➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂❤ (@habra211) के नवीनतम पोस्ट टेलीग्राम पर

➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂ टेलीग्राम पोस्ट

➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂❤
1,160 सदस्य
1,375 तस्वीरें
4 वीडियो
अंतिम अपडेट 09.03.2025 05:57

➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂ द्वारा टेलीग्राम पर साझा की गई नवीनतम सामग्री

➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

05 Mar, 18:37

262

ካንቺጋማ
አብረን በላን  አብረን ጠጣን
አብረን ገባን  አብረን ወጣን

ካንቺጋማ
ተደባደብን  ተቃቀፍን
አንዴ ዳበስ   አንዴ እፍን
አንዴ ቦረሽ  አንዴ ምጥጥ
አንዴ ፈገግ  አንዴ ፍጥጥ

ካንቺጋማ
ተለያየን  ተራራቅን
ተኮራረፍን  ተታረቅን
ተፋቀርን  ተዋደድን
ጅራፍ ፈታን  ሳር ገመድን
እንደ አዲስ ተኮራረፈን
እንደገና ልንታረቅ
አንቺ ከኔ ስታነቢ
እኔ ካንቺ ስነፋረቅ
ተለያይተን ላይሆንልን
አብረን ሆነን ላንስማማ
ስንታደል ሁሉን ባንዴ
ከዛን ሁሉን ስንቀማ


ካንቺጋማ 
ብርሃን ላይ ስንቴ አበራን
ጠሃዩዋ ላይ አንፀባረቅን
ጨረቃ ላይ መንገድ ሰራን

ልታጎርሺኝ ስትዘረጊ
ስትመልሺ ልጎርስ ስል
ተደብቄሽ ስታነቢ
አይንሽ እሳት እስኪመስል
አንዴ አብረን ስንጨፍር
አንዴ አብረን ስንመለኩስ
በፀሎት ጧፍ እንደችቦ
ደማቅ ፍቅር ስንለኩስ
ስንመፀውት ከሰው ዘርፈን
እኔ እና አንቺ አብረን ሆነን
አንዴ ፊቱ ስንፀድቅ
አንዴ ደግሞ ስንኮነን

ተኳረፍን  ተታረቅን
ተፋቀርን ካንቺጋማ
ተለያይተን ላይሆንልን
አብረን ሆነን ላንስማማ
ሁሉም ጣዕም አጣጣምነው
ተጋራነው ሁሉን ስልጣን
ዳግም መሬት ልንለጠፍ
ከጠፈር ላይ እየወጣን

@Habra21 🌹💋
➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

24 Feb, 18:13

650

እንጀራ መሻገት ሊጀምር ሲል ታሞቂዋለሽ,,,, አይ ነገ አሞቀዋለሁ ብትይ መሻገቱ እየባሰ ይሄዳል,,,,,
ሳታሞቂው በቆየሽ ቁጥር መበላሸቱ ይብሳል::
አሙቀሽ መበላት የምትችይውን ነገር ባለማድረግሽ አውጥተሽ ትጥይዋለሽ!
አእምሮም እንደዛው ነው ማዳን እየቻልሽ እስኪሻግት ከጠበቅሽው ይጥልሻል ወይም ያጠፋሻል::
ሰላም ምሽት😊
@Habra21
➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

15 Feb, 19:05

841

ለምትወዶቸው
➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

02 Feb, 12:54

870

🌹🌹🌹🌹🌹
➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

31 Jan, 16:45

533

የናፈቀኝ ነገር
ያልኖርኩበት ሃገር!
ማንም ሰው ሳያውቀኝ÷ ከዜሮ መጀመር
ጠዋት የምሰማው
የማላውቃትን ወፍ፣ አዲስ አዘማመር።

የፈለግሁት ነገር
መኖሪያ መቀየር
ልብሴንም መቀየር
ለየት ቢልልኝ
የምጠጣው ውሃ÷  የምስበው አየር።

መራመድ የሚያምረኝ
በአዲስ ጎዳና ላይ  ÷ በኔ እግር የነቃ
ባገኝ አዲስ  ሃሳብ
አዲስ አይነት እውነት ÷ ወይም አዲስ ቋንቋ።

ማየት የምመኘው ÷ያልራቀ ወደላይ
ሰማያዊ ሳይሆን ÷አዲስ አይነት ሰማይ
በማላውቀው ቀለም ÷ አዲስ አይነት ፀሃይ።
.
.
.
የማውቀውን ሁሉ
መተካት በመሻት
ወደማይታወቅ
ህይወቴን ብሸሻት
የማልሰለቸውን ÷ አጣሁት ፈልጌው
(ስገምት ችግሩን)
አዲሱን የሚያስረጅ ÷ እኔ ነኝ አሮጌው።

በርግጥ እንኳን ማርጀት ÷ መኖር ይለመዳል?
መሰልቸትን መቻል÷ ከናፍቆት ይከብዳል?

በማውቀው  አኗኗር÷ መኖር ከከበደኝ
ወደማይታወቅ ÷ ልቤ ካሰደደኝ
እኔ የሌለሁበት ÷ ማንስ በወሰደኝ?
ወላጅ ባገኘሁኝ
በሆነ አይነት ታምር÷  ዳግም በወለደኝ??



@Habra21
➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

30 Jan, 08:05

561

እነዚህ ሰዎች ፊሊፒንሳዊ አባትና ልጅ ናቸው። ልጁን ያለእናት እያሳደገው እያለ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ጊዜ ጣላውቸው የጎዳና ተዳዳሪ ሆኑ። ነገሮች ከቁጥጥሩ ውጭ ቢሆኑበትም አባትዮው በፍፁም ተስፋ አልቆረጠም። ይልቁንም ተስፋውን ሁሉ በልጁ ላይ አደረገና ያገኘውን ሁሉ የጉልበት ስራ ሳይመርጥ ቀንና ሌሊት እየሰራ ልጁን አሳድጎና አስተምሮ በማኒላ ዩኒቨርስቲ በዶክትሬት ዲግሪ እንዲመረቅ አስቻለው። ልጁም በምረቃው ቀን እንዲገኝለት ሲልክበት አባትዮው ለአንተ ክብር የሚመጥን አልባሳትና ውበት ስለሌለኝ በጓደኞችህ ዘንድ እንዳላሳፍርህ አልመጣም፤ ከእኔ ጋር መታየትም የለብህም የሚል መልስ ስጠው።

ነገር ግን ልጅዮው የእኔ ክብር አንተ አባቴ እንጅ አልባሳትህና ውበትህ አይደለም፤ ደግሞስ ክብርህንና ውበትህን ያጣኸው እኔን የተከበረና ውብ ለማድረግ አይደለም እንዴ? ታዲያ አንተ ምንስ ብትሆን እኔ በአንተ እኮለራሁ እንጅ እንዴት አፍራለሁ? በማለት አሳምኖ እንዲመጣለት አድርጎ በክብርና በደስታ እያቀፈ ፎቶ ሲነሳ ውሏት!

ክብር ዋጋ ከፍለው ለክብር ላበቁ አባቶች!
@Habra211 on telegram
➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

21 Jan, 12:02

948

🔹🔹🔺🔹🔹🔺

ስንት ጊዜ ይፈጃል ምን ያህል አመታት
ስንት ሰዉ ይበቃል ትዝታን ለመርሳት

ምን የሚሉት ጂኒ ካንተ ጋር አሰረኝ💙
የትኛዉ መለኮት በፍቅርህ ጠፈረኝ

በየትኛዉ ጥበብ በየትኛዉ ዘዴ
በየትኛዉ ብልሀት አወከዉ የሆዴን

እንጃ................
ጊዜም መልሱ ጠፋበት መሰለኝ
ካንተ ጋር ይነጉዳል ጥያቄ እያጫረኝ

ስንት ዘመን ቀረኝ
ስንት እድሜ ይተርፈኝ
መቼ ያሳርፈኝ


ትዝታህ ጠቢቡ
ትዝታህ ብልሁ

ትዝታህ ብልጥ ወዳጅ🔻
እያሳሳቀ ነዉ አብሮ ሚያሳቅቀኝ
እያጫወተ ነዉ እድሜዬን የቀጨኝ

ወይ እሱ ይተወኝ ወይ አንተ ደግመህ ና
ትዝታህን ዉሰድ እኔን መልስና።❤️


ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

           ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️
@Habra211 🌹🌹🌹🌹
               
➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

26 Dec, 05:39

1,141

ጎደኛ ሲያፈቅር ኪስ ይመለከታል
  የጎደለብህ ቀን ጀርባ ይሰጥሃል
ሚስት ስታፈቅር ደምግባት ታያለች
    የረገፈ ለታ ትታ  ትሄዳለች
  ዘመድ ሲያፈቅርህ ዝናን ተመልክቶ
ጀርባውን ይሰጣል ቀን ሲጥልህ አይቶ
    እናት ስታፈቅር የላትም ዳርቻ
  ነፍሷን ትሰጣለች እሷ ላንተ ብቻ

እናትዬ  🌹🌹💋💋

@Habra21
➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

12 Dec, 17:43

1,563

አንድ አንዴ ይቅርታ የነበረውን ነገር አይመልስም ንፁህ ልቦች ከቅጣትና ከበቀል ይልቅ ይቅርታን ያስቀድማሉ ለይቅርታ ልባቸው ቅርብ ስለሆነ ሁሌም ለሰው ይራራሉ ጥፋት ሲደጋገምባቸው ግን ስህተት መሆኑ ቀርቶ ውሳኔ ይሆናልና ያኔ ጥፋትህን ብቻ ሳይሆን አንተንም በመርሳት ነው ይቅር የሚሉህ አንድ አንዴ ይቅርታ የነበረውን ነገር አይመልስምና
መጀመሪያ እንጠንቀቅ ።

@ Habra211
➾▂▃Ĥabŕă-pictures▃▂

09 Dec, 19:08

1,643

የሽቶ ጠርሙሱን መስበር ጠረኑን ተጋኖ እንዲሸት ያደርጋል፤ ግን ለመጨረሻ ጊዜ ነው!።

@Habra211