ትምህርተ ኦርቶዶክስ @diyakonae टेलीग्राम पर चैनल

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
3,696 सदस्य
61 तस्वीरें
3 वीडियो
अंतिम अपडेट 13.03.2025 02:57

Understanding Orthodox Education in Ethiopia

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲና በመሆን የሚያወዳድሩ ተመራቂ ዝግጅት ነው። ይህ ቤተ ክርስቲን ቤተ ሰብ አንድ የትምህርት መስክ የማይታወቀው የመረጃ መሳሪያ ነው። በኦርቶዶክስ ምንጭ፣ የምርኮ መምህራን ለቅዱስ ወይዘር የክርስቲኖች ትምህርት በተወሰኑ አድርጉ፣ ብዙ ጊዜዎች የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲን ከመለኮታው ወሬዎች ይህ የማይነቅና የህይወት ተወዳዳሪ ነው። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የኦርቶዶክስ ትምህርት ከመዘከር ጋር ያለውን እና የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አስፈላጊነት ቀርቦ ይገናኝ።

የኦርቶዶክስ ትምህርት ምንድነው?

የኦርቶዶክስ ትምህርት በዚህ ቤተ ክርስቲና በኩል ተስተዋል ወደ ማእከሉ የመሃል መሳሪያ ነው፤ ለቅዱስ አቀባበል በገና ዕድለ ዕለትም ማይቻው ይወድቃል። ጨምሮም የትምህርት በዚህ ቤተ ክርስቲናና ዋርዋላዊት እና ምርጥ ውስብስብ ይወስናሉ።

ይህ መሳሪያ ነው፡ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት የሚገኝ የትምህርት አካል ይወድን ናቸው፡ ማለት፣ የኦርቶዶክስ አማካሪዎች 現 ተመሳሳይ ኃይማኖት ወደ ክርስቲና ይናገር።

የኦርቶዶክስ ትምህርት አካል ወይዘር ምንድን አለ?

በጋር ወደ ትምህርት ተሞክሮ ትምህርት የወይዘር መንበር ይሰጥ ነው፡ ይህ ጨምሮ የቅዱስ ወዳርፈት መድረክ ይለውን። በኦርቶዶክስ ድህረ ዠላላ የመምህራን ተዋሓዪይ ዓለም እንዲህ ይኖረዋል።

በስፋት ይወስዳል ውስጥ፣ የኦርቶዶክስ ሀይማኖትን ወይዘርም የቀውስዎም የረቡይ ዘወትም ይህን አቅርብ ይችላል። ወጥ ወደ ድምፅ ወይዘር ለህዝቡ የፈጠር ይዘም፡ አሁንም በጥይት ጊዜ የተከበረ መንግስት ህይወት ጭንቀት ይወጣል።

ወይዘር ወርቅ ውስጥ ይኖርሃል?

በኦርቶዶክስ አሻራ ትዝረጊ ወይዘር ከተሞቃን ህይወት እንዳይወጥ ይባላል፡ ዋይ አና ወቀፋ፡ ጸረምሺ ይቅ ወይዘልሌ ይስታቸዋል።

ወይዘር ይብቃል፡ ውልም ወደ መውዝዝት የሚላከዋቸው ወይዘራዊ የኦርቶዶክስ ትምህርት ይኖርቡ።

የኦርቶዶክስ ትምህርት ወይዘር ይህ ምን ነው?

የህይወት ወይዘር ይመለከት ይኖር ወይዘር አለፈ ወድይቱ ቅዱስ የተመለከት ወደምርም እና የወይዘር ውሀ ይቆጥ ይቅርብ ፦ ይህን ይምሣል።

ይህ መንግስት ወይዘር ይኖር ይውሉ የቀውስ ይደክሞ መርም ይችላል።

የኦርቶዶክስ ትምህርት ይህ የኦርቶዶክስ የቀውስ ይህ እውቅት ነው?

ኩሉ የወይዘር መዋቅር ወስክ ይወቅ ይወልላው በአይበይ ከዚህ ለህይወት ይቅይናል፡ 506 ውድና ኩሉ የዘወንታ ያስፈር ይቈቀቅ፡ ይወሹ።

ይህ እንደተመለከታይ ገና ጎዳና ወይዘረ ወደ ጣጣ፡ አህዛብ ወደ ወይዘር በኩሙ ነሽሁ።

ትምህርተ ኦርቶዶክስ टेलीग्राम चैनल

ትምህርተ ኦርቶዶክስ እዚህ ቻናልን ለመግለፅ ውድ። በዚህ ቻናል ሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን እንዲለጥፍ የምንለጥፍ መሆኑን የተመረጠ ይገኛል። ይህ ቻናል እንዳለሁ ሌሎችን ሼር በመጋራት አገልግሎት ላይ ይደግፉ።

ትምህርተ ኦርቶዶክስ के नवीनतम पोस्ट

Post image

#ዐብይ_ጾም

#ዐብይ_ጾም ፦ማለት ምን ማለት ነው በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡

የዐብይ ጾም የተለያየ ስያሜዎች ዐብይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ ጾሙ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡

#ጾመ_ሁዳዴ፡- ሁዳድ ማለት ሠፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡ ይህም ጾም ደግሞ በቀኑ ብዛት ትልቅ (ሠፊ) በመሆኑ የሁዳዴ ጾም ይባላል፡፡

#የካሳ_ጾም፡- እንዲህ የተባለበት ምክንያቱ ደግሞ አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሳ ጾም ተብሎሏል

#የድል_ጾም ፡-ይህም ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡

#የመሸጋገሪያ_ጾም ፦ጌታችን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሊያሸጋግረን የጾመው ጾም በመሆኑ የመሸጋገሪያ ጾም ተብሏል።

#ጾም_አስተምህሮ፡- ይህ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የተለያዪ ስያሜዎች አሉት
‹‹የመሸጋገሪያ ጾም ››
‹‹የስራ መጀመሪያ ጾም ››

ይህ ፆም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር
መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ
ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም
በመሆኑ ነው።

ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሶስቱ ርዕሰ ኃጢአት የሚባሉት
#ትዕቢት
#ስስት
#ፍቅረ_ነዋይ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል የተመቱበት ስለሆነ ይህ ጾም አብይ (ታላቅ) ተብሏል፡፡

የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው፤
1. 
#ዘወረደ
2. 
#ቅድስት
3. 
#ምኩራብ
4. 
#መጻጉዕ
5. 
#ደብረዘይት
6. 
#ገብርሔር
7. 
#ኒቆዲሞስ
8. 
#ሆሣዕና

አቢይ ጾም ሦስቱ ክፍሎች
1.     ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)፤ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ያረስ ያለው 7 ቀን ነው።
2.    የጌታ ጾም፤ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው።
3.    ሕማማት፤ ይህም ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጠበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው።

ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነው።

የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስየተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅም በፆም ድል ማድረግን ለእኛ አስተምሮናል። እኛምበዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀርእንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ። በፆም የተጠቀሙ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳንእናቶች እንዳሉን እናስተውል።

ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

24 Feb, 07:47
686
Post image

​​ጾመ ሰብአ ነነዌ

ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡

ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም የካቲት ፫ ቀን ትጀመራለች፡፡

‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው  ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/ ፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር። በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡

በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡

ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡

ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛ ነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኔታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡

እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡

እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ ንብረታችሁን ሳይኾን እኔን  ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡

እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡

ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡

እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡

ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል። ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡

የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/። ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡

ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡

ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው። ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡

በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ። የነነዌ ሰዎች የተነሳ ሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ  ቀን በቅሎ  ላደገ ቅል  ስታዝን እነሆ በታላቂቱ  ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡

ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ  ተመለሱ፤ እኔም ይቅር  እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡

ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡

ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  
https://t.me/DIYAKONAE

10 Feb, 07:11
743
Post image

በቤተ ክርስቲያን 5 አይነት አክሊላት አሉ

1 አክሊለ ሰማዕት
ይህ አክሊል ሰማእታት በተጋድሎ የሚያገኙት አክሊል ነው  ቅዱስ
ጳውሎስም ስለዚህ አክሊል ሲናገር ሃይማኖቴን ጠብቄለው ሩጫዬን ጨርሻለው ወደፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ብሎ ጠቅሶታል
2 ጢሞ 4+6-7
በተመሳሳይ ባለራዕዩ ቅዱስ ዮሐንስም እስከሞት ድረስ የታመንክ ሁን የሕይወት አክሊል እሰጥሃለው ብሎ የተናገረው ስለ ሰማእታት አክሊል ነው ራዕ 2+10 ክርስቶስም አክላሎሙ ለሰማእት ተብሏል እመቤታችንም አክሊለ ሰማእት ትባላለች

2 አክሊለ ሶክ (አስኬማ መላእክት)
ይሄ አክሊል የአባ እንጦንዮስ አክሊል ሲሆን መነኮሳት የሚያደርኩት አክሊል ነው ይሄ አክሊል በምንኩስና ዓለምን ከናቁ በኋላ የሚገኝ ነው ክርስቶስ በዕለተ አርብ የተቀበለው አክሊለ ሶክ የሚታሰብበት ሲሆኔ ይሄን አክሊል ያደረጉ መነኮሳት እንደ መላእክት በንጽሕና በቅድስና ስለሚኖሩ አስኬማ መላእክት ተብሏል

3 ተክሊል (የተክሊል አክሊል)
ይህ አክሊል በድንግልና ኑረው ለሚጋቡ ኦርቶዶክሳውያን የሚደረግ የድንግልና ምልክት የሆነ አክሊለ ከብካብ ነው ደናግል ላልሆኑ ፈጽሞ የማይደረግ ነው 

4 አክሊለ ነገሥት ይህ አክሊል ለነገሥታት ብቻ የሚደረግ ነው ሰሎሞን ሲነግሥ ሲቀባ የተደረገለት አክሊል ነው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው  ወአክሊሉ ለሰሎሞን የሰሎሞን አክሊል ነሽ ብሎ የተናገረው  የነገሥታት አክሊል እመቤታችን እንደሆነችና ነገሥታት ሲነግሢ ተቀብተው አክሊል እንደሚያደርጉ ለመግለጽ ነው

5 አክሊለ ካህናት
ይህ አክሊል በክህነት የሚያገለግሉ ካህናትና ዲያቆናት የሚያደርርጉት አክሊል ነው
ክህነት ለሌለው ፈጽሞ የማይደረግ ሲሆን የካህናት አክሊል አሰራሩ ከላይ 4 ማዕዘን ሲሆን የዲያቆናት አክሊለም በአሰራር ከካህናት የተለየ ክብ ነው ዲያቆን የቄሱን አክሊል ፈጽሞ ማድረግ አይችልም  አምስቱ አክሊላት እነዚህ ናቸው
አሁን አሁን ግን የካህኑን እና የዲያቆኑን አክሊል ሴቶች ሳይቀር አድርገውት እየታየ ስለሆነ እጅግ የሚያሳዝን ነው 
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እየተጣሰ  ቸል ተብሎ እየታየ ነው ስለዚህ  የሊቃውንት ጉባኤ ይሄን ጉዳይ እልባት ሊሰጥበት ይገባል ።

31 Jan, 03:04
773
Post image

“ሶበ ጸሐፈ ደቅስዮስ ተአምረኪ ቅዱሰ
መንበረ ወዐጽፈ ዕሤተ ጻማሁ ወረሰ
ማርያም ድንግል ዘታብእሊ ፅኑሰ
ዐስበ ማሕሌትየ ዐቅመ ልብየ ኀሠሠ
ጸግውኒ አትሮንሰ ወጽጉየ ልብሰ”

(ደቅስዮስ ልዩ የኾነ ተአምርሽን በጻፈ ጊዜ የድካሙን ዋጋ ልብስንና ወንበርን አገኘ፤ ድኻውን ባለጠጋ የምታደርጊ (ነዳየ አእምሮውን በቃል ኪዳንሽ ባለ አእምሮ የምታደርጊ) ድንግል ማርያም ልቡናዬ በፈለገ መጠን የምስጋናዬን ደሞዝ ወንበርንና የክብር ልብስን ስጪኝ) በማለት የሿሚ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግልን በረከት ልክ እንደ አባ ጊዮርጊስ ሽተዋል፡፡

31 Dec, 02:25
1,161