BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2 @bspschool Channel on Telegram

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

@bspschool


SARIS, AKAKI KALITY

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2 (English)

Welcome to the official Telegram channel of Bulbula G/Secondary School 2, located in Saris, Akaki Kality. Our channel, @bspschool, is dedicated to providing students, parents, and the community with important updates, news, and information about our school. Bulbula G/Secondary School 2 is a renowned educational institution known for its high academic standards, qualified teachers, and commitment to providing a well-rounded education to all students. We offer a wide range of subjects and extracurricular activities to ensure that each student has the opportunity to excel both academically and personally. On our Telegram channel, you can expect to find announcements about upcoming events, exam schedules, parent-teacher meetings, and other important information. We also share success stories of our students, highlight achievements of the school, and provide tips and resources to help students succeed in their studies. Whether you are a current student, a proud parent, or a member of the community interested in our school, our Telegram channel is the perfect place to stay informed and connected. Join us today to be a part of the Bulbula G/Secondary School 2 community and discover all that our school has to offer. We look forward to welcoming you aboard! #BSPSchool #Education #Saris #AkakiKality

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

06 Dec, 17:31


እንደምን አመሻችሁ ተማሪዎች?ሁሉ ሰላም ነው?መልካም!የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ነገ ቅዳሜ ማጠናከሪያ ትምህርት የሚቀጥል መሆኑን አውቃችሁ በጊዜ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን ።

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

29 Nov, 19:17


ሰላም ናችሁ ተማሪዎች?ነገ በቀን 21/03/2017 ዓ.ም ለ11ኛ እና ለ12ኛ ክፍል የማጠናክሪያ ትምህርት አለመኖሩን እናሳስባለን ።

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

25 Nov, 14:04


ለማስታወስ ያክል የተለጠፈ

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

22 Nov, 07:26


MID EXAM SETTING ARRENGEMENT 2017

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

15 Nov, 03:55


https://youtu.be/pduM7mqvfK0?si=8ejkbVnh2vAyRfzx

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

11 Nov, 08:52


ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ምስል👏👏👏👏👏👏

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

26 Oct, 19:07


Video from Mastewal B.

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

24 Oct, 13:43


ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

https://placement.ethernet.edu.et

https://t.me/moestudentbot

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

23 Oct, 11:56


Audio from Mastewal B.

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

23 Oct, 11:55


Audio from Mastewal B.

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

21 Oct, 06:04


Today is Monday. It is English day.

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

19 Oct, 19:01


09/02/2017 ዓ.ም

በቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በዛሬው እለት ለመምህራን ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናው በተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እና የተማሪዎችን የእንግሊዝኛና የሒሳብ ውጤት ውጤትን ለማሻሻል የ CPD ሚና በሚል ርዕስ ዙሪያ ስልጠናው ተሰጥቷል።

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

18 Oct, 16:22


ተማሪዎችን በሒሳብና እንግሊዝኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጀው ስትራቴጂ አፈጻጸምን አስመልክቶ በተካሄደ የክትትልና ድጋፍ ግብረ መልስ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

(ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶችና በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን በውይይቱ በድጋፍና ክትትሉ የተሳተፉ ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ ርዕሳነ መምህራን እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው በ2017 ዓ.ም የትምህርት አመት ትኩረት አድርጎ እየተንቀሳቀሰባቸው ከሚገኙ ተግባራት መካከል ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ ማድረግ መሆኑን ጠቁመው ተማሪዎች በሁለቱ የትምህርት አይነቶች የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችል ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን አመላክተዋል።

ዶክተር ዘላለም አያይዘውም ቀደም ሲል ስትራቴጂው ለትምህርት ተቋማት መውረዱን በመጥቀስ በየትምህርት ተቋማቱ የስትራቴጂው አተገባበር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የድጋፍና ክትትል ስራ መሰራቱን ገልጸው በዛሬው ውይይትም በድጋፍና ክትትሉ ግብረመልስ ላይ በመወያየት በቀጣይ በተቋማቱ የተቀራረበ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ታስቦ መካሄዱን አስገንዝበዋል።

የድጋፍና ክትትል ግብረመልሱም ቀርቦ የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረበው ግብረ መልስ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አቅርበው በኃላፊዎች ምላሽና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራትን የተመለከተ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

(ዘገባው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ነው)

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

15 Oct, 18:24


ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም
   
                ማስታወቂያ

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈትናችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ (300 እና በላይ አምጥታችሁ ያለፋችሁ) እና በሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን እስከ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ብቻ እንድትሞሉ መልእክት መተላለፉ ይታወቃል።

ስለሆነም እስከ ዛሬ ድረስ ያልመጣችሁና ያልሞላችሁ ተማሪዎች ነገ የመጨረሻ ቀን ስለሆነ እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመምጣት እንድትሞሉ እናሳውቃለን።

                               ት/ቤቱ

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

08 Oct, 17:34


መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የሬሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆ

በ2016 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ለተፈተኑ ተማሪዎች በሬሚዲያል (ማካካሻ) ፕሮግራም ለመማር የሚያበቃው የመግቢያ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

በዚህም በመንግሥት ወጪ ለሬሜዲያል መግቢያ ነጥብ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ለወንዶች 204 ሲሆን ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ሴቶች ደግሞ 192 መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በግል ለመማር ደግሞ 31% ከመቶ ውጤት ሆኖ መወሰኑ ተገልጿል።

የትምህርት ቤታችን የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን!!

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ (300 እና በላይ) እና በሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ በየትምህርት ቤታቸው መሙላት እንደሚችሉም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

07 Oct, 18:33


27/01/2017 ዓ.ም

                 ማስታወቂያ

ለቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማታ ተማሪዎች በሙሉ፤


የማታ ትምህርት የተጀመረ ቢሆንም ተማሪዎች ተሟልታችሁ የተገኛችሁ ባለመሆኑ ከነገ ጀምሮ በትምህርት ገበታችሁ ላይ በሰዓቱ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

                                   ት/ቤቱ

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

07 Oct, 11:01


🏆🏆🏆🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🏅🏅🏅🏅
ለትምህርት ቤታችን ማኅበረሰብ በሙሉ፣
          
                እንኳን ደስ ያላችሁ/አለን!!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2016 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም በዛሬው ዕለት መስከረም 27/2017 ዓ.ም ተካሂዷል።

ከትምህርት ቤታችን ውድ ተማሪዎች መካከል የሆነችው ተማሪ ያስሚን ከድር ሽፋ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ካሉ የመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል 1ኛ በመውጣቷ ከአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አበቤ የላፕቶፕ ኮምፒውተርና የሰርቲፊኬት ሽልማት ተርክቶላታል። በተጨማሪም የሒሳብ ትምህርት ፈተናን 100 በማምጣቷ በስሟ የተቀረጸ ሜዳሊያ ከክብርት ከንቲባ ተበርክቶላታል።

ሌላኛው የትምህርት ቤታችን ተማሪ የሆነው ኤፍሬም ካሳ ተገኘ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ካሉ የመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል 2ኛ በመውጣት የታብሌትና የሰርቲፊኬት ሽልማት ከክብርት አዳነች አበቤ ተርክቶለታል።

በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ሌሎች ተማሪዎቻችን ተማሪ ሥምረተ መድኅን ሲሳይ፣  ተማሪ መአሩፍ በድሩ፣ ተማሪ ቤተልሔም ጨርቆስ ታብሌትና ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

እንዲሁም አምስቱ ተማሪዎቻችን እያንዳንዳቸው 20,000(ሃያ ሺህ ብር) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይሰጣቸዋል።

በተጨማሪም ተማሪያችን ያሥሚን ከድር ሽፋ  በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኩል የትምህርት እድል (SCHOLARSHIP) ተሰጥቷታል። በዚህ የሽልማት መርሃ ግብር የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ፣ የትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ ተሸላሚ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና የት/ቤቱ ርዕሳነ መምህራን፣ ተገኝተዋል።

በድጋሜ ለዚህ ውጤትና ሽልማት የበቃችሁ ውድ ተማሪዎቻችንና ወላጆች እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን የትምህርት ቤታችን መምህራንም ይህ ውጤት የተገኘው በእናንተ ያልተቋረጠ እገዛና ጥረት በመሆኑ እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳንም ደስ ያለን!!

🏆🏆🏆🏆🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🏅🏅🏅🏅

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

07 Oct, 11:00


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ በ2016 ዓ.ም 21.4% ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን እና ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ5% እድገት መመዝገቡን ጠቁመው በዛሬው መርሀ ግብር ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ባሻገር ተማሪዎቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ያሳለፉ የትምህርት ተቋማት ዕውቅና እንደተሰጣቸው አስታውቀዋል።

በዕውቅና መርሀ ግብሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበችው ተማሪ ሲፈኔ ተክሉን ጨምሮ ለሶስት ተማሪዎች የውጭ ሀገር የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ ተገልጿል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- [email protected]

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

07 Oct, 11:00


በ2016 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ ውጤት ያስመዘገቡ 484 የከተማችን ተማሪዎችን ሸልመን አበረታተናል።

(መስከረም 27/2017 ዓ.ም) ትምህርት የእድገት ሁሉ መሰረት መሆኑን ተገንዝበን በትምህርት ስርዓታችን ላይ የተፈጠረውን ስብራት ለመጠገን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ ከአምናው በ 5% እድገት ያሳየ ውጤት አስመዝግበናል።በዚህም በሀገር አቀፍ እና በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና አመራሮችን አመስግነን እውቅና ሰጥተናል።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከፍተኛ ዉጤት ባስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ፤

1ኛ ከፍተኛ ዉጤት - 575 ባስመዘገበችው ተማሪ ሲፈን ተክሉ፣

2ኛ ውጤት - 573 ባስመዘገቡት ተማሪ ማዕዶት እስክንድር እና ተማሪ ሶሊያና ሀብታሙ

3ኛ ውጤት - 570 ባስመዘገበችው ተማሪ ያስሚን ከድር

እጅግ የኮራን ሲሆን ከተበረከተላቸው እውቅና እና ሽልማት በተጨማሪ የውጭ ሀገር የትምህርት እድል(Scholarship) ሽልማት አበርክተንላቸዋል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

4,393

subscribers

1,065

photos

26

videos