أحدث المنشورات من Bilal Nur (@bilalnur1) على Telegram

منشورات Bilal Nur على Telegram

Bilal Nur
#ETHIOPIA
2,392 مشترك
89 صورة
7 فيديو
آخر تحديث 06.03.2025 15:05

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة Bilal Nur على Telegram

Bilal Nur

07 Dec, 17:11

171

" በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

#EEP
Bilal Nur

05 Dec, 12:38

272

👉 የሪል ስቴት አልሚ ግዴታዎች ምንድናቸው ?

የሪልስቴት አልሚ በውል ሰነዱ በህንጻ እዋጁ እና በሌሎች የህግ ማዕቀፎች የተመላከቱ ግዴታዎችን ማክበር እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪነት የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል ፡-

1) ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡

2) በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር አይችልም፡፡

3) ቤቶቹን ለመገንባት የሚያስችለውን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከመረከቡ በፊት ደንበኞችን መመዝገብና ቅድመ ክፍያዎችን መሰብሰብ አይችልም፡፡

4) በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም።

5) የመኖሪያ ቤት ገዢ ደንበኞች ማኀበር እንዲያቋቋም ያበረታታል ፤ የህንጻ መግለጫ ያስረክባል።

6) ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የተሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫ፣ የቤቱ የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት፣ አርክቴክቸራል፤ ሳኒተሪ ፣ ስትራክቸራል እና ኤሌክትሪካል ዲዛይን፤ የግንባታ ፍቃድና የሪል ስቴት ልማት ፍቃዱን ቅጂዎች ከውል ሰነዱ ጋር አያይዞ ለደንበኛው መስጠት አለበት።

7) ደንበኛው ለከፈለው ገንዘብ ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት አለበት።

👉 ዋስትና ስለመስጠት ፦

የአገር ውስጥ አልሚ ቤቱን ሳይገነባ ለቤት ፈላጊዎች በቅድሚያ በሚሽጥበት ወቅት የሚከተሉትን የዋስትና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፡፡

1) የሪል ስቴት አልሚው በቤት ቅድሚያ ሽያጭ ስልት ለመስራት መፈለጉን አግባብ ላለው አካለ አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት፡፡

2) ከቤት ገዥዎች የሚሰበስበውን ገንዘብ አግባብ ካለው አካለ ፈቃድ መሰረት በሚከፈተው የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ፣

3) የሪል ስቴት አልሚው በቅድሚያ መሽጥ የሚፈልገውን ቤት የመስሪያ ቦታ የይዞታ ማስረጃ ቤቱ ለተጠቃሚዎች ተገንብቶ እስከሚተላለፍ ድረስ በሚመለከተው አካል እንዳይሽጥ እንዳይለወጥ እንዲታገድ ማድረግ፤
📌 በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡
አዋጁ ከላይ በ PDF ተቀምጧል።
#ቲክቫህ
=====================
Bilal Nur

05 Dec, 12:37

239

👆
ረቂቅ አዋጁ ፀደቀ

የህ/ተ/ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ዛሬ በምክር ቤት የፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የሪል ስቴት አልሚ ድርጅት ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ እንደማይችል አስቀምጧል።

በተጨማሪ በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር እንደማይችልም አስቀምጧል።

የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?

👉 የሪል ስቴት አልሚ የቦታና የተናጠል ይዞታ ማረጋገጫ አሰጣጥን በተመለከተ ፦

1) በከተሞች ለሪል ስቴት ልማት የሚውል ቦታ በሚከተለው አግባብ የሚቀርብ ይሆናል፤

ሀ. በአዲስ አበባ ከ5 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፤
ለ. እንደከተሞች ተጨባጭ የቤት ፍላጎትና ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባለ ከተሞች ከ1 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፣
ሐ. ከነዚህ ባነሰ ስፋት ቤት ለሚፈልጉ ከተሞች ደግሞ 500 ቤት በላይ የሚገነባና የሚያስተላልፍ የሪል ስቴት አልሚ መሬት ቅድሚያ ተሰጥቶት በስፋት እንዲቀርብለት ይደረጋል።

2) የሪል ስቴት አልሚው የገነባውን ቤት በተናጠል ለቤት ፈላጊ በሽያጭ ለማስተላለፍ ግንባታው የተፈቀደለትን መስፈርት አሟልቶ 80 በመቶ ሲጠናቀቅ ለየቤቱ የተናጠል የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል፤
Bilal Nur

09 Nov, 07:16

925

#ጥቆማ #የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ አውጥቷል።

ለTRAINEE CABIN CREW በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ (ዝቅተኛው) 200 ነጥብ ያስመዘገበ ለማመልከት ብቁ ነው።

የዕድሜ ገደቡ ከ19 እስከ 30 ዓመት ነው።

ቁመት ቢያንስ 1.58 ሜትር እና 212 ሴ.ሜ የሆነ ክንድ ለሴት እንዲሁም ለወንድ ቢያንስ 1.70 ሜትር ቁመት መሆን አለበት።

የምዝገባ ጊዜው ከህዳር 08/2017 ዓ/ም እስከ ህዳር 12/2017 ዓ/ም ነው።

ምዝገባው ፦
- በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አዲስ አበባ (በኦንላይን ልክ ማመልከቻው ሲከፈት ይፋ ይደረጋል)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (አርባ ምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ባህር ዳር)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (ድሬዳዋ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ( ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ)
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ) ይከናወናል።

ተጨማሪ መረጃዎች፣ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣ ዝርዝር ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም የወጡ ማስታወቂያዎች በዚህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረገጽ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ይመልከቱ 👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies

@bilalnur1
Bilal Nur

09 Nov, 05:39

741

በአዲስ አበባ የምርቶች መሸጫ ዋጋ ተመን‼️
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የግብርና ምርቶች መሸጫ ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 6/2017 ዓ.ም እና ዕሁድ ገበያዎች ጥቅምት 30 እና ህዳር /2017 ዓ.ም የሚቀርቡ የአትክልት፣ የፍራፍሬ፣ የሰብል ምርቶች እና የፋብሪካ ምርት ውጤቶች የመሸጫ ዋጋ መረጃ ከላይ የተያያዘው ነው።
⬇️⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇⬇️⬇️
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ
@bilalnur1
Bilal Nur

07 Nov, 06:02

923

ዛሬ የመጨረሻው ቀን ነው 👆👆
Bilal Nur

07 Nov, 05:56

810

የዲቪ አሞላል ማብራሪያ ለምትፈልጉ 👇
https://youtu.be/gD3oNHbbSko
ለዲቪ የሚያስፈልግ የትምህርት ደረጃ 👇
https://youtu.be/oAE3anXTuRg
Bilal Nur

07 Nov, 05:56

834

#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ
ዲቪ ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

ለማመልከት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ 👇
https://dvprogram.state.gov/
Bilal Nur

06 Nov, 19:25

881

ለ አንዴ መርማሪ ፖሊስ ሁኑ
ጊዜው ትምህርት የተከፈተ ሰሞን ነው አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ ሰው ተገድሎ ይገኛል.🤔🤔
እና መርማሪ ፖሊስ 4 ተጠርጣሪዎችን በመያዝ ጥያቄ መጠየቅ ይጀምራል...

1.የመጀመሪያ ተጠርጣሪ ሒሳብ አስተማሪ ነው
👮‍♂️መርማሪ እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል ሟች ተገደለ በተባለበት ሰዓት የት ነበርክ?

👨‍አስተማሪ :- ለተማሪዎች ጥያቄ እያወጣሁ የበር ሲል ይመልሳል!

2. ሁለተኛ ተጠርጣሪ :- ፅዳት ሰራተኛ ናት
መርማሪ እንዲህ ሲል ይጠይቃታል ሟች ተገደለ በተባለበት ሰዓት የት ነበርክ?

👧 ፅዳት ሰራተኛ :- ቢሮ እያፀዳው ነበር ስትል ትመልሳለች!

3.ሶስተኛ ተጠርጣሪ English አስተማሪ ነው
👮‍♂️መርማሪ እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል ሟች ተገደለ በተባለበት ሰዓት የት ነበርክ?

👨‍አስተማሪ :- የተማሪዎችን የደረጃ ውጤት እየሰራሁ ነበር ሲል ይመልሳል!

4.አራተኛ ተጠርጣሪ የ ትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር ናቸው
👮‍♂️መርማሪ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል ሟች ተገደለ በተባለበት ሰዓት የት ነበሩ?

👨‍ርእሰ መምህር :- ት/ት ቤት ውስጥ አልነበርኩም ሲሉ ይመልሳሉ!

ማን ነዉ መርማሪዉን እየዋሸ ያለዉ?

@bilalnur1
Bilal Nur

06 Nov, 11:36

798

አዳማ አንብታለች

ወጣቷ  በሥራ ባልደረባዋ በስለት ተገደለች

በአዳማ ከተማ  ወንጂ ማዞሪያ  እቴቴ ሬስቶራንት በተባለ ጊቢ ውስጥ ነው ወንጀሉ የተፈፀመው ከቀኑ  7:33 በጠራራ ፀሐይ ሲሆን እድሜዋ 20 መጨረሻዎች የምትገኝ ወጣት ናት

በሆቴሉም ገንዘብ ያዢነትና  የሂሳብ  ሰራተኞችን  የመቆጣጠር ሃላፊነት አላት። 

ጥቃት  የፈፀመባት ከትላንት በስቲያ  አብሯት በሚሰራ ሰራተኛ ነው። ግለሰቡ ለሬስቶራንቱ ፍየል አራጅ  ሲሆን "ቀን አብረው ገበያ ውለው መተዋል ሲሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል።

በግዢ ሰዓት አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር እና ወደ ስራ ቦታ ከተመለሱም  በኋላ ወደ ውስጥ እናውራ ብላ  ይዛው ገባች ነገር ግን እንዳሰበችው መነጋገር  ሳይችሉ በሩን ቆልፎ  ያለ ርህራሄ ጀርባዋን ፣ታፋዋን፣ እጇን እና አንገቷን ወጋግቶ እና አርዶ እንደገደላት ተሰምቷል።

ታዲያ  በሩን ሰብሮ  እርዳታ  ለመስጠት የፖሊስ የአንቡላንስ አገልግሎት ማግኘት  የተቻለው  ከአንድ ሰዓት በኃላ ህይወቷ ካለፈ በኃላ ነበር💔😭 

ወጣቷ በማደጎ ያለ እናት እና አባት
ያደገች መሆኑ ተነግሯል 😥
    
ፍትህ ታገኝ ዘንድ
ድምፅ ሁኗት 🤲

ሼር በማድረግ በግፍ ለሚሞቱ ሴቶች  ፍትህ ጠይቁ!!!

ያማል 😭

🌴🌴🌴

https://www.facebook.com/share/1AWTNirm85/?mibextid=WC7FNe