አንድ ተቀጣሪ በአንድ ወር ውስጥ ከአንድ በላይ ቀጣሪዎች ያሉት ወይም ከራስ ገቢ ላይ ግብር ቀንሶ የመያዝ ግዴታ ያለበት እንደሆነ፣ ተቀጣሪው ከየሦስት ወሩ መጨረሻ በኋላ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ የግብር ማስታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
አንድ ተቀጣሪ ግብር የማሳወቅ ግዴታ የሌለበት ሲሆን ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚሰጠው ግብር ተቀንሶ ቀሪ መሆኑን የሚያሳየው ደረሰኝ ለዚህ አዋጅና ለታክስ አስተዳደር አዋጅ ዓላማ ሲባል ቀጣሪው በየወሩ መክፈል በሚኖርበት ግብር ላይ እንደተሰጠ የግብር ውሳኔ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡