በእግር ኳስ ደጋፊዎች 12ተኛ ተጫዋች ናቸው በመባል ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ይህንን በእጃችን ለማስገባት ጫፍ የደረሰ ዋንጫ ለመውሰድ የእናንተ ተማሪዎቻችን ድጋፍ እጅጉን ስለሚስፈልገን ሀዋሳና አካባቢዋ ላይ የምትገኙ ተማሪዎቻችን ቡድኑ ለብሶ የሚገባው ቢጫ መለያ በመሆኑ፡ እናንተም ለድጋፍ ስትመጡ ማናቸውንም ቢጫ አልባሳትን በመልበስ፡ ቢጫ ባንዲራ እና ሌሎችም ሜዳውን በሚደምቁ በቢጫ ቀለም ያጌጡ ዲኮሮችን በመጠቀም ሜዳውን የጀርመኑ ክለብ Borussia Dortmund የሚጫወትበትን Signal Eduna Parknን እናስመስለዋለን፡፡
በቀጣይም በፋርማ ዲፓርትመንቶች መካከል የተማሪዎች ውድድር ለማካሔድ ሀሳብ ስላለ በእለቱ በርከት ብላችሁ ስትገኙና ስትደግፉ ያላችሁን የእግር ኳስ ፍቅርና ፍላጎት ስለሚገልጽ በቶሎ የእናንተንም ውድድር ለማስጀመር በእጅጉ ይረዳል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ ታሪካዊ ዕለት የኮሌጃችሁ ደጀን በመሆን የበኩላችሁን እንደምትወጡና ከመምህራኖቻቹ ጎን በመሆን ድጋፍ እንደምትሰጡ React በማድረግ ግለጹልን፡፡ ፋርማ የአሸናፊነት አርማ!
💪💪💪