መስከረም 21/2017
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሴኔት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። በመጀመሪያ
በ2017 ዓመት የሠልጣኞችን አቀባበል በተመለከተ ውይይት የተደረገ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ አማራጮችን ተጠቅሞ ሠልጣኞችን በስፋት ለመቀበል እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል። በዚህም መሠረት ከዚህ ቀደም ከሚቀበልባቸው አማራጮች በተጨማሪ በሬሚዲያል 12 ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን እንደሚቀበል ተገልጿል። የሠልጣኞችን አቀባበል በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው መመሪያ መሠረት እንደሚተገበር ተገልጿል።
በመቀጠል ሴኔቱ የ2017 የሥልጠና ዓመት ካሌንደር (Academic Calender) ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።
በመጨረሻም የ2016 ዓመት ተመራቂ የነበሩ እና በተለያየ ምክንያት ሳይመረቁ የቀሩ ተመራቂዎችን ጉዳይ በተመለከተ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከሪጅስትራር እና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የቀረበለትን ውጤት መርምሮ አጽድቋል።
ዌብሳይት http://www.ftveti.edu.et/
ፌስቡክ https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
ቴሌግራም https://t.me/fdretvti