🏞 ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች 🌆
1⃣ መብላት እና መጠጣት:-
🧠 ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ጾሙ አይበላሽም።
2⃣ ምግብን እና መጠጥን የሚተኩ ነገሮች:-
💉 ምግብ ነክ መርፌ እና መድሓኒቶች ጾምን ያፈርሳሉ።
🩸ለህመምተኛ የሚሰጥ ደም ጾምን ያፈርሳል።
3⃣ የግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈፀም:-
🔵 የፍቶት ጠብታ(መንይ) ቢፈስም ባይፈስምየግብረ-ስጋ ግንኙነት ጾም ያበላሻል።
4⃣ የፍቶት ጠብታን በፍላጎት እና ምርጫ ማፍሰስ(ኢስቲምናእ):-
❌ በመተሻሸት፣በእጅ፣ ደጋግሞ በመመልከት፣ በመሳም.. ወዘተ ከፈሰሰ ጾም ያበላሻል።
💤 በእንቅልፍ ልብ የሚከሰት የዘር ፍሬ መፍሰስ(ኢሕቲላም) ጾም አያበላሽም።
5⃣ አውቆ ማስታወክ:-
🥛ከቁጥጥር ውጭ በራሱ ከወጣ ጾም አያበላሽም።
6⃣ የወር አበባ እና የወሊድ ደም መፍሰስ:-
🩺 ከተለመደው የወር አበባ ቀን ውጭ በበሽታ ምክንያት የሚፈስ ደም(ኢስቲሓዷ) ጾም አያበላሽም።
💡 ከሰውነት ደም ማውጣትን መተው የተመረጠ ነው:-
🆎 ለዋግምት ወይም ደም ለመለገስ ደም ማውጣት ለሊት ማድረጉ ይመረጣል።
🩸ለህክምና ምርመራ ናሙና፣ ነስር፣ ቁስል እና ጥርስ በመንቀል የሚፈስ ደም ምንም ችግር የለውም።
https://T.me/HadithAmharic
🔈ለሌሎችም ያስተላልፉ