#Ethiopia | የካቲት 21/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፤ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ እና የሠራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል።
የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ያትታል።
በዚህም በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።