአንድ ጽንሰ-ሀሳብ ወይም ርዕስ ላይ ችግር ካጋጠመዎት መምህርዎ ሊረዱዎት ይችላሉ። የክፍል ትምህርቱን በተሻለ ለመረዳት፣ ለፈተናዎችዎ እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ  አጋዥ ምክሮችን ለማግኘት መምህዎ ነፃ ሲሆን መወያየት ።

4.ለጥናት ጥሩ ቦታ መምረጥ
አንዳንድ ሰዎች የቤተ መፃህፍት መቼት ሙሉ ዝምታ ይወዳሉ፤ ሌሎች ደግሞ ስራ የበዛበትና ማነቃቂያ ይወዳሉ። አንዳንድ ተማሪዎች በጠረጴዛቸው ላይ መሥራትን ይመርጣሉ፤ ሌሎች ደግሞ ፀሐያማ የሆነ የውጪ ቦታ የበለጠ ምቹ ሆነው ሊያገኙ ይችላሉ።

5. ያንብቡ እና ይከልሱ
የተማርነውን 70% በ24 ሰዓታት ውስጥ እንረሳለን። ከክፍል አንድ ቀን በኋላ አዳዲስ ሀሳቦችን ማየቱ ማቆየት እና ግንዛቤን ለመጨመር ይረዳል። ስለዚህ በእያንዳንዱ ምሽት ፈጣን የግምገማ ጊዜ ይውሰዱ። ከመቀጠልዎ በፊት ምዕራፎችን ወደ ክፍሎች ይከፋፍሏቸው እና በእያንዳንዱ መጨረሻ ላይ ያለውን ጽሑፍ ይከልሱ። ሙሉ ምዕራፎችን እንደገና ማንበብ ሳያስፈልግ በቀላሉ መገምገም እንዲቻል የንባቡን ወሳኝ ገጽታዎች በማጠቃለል ማስታወሻ መያዝ።

6. እቅድ ይጠቀሙ
የክፍል እና የቤት ስራዎችን፣ ፕሮጀክቶችን እና ሌሎችንም ፕሮግራም ማስያዝ፣ ተደራጅቶ ለመቆየት ወሳኝ ነው። ማንኛውንም አስፈላጊ ነገር እንዳይረሱ የጊዜ ገደቦችን፣ ቀኖችን እና ሰአቶችን ለመከታተል እቅድ ይጠቀሙ።

7.ቁሳቁሱን በዓይነ ሕሊናህ መመልከት
ትምህርቱን በማጣመር እና ቁልፍ ቃላትን እና ፅንሰ-ሀሳቦችን በማስመር ወይም በማድመቅ በክፍል ማስታወሻዎችዎ በጣም አስፈላጊ ክፍሎች ላይ ያተኩሩ። የተወሳሰቡ ፅንሰ-ሀሳቦችን እንዲረዱ የሚያግዙ ምስሎችን ለመፍጠር ወደ ስዕላዊ መግለጫዎች፣ የአእምሮ ካርታዎች ወይም ዝርዝር መግለጫዎች እንደገና ለመቅረጽ ይሞክሩ።

8. ጎበዝ ተማሪዎች እንዲያስረዱህ አድርግ/ጊ
በተለይም በአንድ ርዕስ ላይ ልዩ ችሎታ ያላቸው ወይም የላቀ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች እንዲያስረዱህ/ሽ ጠይቅ/ቂ። እንዲሁም በተለያዩ ድህረ ገፆች የሚያስተምሩ መምህራንን ለመረዳት መጣር።

9. በመረዳት ላይ ያተኩሩ
ማስታወስ ማለት እውነታዎችን ለማስታወስ እና ለመድገም መንገዶችን መፈለግ ማለት ነው። መረዳት ትንሽ ጠለቅ ያለ ነው እና አዲስ እውቀትን በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ምን ያህል በጥሩ ሁኔታ መተግበር እንደሚችሉ እና ከሌሎች ፅንሰ-ሀሳቦች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ማወቅን ያመለክታል። የማጠቃለያ ፈተናዎች ብዙውን ጊዜ ማስተዋልን ይፈትኑታል እንጂ ማስታወስን ብቻ አይፈትኑም።

10. በክለሳ ክፍለ ጊዜ መገኘት
በፈተናው ቅርጸት እና በጥያቄዎች ውስጥ ምን ሊካተቱ እንደሚችሉ እንዲሁም በጥናትዎ ወቅት ትኩረት ሊሰጡባቸው የሚገቡ ቁልፍ ርዕሶች ላይ ጠቃሚ መረጃ የሚማሩበት በዚህ ነው።

11. እረፍት ይውሰዱ
አንጎልዎ እና ሰውነትዎ እንዲያድሱ እድል ይስጡት። እንደ ፎርብስ ዘገባ፣ የ25 ደቂቃ የረጅም ጊዜ የጥናት ክፍለ ጊዜዎችን ከአምስት እስከ 10 ደቂቃ ዕረፍት ይውሰዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወደ አንጎል የደም ፍሰትን ይጨምራል ይህም የበለጠ ጉልበት እና የተሻለ ግንዛቤ ይሰጥዎታል.

12. እራስዎን በደንብ ይንከባከቡ
ጊዜን ለመቆጠብ አላስፈላጊ ምግቦችን መመገብ የሚመከር ስልት አይደለም። በምትኩ እንደ ትኩስ፣ ፍራፍሬ እና አትክልት ያሉ ​​“የአንጎል ምግቦችን”፣ ከፕሮቲን እና ጤናማ ስብ ጋር ሚዛናዊ በሆነ መልኩ አእምሮዎን ለማቀጣጠል ያቆዩ። ለእንቅልፍም ተመሳሳይ ነው: ከፈተናው በፊት ባለው ምሽት ሳይበዛ እረፍት ለማግኘት እቅድ ያውጡ.

13. እራስዎን ያረጋጉ
በመጨረሻው ሳምንት በሁሉም የፈተና መሰናዶዎ ውስጥ መጨናነቅ ወደ  ጭንቀት ሊመራ ይችላል። ትምህርቱን ወደ ርእሶች ይከፋፍሉት እና መረጃን ሙሉ በሙሉ ወደ እውነተኛ ግንዛቤ ለመውሰድ ከፈተናው በፊት ለመመልከት ጥቂት ቁልፍ ሀሳቦችን በማስታወሻ ለይ ይፃፉ ።

14. የፈተናውን ቅርፀት ማወቅ
የተለያዩ ሙከራዋች፣ ሞደል ፈተናዎች የተለያዩ አካሄዶችን ይፈልጋሉ። ብዙ ምርጫ ማለት በትርጉሞች እና ጽንሰ-ሐሳቦች ላይ ማተኮር ማለት ነው. የፅሁፍ ሙከራዎች ስለቁሳቁሱ ፅንሰ-ሃሳባዊ ግንዛቤ እንዲያሳዩ ይፈልጋሉ። ስለዚህ ፈተናዎች እንዴት እንደሚዘጋጁ እንዲያውቁ የፈተናውን ቅርጸት መምህሩን ይጠይቁ።

15. ሌሎችን በማስተማር መማር
ለክፍል ጓደኛዎ ፅንሰ-ሀሳቦችን ማስረዳት ትምህርቱን እራስዎ በትክክል መረዳትዎን ለማረጋገጥ እና እንዲማሩ ለመርዳት ጥሩ መንገድ ነው። ፅንሰ-ሀሳብን ለማብራራት አዳዲስ መንገዶችን ሲያገኙ፣ መረጃውን ለሌሎች በማቀናበር እየተካኑ ነው።

16. ቃላት መፍጠር
የኮርስዎን ይዘት ወደ አጭር ክፍሎች መከፋፈል እና ምህፃረ ቃላትን ፣ ሀረጎችን ፣ ግጥሞችን ወይም ዘይቤዎችን መፍጠር ጠቃሚ እና አስደሳች - ጽንሰ-ሀሳቦችን ለማስታወስ የምንጠቀምበት ሌላኛው ዘዴ ነው።

17. እውቀትዎን ይፈትሹ
ቅርጸቱን አንዴ ካወቁ፣ ፈተናው ሊሸፍን ይችላል ብለው ባሰቡት መሰረት የልምምድ ፈተና ለመፍጠር ይሞክሩ። ይህ ትምህርቱን በጥልቅ ደረጃ እንዲረዱ እና ግልጽ የመማሪያ ዓላማዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳዎታል። ከዚያ እራስዎን እና የጥናት ቡድንዎን ለመጠየቅ የተግባር ፈተናዎን መጠቀም ይችላሉ። በዚህም ለራስ ፈተና በማዘጋጀት መለማመድ

18. ትምህርት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ ተማሪዎች እራስን መለየት
ይህም አንዳንድ ተማሪዎች በትምህርታችን ውጤታማ እንዳንሆን በወሬ ዝለን፣  ጫዋታ፣ ልፊያ፣ ፌዝ፣ እና ቀልድ በጥቅሉ ለትምህርት ትኩረት ከማይሰጡ እራሳቸውን ከመቀየር ይልቅ ሌሎችም እንደነሱ እንዲሆኑ ከሚጥሩ ተማሪዎች ጋር አብረህ/ሽ እየዘለልክ/ሽ ጊዜህን/ሽን ከማጥፋት መቆጠብ።

Mr.Andualem Kassa

Pharo School - Assosa

21 Jan, 11:26


ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የሁለተኛ  ሩብ አመት ማጠቃለያ  ፈተና ጥያቄ የ1ኛ ሩብ አመት ትምህርትን ስለሚያካትት በዚሁ መሠረት ልጆቻችሁ እንዲዘጋጁ ክትትል እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ት/ቤቱ

Pharo School - Assosa

21 Jan, 09:42


ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የሁለተኛ ሩብ አመት ማጠቃለያ ፈተና ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ከጥር 21-23፣ 2017; ከ9ኛ-10ኛ ከጥር 20-24፣ 2017 እንዲሁም ለ11ኛ ከጥር 21-23፣ 2017 ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች በቀረበው የፈተና መርሀግብር መሠረት ለልጅዎ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያድርጉ።

Pharo School - Assosa

17 Jan, 14:28


የፋሮ አንደኛ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሠላም በር ትምህርት ቤት የዱቄትና የስኳር ድጋፍ አደረገ
...................................
(ጥር 9/2017 ዓ.ም-አሶሳ) የሠላም በር አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም መጀመሩን ተከትሎ በአሶሳ የሚገኘው የፋሮ አንደኛ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለምገባ አገልግሎት የሚውል የዱቄት እና የስኳር ድጋፍ አደረገ።

የፋር ትምህርት ቤት ርዕሠ መምህር ተስፋዬ  ሸዋረጋ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት የትምህርት ቤቱን ተማሪዎች መምህራንን እና የአስተዳደር ሠራተኞችን በማስተባበር ከ23 ሺህ ብር በላይ በማሠባሠብ 150 ኪሎ ፉርኖ ዱቄት 100 ኪሎ የበቆሎ ዱቄት እና 50 ኪሎ ስኳር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው ይህም ትምህርት ቤቱ የጀመረውን የምገባ አገልግሎት በመጠኑም ቢሆን ያግዛል ብለው በቀጣይም ድጋፉ እንደሚቀጥል አክለዋል።

የሠላም በር ትምህርት ቤት ርዕሠ መምህር አበበ ሞላው በበኩላቸው   በትምህርት ቤቱ ምገባውን ለማስጀመር በዕቅድ ከተያዙ 60 ተማሪዎች መካከል 20 ተማሪዎችን መመገብ መጀመራቸውን ጠቁመው የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና መምህራን ይህንኑ ለማሳካት ከ14 ሺህ ብር በላይ ማሠባሠብ መቻሉን ተናግረዋል።

በመጨረሻም ርዕሰ መምህሩ የፋሮ ትምህርት ቤት ላደረገላቸው ድጋፍ በትምህርት ቤቱ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘገባው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

Pharo School - Assosa

06 Jan, 04:02


ውድ ወላጆች
ሰላም ለእናንተ ይሁን!

ዛሬ ሰኞ (28-04-2017ዓ.ም) የት/ቤቱ መምሀራን ፕሮግራም ስላላቸው የተማሪዎች መውጫ ስዓት 6፡15 መሆኑን እየገለጽን በተገለጸው ስዓት ልጆጃችሁን መጥታችሁ እንድትወስዱ በትህትና እናሳስባለን፡፡

ት/ቤቱ

Pharo School - Assosa

30 Dec, 09:13


ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የ1ኛ ሩብ አመት አጋማሽ ፈተና ውጤት ከዛሬ ታህሳስ 21-23 ይሰጣል።

ስለዚህ የልጅዎን ውጤት በማየት እገዛ በሚያስፈልጉ የትምህርት አይነቶች ላይ አስፈላጊውን ክትትል እና እገዛ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

ት/ቤቱ

Pharo School - Assosa

25 Dec, 16:07


ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ትምህርት ቤቱ ከዚህ በፊት መስሪያ ወረቀት ለሚያስፈልጉ ፈተናዎች ሁሉ ምንም ሳይሰስት ለተማሪዎች እየሰጠ ነበር።

ይሁን እንጂ ከነገ ታህሳስ 17 ፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጡ ፈተናዎች መስሪያ ወረቀት ለሚያስፈልጋቸው የትምህርት አይነቶች ( ሂሳብ፣ Physics፣ እና Chemistry) ተማሪዎች ይዘው እንዲመጡ እናሳስባለን።

ት/ቤቱ

Pharo School - Assosa

19 Dec, 12:48


ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የሁለተኛ ሩብ አመት አጋማሽ ፈተና ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ከታህሳስ 16-18 እንዲሁም ከ9ኛ-11ኛ ከታህሳስ 15-19 ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች በቀረበው የፈተና መርሀግብር መሠረት ለልጅዎ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያድርጉ።

Pharo School - Assosa

11 Dec, 13:10


ውድ ቤተሰቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


1. ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል (ከ5 እና 7ኛ ውጭ) የእንግሊዝኛ መፅሃፍ ስላለ ከነገ ታህሳስ 3 ጀምሮ ት/ቤት በመምጣት ሰኔ 30 ላይ የሚመለስ የመፅሐፉን ዋጋ አስይዛችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

2. በሁለተኛ ደረጃ ማለትም ከ9-11 ለሁሉም ተማሪ የሚደርስ በሁሉም ት/ት አይነት በቂ መፅሐፍ ስላለን የመፅሐፉን ዋጋ አስይዛችሁ እንድትወስዱ ጭምር እናሳውቃለን።

ት/ቤቱ

Pharo School - Assosa

02 Dec, 10:26


ውድ ቤተሰቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የ2ኛ ሩብ ዓመት ግብ መጣያ ቅጽ በልጆቻችሁ አመካኝነት ልከናል፡፡ ስለዚህ የ1ኛ ሩብ ዓመት ውጤት መነሻ በማድረግ እንዲሁም የልጆቻችሁን የማሻሻል አቅም በማገናዘብ ለ2ኛ ሩብ ዓመት ግብ በሁሉም የት/ት አይነት እንዲጣል ስንል በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

ት/ቤቱ

Pharo School - Assosa

15 Nov, 11:32


እንኳን ደስ ያለን ፤ እንኳን ደስ ያላችሁ !!!
ከቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ተማሪ መናሂል አህመድ በዘጠነኛ ሀገር አቀፍ የሳይንስና የምህንድስና የፈጠራ ስራ ውድድር ላይ ሁለተኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆናለች፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮም ለሆሞሻ የፋሮ ፋዎንዴሽን የሴቶች አደሪ ትምህርት ቤትንና ተማሪዋን ሲያግዟት ለበሩ መምህራን ብሎም ለቤተሰቦቿ እንኳን ደስ ያላችሁ ይላል፡፡

ተማሪ መናሂል በሆሞሻ ወረዳ በሚገኘው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ከሌሎች ሴት ተማሪዎች ጋር በመወዳድር ወደ ትምህርት ቤቱ የተቀላቀለችና ብርቱ ተማሪ መሆኗንም ለማዎቅ ችላናል፡፡ ዘገባው የቢሮው ኮሚኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡

Pharo School - Assosa

14 Nov, 09:29


ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የአንደኛ ሩብ አመት ማጠቃለያ ፈተና ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ከህዳር 11-13 እንዲሁም ከ9ኛ-11ኛ ከህዳር 11-14 ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች በቀረበው የፈተና መርሀግብር መሠረት ለልጅዎ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያድርጉ።

Pharo School - Assosa

19 Oct, 06:52


ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የአንደኛ ሩብ አመት አጋማሽ ፈተና ከጥቅምት 13-15 ይሰጣል፡፡ ስለዚህ
ከዚህ በታች በቀረበው መርሀግብር መሠረት ለልጅዎ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያድርጉ።

Pharo School - Assosa

18 Oct, 04:21


https://youtu.be/P1AKSndtnO4?si=g238nwimPfllq1fw

Pharo School - Assosa

14 Oct, 10:12


ውድ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች
ሰላም ለእናንተ ይሁን!!


በክፍያ ላይ ስለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እየጠየቅን ሲስተሙ አሁን ስለተስተካከለ ወርሃዊ የትምህርት ክፍያውን መክፈል ትችላላችሁ፡፡

ት/ቤቱ

Pharo School - Assosa

11 Oct, 06:21


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን


የጥቅምት ወርሃዊ የትምህርት ክፍያ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ስለሆነ ክፍያውን ከወዲሁ እንድትፈፅሙ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ
ከጥቅምት 11 ጀምሮ ቅጣት ስላለው ከወዲሁ ቀድመው ይክፈሉ፡፡

Pharo School - Assosa

11 Oct, 06:14


ውድ የፋሮ ት/ቤት ቤተሰቦች
ሰላም ለእናንተ ይሁን!

ትምህርት ቤታችን የተማሪዎችን አቅም ለማጎልበትና የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማገዝ በየሩብ አመቱ ሁለት ጊዜ የመልመጃ ጥያቄዎችን/worksheet በማዘጋጀት ይልካል።
የዚህ ተግባር ዋና አላማ
1. ተማሪዎች በቤት ውስጥ ሆነው እንዲያጠኑ ያግዛል። ብዙ ጊዜ የቤት ስራ ወይም መልመጃ ካልተሰጣቸው ነፃ ነን ብለው ያስባሉ።
2. ተማሪዎች በወላጆቻቸው ወይም በቅርብ ቤተሰብ እገዛ/ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችላል።

ነገር ግን አንዳንድ ቤተሰብ ከት/ቤት የሚላኩ መልመጃዎችን ሙሉ በሙሉ ተማሪውን ሳያሳትፋ እራሳቸው በመስራት ይልካሉ። በዚህ ምክንያት ተማሪው ምንም ሳይጠቀም ያልተገባ ውጤት እንዲያገኝ በር ይከፍታል።
ስለሆነም ሁሉም የተማሪ ወላጅ ከዚህ ድርጊት በመቆጠብ ልጆች ራሳቸውን ችለው እንዲሰሩ በማድረግ እንዲተባበረን በትህትና እናሳስባለን።
ሠላም

Pharo School - Assosa

10 Oct, 16:54


ውድ ወላጆች/አሳዳጊውች

ወርሀዊ የትምህርት ክፍያን በእጅ ስልክዎ ለመክፈል ይህንን አጭር ቪድዮ ይከታተሉ።

Pharo School - Assosa

08 Oct, 16:28


ውድ የፋሮ ቤተሰቦች
ሰላም ለእናንተ ይሁን!


ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ የትምህረት አገልግሎት ክፍያ አዋሽ ባንክ በመሄድ የሚፈፀም ይሆናል። እንዲሁም የልጆቻችሁን የት/ት ቤት መለያ ቁጥር ወይም በት/ት ቤት  ያስመዘገቡትን ስልክ ቁጥር በመጠቀም በሞባይል ስልክዎ ክፍያ መፈፀም ይችላሉ።

ማሳሰቢያ
1. ከተቀመጠው የክፍያ መጠን ውጪ ቀንሶ ወይም ጨምሮ መክፈል በፍፁም የተከለከለ ነው።
2. የክፍያ ቀን ወር በገባ ከ1 -10 ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ነው። ከዚያ ካለፈ የ 10% ቅጣት ይኖረዋል።


እንድታውቁ
👉 የነባር ተማሪዎች የክፍያ ኮድ አልተቀየረም።

👉 ሲስተሙ ላይ የአዲስ ተማሪዎች ስም የአያት ስም ስለሚያሳይ ክፍያ ላይ ምንም ተፅዕኖ የለውም።

👉ክፍያ የሚፈፀመው በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ ነው።

👉 ክፍያ ሲፈፀም ት/ቤቱ በሲስተሙ አመካኝነት ስለሚያውቅ ደረሰኝ ማምጣት አይጠበቅባችሁም።

👉 ባንክ ቤት ሂዶ ለመክፈል የተማሪ የክፍያ ኮድ ማለትም 33*****ያስፈልጋል።

👉 የአዋሽ ባንክ አካውንት የሞባይል ባንኪንግ ላላችሁና ባንክ ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ እጃችሁ ባለው ስልክ መክፈል ለምትፈልጉ ወላጆች የአከፋፈል ሂደቱን በተመለከተ የሚያግዛችሁ ቪድዮ እንለቅላችኋለን።

Pharo School - Assosa

06 Oct, 07:59


ውድ የተማሪ ወላጆች
ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
የተማሪን መፅሀፍ በየክፍል ደረጃ የተቀመጠውን ሊንክ በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
የ1ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade1TextBooks
የ2ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade2TextBooks
የ3ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade3TextBooks
የ4ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade4TextBooks
የ5ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade5TextBooks
የ6ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade6TextBooks
የ7ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade7TextBooks
የ8ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade8TextBooks
የ9ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade9TextBooks
የ10ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade10TextBooks
የ11ኛ ክፍል
https://t.me/PharoGrade11TextBooks

Pharo School - Assosa

03 Oct, 16:29


የተወደዳችሁ የፋሮ ቤተሰቦች
ሰላም ለእናንተ ይሁን

የ11ኛ ክፍል አዲስ ተማሪ ምዝገባን ይመለከታል።

ት/ቤታችን ባለው ውስን ክፍት ቦታ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን መመዝገብ ይፈልጋል።

ስለዚህ የ10ኛ ክፍል ውጤት ኮፒ በመያዝ ነገ አርብ መስከረም 24፣ 2017 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።


👉 የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ሰኞ መስከረም 27፣ 2017 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል።

ውድ የፋሮ ቤተሰቦች ይህንን ማስታወቂያ የ11ኛ ክፍል ት/ት ፍላጎት ላላቸው ወላጆች ያሳውቁልን🙏🙏

Pharo School - Assosa

01 Oct, 22:41


ውድ የነባር እና አዲስ 9ኛ ክፍል ተማሪ  ቤተሰቦች
ሰላም ለእናንተ ይሁን


ለ9ኛ ክፍል አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ

1. የአዲስ ተማሪዎች ውጤት የሚገለፀው  ነገ ረቡዕ መስከረም 22/2017 ከጧቱ 3:30 ሰዓት ላይ ሲሆን ምዝገባ የሚከናወነው ከመስከረም 22-24/2017 ይሆናል።


2. የ9ኛ ክፍል ትምህርት ሰኞ መስከረም 27/2017 ዓ.ም ይጀምራል። ስለዚህ ሁሉም ተማሪ ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ, ምሳ በመያዝ እንዲሁም ዪኒፎርም በመልበስ ት/ቤት ጧት 2:00 ሰዓት ላይ መገኘት ይኖርባችኋል።


ማሳሰቢያ

ነባር ሆናችሁ ነገር ግን ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች እስከ ረቡዕ መሰከረም 23/2017 መጥታችሁ የማትመዘገቡ ከሆነ በምትካችሁ ተጠባባቂ ተማሪ የምንመዘግብ ይሆናል።

ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የሚመጡ ወላጆችን የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

              ት/ቤቱ

Pharo School - Assosa

30 Sep, 16:48


ውድ የትምህርት ቤታችን ቤተሰቦች

ሰላም ለእናንተ ይሁን!!!


ጉዳዩ:- የመውጫ ካርድ/Exit Card/ ይመለከታል

ልጅዎ ያለእርስዎ እርዳታ የሚወጣ ከሆነ እንዲሁም በባጃጅ የሚሄድ ከሆነ Exit Card ያስፈልጋል። ካርዱን ለልጅዎ ለመስጠት ት/ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን ፎርም መፈረም ይጠበቅባቹሃል።

ስልዚህ መውጫ ካርድ ለልጅዎ እንዲሰራ ፍላጎት ያላችሁ ወላጆች የልጅዎን ፎቶ በመያዝ ነገ መስከረም 21/2017 ት/ቤት መጣችሁ መፈረም ይጠበቅባቹሃል።


ማሳሰቢያ
- በባጃጅ የሚሄዱ ተማሪዎች መውጫ ካርዱን መያዝ ያለባቸው ሹፌሮች ናቸው።
- ነገ የመጨረሻ
ቀን ነው።

Pharo School - Assosa

25 Sep, 14:45


ለ9ኛ ክፍል አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች በሙሉ

ጉዳዩ፡- የመግቢያ ፈተና ቀንን ስለማሳወቅ፤

ፋሮ  ት/ቤት በ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ባለው ውስን ክፍት ቦታ ተማሪዎችን በመመዝገብ የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስኬድ ምዝገባ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ለመማር ፍላጎት ያላችሁ እና አማካይ የሚኒስትሪ ውጤት  50 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ሰኞ መስከረም 20/2017 ዓ.ም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ማክሰኞ መስከረም 21፣ 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
       
ት/ቤቱ

ማሳሰቢያ
•  የማይመለስ አንድ የ8ኛ ክፍል ካርድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፣

Pharo School - Assosa

18 Sep, 19:30


አስደሳች ዜና!
ውድ የፋሮ ት/ቤት ቤተሰቦች!
እንኳን ደስስስ አላችሁ!!!

ት/ቤታችን ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል!!👏👏👏👏👏🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇👌👌🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫 የትምህርት ቤታችን የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ወደ 9ኛ ክፍል ሙሉ በሙሉ (100%) ማለፍ ችለዋል።

እንዲሁም ክልሉ ካስፈተናቸው 17,700 ተማሪዎች መካከል የክልሉን 2ኛ (93)፣ 4ኛ(90) እና በአራት ተማሪዎች 6ኛ(89) ከፍተኛውን ውጤት በማስመዝገብ 6 ተማሪዎችን Top 10 ውስጥ በማስገባት ት/ቤታችን በክልሉ ታሪክ ሰርቷል።

በተጨማሪም ሁሉም ተማሪዎች ከ50 በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ስሆን 85% የሚሆኑ ተማሪዎቻችን ደግሞ ከ70 በላይ ማስመዝገብ ችለዋል።

የሁሉም  ተማሪዎቻችን አማካይ ውጤትም 77.44 ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህ ውጤት የመጣው በመምህራን እና ወላጆች እገዛ እንዲሁም በልጆቻችን ጥረት ስለሆነ ወላጆች፣ መምህራኖቻችን እንዲሁም ተማሪዎቻችን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!!!

እንዲሁም ለክልሉ ነዋሪዎች እና የፋሮ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ ደስ ብሎናል!
🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

ሁሌም ለላቀ ውጤት ተግተን እንሰራለን!!

Pharo School - Assosa

13 Sep, 16:42


ወድ የትምህርት ቤታችን ቤተሰቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን!
እንኳን ለ 2017 ዓም የት/ት ዘመን በሠላም አደረሳችሁ!!
የ2017 ዓ.ም ትምህር ቤት አጀማመር እና የሚያስፈልጉ ነገሮችን ከዚህ በታች በዝርዝር አስፍረናል።
👉 ትምህርት ቤታችን መስከረም 7/2017 ዓ.ም ለተማሪዎች ክፍት ይሆናል። በዕለቱ ተማሪዎች መማሪያ ክፍሎቻቸውን ያውቃሉ፣ ከመምህራኖቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ እንዲሁም የተለያዩ መመሪያዎችን ይሰጣሉ።
በዕለቱ ለግማሽ ቀን ብቻ ስለሚቆዩ ምሳ ይዘው አይመጡም።
👉 መስከረም 8 መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ነው።
ስለሆነም ተማሪዎች የሚከተሉትን ማሟላት አለባቸው።
1. ሙሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን አሟልተው መምጣት አለባቸው።
2. የትምህርት ቤቱን ንፁህ እና ያልተቀደደ ዩኒፍርም ለብሰው መምጣት አለባቸው።
3. ሙሉቀን ስለሚቆዩ ምሳ እና ውሃ ይዘው መምጣት አለባቸው።
4. ፀጉር ማንጨባረር፣ ጌጣጌጥ መልበስ እና ተገቢ ያልሆነ አለባበስ በፍፁም የተከለከለ ነው።
5. ያለፈቃድ እና ያለ በቂ ምክንያት መቅረት በፍፁም የተከለከለ ነው።
መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንልን።
ሠላም🙏

Pharo School - Assosa

11 Sep, 13:55


አስደሳች ዜና!
ውድ የፋሮ ት/ቤት ቤተሰቦች!
እንኳን ደስስስ አላችሁ!!!
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ሆሞሻ የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማለፍ ችለዋል!
ለትምህርት ቤቱ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ የክልሉ ነዋሪዎች እና የፋሮ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ ደስ ብሎናል!
🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ለላቀ ውጤት ተግተን እንሰራለን!

Pharo School - Assosa

11 Sep, 13:42


የተወደዳችሁ የፋሮ ት/ቤት ቤተሰቦች
እንኳን ለ2017 ዓ.ም በሰላም በጤና አደረሳችሁ!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

አዲሱ አመት በሀገራችን ሰላም የሚሰፍንበት፣ አንድነታችን የሚፀናበት፣ የበረከት እና የመባረክ አመት ይሁንልን🙏
መልካም በዓል!

Pharo School - Assosa

06 Sep, 14:41


ውድ የትምህርት ቤታችን ቤተሰቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን።
እንኳን ለ2017 ዓ.ም የት/ት  ዘመን በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
💥🔥💥⭐️💫💥🌟💥💫💥💥

ለተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶች

ከ 1ኛ - 4ኛ ክፍል
* 8 ባለ ሀምሳ ገፅ  ደብተር
* 2 ባለ 32 ገፅ ደብተር
* 1 የስዕል ደብተር
* 1 የእጅ ፅሑፍ ደብተር ባለ አራት መስመር
* 2 እርሳስ
* አንድ ፓኬት ባለቀለም እርሳስ
* 2  ላጲስ
* 2 መቅረጫ
* 1  እስኪርብቶ
*  1 ኮምፓስ
ከ 5-6  ክፍል

* 9 ባለ ሀምሳ ገፅ  ደብተር
* 1 ባለ 100 ገፅ  square ደብተር
* 1 የስዕል ደብተር
* 1 የእጅ ፅሑፍ ደብተር ባለ አራት መስመር
* 2 እርሳስ
* አንድ ፓኬት ባለቀለም እርሳስ
* 2  ላጲስ
* 2 መቅረጫ
* 1  እስኪርብቶ
*  1 ኮምፓስ

ከ 7 -8
* 9 ባለ ሀምሳ ገፅ  ደብተር
* 1 ባለ 100 ገፅ  square ደብተር
* እስኪርብቶ
* ኮምፓስ

ከ 9 -11

* 11ባለ መቶ ገፅ  ደብተር
* 1 ባለ 100 ገፅ  square ደብተር
* እስኪርብቶ
* ኮምፓስ

ብትችሉ የምትገዙት ደብተር Radical ወይም Sinarline ቢሆን ይመረጣል።

Pharo School - Assosa

20 Aug, 05:55


የ11ኛ ክፍል መግቢያ ፈተና አርብ ነሐሴ 17/2016 የሚሰጥ በመሆኑ አመልካች ተማሪዎች በእለቱ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን።
ፈተናው የ10ኛ ክፍል እንግሊዘኛ እና ሒሳብ ትምህርትን ያካተተ ነው::
መልካም ዕድል!