Latest Posts from ለሙስሊሟ እህቴ (@lemuslimuaehte) on Telegram

ለሙስሊሟ እህቴ Telegram Posts

ለሙስሊሟ እህቴ
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
بسم الله الرحمن الرحيم
በቻናላችን
ዲናዊ እውቀቶች
ስለሒጃብ ማብሪራያዎች
ስለ ትዳር ምክሮች



እናንተን ያዝናናል ያስተምራል የምንላቸው
በአላህ ፍቃድ ለናንተ እናደርሳለን።

ከናንተ ሚጠበቀው join ማረግ ነው።
@lemuslimuaehte

for any comment 👇
@fitayebot
3,409 Subscribers
1,032 Photos
199 Videos
Last Updated 01.03.2025 09:45

Similar Channels

ISLAMIC-QUOTES✍
2,371 Subscribers
ሱናህ(السنة)
1,244 Subscribers

The latest content shared by ለሙስሊሟ እህቴ on Telegram


📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 2⃣9⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣6⃣

ረመዷን ታላቁ እንግዳ!!
---------------------

👉ይህን ታላቅ እንግዳ ለመቀበል ከወሬ ያለፈ ተግባራዊ ቅድመ-ዝግጅት ያስፈልገናል።

👉ራሳችንን ነፍሳችንን ተግባራችንን ፈትሸን ኸይርን በማብዛት ከባለፈው የተሻለ ረመዷን ለመፆም እንዘጋጅ!!

👉►የኸይር ወር ነውና ሶደቃ፣ቁርዓን፣መሰል መልካም ነገሮችን እናብዛ...!!

⭕️በሸዕባን 22 /1446 ھ በወንድም ኑረዲን ቻናል የተደረገ ወሳኝ ማስታወሻ ይደመጥና ይሰራጭ ሐያ....!!


🎙በወንድሜ አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ ሀፊዞሁሏህ

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

@lemuslimuaehte

ፈገግተኛው ጀናዛ
****


(ምን ብታይ ይሆን እንዲህ ፈገግ ያልከው)
ጌታዬ ሆይ! ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ
አድርግልኝ

መዲነቱል ሙነወራ ውስጥ ጀናዛ በማጠብ ሥራ ላይ የተሠማራ አንድ ግለሠብ በሬሳ አጠባ ወቅት ከገጠሙት ድንቅ ነገሮች መካከል አንዱን እንዲህ ሲል ይተርክልን ይዟል…

"ተክለ ሰውነቱ ከሲታ ሲበዛ የቀጨጨ አካሉ በተበጫጨቀ ልብስ የተሸፈነ ካገኘ በልቶ ካጣም ባዶ ሆዱን የሚያድር የአላህ ባርያ።

ለሊት ለተሀጁድ ቆሞ የጌታውን ቁርአን
እያነበነበ የሚያነጋ። ከሰዎች አይቀላቀልም ብቸኝነት የህይወት ጌጡ ናት። በተበጫጨቀ ጨርቅ የተሸፈነ ጀናዛውን ወደ ማጠቢያ ክፍሉ ይዘነው ገባን በተዘረጋው የጀናዛ ማጠቢያ እንጨት ላይ አስተኝተን ልብሱን አወለቅንለት።

ጆሯችን መልካም ይሰማ ዘንድ በማሰብ ቁርአን በስፒከር ከፍ አድርገን ከፍተን ማጠብ ጀመርን።

ነፍሴ በእጄ በሆነችው ጌታ እምላለሁ ጀናዛው የቁርአን አንቀፆቹን ሲሰማ ፈገግ አለ ከፈገግታው የተነሳ ጥርሶቹ ተከፍተው ድዶቹ ይታዩ ጀመር።

ቁርአኑን ስንዘጋው የተከፈቱት ነጫጭ ጥርሶቹ ይከደናሉ የቁርአኑን ድምፅ ከፍ ስናደርገው
ፈገግታና ሳቅ ከፊቱ ላይ ይታያል። በግርምት ተውጠን የሱን መልካም ኻቲማ እንዲወፍቀን አላህን እየተማፀንን አጥበን ጨረስን" ይሉናል
የታሪካችን አቅራቢ።

ገጠመኙን እንዲህ በማለት ቀጠሉት "ከተቀበረ ከአስራ ሁለት አመታት በኋላ የመቃብሩ ስፍራ ለልማት ተፈለገና ተለዋጭ ቦታ ተሰጠን በቅርብ ጊዜ የሞቱትን አፅማቸውን አውጥተን ወደ አዲሱ የመቃብር ስፍራ ወሰድን።

ከቀናት በኋላ ተጠራንና ወደቦታው አቀናን ከአንድ ጉድጓድ አጠገብ ስራውን ያቆመ አንድ ዶዘር ወዳለበት አካባቢ ስንጠጋ ደስ የሚል ጠረን ይሸተን ጀመር ወላሂ ከፈኑ እንኳ አልበሰበሰም ሰውነቱም አልተቀየረም ከሰአታት በፊት የተቀበረ አዲስ ጀናዛ ነበር የሚመስለው አፈር አካሉን መብላትን እንቢ አለች ቁርአንን ታቅፎ የኖረን ሰውነት ለመብላት እንዴትስ ያስችላታል?!

ከፈኑን ስንገልጠው ያ ቁርአን ሲሰማ የሚንቀሳቀሰው ጀናዛ ነበር"

«የውመል ቂያማ ለቁርአን ባልደረባ አንብብ ደረጃውንም ከፍ ብለህ ውጣ ያንተ ማረፊያ የመጨረሻ አንቀፅ ቀርተህ በቆምክበት ስፍራ ላይ ነው ይባላል»

እውነተኛ ታሪክ እንጂ ልቦለድ አይደለም
አንብቦ ለሌላ ባካፈለ ሰው ላይ ሁሉ የአላህ እዝነት ይስፈንበት

• ሸዕባን ከረመዷን ወር በፊት መግቢያ በር ብቻ አይደለም ።

• ሸዕባን ኸይር ከሚመረትበት የበለጠ ኸይር ወደሚመረትበት መሸጋገሪያ ድልድይ ነው።

• ሸዕባን ከፊት ለፊታችን ትልቅ ወር እየመጣ እንደሆኑ ማብሰሪያ ፊሽካ የተዘጋጁ ደወል ነው።

• ሸዕባን ከረመዷን በፊት በቀሩት ጥቂት ቀናት ነፍስን ማዘጋጃና መለማመጃ መድረክ፤ ከብዙ ዝንጋቴ በኋላ ወደ አላህ የመመለሻ ወር ነው።

• ሸዕባን ከኖርማልና ከተለመደው የዒባዳ ሁኔታችን ወጥተን ለተሻለ መታዘዝ መስፈንጠሪያ ቦርድ ነው።

• ረመዷን ያለ-አንዳች መንፈሳዊ ዝግጅት ዝም ተብሎ የሚገባበት ወር አይደለም ።

የረመዷንን ለዛና ጥፍጥና ማጣጣም የፈለገ ከወዲሁ ሸዕባን ላይ ነፍሱን በፆም፣ በቁርአን ፣ በዚክር፣ በሰደቃ፣ በመልካም ሥራ ያለስልስ።በውስጡ ኢስቲግፋር፣ ዱዓና ዚክር አብዙ፣ ቁርአን አብዝታችሁ ቅሩ፣የበደላችሁትን ካሱ፣ ለበደላችሁ ይቅር በሉ፣ የወሰዳችሁት የሰው ሐቅ ካለ መልሱ።

አላህ ሆይ ፅናትን ለግሰን። ሸዕባንን ባርክልን። ለረመዷን ደርሰው፣ ፆመውት፣ ፆማቸውም ተቀባይነት ከሚያገኙት አድርገን።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

الكهف
وَاصْبِرْ نَفْسَكَ مَعَ الَّذِينَ يَدْعُونَ رَبَّهُم بِالْغَدَاةِ وَالْعَشِيِّ يُرِيدُونَ وَجْهَهُ وَلَا تَعْدُ عَيْنَاكَ عَنْهُمْ تُرِيدُ زِينَةَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَلَا تُطِعْ مَنْ أَغْفَلْنَا قَلْبَهُ عَن ذِكْرِنَا وَاتَّبَعَ هَوَاهُ وَكَانَ أَمْرُهُ فُرُطًا 28
ነፍስህንም፤ ከእነዚያ ጌታቸውን ፊቱን (ውዴታውን) የሚሹ ኾነው በጧትና በማታ ከሚግገዙት ጋር አስታግስ፡፡ የቅርቢቱንም ሕይወት ሽልማት የምትሻ ሆነህ ዓይኖችህ ከእነሱ (ወደ ሌላ) አይለፉ፡፡ ልቡንም እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውን ፍላጎቱንም የተከተለውን ነገሩም ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ፡፡

ኪታብ (ቁርዐን)
http://onelink.to/amharicquran

የቀልብህን መስተካከል በፈለግክ ጊዜ፤ ምላስህን በመጠበቅ አግዛት።

ውሎህ መልካም ይሆን ዘንድ ጉዞህን ከነዚህ አካላት ጋር አድርግ:-
-አላህን የሚፈራና አመስጋኝ ከሆነ አካል ጋር
-ንቁና አዋቂ ከሆነ አካል
-ከስህተቱ ተመላሽ ከሆነ አካል
-ቅን አመለካከት ካለው አካል

ሂጃብ/ኒቃብ፡

ሴት ልጅ በዱንያ ከባለጌዎች ተንኰል፡ ለከፋ፡ ጉንተላ፡ ችግር...

በአኼራ ደግሞ ማቀጣጠያዋ የሰው ልጅና ድንጋይ ከሆነው ከጀሃነም እሳት የምትጠበቅበት ጋሻ ነው።

የሴት ልጅ ነፃነት ያልለው ትክክለኛ የሴት ልጅ ሂጃብ በመልበስ ነው።

ሴት ልጅ ከሂጃብዋ በተራቆተች ቁጥር፡ ለዱርዬዎችና ለጀሃነም እሳት መግጋለጧ/መቅረቧ አይቀሬ ነው።

~የራስሽ መርህ ይኑርሽ!
~~

~ትክክል እስከሆንሽ ድረስ በህይወትሽ ማንንም ጣልቃ አታስገቢ! ያንቺ ህይወት ያንቺ ብቻ ነው።

~የራስሽ መርህ....አቋም ይኑርሽ.....የመከረሽ .....እንዲህ አድርጊ.....አይዞሽ ያለሽ ሁሉ አብሮሽ ይዘልቃል ወይንም ደግሞ ላንቺ መልካም አሳቢ ነው ማለት አይደለም።

~ለቀረበሽ ሁሉ አንቺነትሽን በማብራራት ላይ አትድከሚ......ማንነትሽንም በጣም ግልፅ አታድርጊ!

~በሆነ መንገድ ስትጓዢ ትክክል እንዳልሆነ ከተረዳሽ ያን መንገድ ከመጓዝ አቁሚ።

~ራስሽን አስከብሪ....በማይመጥንሽ ቦታ ላይ አትገኚ.......ተለማማጪ አትሁኚ......ከአሏህ እንጂ ከሰው ብዙ አጠብቂ።

~ዋጋ መክፈል ላለብሽ ነገር ወደ ኋላ ሳትይ ዋጋ ክፈይ...... በሰው ግን አትመሪ! ልክ ገደል ላይ እንዳለች ዛፍ በሰው ወሬ አትወዛወዢ።

~ያንቺ ህይወት ያንቺ ብቻ ነው። ያለእርሱ መኖር ማትችይ ሚመስላቸውን ሰዎች እንዴት ያለእነርሱ መኖርና ስኬታማ ጀግና ሴት መሆን እንደምትችይ በደንብ አሳያቸው።
𝓾𝓶𝓾 𝓶𝓮𝓻𝔂𝓮𝓶✍️

https://t.me/medi_bint_seid_umu_meryem