BYD ከድሮን አምራች ዲጂአይ ጋር በመተባበር “ሊንጊዋን” የሚል አዲስ በተሽከርካሪ ላይ የተገጠመ የድሮን ሲስተም አስተዋውቋል።
ይህ ስርዓት የድሮን ቴክኖሎጂን በቀጥታ ከተሽከርካሪዎች ጋር በማዋሃድ፣ አሽከርካሪዎች የአየር ላይ ምስሎችን እንዲይዙ፣ አካባቢውን እንዲከታተሉ እና በጉዞአቸው ላይ የመዝናኛ ክፍል እንዲጨምሩ በማድረግ የማሽከርከር ልምድን ለማሳደግ ያለመ ነው።
የሊንጊዋን ሲስተም ዋጋው 16,000 ዩዋን (በግምት 2,200 ዶላር) ሲሆን በተለያዩ የ BYD ሞዴሎች የሚካተት ነው። ፋንግ ቼንግ ባኦ ባኦ 8 ኦፍ-ሮደር ይህ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የመጀመሪያው ተሸከርካሪ ሆኗል።
የድሮን ሲስተም ለመቀበል የታቀዱ ሌሎች ሞዴሎች Yangwang U8፣ Fang Cheng Bao Bao 5፣ Titanium 3 (Tai 3)፣ Denza N9፣ BYD Tang L እና BYD Sealion 07 DM-i ናቸው።
"ሀገራችን ላይ የገቡት ከዚህ ውስጥ YangWang U8 እና Fang Cheng Bao 5 ስለሆኑ ምን አልባት እነዚህ መኪኖች ላይ ይህንን ቴክኖዎሎጂ የምንመለከት ይሆናል::" ዮናታን ደስታ
@OnlyAboutCarsEthiopia