ነጃሺ : በጥንቱ የግእዝ ቋንቋ "ንጉሥ/አለቃ" የሚለውን ትርጉም ይሰጣል።
- እንደጥቅሉ; በጥንቱ ዘመን ለሀበሻ (የጥንቷ ኢትዮጵያ) ነገሥታት የሚሰጥ የማዕረግ ስም ሲሆን...
...ለሮማ ነገሥታት “ቀይሰር/ቄሳር” ወይም ለፋርስ ነገሥታት “ኪስራ/ሖስራው” ከሚለው ማዕረግ ጋር ተመሳሳይ ነው።
√ ይህ ማዕረግ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ታዋቂ የሆነው; ወደ ሀበሻ የተሰደዱት ሰሃቦችን ተቀብሎ ጥበቃና ከለላ ባደረገው በነጉስ “አስሃማህ ቢን አብጀር” ሲሆን;...
... ይህም ንጉስ ማንም የማይበደልበት ፍትሃዊ ንጉስ እንደነበርና መጨረሻ ህይወቱ ላይ እስልምናን እንደተቀበለ ፤
ብሎም ሰዎችን ወደ እስልምና ይጣራ እንደነበርና በሱ ምክንያት ታላቁ ሰሃቢይ ዐምር ኢብኑል-ዓስ እንዳሰለመ በታሪክ ማህደር ላይ ተጠቅሷል።
🎧 የዚህ ታላቅ ንጉስ ታሪክ በድምፅ መልኩ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ👇
🔗 t.me/abulmusayabhamza/1750
- ይሄን አጭር ፅሁፍ የፃፍኩበት ምክንያት: ምናልባት ይሄ ጥያቄ ግር ያለው ሰው ሊኖር ይችላል ብዬ ነው👇
🔗 https://t.me/islamic_question/6953