JUECSF Main & Beco (@juecs_fellowship)の最新投稿

JUECSF Main & Beco のテレグラム投稿

JUECSF Main & Beco
ይህ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስትያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማህበር (EvaSUE) የጅማ ዩኒቨርስቲ (Main and Beco Campus) ወንጌላውያን ክርስትያን ተማሪዎች ህብረት የመገናኛ የtelegram channel ነው


ለማንኛውም ጥያቄ :
@juecsfmainbeco
0936281818

ንግድ ባንክ አካውንት
1000306692147
(Naol Ararsa and/or Tigist Dereje)
1,512 人の購読者
1,345 枚の写真
19 本の動画
最終更新日 09.03.2025 12:13

類似チャンネル

Amharic Spritual Books
4,646 人の購読者
Blaze Movement
1,559 人の購読者

JUECSF Main & Beco によってTelegramで共有された最新のコンテンツ

JUECSF Main & Beco

15 Feb, 06:10

1,024

ሰላም ቅዱሳን !

ዛሬ(ቅዳሜ ) እንደተለመደው 11:30 ላይ የአጠቃላይ ህብረታችን የአምልኮ ጊዜ ይቀጥላል። ስለሆነም ሁላችንም ማስታወሻ እና መፅሀፍ ቅዱሳችንን እየያዝን  በአንድነት ሆነን ጌታን ለማምለክ በጊዜ እንድንገኝ ስንል በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።

“እግዚአብሔር አምላክሽ በመካከልሽ አለ፤ እርሱ ብርቱ ታዳጊ ነው፤ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩ ያሳርፍሻል፤ በዝማሬም በአንቺ ላይ ከብሮ ደስ ይሰኛል።””
  — ሶፎንያስ 3፥17 (አዲሱ መ.ት)

ዛሬ(ቅዳሜ)- 11:30-2:00
💒መሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ

ተባረኩ!

@JUECS_Fellowship
JUECSF Main & Beco

08 Feb, 05:13

1,231

የተወደዳችሁ  ቤተሰቦቻችን

ዛሬ(ቅዳሜ ) እንደተለመደው 11:30 ላይ የአጠቃላይ ህብረታችን የአምልኮ ጊዜ ይቀጥላል። ስለሆነም ሁላችንም ማስታወሻ እና መፅሀፍ ቅዱሳችንን እየያዝን  በአንድነት ሆነን ጌታን ለማምለክ በጊዜ እንድንገኝ ስንል በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።

“እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም።”
— ምሳሌ 19፥23

ዛሬ(ቅዳሜ)- 11:30-2:00
💒መሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ

ተባረኩ!

@JUECS_Fellowship
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 10:00

1,265

☕️ Coffee Challenge: Day #5 ☕️

ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።
        ምሳ 19: 17

💰 ዛሬ ቡና እና ሻይ ባለመጠጣት 10 ብር ይለግሱ!

🎯 አላማው በPurelove team የሚሰሩ ስራዎችን ለመደገፍ ገቢ ለማሰባሰብ ነው።

ስለተሳተፋቹ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ  !
💙 Pure Love Team 💙
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 09:37


JUECSF Main & Beco pinned «»
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 08:25

990

👆👆ነገ (ቅዳሜ ) ባለው የ ህብረት ጊዜ በህብረት ለመዘመር የተመረጡ መዝሙሮች ናቸው እየሰማችኋቸው እንድትቆዩ ይሁን::
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 08:24

1,163

የደረቁ አጥንቶች
ህይወት የሌላቸው
እግዚአብሔር ስትመጣ
በህይወት ኑሩ አልካቸው

ድምፅህን ይሰማል የሞተው ነገር
የማይታዘዝ የለም አንተ ስትናገር
ለሰው የማይቻል ለአንተ ይቻላል
የደረቀው አጥንት ታላቅ ህዝብ ይሆናል

ትችላለህ2
የሞተውን ነገር ትቀሰቅሳለህ
ትችላለህ
ይቻልሃል2
የሌለውን ነገር ፈጠረህ ታኖራለህ ይቻልሃል

የሞት ጣር ሲይዘኝ
የዓመፅ ፈሳሽ ሲያስፈራኝ
በጨነቀኝ ጊዜ አምላኬን ጠራሁኝ
ከመቅደሱም ሰማኝ
ጩሀቴን አደመጠ
ሰማይን ዝቅ አድርጎ
አምላኬ ወረደ

ከስሞች ሁሉ በላይ ስምህ እጅግ ከፍ ያለነው
ለዚስም ማይገዛየማይታዘዝማነው
ኢየሱስ የሚለው ስም የፀና አለቴ ነው
ስሙን ጠርቼ በእምነት መች አፍሬ አውቃለው
ኢየሱስ ስልህ ስምህን ስጠራ
ያስጨነቀኝ ተጨነቀ ያስፈራራኝ ፈራ
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 08:24

887

ወዶ አይደለም ፍጥረት ሰዎች የሚርበደበደው
ከወዲህ ተጠርቶ ከማዶ ይሰራል
ድንገት ደርሶ የጠላትን ምሽግ ያሸብራል

አዝ፦ ኢየሱስ የሚለው ሥም ብርቱ ጉልበት አለበት
አይቻለሁ ጠላቶቼ ሲመታ ሲያንቀጠቅጥ (2x)

እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው
ከሥም ሁሉ በላይ ሥምም የተሰጠው
በሰማይም ኢየሱስ ነው
በምድርም ኢየሱስ ነው
ከምድር በታች ኢየሱስ ነው
በሁሉ ላይ ኢየሱስ ነው (2x)

የበሽታ ብርታት የደዌ ጉልበት
አይፈልግም የጌታ ሥም እንዲጠራበት
በሥጋ ለባሽ ላይ የሚበረታው
ያውቃል ከተጠራ ሥሙ እንደሚነቅለው

አዝ፦ ኢየሱስ የሚለው ሥም ታላቅ ጉልበት አለበት
አይቻለሁ ለህመሜ ሲሆን መድኃኒት (2x)

እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው
ከሥም ሁሉ በላይ ሥምም የተሰጠው
በሰማይም ኢየሱስ ነው
በምድርም ኢየሱስ ነው
ከምድር በታች ኢየሱስ ነው
በሁሉ ላይ ኢየሱስ ነው (2x)

የመከራን ጭጋግ የሚችል መግፈፍ
በእውነተኛው በረከት የሚያትረፈርፍ
የባዶ ሸለቆ የመሙላት ሚስጥር
ሲጠራ ነው የኢየሱስ ሥም በታላቅ ክብር

አዝ፦ ኢየሱስ የሚለው ሥም ደግነትም አለበት
አይቻለሁ በጓዳዬ ሲሆንልኝ በረከት (2x)

እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው
ከሥም ሁሉ በላይ ሥምም የተሰጠው
በሰማይም ኢየሱስ ነው
በምድርም ኢየሱስ ነው
ከምድር በታች ኢየሱስ ነው
በሁሉ ላይ ኢየሱስ ነው (2x)
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 08:23

475

አዝ ፣
 ::ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ
ወደር ፡ የማይገኝልህ
ከሞት ፡ ያድናል ፡ ስምህ ፪X

ጌታዬ! ስምህ ፡ ኃይል ፡ አለው
አጋንንትን ፡ ይቀጠቅጣል
ለስሜትም ፡ ከመገዛት
ከማይረባም ፡ ልማድ ፡ ያላቅቃል
ጥላቻንም ፡ አስወግዶ
ሁሉን ፡ አንድ ፡ ያደርጋል ፡ በፍቅር
መራራን ፡ ሕይወት ፡ ለውጦ
ያጣፍጠዋል ፡ እንደማር

አዝ ፣
 ::ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ
ወደር ፡ የማይገኝልህ
ከሞት ፡ ያድናል ፡ ስምህ ፪X

በነፍስ ፡ በሥጋ ፡ ሥልጣን ፡ አለህ
የበሽታን ፡ ሥር ፡ ትነቅላለህ
የታወረውን ፡ ዓይን ፡ አብርተህ
የጐበጠውን ፡ ታቃናለህ
ፍፁም ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ስምህ ፡ ያድናል
የተጨነቁትን ፡ በሕመም
ከድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ያወጣል
ወደሚደነቅ ፡ ብርሃን ።

አዝ ፣
 ::ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ
ወደር ፡ የማይገኝልህ
ከሞት ፡ ያድናል ፡ ስምህ ፪X

ስምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው
ጠልቆ ፡ ወደ ፡ ውስጥ ፡ ይገባል
የደረቀውን ፡ አጥንት ፡ አረስርሶ
ስብራትን ፡ ይጠግናል
ሽባውን ፡ አዘልለህ
የዛለውን ፡ ጉልበት ፡ ታጸናለህ
ልብን ፡ ኩላሊትን ፡ መርምረህ
ለደካማ ፡ ኃይልን ፡ ትሰጣለህ ።

አዝ ፣
 ኢየሱስ ፡ ሆይ...

በዕምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ የቀረበ
በሕያው ፡ ስምህ ፡ ይድናል
ከሞት ፡ ባሻገር ፡ ያለውን
የዘላለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳል
ቸሩ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
በዕውነት ፡ አንተ ፡ ፍቅር ፡ ነህ
ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ!
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ ።

አዝ ፣ ኢየሱስ ፡ ሆይ...
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 08:23

405

ኢየሱስ የሚለው ስምህ
ልዩ ትርጉም አለው ለእኔማ
ስጠራው ስደጋግመው (2x)

መጽናኛዬ ነው መበርቻዬ ነው ሆ!
ከፍታዬ ነው መነሻዬ ነው ሆ!
መጽናኛዬ ነው መበርቻዬ ነው ሆ!
ከፍታዬ ነው ስሙ ኢየሱስ የሚለው

አዝ:እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስምህ

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (4x)
በስምህ ውስጥ አለ ሰላም
በስምህ ውስጥ አለ
በስምህ ውስጥ አለ በረከት
በስምህ ውስጥ አለ
በስምህ ውስጥ አለ ኃይል
በስምህ ውስጥ አለ
ኢየሱስ ኢየሱስ በእምነት ላለ
ከሞት የሚያስጥል

(አንተን) ደብቄ እንኳን፡ እራሴን ላሳይ
(እየሱሴ) እንደው በአጋጣሚ ስምህን ሲያነሱ ሳይ
(እየሱሴ) እንባ ይቀድማኛል ምሆነውን አጣለሁ
(እየሱሴ) ፊቴ ድቅን ይላል ያረክልኝ ሁሉ
(እየሱሴ) ቆሜ አደባባይ ገና አወራዋለው
(እየሱሴ) በስምህ አላፍርም አለም ሁሉ ይስማው
(እየሱሴ) ክብርስ ቢሉ የቱ ክብሬ ነው
(እየሱሴ) ሁሉን ያገኘሁት ስምህን አምኜ ነው

አዝ:እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስምህ


በስምህ ውስጥ አለ ሕይወት
በስምህ ውስጥ አለ
በስምህ ውስጥ አለ ክብር
በስምህ ውስጥ አለ
በስምህ ውስጥ አለ ስልጣን
በስምህ ውስጥ አለ
ኢየሱስ ኢየሱስ በእምነት ላለህ
ታሪክ የሚቀይር

ስምህ መፍትሄ ነው ለጥያቄ ሁሉ
(እየሱሴ) ኧረ ማን አፍሯል በስምህ ተማምኖ
(እየሱሴ) የስምን ጉልበት እኔም አውቀዋለው
(እየሱሴ) በስምህ ታምኜ ያለፍኩት ስንቱን ነው
(እየሱሴ) ለሞተው ነገር ሕይወት የሰጠህ
(እየሱሴ) ያበቃው ነገር ተስፋ እየቀጠለ
(እየሱሴ) ብዙዎች ሲጠፉ በሕይወት ያለሁት
(እየሱሴ) ታምኜው ነው ስምህን እዚህ የደረስኩት

ኢየሱስ ኢየሱስ ብዬ ስለው ብዬ ስለው
ሃይሌ ይታደሳል በረታለሁ በረታለሁ
ኢየሱስ ኢየሱስ ብዬ ስለው ብዬ ስለው
ከክብር ወደ ክብር እሻገራለሁ እጨምራለሁ
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 08:23

350

ሃሌሉያ እያሉ መላዕክት በሙሉ
ኢየሱስ ለሚል ስም ይንበረከካሉ
አይነፃፀርም ከተዋረዱቱ
ስሙ ከፍ ያለ ነው በሰማይ ካሉቱ
ልቆ ከፍ ያለ የተከበረ
በሰማያት ላይ አንድ ስም አለ
ስሙን ሊያከብር ጰራቅሊጦስ
ከሰማይ መጥቷል መንፈስ ቅዱስ

በስሙ ላይ (ክብር አለ)
ክብር አለ (ክብር አለ)
ማዳን አለ (ክብር አለ)
ፍቅር አለ (ክብር አለ)
እዚህ ስም ላይ (ክብር አለ)
ዘይት አለ (ክብር አለ)
ማዳን አለ (ክብር አለ)
ቅባት አለ (ክብር አለ)

የትኛው ተራራ ነው
ስሙ ሲጠራ የሚቆመው
የትኛው ሸለቆ ነው
ይኼ ስም የማይሞላው
የትኛው በሽታ ነው
በዚህ ስም ፊት የሚቆመው
የትኛው ሰይጣን ነው
ስሙ ሲጠራ የሚቆመው

በስሙ ላይ (ክብር አለ)
ክብር አለ (ክብር አለ)
ቅባት አለ (ክብር አለ)
ማዳን አለ (ክብር አለ)
የሱ ስም ላይ (ክብር አለ)
ክብር አለ (ክብር አለ)

ቅዱስ ስሙን አመልካለሁ ለሌለው እኩያ
አሁንም ክብር ይሁን ለኢየሱስ ስም ሃሌሉያ

እውር የሚያበራ ሽባን የሚተረትር
ከአብ የተሰጠን የክርስቲያን በትር
ጻድቅ ሰው ጠርቶ መች ተሸነፈ
ክፉ መች አገኘው እንዳሰፈሰፈ
 
እዚህ ስም ላይ (ክብር አለ)
ፈውስ አለ (ክብር አለ)
ታምራት አለ (ክብር አለ)
ህይወት አለ (ክብር አለ)
ድነት አለ (ክብር አለ)
ከፍታ አለ (ክብር አለ)

ክብር አለ (ክብር አለ)

የኢየሱስ ከስሞች ሁሉ በላይ ነው
እንኳን በምድር መንግስተ ሰማይ
ሁሉ አሻቅቦ ሚያየው ወደ ላይ
የኢየሱስ ስም የስሞች ማማ
ፃድቅ ጀግኗል ስሙን ሲሰማ

ክብር አለ (ክብር አለ)