أحدث المنشورات من Medina Tube || መዲና ቲዩብ (@medinatube) على Telegram

منشورات Medina Tube || መዲና ቲዩብ على Telegram

Medina Tube || መዲና ቲዩብ
3,667 مشترك
228 صورة
58 فيديو
آخر تحديث 01.03.2025 10:58

قنوات مشابهة

Ethio Menzuma
10,202 مشترك
Waataa Technology
1,388 مشترك

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة Medina Tube || መዲና ቲዩብ على Telegram


ሙሀመድ ይባላል....ﷺ

አሏህ ብሎ ያለው ቀና በል አትዘን
የሰላም የፍትህ አርማና ማዕዘን
ደግነት ብቻ ነው ሙሀመድ ያዘዘን

         የኛ ነብይ..ﷺ

ራሱን ለአሏህ ሽቅብ ቀና አድርጎ
ከረሂሙ ጌታ እዝነቱን ፈልጎ
በሙሽሪኮች በደል እየደረሰበት
ስሙ እየጎደፈ ዋሽተው ቀጥፈውበት
ፍፁም በሌለበት እየተወቀሰ
ጌታየ ህዝቦቼን ብሎ ያለቀሰ

        ሙሀመድﷺ

የስልጣኔ አርማ የእድገት ከፍታ
ስሙ እማይረሳ ለሰከንድ ላፍታ
እንኳን ላመነበት በመንገዱ ፀንቶ
አያውቅም ጠላቱን በክፋት አንስቶ

ከመጥፎ ከልክሎ መልካሙን ያሳያል
ከማንም ከምንም ሙሀመድ ይለያል

መከራው ሲጠና በአሏህ ይወከላል
ችግር ሲደራረብ ሀስቢየሏህ ይላል
መደምደሚያው ነብይ ስሙ ማን ይባላል?

«ውዶቼ ሶለዋት እናውርድ
   መልካም ኢስነይን


✍️የሙሂቡን ግጥም
         

@MEDINATUBE

በስሙማ ስንቱ ተፈረጀ💛

ሰላሚያዓላ ጀበል ማብራቱ
ፈሪ አይወድም ጎበዝ ነው ብርቱ
ኑሩ ያበራል ዓለምን ሞልቶ 👏
@MEDINATUBE
@medinatube

አሰላሙ አለይኩም😊 የመጀመርያው ግሩፓችን ስለተደለት አዲሱ ግሩፕ ነው ይቀላቀሉን ADD ❤️ በማረግ ቤተሰብ ይሁን!👍
@ethiomewild2

ሸምሲ ሰማኢ ጠይባ ምርጥ ሀድራ መንዙማ 😍❤️
@MEDINATUBE

ስለ ረሱል ምን ያህል እናውቃለን

ነብያቶች ባጠቃላይ በህይወት ባሉበት ጊዜ የሙሀመድ ነብይነት ካጋጠማቸው የእሱ ተከታይ እና አጋዥ ሊሆኑ ቃል ገብተዋል። እያንዳንዱ ነብይም ለተከታዮቹ ስለ ሙሀመድ ሳይናገር አላለፈም። በትክክለኛው ተውራትና ኢንጅል ውስጥ ሙሀመድ በመገለጫዎቹም ብቻ ሳይሆን በስሙም መጠቀሱ ለዚህ ግልፅ ማሳያ ነው።እንደ ወረቃ፣በሂራ፣ አቡ ተይሃን፣ ዐብደላህ ቢን ሰላም፣ ከዕቡ አልአህባር ፣ዐብደላህ ቢን ዐምር፣ የዐሙሪያው መነኩሴ እንድሁም የሩሙ ንጉስ ( ሂረቅል) አይነት የመፅሀፉ ባለቤቶች ስለሙሀመድ ምስክርነት መስጠታቸው ይሄንኑ አረጋጋጭ ነው። ሊላኩ አካባቢ ደግሞ የሙሀመድ መምጣት ወሬ በሰፊው ተሰራጨ። ጠንቋዮች ሳይቀሩ ስለሙሀመድ صلى الله عليه وسلم መተንበይ ጀምረው ነበር። ታዲያ የዚህ ወሬ መሠራጨት አንዳንዶች ሙሀመድን ዝግጁ ሆነው እንድጠብቁ ጥሩ እድል ፈጥሮላቸዋል። አንሷሮች እስልምናን እንድቀበሉ ፈር የቀደደላቸውም ይሄው ወሬ ነበር። ሰልማንም رضي الله عنه የመነኩሴውን ጥቆማ ተከታትሎ ሰለመ።
@MEDINATUBE

ስለ ረሱል ምን ያህል እናውቃለን?

ነብዩ صلى الله عليه وسلم እድሜያቸው 12 አመት ሲሞላቸው ከአጎታቸውና ከቁረይሽ ነጋዴዎች ጋር በመሆን ለንግድ ስራ ወደ ሻም ተጓዙ። ቡስራ በተባለች ሰፈር ሲደርሱ በሂራ የተባለ መነኩሴ ጋር ተገናኙ። በሂራ በስላሴ የማያምን የጥንታዊዉ ክርስትና እምነት ተከታይ ነው። ለመንገደኞቹ ሰላምታ ካቀረበ በኋላ በመካከላቸው በማለፍ የሙሀመድን እጅ ያዝ አደረገና “የዐለማቱ ሁሉ አለቃ ፣ የዐለማቱም እዝነት ይሄ ነው” ሲል ተናገረ። በምን እንዳወቀውም ሲጠይቁት እናንተ ዳገቱን እንደወጣችሁ መላው ዛፍና ድንጋይ ሱጁድ ሲያደርግ አየሁ። ይሄ ደግሞ ለነብይ ብቻ የሚሰጥ ስጦታ ነው። በመፅሀፋችን ላይ በጀርባው በኩል ከትከሻው ዝቅ ብሎ የነብይነት ማህተም እንዳለው ስለተነገረን በዚህም ማረጋገጥ እችላለሁ አለና ትከሻቸውን ተመለከተ። የእርግብ እንቁላል የሚመስለውን ማህተም ( ከፍ ያለ ስጋ) አገኘ። ከዚያም አቡጣሊብን ሩሞች ተንኮል ስለሚያስቡበት እባክህ ወደ መካ ይዘኸው ተመለስ ብሎ ተማፀነው። አቡ ጣሊብም የንግድ ስራውን በመተው ሙሀመድን ይዞ ተመለሰ።
@MEDINATUBE

በሼህ መሀመድ ሁሴን (ኮምቦልቻ)
👏 ሙሀመድ ባለጣው አምሳያው የታጣው።🥁🥁🥁🥁

👇👇👇👇👇👇👇👇👇ተቀላቀሉን
@MEDINATUBE

👳‍♂ሼህ አብድልወሀብ

#አላሁመሶሌ አላ ሙሀመዴ➋
ኑሪዚልጀላሌ ጀማሌ ጀማሌ
@MEDINATUBE

🎤ሼህ መሀመድ አወል ሀምዛ
ምርጥ መንዙማ
💞በስመላ

@MEDINATUBE

ያኢማመል ሀረም ከንዝ ሙጠልሰሙ

#የሸሆቹ_ሀድራ ሃያትትትት
@MEDINATUBE