Bilal Nur (@bilalnur1)の最新投稿

Bilal Nur のテレグラム投稿

Bilal Nur
#ETHIOPIA
2,392 人の購読者
89 枚の写真
7 本の動画
最終更新日 06.03.2025 15:05

類似チャンネル

Walaloo Jaalalaa
20,684 人の購読者
ECWC BASIC LABOUR UNION
2,092 人の購読者

Bilal Nur によってTelegramで共有された最新のコンテンツ

Bilal Nur

28 Feb, 09:10

247

በባህሪው አደገኝነት ያለው ቆሻሻን ወደ ወንዝ መጣል 1 ሚሊዮን ብር እንደሚያስቀጣ ተገለጸ

👉 በወንዝ ዳርቻና አካባቢ መጸዳዳት ሁለት ሺሕ ብር ያስቀጣል ተብሏል


የካቲት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስአበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት በጋራ ተግባራዊ እንደሚያደርጉት በተገለጸው፤ የወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም ደንብ መሠረት በባህሪው አደገኝነት ያለው ደረቅም ሆነ ፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ መጣል ወይም እንዲጣል በማድረግ በክሎ የሚገኝ ድርጅት 1 ሚሊዮን ብር የሚቀጣ መሆኑ ተገልጿል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በግለሰብ ደረጃ ከሆነ ደግሞ ግለሰቡ 500 ሺሕ ብር የሚቀጣ መሆኑ ተመላክቷል።

በአጠቃላይ በወንዝና በወንዝ ዳርቻ ላይ የሚፈፀሙ የብክለት ወይም የጥፋት ዓይነቶቹ እንደየአይነታቸው ከፍተኛ የሆነ ቅጣትን እንደሚያስተናግዱ የተገለጸ ሲሆን፤ ለአብነትም የፍሳሽ ማጣሪያ ሳይኖረው በወንዝ ዳርቻ እና አካባቢ ላይ የተሽከርካሪ እጥበት ማከናወን 400 ሺሕ ብር እንደሚያስቀጣ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም በወንዝ ዳርቻ ውስጥ ከተፈቀደው የመዝናኛ፣ መናፈሻ እንዲሁም ፓርክ እና ሌሎች ለወንዝ ዳርቻው ልማት አስፈላጊ ከሆነ ግንባታ ውጭ የፕላስቲክ ቤት ወይም ማንኛውንም ዓይነት ግንባታ መገንባት 200 ሺሕ ብር ያስቀጣል ተብሏል።

ፍቃድ የወሰዱም ሆነ ሳይወስዱ ፍሳሽን ቀጥታ በወንዞች ዳርቻ ሲያስወግዱ ቢገኙ 100 ሺሕ ብር ይቀጣሉ ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በወንዝ ዳርቻና አካባቢ መጸዳዳት ሁለት ሺሕ ብር እንደሚያስቀጣ የተገለጸ ሲሆን፤ ኬሚካል ነክ ቆሻሻዎችን የማከሚያ ዘዴ ሳይጠቀም የለቀቀ ግለሰብ 50 ሺሕ ብር ድርጅት ደግሞ 300 ሺሕ ብር እንደሚቀጡ ተነግሯል፡፡

እንዲሁም እንስሳትን ማሰማራት፣ ማስገባት ከተፈቀደው ውጪ ተሽከርካሪ ማሽከርከር 30 ሺሕ ብር፣ ለመዝናኛ፣ ለመናፈሻና ለፖርክ ከተፈቀደ ውጪ ግንባታ መገንባት 200 ሺሕ ብር፣ ከአምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማንኛውም ያልታከመ ቆሻሻ መልቀቅ ደግሞ 300 ሺሕ ብር ያስቀጣል ተብሏል፡፡

በተጨማሪ ማንኛውም በካይ ቆሻሻ ከተፈቀደ የፈሳሽ ማጠራቀሚያ ውጪ ያፈሰስ ግለስብ 50 ሺሕ ብር ድርጅት ደግሞ 400 ሺሕ ብር የሚቀጡ ሲሆን፤ የአትክልትና ፍራፍሬ ተረፈ ምርቶችን በወንዝ ዳርቻ ማስወገድ ግለሰብ 20 ሺሕ ብር ድርጅት ደግሞ 100 ሺሕ እንደሚያስቀጣ ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም ማንኛውም ያልተጣራ ቆሻሻ ወደ ወንዝ መልቀቅ ግለሰብ 150 ሺሕ ብር እንደሚያስቀጣ የተገለጸ ሲሆን፤ ድርጅት ደግሞ 300 ሺሕ ብር ይቀጣል ተብሏል፡፡

ዘይት፣ ጨዋማ ፈሳሽ፣የሞተር ዘይት፣ ነዳጅ ሳሙና ነክ ነገሮችን በወንዝ ዳርቻ ያስወገደ 400 ሺሕ ብር እንደሚቀጣም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ፍቃድ ሳይሰጠው ያልታከመ ቆሻሻን ወደ ወንዝ ያስወገደ ግለሰብ 15 ሺሕ ብር ድርጅት 40 ሺሕ ብር ይቀጣል ተብሏል።

በመሆኑም እነዚህንና ሌሎች የጥፋት አይነቶችን አካትቶ ይዞ የተሻሻለው ደንብ በከተማው ውስጥ የሚገኙ ወንዞችና የወንዝ ዳርቻ እና ገባሮቻቸው ከተለያዩ ቦታዎች በሚለቀቁ በካይ ፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አማካኝነት ተፈጥሯዊ ባህሪያቸውን በመቀየር ለሰው ጤንነትም ጎጂ በመሆናቸው ያንን ከመከላከል አንፃር አስፈላጊ ሁኖ በመገኘቱ ነው ተብሏል።

ከዚህም ሌላ የወንዝ ብክለትን ለመከላከል የተቀመጡ አሰራሮች ተግባራት በማይፈጽሙ አካላት ላይ ተመጣጣኝ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ከጥታፋቸው ተምረው ከተመሳሳይ ድርጊት እንዲታቀቡና የደረሰውን ጉዳት በማስተካከል ወደነበረበት እንዲመልሱ ማድረግ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊነቱ ስለታመነበት መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም ይህ ደንብ አስተዳደራዊ ወሰን ውስጥ በሚገኙ ወንዞችና የወንዝ ዳርቻዎች እና በአካባቢው ደህንነት ላይ ብክለትና አሉታዊ ተጽእኖዎችን በሚያስከትል ማንኛውም ሰው ላይ ተፈፃሚ ይሆናል ተብሏል።

ደንቡን ተረድተው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለማስቻልም ከሦስቱም ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች፣ አስተባባሪዎች እና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱ ተነግሯል፡፡

በአካባቢ ላይ ብክለት በሚያስከትል ወይም ሕገወጥ ሥራዎች ካሉ ኅብረተሰቡ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ በማድረግ ተባባሪ መሆን እንደሚገባውም ተገልጿል።
Bilal Nur

24 Jan, 08:46

777

ይመዝገቡ!

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና #በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ #የግል አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ አድርጉ!

ከዚህ ቀደም በመደበኛ ፕሮግራም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ያላመጣችሁና ፈተናውን በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ የግል አመልካቾች ምዝገባ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

https://register.eaes.et/Online ሊንክ ላይ በመግባት Apply Now የሚለውን ይጫኑ፤ የሚመጣላችሁን ቅፅ በጥንቃቄ ይሙሉ፤ አስፈላጊ ሰነዶችን ይጫኑ፤ የምዝገባ ክፍያ ብር 750 ክፍያ በመፈጸም ምዝገባዎትን ያከናውኑ፡፡

ምዝገባው የሚያበቃው፦ ጥር 20/2017 ዓ.ም

በምዝገባ ሒደቱ ማንኛውም ድጋፍ ቢያስፈልግዎ ከላይ በምስሉ ላይ በተጠቀሱት የስልክ ቁጥሮች በመደወል ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡
Bilal Nur

20 Jan, 15:12

781

Job Title: Sales

Job Type: Remote - Permanent (Full-time)

Work Location: Addis Ababa, Ethiopia

Applicants Needed: Female

Salary/Compensation: 7000 ETB Monthly

Deadline: January 26th, 2025

Description:
Our company, Loul trading, is looking to hire a sales team. We import finishing materials and furnitures, our office is at bole behind skylight hotel.
__________________

Private Client
1 Jobs Posted
__________________

From: afriworket.com | @freelanceethbot | @freelance_ethio | @afriworkamharic
Bilal Nur

20 Jan, 15:12

571

Job Title: እንግዳ ተቀባይ

Job Type: On-site - Permanent (Full-time)

Work Location: Addis Ababa, Ethiopia

Applicants Needed: Female

Salary/Compensation: Monthly

Deadline: February 8th, 2025

Description:

- እንግዳ ተቀባይ (Recieption Realestate & Guest House)

- በዲፕሎማ የተመረቀች ከ6ወር - 1 አመት የስራ ልምድ ጥሩ ተግባቦት ያላት

- ደመወዝ በስምምነት

- ለአዲሱ ገበያ አቅራቢያ የሆነች (6 ኪሎ፣ፒያሳ፣4 ኪሎ)

- 0947976288 or teleg... ... [view details below]
__________________

Private Client
4 Jobs Posted
__________________

From: afriworket.com | @freelanceethbot | @freelance_ethio | @afriworkamharic
Bilal Nur

20 Jan, 15:12

641

Job Title: ሞተረኛ

Job Type: On-site - Permanent (Full-time)

Work Location: Addis Ababa, Ethiopia

Applicants Needed: Male

Salary/Compensation: Monthly

Deadline: February 28th, 2025

Description:
የሞተር ሳይክል መንጃ ፍቃድ ያለው።
- የሚሰጠውን የሞተር ሳይክል በአግባቡ እና በጥነቃቄ መያዝ የሚችል።
- በቂ ተያዥ (ዋስ) ማቅረብ የሚችል ( ዋስትናው መቶ መፈረም የሚችል )
- ቀልጣፋ፣ ታማኝ እና ጠሩ የሰራ ተነሳሽነት ያለው።
- እጅግ በጣም ጥሩ የደንበኞች አገልግሎት አያያዝ መስጠት ሚችል።
- አስፈላጊውን ... ... [view details below]
__________________

Bike Taxi Transport and Logistics service P.L.C
Verified Company
59 Jobs Posted
__________________

From: afriworket.com | @freelanceethbot | @freelance_ethio | @afriworkamharic
Bilal Nur

12 Jan, 07:35

810

#እንድታውቁት

ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።

  የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።

ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።

ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።

አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።

በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።

የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።

ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።

የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።

(ተጨማሪ የጥፋት ዝርዝር እና ቅጣቶቹን ከላይ ያንብቡ)
Source
tikvahethiopia
Bilal Nur

12 Jan, 07:35

566

#ያንብቡ

የተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ከላይ ተያይዛል።

(ዝቅ ያለ የፋይል ጥራት 7.4 ሜጋባይት)

ምንጭ ፦ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን
Bilal Nur

08 Jan, 20:55

949

የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና መስጫ መርሀ ግብር


የ2017 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር የ6፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና የሚሰጠው ከጥር 06-08/2017ዓ.ም ነው፡፡ በመሆኑም ፈተናው በተመሳሳይ በሁሉም ት/ቤቶች በተዘጋጀው የፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ በየትምህርት አይነቱ እንዲሰጥ ክትትል እንዲደረግ እና ከፈተና በኋላ የፈተናው ውጤት በሶስቱም ክፍል ደረጃዎች ከ20% ለተማሪዎቹ እንዲያዝ እንዲሁም የመጀመሪያ ሴሚሰተር ውጤት ትንተናው ቀደም ሲል በተላከው ቅጽ መሰረት ተተንትኖ እስከ የካቲት 03/2017ዓ.ም ድረስ ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

[የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ]
Bilal Nur

08 Jan, 18:56

683

ውድድሩን እንድታሸንፍ ድምፃችንን እንስጣት

የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ አመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነችው እህታችን አሲያ ከሊፋ የሂዋዌ የ2025 የግሎባል አምባሳደር ለመሆን ሀገራችንን ኢትዮጵያ በመወከል እየተወዳደረች ትገኛለች::

ሀገራቸውን ከፍ አድርጎ በአለም አቀፍ መድረክ ለማስጠራት እየተጉ ለሚገኙ ታዳጊዎች ድምፅ ልንሆናቸው እና ከጎናቸው ልንቆም ይገባል::

https://bit.ly/425XnmX

desktop
Bilal Nur

08 Jan, 13:01

730

ዛሬ ይጠናቀቃል!

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና #በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ ዛሬ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል!

በመደበኛ መርሐግብር ከዚህ ቀደም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ #ያላለፋችሁና በድጋሜ ፈተናውን መውሰድ የምትፈልጉ አመልካቾች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም የሚሞሉ ቅጾችን በመሙላት፣ አስፈላጊ ሰነዶችን በመጫን እና የምዝገባ ክፍያ በመፈጸም ምዝገባዎትን በቀሩት ሰዓታት ያከናውኑ፡፡

ኦንላይን ለመመዝገብ 👇
https://register.eaes.et/Online