Últimas publicaciones de Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት (@fitcorner) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት

Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት
Will provide different Training & Consultancy on fitness & wellness industry.
1,415 Suscriptores
1,372 Fotos
30 Videos
Última Actualización 01.03.2025 03:02

Canales Similares

ሀበሻ Crypto
8,807 Suscriptores
Wenraya Records
4,734 Suscriptores
Muslims
1,400 Suscriptores

El contenido más reciente compartido por Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት en Telegram


ታላቁ የረመዳን ጾም እና የአካል ብቃት ልምምድ

ከዓላማ (ምክንያት)፣ ከምግብና መጠጥ ክልከላና ከጊዜ ርዝማኔ አኳያ ጾም ብዙ ዓይነት ነው፡፡
በመሆኑም በዚህ ልጥፍ (Post) ታላቁ የረመዳን ጾም (Ramadan Fast) ላይ እናተኩራለን፡፡ በመሰረቱ ረመዳን ጾም ከስፖርት ብቃት፣ ከአካል ብቃት፣ ከጤና፣ ከሰውነት አሰራር ስርዓት ሁኔታና ከመሳሰሉት አንጻር በርካታ ጥናቶች የተደረገበት ጾም ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎች የረመዳን ወር ሲደርስ እንቅስቃሴውን በማቆምና በመቀጠል መካከል ሃሳባቸው ሲከፈል ይስተዋላል፡፡

በረመዳን ጾም ወቅት የአካል ብቃት ልምምድ ማድረግ የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች፦
የሰውነት ክብደት ለመቀነስ (ጾመ + እንቅስቅሴ = ሰውነታችን ስብን የበለጠ እንዲጠቀም ያደርገዋል)፤ የአካል ብቃት እንዳይቀንስ፣ በሽታ የመከላከል አቅም (immunity) ለመጠበቅና ለማሻሻል፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል (ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ውፍረጥ....)፣ ድካም ደካም የሚለውን ስሜት ይቀንሳል - ጉልበት (energy) ከፍ ያደርጋል፤ በስራ ላይ ትኩረትንና የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል፡፡

በረመዳን ጾም ወቅት እንቅስቃሴ ብናቋርጥ (ባንሰራ) ምን ይከሰታል?
የሰውነት ክብደት ይጨምራል (የምናገኘው ካሎሪ ከምናቃጥለው ስለሚበልጥ) ፣ የጡንቻ መጠን ይቀንሳል እንዲሁም የሰውነት አሰራር ስርዓት ጤና ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል በሳውዲ-አረቢያ በተደረገና 173 ቤተሰቦችን ባሳተፈ አንድ ጥናት 59.5 % ያህሉ በረመዳን ጾም ወቅት የሰውነት ክብደታቸው መጨመሩን አሳይቷል፡፡

በረመዳን ወቅት የአካል ብቃት ልምምድ ምክር ሃሳቦች፦
📌ጫናውን ማስተካከል፦ ቀላልና መካከለኛ ጫና ያላቸውን እንቅስቃሴዎች መስራት
📌ራስን ማዳመጥ (የተለየ አለመመቸት ወይም ህመም ካለ)
📌 ሙቅት ቦታዎች ላይ (በጸሃይ) እንቅስቃሴ አለመስራት
📌 ሳውና እና ስቲም ክፍሎችን አለመጠቀም (ውሃ ጥም ስለሚያባብሱ)
📌 በቂ እረፍት መውሰድ
📌 አዳዲስ እንቅስቃሴዎችን፣ አዲስ ግብ ወይም አዲስ ጫና አለመጀመር
📌 አመጋገብን ማስተካከል (በቂ ፕሮቲን፣ ሃይል ሰጭ ምግቦችንና ውሃ ማግኘት)
📌 የልምምድ ሰዓትና የልምምድ አይነቶችን ከሰውነት አሰራር ስርዓት ጋር በተገቢው ሁኔታ ማጣጣም

ማሳሰቢያ፦ የጤና ችግር ያለባቸውና ከዚህ በፊት እንቅስቃሴ ሰርተው የማያውቁ ግለሰቦች እንቅስቃሴ ከመጀመራቸው በፊት የህክምና ባለሞያ ማማከር ይኖርባቸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ታላቅ የማስ ስፖርት ተካሄደ፤
ሕዳር 15/ 2017 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

**
''የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልፅግና''

ከባለ ግርማ ሞገሱ የአድዋ ሙዚዬም እና በታሪካዊው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል በሚገኘው ቦታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው የተሳተፋበት ታላቅ የማስ ስፖርት ተካሄደ።

ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በተሳተፈበት ማስ ስፖርት ላይ የከተማችን ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ የከተማችን ከፍተኛ አመራሮችና አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተገኝተውበታል።
===//===

እንደማንኛውም አፍሪካዊ ወይም የታዳጊ ሃገር ዜጋ ''የበጀት እጥረት'' ወይም ''Budget Deficit'' ገጠመን ሲባል ሰምተው አያውቁም አንልም። ይህንን ሲሰሙ ምን ማለት እንደሆነ ይገባዎታል። በቀላል አገላለፅ ለስራው ከሚያስፈልገው በጀት ይልቅ ለስራው የተመደበው በጀት አንሷል ማለት ነው።
ወደ ጉዳያችን እንመለስ:-
ቀመር 1: ''በጀት = ካሎሪ'' ነው። ማለትም የካሎሪ እጥረት /Calorie deficit'' ማንኛውም የሰውነት ክብደቱን መቆጣጠር፣ መጨመር ወይም መቀነስ የሚፈልግ ሰው ሊረዳው የሚገባ ፅንሰ ሃሳብ ነው።

ለአብነት ያኽል አንድ 110 ኪ.ግ የሚመዝን ሰው በቀን 3500 ካሎሪ የሚጠቀም ቢሆንና በቀን የሚያገኘው ''ካሎሪ'' መጠን 2900 ቢሆን ግለሰቡ በቀን የ600 'በጀት' ማለት 'የካሎሪ' እጥረት ገጥሞታል።

በቀን የ600 ካሎሪ እጥረት (calorie deficit) ሰውነታችን ላይ ምን ሊያስከትል ይችላል?

የሰውነት የአሰራር ስርዓት ''የበጀት'' እጥረት ሲገጥመው ኘሮጀክት አይሰርዝም ባይባልም የመጀመሪያ አማራጩ ግን 'ከተቀማጭ ሃብት'' (reserved energy) ላይ የጎደለውን መሙላት ነው።

ቀመር 2: ተቀማጭ ሃብት = የሰውነት ስብ (ክብደት)

ይኽም ማለት አንድ ግለሰብ ሆን ብሎ (በልምምድ እና/ወይም በአመጋገብ) በቀን 600 ካሎሪ እጥረት እንዲገጥመው ቢያደርግ በ1 ወር ውስጥ ~ከ2 እስከ 4 ኪ.ግ ክብደት ይቀንሳል። ይኸም በዓመት ከ24 እስከ 48 ኪ.ግ ሊቀንስ ይችላል ማለት ነው።

ይኽንን ''የበጀት እጥረት'' መጨረሻ ስንመዝነው 110 ኪ.ግ ይመዝን የነበረው ግለሰብ በዓመቱ መጨረሻ ከ62 እስከ 86 ኪ.ግ ይመዝናል ማለት ነው።

የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ ቤተሰብ ይሁኑ። በሳይንስ እንመራለን!! ሳይንስን እንተገብራለን!!
===//===

የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ክብረ በዓል በማስ-ስፖርትና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ።
ሕዳር 8/2017 ዓ.ም፤ ሸገር ከተማ፤ ኮየ ፈጨ

===//===
የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ክብረ በዓል በማስ-ስፖርትና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት ተከብሯል።

በዝግጅቱ ላይ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ አመራሮችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተውበታል።

ብልፅግና እስካሁን እያከናዎናቸው የሚገኙትን በርካታ የልማት፣ ከተማን የማዘመንና የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና የሃገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
======//======

➧ በማሕበራዊ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!!!
Telegram=>@FitCorner
Youtube=>http://bit.ly/subscribe_netsisport

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (Exercise) የምግብ ፍላጎት ይጨምራል?
*
በተለመዶ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት የርሃብ ስሜት እንደሚጨምርና የምግብ ፍላጎት ከፍ እንደሚያደርግ ይነገራል፡፡ በዚህ ወገን የሚገኙ ተከራካሪዎች ዋነኛ ነጥብ እቅስቃሴ በምንሰራበት ጊዜ ተጨማሪ ጉልበት (calorie) እያወጣን በመሆኑ ሰውነታችን ተጨማሪ የጉልበት ምንጭ (ምግብ) ስለሚያስፈልገው መሆኑን የርሃብ ስሜት እንደሚኖር ያብራራሉ፡፡

ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የርሃብ ሆርሞኖችን በተለይም ገርሊን (ghrelin) እና ሌፕቲን (leptin) ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሚያደርግ የምግብ ፍላጎት ይቀንሳል፤ የርሃብ ስሜት ላይሰማንም ይችላል ሲሉ የሚከራከሩ አሉ፡፡ ሁለቱም ወገን በየዘርፋቸው ትክክለኛ ነገር አላቸው፡፡ እንቅስቃሴ ተጨማሪ ጉልበት እንድንፈልግ ያደርጋል፡፡ በተቃራኒ በተለይም ከፍተኛ ጫና ያላቸው እንቅስቃሴዎች ደግሞ ለአጭር ጊዜም ቢሆን የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳሉ፡፡

ወሳኙ ነገር ግን የርሃብ ስሜትና አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ምክንያች ከሰው-ሰው ይለያያል። እንቅስቃሴ በሰራን ቁጥር ተጨማሪ ጉልበት ከምግብ ማግኘት እንደሚያስፈልግ አከራካሪ ጉዳይ ባይሆንም በእንቅስቃሴ የምንጠቀመውን የጉልበት መጠን አጋኖ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡
ለምሳሌ፡- አንድ 70ኪ.ግ የሚመዝን ሰው 1ኪ.ሜ ለመራመድ ከ60 – 75 ካሎሪ ብቻ ይጠቀማል፡፡ እርምጃው ከፈጠነ ወይም ዳገት ከሆነ የሚያስፈልገው ጉልበት (ካሎሪ) ከፍ ይላል፡፡ ነገር ግን 250ግ ከሚመዝን አንድ ነጭ ዳቦ 663 ካሎሪ እናገኛለን፡፡ ይህንን 663 ካሎሪ ለማጥፋት ይኸው ግለሰብ ከ125 ደቂቃ በላይ የፍጥነት እርምጃ መስራት አለበት፡፡
=//=

https://www.facebook.com/share/p/v494rztTeRnBerUW/

አዝናኝ ቆይታ በቢሾፍቱ!
.
.
.
https://youtu.be/J90pnB4XpV8?si=xr0Eh8yVzW9FKl0J

ጎፈሬ 🤝 ፊት ኮርነር ስፖርት

ታላቁ ብራንድ ጎፈሬ ለፊት ኮርነር ባቀረባቸው ጥራት ያላቸው ምርቶች ዕውቅና ተሰጥቶታል።


@goferesportswear

ታዋቂው የአካል ብቃት አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ ሽልማት ተበረከተለት፡፡
ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም - ቢሾፍቱ/ደብረዘይት

*🏆***🏆*
'A sound mind in a sound body' (Miletus)
ታዋቂው ግሪካዊ ፈላስፋ ሜሊተስ “ጤናማ አዕምሮን በጤናማ ሰውነት ውስጥ” ማግኘት ያለውን አስፈላጊነት በግልጽ ካሳዩ ቀደምት ጠቢባን መካከል አንዱ ነው፡፡ ይኽንን ተመሳሳይ ዓላማ ለማሳካት ሲባል ኢንተር ጂም የተመሰረተው ከዛሬ 22 ዓመት በፊት ነበር፡፡ ይኽንን ጂም በወጣት እድሜያቸው ከነፃነት ጋር በመሆን የመሰረቱና በጂሙ ለረጅም ጊዜ ስልጠና የወሰዱ ግለሰቦች በአንድ ላይ በመሰባሰብ ለኢንስራክተር ነፃነት ካሳ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እና ለጂም-ኢንደስትሪው ላበረከተው አስተዋፅኦ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው የዋንጫ 🏆🏆 ሽልማት አበርክተውለታል፡፡

የፊት ኮርነር ስፖርት - ከቤት ውጭ የአካል ብቃት ስልጠና እና ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራም
ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም - ቢሾፍቱ/ደብረዘይት

**
“በጂምናዚዬም ውስጥ ከሚሰጡ ተግባራት በተጨማሪ ከቤት ውጭ የአካል ብቃት ስልጠና፣ ልዩ ልዩ የውድድር መልክ ያላቸው ጨዋታዎችና የመዝናኛ ፕሮግራም ለሰልጣኞችም ለአሰልጣኞችም ጠቃሚ ነው፡፡” (ኢንስትክተር ነፃነት ካሳ)

ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ (ቢሾፍቱ/ደብረዘይት) በሚገኘው ሊሳቅ ሪዞርት ከቤት ውጭ የአካል ብቃት ስልጠናና ልዩ ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች የተከናወኑ ሲሆን ይህም አካላዊ፣ አዕምሮአዊና ማህበራዊ ችሎታን ከማሳደግ በተጨማሪ አማራጭ የስልጠና ሂደትን በመከወን የስልጠና ተነሳሽነትን ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጧል፡፡
በዚህ መርሃ ግብር ላይ ውሃ ውስጥ የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ውድድሮች፣ የጀልባ ጉዞ፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎችና የአካልና የአዕምሮ ብቃትን የሚፈትኑ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች ተካትተው ነበር፡፡