IU Accounting and Finance Department @iuacfn2013 Channel on Telegram

IU Accounting and Finance Department

@iuacfn2013


A communication platform of Injibara University Accounting and Finance Department with its students of any program.

IU Accounting and Finance Department (English)

Welcome to the IU Accounting and Finance Department Telegram channel! Here, students of any program within the department at Injibara University can come together to communicate, share information, and stay connected. The channel, with the username @iuacfn2013, serves as a valuable resource for students seeking updates, announcements, and support related to their accounting and finance studies.nnWho is it for? This channel is specifically designed for current students, alumni, and faculty members of the Accounting and Finance Department at Injibara University. Whether you are pursuing a degree in accounting, finance, or any related field, this channel is the perfect platform for you to engage with others who share your academic interests.nnWhat is it? The IU Accounting and Finance Department Telegram channel is a communication hub where members can stay informed about departmental events, job opportunities, internships, and academic resources. It also serves as a space for students to ask questions, seek advice, and connect with their peers outside of the classroom.nnWe invite you to join our growing community on Telegram and become a part of the conversation. Stay up to date with the latest news, network with fellow students, and enhance your academic experience with the support of your department. Don't miss out on this valuable opportunity to engage with the IU Accounting and Finance Department!

IU Accounting and Finance Department

08 Nov, 14:16


2015 E.C. Academic Calendar

IU Accounting and Finance Department

26 Dec, 14:29


#የጥሪ ማስታወቂያ
#ለዩኒቨርሲቲያችን የመደበኛ መርሀ-ግብር ተማሪዎች በሙሉ
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሥራ እንዲቀጥል በመወሰኑ 1ኛ እና 2ኛ ዓመት እንዲሁም 3ኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪዎች ጥር 02 እና 03 ቀን 2013 ዓ.ም ሪፖርት እንድታደርጉና ትምህርታችሁን እንድትጀምሩ እናሳስባለን።
#የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት

IU Accounting and Finance Department

10 Dec, 13:40


ቅዳሜ (03/04/2013) ጀምራችሁ የምትገቡ ተማሪዎች አሳይመንታችሁን
1.ተመራቂ ተማሪዎች በ10 ቀን ዉስጥ ለመምህሮቻቸሁ ገቢ እንድታደርጉ
2. 2ኛ ዓመት ኤክስቴንሽን ተማሪዎች እስከ ሚቀጥለው ሳምንት ለመምህሮቻቸሁ ገቢ እንድታደርጉ ::
ማሳሰቢያ: ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ገቢ ለማድረግ የመጣ ተቀባይነት የለውም።

በደህና ግቡ

IU Accounting and Finance Department

04 Dec, 13:51


የእንጅባራ ኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ከታኅሣሥ 3-4/2013 ዓ.ም እንድትገቡ ተወስኗል።
#የ1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎችን የመግቢያ ቀን በሌላ ማስታወቂያ የምንሳውቅ ይሆናል።

IU Accounting and Finance Department

04 Nov, 13:54


#ለዩኒቨርሲቲያችን ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከጥቅምት 27 እስከ 29/2013 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ጥሪ የተደረገላችሁ የዩኒቨርሲቲያችን ተመራቂ ተማሪዎች አሁን ካለው ሀገራዊ ሁኔታ አንጻር ላልተወሰነ ጊዜ ባላችሁበት እንድትቆዩ እያሳሰብን የመግቢያ ቀን በማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
#እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

IU Accounting and Finance Department

04 Nov, 13:20


ውድ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የመመለሻ ቀናችሁ አሁን ባለው የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፡፡
የመግቢያ ቀናችሁን ወደፊት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

Please all, share this information to all your friends as fast as possible. I tried to call for some of them but most students'phone is not working.

IU Accounting and Finance Department

04 Nov, 06:22


ውድ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የመመለሻ ቀናችሁ አሁን ባለው የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፡፡
የመግቢያ ቀናችሁን ወደፊት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

IU Accounting and Finance Department

03 Nov, 13:53


Final Calendar

IU Accounting and Finance Department

21 Oct, 15:19


You well come our GC students.

IU Accounting and Finance Department

21 Oct, 15:18


Dears
Greetings
Injibara University will be welcoming graduating batches from Tikimit
27 to 29/2013 E.C

IU Accounting and Finance Department

02 Oct, 19:35


ለዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች

በርካታ ተማሪዎች ተመራቂ ተማሪዎች መቸ እንደምገባ ንገሩን እያላችሁ በተለያዬ ሁኔታ ጥያቄ እያቀረባችሁ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በሳ/ከፍ/ት/ሚኒስቴር የተሰጠው አቅጣጫ ዩኒቨርሲቲዎች እስከ መስከረም 25/2013 ዓ.ም ድረስ ሙሉ ቅድመ ዝግጅታቸውን እንዲጨርሱና ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ቅድመ ዝግጅቱን ባቋቋመው ኮሚቴ እየዞረ ዩኒቨርሲቲዎችን አረጋግጦ ተፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ አሟልተዋል መጀመር ትችላላችሁ ሲል ብቻ መክፈት እንደሚችሉ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ዩኒቨርሲቲያችንም የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የሚመለከተው ኮሚቴ አረጋግጦ ጀምሩ ሲል በዩኒቨርሲቲው የመግቢያ ቀኑ የሚወሰን እና ጥሪ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፍ መሆኑን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁ እያሣሠብን እስከዚያ ጊዜ ድረስ ግቢ ከተገባን በኋላ የሚኖረን የቆይታ ጊዜ አጭር ስለሆነ፡-
1. የተሰጡ የግልና የቡድን አሳይመንቶችን እየሰራችሁ እንድትቆዩ
2. የመመረቂያ መፅሄት ለማዘጋጀት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ስለሆነ እንደገባን ከ1ኛው ቀን ጀምሮ የፎቶ ማንሳት መርሃ ግብር ስለሚካሄድ ልብስ የማዘጋጀት ስራ እንድትሰሩ ስንል እናሳስባለን፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት

IU Accounting and Finance Department

22 Sep, 12:14


የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን መቀበል ከመጀመራቸው በፊት የተቋማቱ ዝግጁነት እንደሚረጋገጥ ተገለጸ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በጅማ ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ መጀመሪያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል የትምህርትና ስልጠና ተቋማት መልሶ የመክፈት ሂደትና ዝግጅት በሚል ርዕስ ምክረኃሳብ አቅርበዋል፡፡

በ2012 ዓ.ም የተቋረጠዉን ትምህርት በልዩ ዕቅድ ለማጠናቀቅ በሚሰሩ ስራዎችና ትምህርት ሲጀመር ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች እንዲሁም ቀደም ተብለው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች ምን መምሰል እንዳለባቸው በምክረሃሳባቸው ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

በጉባኤው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው መች እንክፈት  ለሚለው ትክክለኛ መልስ እያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ በዓለም የጤና ድርጅት መለኪያ መስፈርት መሰረት ደረጃውን ጠብቆ በተዘጋጀ ዝርዝር በጥልቀት የዝግጅት መጠኑ ተፈትሾ ዝግጁ ሲሆን ብቻ ነው ብለዋል፡፡  በዚያ መሰረት የተቋማት ዝግጅት ይፈተሻል። በዳሰሳውም መሰረት መቀበል እንደሚችሉ ፍቃድ ይሰጣል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንደገለፁት ቅድሚያ ለተመራቂዎች በመስጠት ተማሪዎችን በመከፋፈል በትንሽ ቁጥር ይጀመራል፡፡ ይህም ከሚታዩ ነገሮች እየተማርን የተማሪ ቁጥር ለመጨመር እድል ይሰጠናል ብለዋል፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙ በምን እንደሚመራ ከጤና ሚኒስቴር  ጋር በመሆን ፕሮቶኮል ይዘጋጃልም ብለዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች የለይቶ ማቆያ ማዕከላት እንደመሆናቸው የክልል መንግስታት ስራ ይጠበቅባቸዋል። አማራጭ የኳረንቲን ቦታዎችን ማዘጋጀትም ግድ ስለሚላቸው እዚያ ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡  

ተማሪዎችን በማጓጓዝ ሂደት ችግር እንዳያጋጥም ከትራንስፖርት ሚኒስቴርና ጤና ሚኒስቴር  ጋር በትብብር እንሰራበታለን ብለዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል የሚያስችል እቅድ ካሁኑ አዘጋጅተው ከአስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን ጋር በመወያየት የጋራ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ የበፊቱን አሰራር ይዘን መቀጠል አንችልም፡፡ ዝግጅታችንን ተጋላጭነታችንን አውቀን ተማሪ እንቀበላለን።  አንድ ብሎክ ወይም አንድ ካምፓስ ኮቪድ 19 ቢያጋጥም ምን እናደርጋለን ከሚለው ጀምሮ በዝርዝር መስራት እና እያንዳንዱ እቅድ ያለተማሪዎች እገዛ ተፈፃሚ ስለማይሆን ወደነሱ ለማስረፅ መስራት የግድ ይለናል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንዳሉት ጊዜው የተማሪዎች ህብረት ኃላፊነት የሚፈተንበት  ነው። የተማሪዎች ህብረት አባላት የመፍትሄ ኃሳብ ሆናችሁ ለተፈፃሚነቱ ከዩኒቨርስቲያችሁ ጋር በትብብር እንድትሰሩ ከእናንተ ይጠበቃል፡፡ ሰላማችሁን ማስጠበቅና ለደህንነታችሁ ዘብ መቆም ለትምህርታችሁ ቀጣይነት ዋስትና ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ዩኒቨርስቲዎች መከፈታቸው ላይ ብቻ ሳይሆን ተመልሰው እንዳይዘጉም ጭምር የተማሪዎች ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን አስመልክቶም የትኞቹ በዩኒቨርስቲዎች ይቅረቡ የትኞቹ በተማሪዎች ይሟሉ የሚለውን ከተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ለይቶ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ውይይቱ ተቋማት የት ላይ እንደሆኑ ለይተን ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ግንዛቤ ለመያዝ ታስቦ የተካሄደ ነው ብለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪዎች በአሁኑ ጊዜ ቁርጠኝነት የሚፈልግ የለውጥ ስራ እየሰራን እንደሆነ መገንዘብ እና በዛው መጠን መፍጠን ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡ ተማሪዎችን ወደትምህርት የመመለስ ሂደት ባለድርሻ አካላትን በተገቢው መንገድ የማቀናጀት ኃላፊነት ተወስዶ መሰራት ያለበት ጉዳይ ነውም ብለዋል፡፡

ተማሪዎችን ከመመለስና የኮቪድ 19 ለይቶ ማቆያ ቦታዎችን ከማዘጋጀት አንፃር የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስታት እያንዳንዱ የራሱን ኃላፊነት ወስዶ እንዲሰራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ እንደከፍተኛ ትምህርት ዓለም አቀፋዊና አገራዊ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ ምርምር ላይ የተገኘውን እውቀት ተጠቅመን ለአገር የሚውል አድርገን መጠቀምም ይገባናል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ስራውን በማስፈፀም ሂደት ኃላፊዎች የኮሙኒኬሽን ክፍተት እንዳይኖር በመነጋገር ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመው አመራር የሁሉ ነገር ቁልፍ እንደመሆኑ በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ነገ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንደሚወያይና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል የተባለ ሲሆን ከዚያም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተቋማቱን ለመክፈት ያበቃሉ ተብለው የተቀመጡ ዝርዝሮችን በመያዝ በዩቨርስቲዎች በመገኘት ብቁ መሆን አለመሆናቸው ታይቶ አስፈላጊውን መስፈርት ካሟሉ ብቻ እንዲከፍቱ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ወደኃላ የቀራችሁ ዩኒቨርስቲዎች ካላችሁ ፈጥናችሁ ዝግጅታችሁን አጠናቅቁ ብለው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ጉዳዩንም እንደፕሮጀክት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለባቸው አስበዋል፡፡

ከተሳታፊዎች የተለያዩ ስጋት ናቸው ተብለው የተነሱ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በሂደት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ ለመፍታት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

IU Accounting and Finance Department

21 Sep, 11:43


The above 4 uploaded documents are Assignments from 30% for AcFn 2nd year EXTENSION students.