በስምህ ውስጥ ሞገስ
በስምህ ውስጥ ድል አለ
በስምህ ውስጥ ፈውስ
የጸና ግምብ ነው ስምህ የጻድቅ መሸሻ
ከዚህ ዓለም ግብግብ መሸሸጊያ ዋሻ
ከድካም ህመሜ የምፈወስበት
ኢየሱስ ያንተ ስም መድሃኒት አለበት
ኢየሱስ ኢየሱስ እግዚአብሔር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃን አብሪ ስም አለህ
ስምህ ማንነትህ ማንነትህ ስምህ
እንደተጠራህበት እንደዚያው መሆንህ
አዳኝ ሲሉህ አዳኝ ነህ ህይወት ሲሉህ ህይወት
ኢየሱስ ያንተ ስም እውነተኛ እውነት
ኢየሱስ ኢየሱስ እግዚአብሔር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃን አብሪ ስም አለህ
በሰልፉ ሜዳ ላይ በውጊያው መንደር
ስምህ የጦር እቃችን የማይበገር
የልጆችህ አንገት ቀና የሚልበት
ኢየሱስ ያንተ ስም ታላቅ ሃይል አለበት