来自 Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️ (@orthdoxswallper) 的最新 Telegram 贴文

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️ Telegram 帖子

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️
የኦርቶዶክስ የሆነ ለስልኮ ፎቶ ከፈለጉ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ይህንን ቻናል ለኦርቶዶክስ ቤተሰብ በመላክ ይተባበሩን@orthdoxswallper
5,952 订阅者
1,520 张照片
29 个视频
最后更新于 11.03.2025 07:43

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️ 在 Telegram 上分享的最新内容

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

22 Nov, 14:32

1,280

#የኦርቶዶክስአባቶችwallpaper ❤️❤️❤️ ❤️ ❤️❤️ ❤️❤️❤️ @orthdoxswallper
Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

21 Nov, 12:31

1,442

#የሚካኤልምስል
🔔#ኅዳር_⓬ ቀን ታላቁ #መልአክ_ቅዱስ_ሚካኤል በኢዮር ባለች በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአስሩ ነገድ መላእክት ላይ ❝#አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው❞ ። እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው #ቅዱስ_ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል ።


🥰እንኳን ለታላቁ ለሊቀ መላእክት ❝ ለቅዱስ ሚካኤል ❞ አመታዊ ክብረ ብዓል በሰላም አደረሳችሁ 🙏

የታላቁ መላአክ የቅዱስ ሚካኤል ጠቡቆቱ ፣ ምልጃው ፣ ደግነቱ ከእኛ ጋር ለዘላለም ፀንቶ ይኑር ❝አሜን❞። ቀናችን መገዳችን ስራችን ትምህርታችን ቅዱስ ሚካኤል ይባርክልን ❝አሜን❞።

መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ
❝ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ማሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ❞ ትንቢተ ዳንኤል ፲፥፲፫



                   ⓬አሜን⓬
Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

21 Nov, 09:09

725

ኅዳር ፲፪

❤️ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት❤️

ኅዳር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን የተራዳበት ቀን ነው።

ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው ።

ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው ። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ ።

እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ ። ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ።

ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ይማረን የቅዱስ ሚካኤል በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝️@orthdoxswallper✝️
✝️@orthdoxswallper✝️
Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

20 Nov, 17:35


Channel name was changed to «Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️»
Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

20 Nov, 15:58

1,154

#ሚካኤል ❤️❤️❤️
Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

19 Nov, 14:06

1,349

#ኦርቶዶክስጥቅሶች
Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

18 Nov, 17:05

1,439

#wallpaper
Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

17 Nov, 14:39


Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️ pinned «https://t.me/orth889 👆👆 ከታች ያለዉን የቻናሉ መወያያ ጉሩብ ነዉ ያልተቀላቀላችሁ በትህትና 🙏🙏 እንድትቀላቀሉና ጉሩቡን እንድናሳድገዉ🙏🙏»
Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

17 Nov, 14:38


Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️ pinned «https://t.me/Pottery3 https://t.me/Pottery3 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆የእናቶቻችን የስራ ዉጤቶች ስራዎች ናቸዉ ገብታችሁ እዩላቸዉ 🙏🙏🙏»
Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

17 Nov, 14:33

1,566

ኅዳር ፰

አርባዕቱ እንስሳ

ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ።

እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።

©ስንክሳር

@Orthdoxswallper
@orthdoxswallper