ባንድ ምላስ መንታ ወሬ
----------------------
አንድ ሰሞን ማሬ ውዴ አይነት ጨዋታ ከሆነ አዳም ጋር ፎንቃ ቢጤ ጀምራ ሂወቴ መኖሬ ያለሱ ባዶ ነው...ንገሩት ናፍቆኛል ምናምን በሚሉ ፖስቶች
ፌስቡኩን፣
ቴሌግራሙን፣
ቲክቶኩን፣
ኢሞውን
የሚዲያውን መንደር እንዳለ...
የሮማንስ ቀበሌ ካላደረኩ በሚል ቀውጢ ስትል ቆይታ ወር እንኳ ሳይሞላው በውል በማይታወቅ ተልካሻ ምክንያት
ጥርግ በል፣
አንተ ብትሄድ ሌላ ይመጣል፣
ቀረሁብህ እንጂ አልቀረህብኝም,,,
ንገሩት አስጠልቶኛል"
ምናምን እያለች ፕሮፋይል በመቀያየር በቻይንኛ ድጋሜ በሚዲያ መንደር ከወንድ ነፃ ነኝ አይነት ማስታወቂያ የምታሸሙር ባንድ ምላስ መንታ ወሬ የምትቀምር ሴት ሳይ ሆዴን ያዞረኛል።
እግሬን ያጥወለውለኛል።
እህቴ ተረጋጊ በቃ ይህ አይነት ሙድ ከተበላበት ቆዬ ተነቅቶበታል ይልቅ ቆም ብለሽ አስቢና ለባልሽ ሚስት ሁኝ ሚስትነትን አምነሽ ኑሪበት ገና ስታገቢ ቢፈታኝ በሚዲያ ስሙን አጠፋዋለሁ በሚል የበቀል ስሜት ገብተሽ የራስሽን ህይወት አትመርዥ ፀፀቱ ለራስሽ ነው።
አሏህ ካዘነላቸው ውጭ የዚህች አይነት ሴቶች ናቸው በንፁህ ወንድ ህይወት ውስጥ ገብተው ህይወቱን ያመሰቃቅሉና በደለኝ ፣ጨቆነኝ እያሉ በውሸት ሌሎች እህቶች ትዳር እንድጠሉ የሚያደርጉት የዚህን ፀባይ ባለቤት የሆኑ ሴቶችን ተጠንቀቋቸው።
....ኑረዲን
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi