***
ሚቴዩ ፣የካቲት 20/2017 ዓ.ም
ለተከታታይ ቀናት የማጣሪያ ውድድር ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ለፍጻሜ በቀረቡት ሁለት ቡድኖች መካከል በወቅታዊ የአገራችን የወደብ ጥያቄ ዙሪያ በማተኮር አለም አቀፍ ድንጋጌዎችን መሠረት ያደረገ እጅግ ማራኪና አስተማሪ በአጠቃላይ ታዳሚውን ያስደመመ ውድድር (ክርክር) ተደርጓል።
ምስለ ችሎቱን የዩኒቨርሲቲው ህግ ትምህርት ቤት አንጋፋ መምህራን(ዳኞች) የሆኑት በመሐል ዳኛነት ዳኛ ጌታሁን ተሾመ ጨምሮ ዳኛ ምንዳ ግርማ ፣መዝገቡ አቢይ፣እውነቱ ተስፋዬ እና ዳኛ ተግባሩ ተረፈ ክርክሩን በስርዓት የመሩት ሲሆን ምስለችሎቱን የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳት ዶ/ር ተረፈ ጌታቸው ፣ የአካዳሚክ ዳይሬክተር የሆኑት ጥምቀቴ አለሜ (ረ/ፕ)፣ መምህራን እንዲሁም ተማሪዎች እስከፍጻሜው ተከታትለውታል።
እንደህግ ትምህርት ቤቱ ዲን መምህርት ሮዚና መኮንን ገለጻ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ጊዜያት በአገር አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ውድድሮች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ዝና ያለውና በተለያዩ ጊዜያት የዋንጫ ተሸላሚ ስለመሆኑ ጠቁመው ፤የዛሬው ውድድር ዋና አላማ በቅርቡ በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት አገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ላይ ዩኒቨርሲቲያቸውን የሚወክሉ ተማሪዎችን ለመምረጥ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
በዛሬው ውድድር አሸናፊ ለሆነው የአምስተኛ አመት ተማሪዎች እንዲሁም በተለያዩ የውድድሩ መስፈርቶች ለተመረጡ ተማሪዎች የእውቅና የምስክር ወረቀት ከዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት እጅ የተቀበሉ ሲሆን በፍጻሜው ውድድር በbest ora list 1ኛ ተማሪ ፋሲል ዘለቀ እንዲሁም ከሴቶች female best ora list በመሆን ደግሞ ተማሪ ቅድስት ዘራአንበሳ አሸናፊ ሆነዋል።
በመጨረሻም ዶክተር ተረፈ ጌታቸው ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር የምስለ ችሎት (Moot court) ውድድር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል ፤ ከዚህም በዋናነት ተማሪዎች ከአቻዎቻቸው ጥሩ ልምድ እንዲቀስሙ ከማስቻሉም በላይ የሚገኙበትን ተቋም በማስተውወቅ በኩል ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጥ በንግግራቸው አስረድተው ይህ ፕሮግራም በዚህ መልኩ እንዲሳካ ለሰሩ የኮሌጁ መምህራን የተሰማቸውን አድናቆት በመግለጽ አመስግነዋል።
Mizan-Tepi University
Light of the green Valley!
facebook :https://www.facebook.com/p/Mizan-Tepi-University-MTU-100067612844902/
website: www.mtu.edu.et
telegram: https://t.me/mtueduet
Email: [email protected]
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/MTU_Main_Campus